የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

Description
በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በሕይወት ላይ ያተኮሩ ጽሑፎችና ሌሎች ኦርቶዶካሳዊ ትምህርቶች በጽሑፍና በድምጽ ይቀርብበታል
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

3 months, 3 weeks ago

[⚪️#አንድ_ጥያቄ

●✥ ከመንፈስ ፍሬዎች መካከል ቀዳሚነትን የሚይዘው የትኛው ነው ●✥](https://t.me/orthoxy_ewet)

3 months, 3 weeks ago

"ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ብርቱ (ጠንካራ) ምንም የለም። ይህችውም ከሰማይ ከፍ ያለች ከምድርም ይልቅ የሰፋች ናት። አታረጅም ነገር ግን ዘወትር ታበራለች።"…

"ቤተ ክርስቲያን በዘመናት ሁሉ ትሰፋለች። መታሰቢያዋም የሚጠፋ (የሚሞት) አይደለም።"…

"ቤተ ክርስቲያን በስንቶች ውጊያ ተደርጎባት ነበር? አልተሸነፈችም እንጂ። የተዋጓት አላውያን፣ የጦር መሪዎች፣ ነገሥታቱስ ምን ያህል ናቸው? የተማሩና ኃይልን የተሞሉ ጎበዞች ሐዲሲቷን ቤተ ክርስቲያን በብዙ ጎዳናዎች ተዋግተዋት ነበር። ሊነቅሏት ግን አልቻሉም። ነገር ግን እርሷን የተዋጉ ጥቂቶች ለዝምታና ቶሎም ለመረሳት ተላልፈው ተሰጥተዋል። የወጓት ቤተ ክርስቲያን ግን ከሰማይ በላይ ከፍ ከፍ ብላለች። ቤተ ክርስቲያንን ድል ከማድረግስ ፀሐይን ማጥፋት (ማጨለም) ይቀላል። ሰው ሆይ! ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ኃያል ምንም የለም። ከሰው ብትጣላ ወይ ታሸንፋለህ አልያም ትሸነፋለህ። ቤተ ክርቲያንን ግን ብትጣላ፣ ታሸነፍ ዘንድ የሚቻልህ አይደለም። እግዚአብሔር ከሁሉ ይልቅ ኃያል ነውና። እግዚአብሔር መስርቷታል፣ እንግዲህ ማን ሊነቀንቃት ይችላል? "

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(በዲያቆን አቤል ካሳሁን የተተረጎመ)

3 months, 3 weeks ago

"ሌቦች ወርቅና ብር ያለውን እንጂ ድርቆሽና ገለባ እንዲሁም ሰንበሌጥ ያለውን ቤት አይበረብሩም፡፡ ዲያብሎስም የሚያጠቃው (የሚፈትነው) መንፈሳዊ ምግባራትን የሚያበዙትን ሰዎች ነው፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

4 months ago

#ጌታችን_ለምን_በሌሊት_ተጠመቀ?
በኃጢአት ጨለማ ስለነበረ ሕዝብ የጽድቅ ብርሃን እንዲወጣለትና በጨለማ የሚመስል ኦሪት ይኖር ስለነበረ ለሕዝብ ብርሃን የሆነ ወንጌል መገለጡን ለማሳየት ነው፡፡ ኢሳ.9፥2

አንድም ጌታ ልደቱ፣ ጥምቀቱ፣ ትንሣኤው እንዲሁም ምጽአቱ በሌሊት ነው፡፡ ይኽም የሆነበት ምክንያት፡- ሌሊቱን ተከትሎ የሚመጣው ብርሃን በመሆኑ ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሲኦል ወደ ገነት የመሸጋገራችን ምሳሌ ነው፡፡

አንድም መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል የሚወርድ ነውና በጌታ ላይ የወረደው ርግብ እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ባሉ ነበር፡፡ በሌሊት ርግብ የለም ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ይታወቅ ዘንድ፡፡

