የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion ? @Share_Home
Last updated 1 month, 2 weeks ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 7 months, 4 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 9 months, 4 weeks ago
ሰላም ለናንተ ይሁን ቤተሰብ እንዴት አመሻችሁ እስቲ ውስጣችሁ ያለውን አካፍሉን
ፀሎት
ቃል
ግጥም
መዝሙር
ቤተሰብ በጣም ይቅርታ ኦንላየን ፈተና ስለነበረብኝ የዛሬው ላይቭ ማገልገል አልቻልኩም ሌላ ፕሮግራም አዘጋጅቼ አሳውቃችኃለው ሌሎች አገልጋይ ጋብዘን በሌሎችም የምንባረክ ይሆናል የተወደዳችሁ ናችሁ
ለነፍስህ ዋጋ ስጥ
አምላክ እስትንፋሱን እፍ ብሎ ያለባት
ክብሩን ሁሉ ጥሎ መጥቶ የሞተላት
የሰው ልጆች ነፍስ ዋጋዋ ውድ ነው
የዓለም ሀብት ቢተመን ከቶ የማይተካው.
እንደቀላል ነገር ሰው ሰውን ሲገድል
በየጥጋ ጥጉ ተወስዶ ሲጣል
ተራ ነገር ይመስላል የነፍስ መጥፋት
ይተካ ይመስል ዝም ብሎ ማየት.
ግና መች በቀላሉ ሆነ የሚተካ
አንዴ ካመለጠ ሁሉ ሳይሳካ
እንዲህ በቀላሉ የምናየው ሳይሆን
ነፍስ እጅግ ውድ ነው ቀድመን ከተረዳን.
ወዳጄ ይቺ ነፍስ አምላክ የሰጠህ
በሕይወት ኑር ብሎ የቀጠለልህ
የሁለት ዓለም ጌታ ይፈልጋታልና
ለነፍስህ ዋጋ ስጥ አስተውልና.
የነፍስህ መገኛ ምንጭ የሆነው
ጌታ ኢየሱስ በመስቀል የሞተው
የራሱ ሊያረጋት ደግሞ ሊከብርባት
የዘላለም ሕይወት በነፃ ሊሰጣት
ይፈልጋልና ይሄ ውድ ጌታ
በሰላም ሊያኖራት ከቅዱሳን ተርታ
ስጠው ለኢየሱስ ነፍስህን ሳትሳሳ
ሕይወት ነውና ሞትን ድል የነሳ.
አይ አልፈልግም ብለህ ከወሰንክ
እንደ ስጋ ፍቃድ ለመኖር ካሰብክ
ለስጋ የሚመች አንድ መንግስት አለ
በጨለማ የሚኖር ሲኦል የተጣለ.
ሃሳብ እና እቅዱ ጥፋት የሆነ
የሚያርድ የሚገድል እጅግ የጨከነ
ዘወትር የሚተጋ ነፍስህን ሊያጠፋ
ወደ ሲኦል ሊወስድ የማይቆርጥ ተስፋ.
የነፍስህ ፍፃሜ ከሁለት አንዱ ነው
በመረጥከው መንገድ የሚወስነው
ጊዜያዊ ሳይሆን የዘላለም ቦታ
ነፍስህ ምታርፍበት ከምድር ተለይታ.
እናማ ወዳጄ ነፍስህ ለዘላለም ምታርፍበት ስፍራ
በህልውናው ውስጥ እንዲሆን ከአብ ጋራ
ሕይወት የሆነውን ኢየሱስን ምረጥ
ውድ ነውና ለነፍስህ ዋጋ ስጥ.