#መንፈስ_ቅዱስ_ለምን_ጌታ_ከውኃ_ከወጣ_በኋላ_ወረደ?
ሀ. ዮሐንስን ያከብሩት ነበርና መንፈስ ቅዱስ የወረደው ለዮሐንስ እንጂ ለጌታ አይደለም ይሉ ነበርና ምክንያቱን ጌታ ውኃ ውስጥ እያለ ከዮሐንስ አልተለየም ነበርና፡፡
ለ. ውኃን የሚባርክ መልአክ እንዳለ ያውቁ ነበርና ውኃውን ለመባረክ አንጂ ለጌታ አይደለም እንዳይባል፡፡
ሐ. ማረፊያ ያጣች ርግብ በባሕር ስትበር አረፈችበት ይሉ ነበርና ሐሳባቸውን በሙሉ ያጠፋ ዘንድ ከውኃ ውስጥ ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወረደ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

4 months ago

#በጥምቀት_ዙሪያ_የሚነሱ_ጥያቄዎች_እና_መልሶቻቸው
#ጌታችን_ለምን_ተጠመቀ?
1. ምሥጢርን ለመግለጥ፡-
ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ግልፅ ሆኗል፡፡ አብ በደመና “የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው” በማለቱ አብ የወልድ አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ሲያስረዳ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ ተቀመጠ ወልድም በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ታየ፡፡ ስለዚህ ምሥጢርን ለመግለጥ ስንል የአንድነት የሦስትነት ምስጢር በጐላ ሁኔታ እንዲታወቅ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ /ማቴ. 3፥16/

  1. ትንቢቱን ለመፈፀም፡-
    በመዝሙር 46/47/፥16 ላይ “አቤቱ ውሆች አዩህ፣ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ ውሆችም ጮኹ፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም ተጠመቀ፡፡

  2. አርአያ ሊሆነን፡-
    ተጠምቆ እንድንጠመቅ አደረገን ሥርዓትን ሠራልን ቀድሞ በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረን አሁንም አርአያ ምሳሌ ሆነን፡፡ ለዚህም ነው ምሳሌን ከእኔ ተማሩ ያለን፡፡ /ማቴ 11፥29/ ለትምህርት ለአርአያ /ዮሐ. 13፥1-17/

  3. የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡-
    አዳምና ሔዋን ፍዳው በፀናባቸው መከራው በበዛባቸው ጊዜ የሚያቃልልላቸው መስሏቸው ዲያብሎሰ ስመ
    ግብርናችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ ባላቸው ጊዜ አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ (አዳም የዲያብሎስ የወንድ አገልጋይ) ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ዲያብሎስም ይህንን ደብዳቤ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው፡፡ በዮርዳኖስ ያስቀመጠውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ ደምስሶታል፡፡ ይህንን ጽሕፈት ለመደምሰስ ነው ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፡፡” ያለው ቆላ 2፥14

#ጌታችን_መች_ተጠመቀ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም ዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፡፡ /ሉቃ. 3፥23/

#ጌታችን_ስለምን_በ30_ዓመት_ተጠመቀ?
በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር ተልእኮ እና መንፈሳውያን አገልግሎቶች ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር፡፡ እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ልማድ አልነበረም፡፡ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው፡፡ /ዘፀ. 4፥3፤1ዜና መዋ. 23፥24፤ 1ጢሞ. 3፥6-10/ ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዓመቱ ነበር፡፡

ዮሐንስ መጥምቅም የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው፡፡ ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛ ቀን ተሰጥቶት ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያስወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ነው፡፡

ክርስቶስ የተጠመቀው ክብር ሽቶ ሳይሆን የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር፣ ውኃውን ለመቀደስ፣ የአዳምን ልጆች የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስህተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው፡፡ ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በማረፍ አብ በደመና ‹‹ይህ ልጄ ነው›› ብሎ ሲመሰክርለት ምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በጉልህ ተረጋግጧል፡፡ /ማቴ. 3፥16/

#ጌታችን_በዮሐንስ_እጅ_ለምን_ተጠመቀ?

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትሕትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ይህንንም ያደረገልን አብነት ሊሆነን ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን ‹‹መጥተህ አጥምቀኝ ›› ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ጌታ ስሆን በባርያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት እጅ ተጠመቁ›› ሲል ነው፡፡

ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነትን የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ ክብር እንዲሆነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም፡- እርሱ እከብር አይል ክቡር እጸድቅ አይል ጻድቅ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ጌታችንን_በማን_ስም_አጠመቀው?

ጌታችን ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለው ጊዜ "ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለሁ አንተን በማን ስም ላጥምቅህ? በአብ ስም እንዳላጠምቅህ አብ አባትህ ባንተ ሕልው ነው በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳላጠምቅህ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትህ ባንተ ሕልው ነው ታዲያ በማን ስም ላጥምቅህ?" ብሎ ቢጠይቀው ጌታም ‹‹እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ›› ብለህ አጥምቀኝ አለው፡፡

#ዮሐንስ_ጌታን_ሲያጠምቀው_እጁን_ለምን_አልጫነበትም?
- ዮሐንስ በጥምቀት አከበረው /ልዕልና ሰጠው/ እንዳይባል፡፡
- መለኮትን በእጅ መንካት ስለማይቻል

#ጌታችን_ጥምቀቱን_ለምን_በዮርዳኖስ_አደረገው?
በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ጌታ ጥምቀቱን በዮርዳኖስ ያደረገው ስለዚሁ አስቀድሞ የተነገረውን ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ‹‹ባሕር አይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ›› /መዝ.113፥3/ ከዚህም ጋር ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት ተከፍሎ እንደገና እንደሚገናኝ በግዝረት በቁልፈት (በመገዘርና ባለመገዘር) ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታችን ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገልጽ ትርጉም አለው፡፡ እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምደረ ርስት ገብተዋል፡፡ ያመኑ የተጠመቁ ምዕመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ፡፡ ሌላው በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የዕዳ ደብዳቤ ይደመስስልን ዘንድ /ቈላ. 2፥14/

#ጌታችን_ለምን_በውሃ_ተጠመቀ?
እግዚአብሔር አምላክ በዘመነ ኦሪት ሰብዐ ትካትን በንፍር ውሃ ፈርኦንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ካጠፋ በኋላ ሰዎች ውሃ ለመዓት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምሕረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ በውሃ ተጠመቀ ( ዘፍ 7÷17፤ ዘጸ 14÷1-29)

አንድም ውሃ እሳትን ያጠፋል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ከገሃነመ እሳት ትድናላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ውሃ መልክን ያሳያል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ መልክዓ ሥላሴን የአምላክን ቸርነት ርህራሔ ታያላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም በማር በወተት ቢጠመቅ ኖሮ እነዚህ ለባለጸጎች እንጂ ለድሆች አይገኝም ውሃ ግን በሁሉ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ጥምቀት የታዘዘ ለሁሉ ነው ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ቢታጠብበት ያቆሽሻል እንጂ አያነጣም ውሃ ግን እድፍን ያስለቅቃል እናንተም በማየ ገቦ ብትጠመቁ ከኃጢአት ትጠራላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ተክል ላይ ቢያፈሱት ያደርቃሉ እንጂ አያለመልሙም ውሃ ግን ያለመልማል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋ ወነፍስ ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡ (ዮሐ 19÷35)