✍ገጣሚት ሃና መኮንን
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
ሰላም ለእናንተ ይሁን ቤተሰብ እንዴት አመሻችሁ
ጌታን አመሰግኑልኝ
ይሄ ጅማሬ ነው ብዙ መፅሀፍቶች ለማሳተም ጌታ እንደሚረዳኝ አምናለው።
ከአምሳ በላይ ድንቅ ግጥሞች አንብባቹ ተባረኩበት ለሌሎች ሼር አድርጉት
የእናንተው
ኤርሚያስ ክፍሌ ነኝ
ቃልህ
----------*
የእረፍቴ ስፍራ፣ማግኛ ነው ሰላሜ
ዘውትር እያጠጣኝ፣ሚያኖር በልምላሜ
የህይወት እንጀራ፣ከድካም ማገገምያ
በልቤ የፃፍከው፣የህይወት መመርያ
መታመኛ ጋሻ፣ጠላት መመከቻ
ብሩህ መስታወት ነው፣ውስጥን መመልከቻ
መልህቅ ነው ለኑሮ፣በማዕበል ለሚርድ
ፍቱን መድሀኒት፣በልጦ የሚወደድ
ቃልህ
ነፍስን ማረጋግያ፣በማዕበሉ መሀል
ፃድቅ አሰላስሎት፣ከግቡ ይደርሳል
አይደል ሳለሳል፣እያመንኩት ስኖር
እጅግ ደስ ይለኛል፣በእጄ ይዤው ስዞር
ቃልህ
ስንቴ በረታሁበት፣ዳንኩበት ስንት ጊዜ
ነፍሴን ገላገላት፣ከሀጥያት አባዜ
ስንቅ ሆነኝ ለህይወት፣ብርሀን ለመንገዴ
ቃል አይገልጥልኝም፣ቃልህ ለመውደዴ
አንተን እንዳልበድል፣በልቤ ሰውሬ
በብሩቱ ወድጄው፣አለው እስከዛሬ
ውዴን ሚያወራልኝ፣የሆነኝ ወዳጄ
ቃሉ አላጣጥልም፣በፍፁም ለምጄ
ሁል ጊዜ ተወዳጅ፣ሁል ጊዜ ብርቅ ነው
ልቤ ሚለውን ነው፣ብዕሬ የሚፅፈው
ውዴ ሆይ ቃልህ እወደዋለው
✍ኤርሚያስ ክፍሌ
ሁላቹም ላይክ አድርጉ እስኪ
react and share
@Kegetemku_leyesus
ለምን ተከተልከው
በፊት በፊት ጥንት አባቶቻችን
ጌታን ሲከተሉ ትተው ያላቸውን
በእውነት ነበረ ምንም ሳይጠብቁ
የጌታን መገኘት ብቻ እየናፈቁ.
ሀብት ቢሰጣቸው ወይም ቢነሳቸው
ሁኔታው አይደለም ስር መሰረታቸው
ይልቅስ ትልቁ ዋና ጉዳያቸው
ሲያገኙት ሁል ጊዜ ደስታ ሚሰጣቸው
አንዴ ለገባቸው ለተረዱት ጌታ
ዘላለም መኖር ነው በሐሴት በደስታ.
ግን ዛሬ የምናየው ነገር
በፊት የምናቀው ለክርስቶስ መኖር
እጅግ ያሳዝናል የሚሰማው ሁሉ
በትውልድ መሃል ክርስቶስ መቅለሉ.
ክርስቶስን ሳይሆን ተቋም ተከትሎ
በነፈሰበት ሲነፍስ ኢየሱስን ጥሎ
ብርሃን አስመስሎ ጠላት ሲያታለው
ላዩን አሰማምሮ ሲኦል ሊጥለው
ያሳዝናል ህዝቡ ያለበት ሁኔታ
ጨለማ ከቦት እንዲያ ስንገላታ.
ወዳጄ
የሚሆነውን ሁሉ ዝም ብዬ ሳየው
ዘመኑን በአትኩሮት ሆኜ ሳስተውለው
ውስጤ ፈጠረብኝ አንድ ጥያቄ
ትውልዱ ያለበትን ሁኔታ ማወቄ.
ለምን ይሆን ጌታን እንዲህ የተከተልከው
በልብህ ላይ ሾመህ ልትኖር ያሰብከው
እስቲ መልስልኝ ወዳጄ ሆይ ልስማህ
ለዚህ ጥያቄ መልስ አንተ ምን ትላለህ.
አንዳንዶች በሃይማኖት አጥር ታጥረው
ከኢየሱስ ይልቅ ስርዓቱን አይተው
ወደነበሩበት የቀድሞ ሕይወታቸው
ሲመለሱ ይታያል እውነት መስሏቸው.
የክርስትና መርህ መጓዝ ነበረ ሁሉን ነገር ጥሎ
መስቀል በመሸከም ጌታን ተከትሎ
ለራስ የሚባል ሕይወት የሌለበት
ኢየሱስን አይቶ መኖር በመሰጠት.
ግን አሁን ላይ ሁሉም ተቀይሯል
በዚህ ክፉ ዘመን ክርስትና ቀሏል
ኢየሱስን ሳይሆን እጁን ብቻ አይተው
ለራስ የሚኖሩ ይህን ዓለም ወደው
ሞልተዋል በዓለም እውነቱን የካዱ
እግራቸው ወደሞት መንገድ የተነዱ.
እናማ ወዳጄ ዛሬም እልሀለው
ጌታ ኢየሱስን ለምን ተከተልከው
ገብቶህ ከሆነ ተረድተህ እውነቱን
ወደ አብ መድረሻ ብቸኛ መንገዱን
እንኳን ተከተልከው ይህን ውድ ጌታ
ሕይወት የሆነውን የዘላለም ደስታ.
✍ገጣሚት ሃና መኮንን
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus
ሰላም ቤተሰብ እንዴት አመሻችሁ የአባቴ ምርጦች
ሰላም ያባቴ ብሩካን እስቲ ዛሬ ቤተክርስቲያን የተማራችሁት አካፍሉን
ክርስትና መገለጥ ነው
-------
መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎች ጥበብን ይሻሉ
እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን 1ኛ ቆሮ1:23
በህይወቴ በጣም የሚያስደስተኝ እና የማመሰግንበት ምክንያት ክርስቶስ ስለበራልኝ ነው።
እንደነገርኳችሁ ክርስትና መገለጥ ነው መፅሀፍም እግዚአብሔር ብርሀን ነው ለእኛም በራልን እንዲል ሞኝነት በሚመስል መንገድ ስለበራልኝ ጌታን መውደድ ማመን ከማመን አልፎ ወደ መስበክ ስላመጣኝ ጌታዬን አመሰግናለው
በእውቀት ሚገኝ ቢሆን ብዙዎች ያገኙት ነበር እኔ ግን አላገኘውም በሀብት በቁንጅና በጉልበት ቢሆን እንደዛው
ግን ጌታዬ ለእኔ ለሞኙ ለእኔ ለደካማው ለእኔ ለምስኪኑ አበራልኝ ምን አይነት መታደል ነው በእውነት ስምህ ይባረክ
እርሱ እኮ ከመታወቅ በላይ ነው
በዘላለም ውስጥ እንኳ ሰማይ ሄደን እንኳ የከበረው ሰውነት ለብሰን እንኳ አውቀን አንጨርሰውም ግን በራልን ስሙ ይክበር
አይገርምም አማኑኤል ብለን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ብለን ሳንጨርስ ጭራሽ ውስጣችን ገብቶ አደረ
በእውነት ክርስቲያን መሆን መታደል ነው
በእውነት ይሄ ሚስጥር መረዳት መመረጥ ነው ስሙ ይባረክ።
❝በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና፦ የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።❞
—ሉቃስ 10: 21
ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር አድርጉት
react And Share
@Kegetemku_leyesus
??ይ?️ላ?️ሉን??
የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion ? @Share_Home
Last updated 1 month, 2 weeks ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 7 months, 4 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 9 months, 4 weeks ago