4 months ago

"የማይበድል ባሪያ የማይምር ጌታ የለምና፤ ጌታ ሆይ:- አቤቱ እኔን ኃጢአተኛውን ይቅር በለኝ"
አባ ዕብሎይ

4 months, 1 week ago

"ከንቱ ውዳሴ በመንገድ ሁሉ የሚከተልህ የተሸሸገና ጭንብል ያጠለቀ ሌባ ነው። አሳዳጅ በመሆኑ በጣም ደኅንነት በሚሰማህ አሳቻ ሰዓት ሳታውቀው ይዘርፈሀል፤ ይገድልህማል። "

ቅዱስ ጎርጎርዮስ

4 months, 1 week ago

#የመጨረሻ_ክፍል

#ራስን_መግዛት (ክፍል- ፭)

#ምኞትና_የበላይነት

መንፈሳዊው ሰው ምኞቱን፣ ደስታውን መውደዱንና የበላይነቱን አስመልክቶ ራስን መግዛት አለው:: በራሱ ዓይኖች ፊት ራሱን አዋቂ አድርጎ ሲያገኘው ወይም በአመለካከቱ ውስጥ ራሱን አጽድቆ ሲመለከት ወይም ደግሞ ራሱን ከሚያስበው በላይ ከፍ አድርጎ ሲያስብ ራሱን ለመግዛት ይጥራል፡፡ ሮሜ 12፥3

ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔር ከሰጠው ጸጋ በላይ ራሱን ሊያልቅ አይሞክርም፡፡ ዲያብሎስ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ ብሎ በትዕቢት የተነሣው ራሱን መግዛት ባለመቻሉ ስለሆነ ወድቋል። ኢሳ. 14፥14

መንፈሳዊው ሰው ራሱን የሚገዛው ውዳሴ ከንቱን አስመልክቶ ብቻ ሳይሆን ስጦታዎችንም በተመለከተ ነው:: ወይም ደግሞ ሰውየው ራሱን ከፍ ከፍ እንዳያደርግ እግዚአብሔር እርሱነቱን የሚገዛበትን መንገድ ያመቻችለታል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ የተናገረውን ቃል አትርሱ! «ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።» 2ኛ ቆሮ. 12፥7።

#ወንድሜ_ሆይ! አሳብህ ከፍ ከፍ ባለብህ ጊዜ ሁሉ ተቆጣጠረው። ራስህን ከተሰጠህ በላይ አድርገህ አትገምት፡፡ አንተነትህን ከሌሎች ጋር አነጻጽረህ ወደምትመለከትበት ደረጃ የሚመሩህ ምኞቶችህን ግታቸው፡፡ ራስህን ከፍ ከፍ ብሎ ስታየው ወይም ደግሞ በፊትህ ታላቅ ሆኖ ስታገኘ ው ታዛዥነትህን፣ ትሕትናህን፣ ለሌሎች ያለህን ክብር በማጣት ላይ መሆንህን እወቅ፡፡ በማንኛውም ጊዜ ከፊት ለፊትህ የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አኑር። «ትዕቢት ጥፋትን ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።» ምሳ. 16፥18::

#በሕይወት_ዙሪያ

ራስን መግዛት መላ ሕይወትን ያጠቃልላል፡፡ መንፈሳዊው ሰው ምቾትንና ድሎትን አስመልክቶ ራስን መግዛት አለው፡፡ እርሱ ሰዓቱን በትክክል ይጠቀማል፡፡ በመሆኑም ጊዜውን ለሚሠራው መንፈሳዊ ሥራ ያከፋፍላል። ቀጠሮ ያከብራል:: በተሰደበ ወይም በተጠቃ ጊዜ ሰራሱ ሊበቀል እንዳይነሳሳ ራሱን ይገዛል፡፡ ገንዘብን በተመለከተም ስለሚቀበለውና ስለሚስጠው ገቢና ወጪ ላይ ራሱን ይገዛል። ከሌሎች ጋር የሚያደርገው ግንኙነት እስከ ምን ድረስ መሆን እንዳለበት ይረዳል:: ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ እንዳያጋድል የልቡን ስሜታዊነትና ፍላጎት ይቆጣጠራል:: ሌላው ቢቀር በአምልኮ፣ በአገልግሎት፣ሌሎችን በመቆጣጠርና ሌሎችም ባሉበት ኃላፊነቶች ውስጥ ራሱን ይገዛል::

#ለማጠቃለል
በዚህ ጉዳይ ላይ የምስጠው ጠቃሚ አስተያየት ራሱን ከውስጥ መቆጣጠር የማይችል ስው ከውጪ የሌሎች ቁጥጥር እንደሚያስፈልጉት የሚገልጽ ነው:: እርሱ ራሱን ከውስጥ መቆጣጠር ካልቻለ ቁጥጥሩ ያለ ፈቃዱ ከውጪ ይመጣል። ከውጪ የሚመጡት ኃይላትም አመሉን በቅርብ የሚያውቀውና ኃላፊነቱን የሚጠይቀው ኅብረተሰብ አንዱ ሲሆን የሚመለከቱት ዓይኖችና የሚሰሙት ጆሮዎች ተጠያቂ ያደርጉታል። ከዚህ በኋላ በፍርሃት ይገዛል ወይም በእፍረት ይሸማቀቃል፡፡ በመጨረሻም በሕግና ከበላይ አካላት በሚመጡ ውሳኔዎች እንዲቆጣጠሩት ይሆናል::

ወይም ደግሞ በመንፈሳዊ ምክሮች ከገደቡ እንዳያልፍ አድርገው ያቆሙታል፡፡ ከዚህ ካለፈ ስህተቱን እንዳይደግም በሚያደርጉት ውጪያዊ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ይወድቃል:: ነቢዩ ዳዊት ራሱን ባለመግዛቱ ብቀላ ከመውሰድ ራሱን ሊከለክል አለመቻሉ በጣም ያስደንቀኛል። በዚያን ወቅት ለእርሱ ውጪያዊ ኃይል ስላስፈለገው አቢግያ በጥበብና በእውቀት እንድትገሥጸው ሆኗል። 1ኛ ሳሙ. 25::

አንድ ሰው ያለራሱ ፈቃድ በሌላ ቁጥጥር ውስጥ ከሚገባ ወይም በውጪያዊ ኃይል ከሚገዛ ይልቅ ራሱን በመንፈሳዊነት ገዝቶ መለኮታዊውን ዋጋ ቢያገኝ ይሻለዋል ይበጀዋልም:: መንፈሳዊው ሰው ግን ራሱን የሚገዛው ከውስጥ ነው:: በዚህ ጊዜ ውጊያዎች ከመጡበትም ምንጊዜም ቢሆን የሚፈልገው የልቡን ንጽሕና እና የተቀደሱ ሥራዎቹን ስለሆነ የተለያዩ መንፈሳዊ እርምጃዎችን ይወስዳል::

(#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#መንፈሳዊ_ሰው_መጽሐፍ  ገጽ 122-128
#በአያሌው_ዘኢየሱስ_የተተረጎመ)

@yehiwot_meaza   @yehiwot_meaza
@yehiwot_meaza   @yehiwot_meaza

4 months, 1 week ago

#ሰው_ሆይ!

በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ " በማለት ተናገር።
አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።

እስኪ ከፍ ካለው ተራራ፣ ከታላቁ ባህር፣ ከምታበራው ጸሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ! አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ 20፥35)። አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው። (ዮሐ 4፥4)

ሰው ሆይ! አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ? ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን?

(ከአቡነ ሽኖዳ የነፍስ አርነት መጽሐፍ)

4 months, 2 weeks ago

ቆየት ያለ የልደት መዝሙር

https://youtu.be/5guXNBZsAEU

YouTube

"ሳር ቅጠሉ ሰርዶ" በዘማሪት አዜብ ከበደ (የዱሮ መዝሙር በድጋሚ የተዘመረ) #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ #መዝሙረተዋህዶ

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago