★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago
[?♂አባቶች ይህንን ይመክሩናል
እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ለኦርቶዶኮስ አማኞች ብቻ የተከፈተ ቻናል ።
✝ክርስትናችን እንዳንኖረው የሚያደርጉን ምክንያቶች በእውኑ ታውቋቸዋላችሁ⁉️](https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk)
ለዚህ ችግር አባቶች ምን አሉ⁉️
የምትፈልጉትን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉ
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቋሚ ስሙ ዮሐንስ የሚለው ስሙ ነው። አፈወርቅ የሚለው ስሙ ግን ስመ ሥርጋዌ (የሽልማት) የቅጽል ስሙ ነው። አፈወርቅ ከሚለውም በተጨማሪ ሌላ ዳንኤል ሐዲስ የሚባል ስመ ሥርጋዌም አለው፡፡ የእነዚህ ሁለት ስሞች ስያሜ መነሻ ታሪክ እንደሚከተለው ነው።
ሊቁ አፈወርቅ የሚለውን ስያሜ ከእመቤታችን እና ያስተምራቸው ከነበሩት በትምህርቱም ደስ ከተሰኙ ምእመናን እንዳገኘው ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡
ቅስና ከተሾመ በኋላ ከላይ እንደገለጽነው በንጉሡ በቴዎዶስዮስና በሕዝቡ መካከል በሐውልቱ መፍረስ ምክንያት ቅራኔ ተፈጥሮ በነበረ ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ ፍላቭያኖስ ንጉሡን ከሕዝቡ ጋራ ሊያስታርቅ ሄደ። ያን ጊዜም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕዝቡን በሚገባ ጣዕም ባለው አንደበቱ አስተማራቸው፡፡ የአንደበቱን ጥፍጥና የተመለከቱት ምእመናንም ይህ ሰው “አፈ ወርቅ" ነው ተባባሉ፡፡ ይህን ማለታቸውም ወርቅ ከማዕድናት ሁሉ የጠራ እንደ ሆነ ዮሐንስም ትምህርቱ የተወደደ የጠራ ነው ማለታቸው ነበር።
ንጉሡ አርቃድዮስ ወንጌላዊው ማቴዎስ “ኢያእመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወልደ ዘበኵራ፤ የበኵር ልጇን እስክትወልድ ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም ነበር” በማለት የተናገረው ቃል ጥያቄ ሁኖበት ይኖር ነበርና ሊቁ በቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስነትን በተሾመ ጊዜ ወንጌላዊው ይህንን ስለምን ተናግሮታል? ወንዶች ሴቶችን በግብር እንደሚያውቋቸው ከወለደች በኋላ በግብር ዐወቃት ማለት ነውን? ብሎ ጠየቀው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም ወንጌላዊው ይህን ማለቱ ስለ ሁለት ነገር እንደሆነ እንዲህ በማለት አስረዳው፡፡
ወንጌላዊው “የበኵር ልጇን እስከ ምትወልድ አላወቃትም ነበር” በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ ያለው እስከ ፍጻሜ የሌለው “እስከ" ይባላል፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚሆን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ “ኢወለደት ሜልኮል እስከ አመ ሞተት፤ ሜልኮል እስክትሞት ድረስ አልወለደችም ነበር" የሚል ገጸ ንባብ እናገኛለን፡፡
በዚህ ገጸ ንባብ ውስጥ ያለው እስከ ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው ከሞተ በኋላ ሊወልድ አይችልምና፡፡ ይህም ማለት ሜልኮል እስከ ዘለዓለሙ አልወለደችም ማለትን ለማስረዳት የገባ እስከ ነው፡፡ የወንጌላዊው ንግግርም ከወለደች በኋላ በግብር አውቋታል ማለት ሳይሆን እስከ ዘለዓለሙ አላወቃትም ለማለት ነው፡፡
በሁለተኛ ደረጃም የእመቤታችንን እመ አምላክነት ክርስቶስን በወለደች ዕለት ዐምስት ነገሮችን ማለትም የጌታ የጌትነቱ መገለጥ፣ የመላእክትን ምስጋና፤ የእረኞችን ፍርሃት፣ የኮከብን በሌላ መንገድ መሄድና የሰብአ ሰገልን ከእጅ መንሻ ጋር መምጣት እስከሚመለከት ድረስ አላወቀም ነበር፡፡
ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የተወደደ ልጇን ክርስቶስን በወለደች ጊዜ ግን እነዚህን ነገሮች ተመልክቶ ወላዲተ አምላክ መሆኗን አውቋልና፡፡ ሊቁ ቃሉን “የበኵር ልጇን እስከምትወልድ ድረስ አላ ወቃትም ነበር” በማለት አመሥጥሮ ተርጕሞታል፡፡
በዚህ ጊዜ በወርቅ የተሣለች የእመቤታችን ሥዕል በዚያ ነበረችና “ሠናየ ተናገርከ ኦ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፤ ሠናየ ተናገርከ ኦ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ፤ ሠናየ ተናገርከ ኦ ዮሐንስ አፈ ዕንቊ፤ አፈ ወርቅ ልሳነ ወርቅ አፈ ዕንቊ ዮሐንስ የተወደደ ነገርን ተናገርህ'' ብላ አሰምታ ተናግራለች፡፡ ንጉሡም ይህንን ከእመቤታችን የተሰጠውን ስም ሥርጋዌ ሰምቶ በመደነቅ ከዚህ በኋላ ስሙ አፈወርቅ ይባል ብሎ አዘዘ።
ከዚህም በተጨማሪ በሦስተኛ ደረጃም አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰታቸው ውስጥ እንደ ገለጹት ንስጥሮስ የተባለ መናፍቅ ኤጲስ ቆጶስነትን በተሾመበት ወራት አንዲት ሴት ከግዳጇ ሳትነፃ ለቤተ እግዚአብሔር ካላት ፍቅር የተነሣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ትገባለች፡፡
ያን ጊዜም የፀሐይ ጨረር ከሰው ሁሉ ተለይቶ በዚያች ሴት ላይ ያርፋል። የተሰበሰበውም ሕዝብ በተመለከተው ገቢረ ተኣምራት ሲደናገጥ ንስጥሮስ ይህችን ሴት በምን ምክንያት ይህ ምልክት እንደታየባት ጠየቃት፡፡
እርሷም ለቤተ እግዚአብሔር ካለኝ ፍቅር የተነሣ ከግዳጄ የምነፃበት ቀን ሳይደርስ ቤተ ክርስቲያን ገብቻለሁ ብላ በፍርሃት ተናዘዘች፡፡ ንስጥሮስም በልቡናው እመቤታችን አምላክን አልወለደችውም የሚል ኑፋቄ ስለነበረበት ይህቺ ሴት ራቁቷን በዐደባባይ እንድትሰቀልና ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው "እግዚአብሔር በዚህ ሥጋ ከሴት እንደተወለደ የሚያምን የተረገመ ይሁን” እያሉ በአፈ ማኅፀኗ ላይ እንዲተፉባት አዘዘ።
የተሰበሰበው ሕዝብም ከሓዲው ጳጳስ ንስጥሮስ እንዳዘዛቸው ሲያደርጉ ቅዱስ ዮሐንስም በዚያ ቁሞ ይሰማ ነበርና የእሱ ተራ ሲደርስው ወደ ሴቲቱ በመቅረብ “እኔ ግን እግዚአብሔር በዚህ ሥጋ በኅቱም ድንግልና ከሴት እንደ ተወለደ አምናለሁ” በማለት ሰዎች ይተፉበት የነበረ አፈ ማኅፀኗን የሰዎችን ምራቅና የእሷንም ደም ሳይጠየፍ የእመቤታችንን ፍጹም ንጽሕና በማሰብ ሳመ፡፡ ያን ጊዜም በቤተ መቅደስ ፊት የነበረች የድንግል ማርያም ሥዕል አፈ ወርቅ ብላ ጠራችው ስለዚህም ዮሐንስ አፈወርቅ ተባለ፡፡ (መጽሐፈ ምስጢር ገጽ 50-51)
ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከተሰጡት ስመ ሥርጋዌ ሁለተኛው ዳንኤል ሐዲስ የሚለው ነው፡፡ ይህ ስም አፈወርቅ እንደሚለው ስም ብዙ ጎልቶ ባይጠራበትም በበጎ ግብሩ ለሊቁ ከመልአኩ የተሰጠው ስም ነው፡፡ መልአኩ ሊቁን ዳንኤል ሐዲስ ያለበት ምክንያት ዳንኤል የናቡከደነፆር ራእይ ንባቡ ከእነ ትርጓሜው ከጠፋ በኋላ ንባቡም ትርጓሜውም በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት እንደተናገረ እሱም የዮሐንስ ራእይ ንባቡ ከነትርጓሜው ከጠፋ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት ስለተናገረ ነው፡፡
[የእግዚአብሔር ቸርነት የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የጸሎቱ በረከት ከእኛ ጋራ ትሁን አሜን፡፡
(ምንጭ፦ ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 15-31)](https://t.me/beteafework)
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በጵጵስና ዘመኑ ከሚታወቅባቸው ደማቅ ሥራዎቹ አንዱ ድኃ ሲበደል ፍርድ ሲጎድል እንደ አባቶቹ እንደ ኤልያስና እንደ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ንጉሡንና ንግሥቲቱን ያለ ፍርሀት በጥብዐት ይገሥፅ የነበረ አባት መሆኑ ነበር። በዘመኑም የንጉሡ የአርቃድዮስ ባለቤት ንግሥት አውዶክስያ የአንዲትን መበለት መሬት ሥልጣኗን ተጠቅማ ነጠቀቻት፡፡
ይህቺ መበለት መሬቷን እንድትመልስላት ደጋግማ ብትለምናትም ንግሥቲቱ እሺ ስላላለች መበለቷ ችግሯን ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነገረችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም የድኃዪቱን መሬት እንድትመልስላት ደጋግሞ ቢነግራትም ንግሥት አውዶክስያ ግን በዕንቢተኝነቷ ጸናች። በዚህ ጊዜም ሊቁ ሳይፈራና ሳያፍር ንግሥቲቱ የድኃዪቱን መሬት ካልመለሰች ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበል አወገዛት፡፡
ንግሥት አውዶክስያም በዚህ ጊዜ እጅጉን ተናዳ የቆጵሮሱን ሊቀ ጳጳስ ኤጲፋንዮስንና የእስክንድርያውን ፓትርያርክ ቴዎፍሎስን አስጠርታ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከግዝቷ እንዲፈታት እንቢ ካለ ግን አብያተ ክርስቲያናትን ዘግታ አብያተ ጣዖታትን በማስከፈት የቀደመውን የስደት ዘመን መልሳ እንደምታመጣው በመንገር ከግዝቷ እንዲያስፈቷት ነገረቻቸው፡፡
እነርሱም ሄደው “ምእመናን ትንሽ ዐረፉ ስንል የቀደመውን የመከራ ዘመን መልሼ አመጣዋለሁ እያለች ነው እባክህ ከግዝቷ ፍታት።" በማለት ተማጸኑት። ሊቁ ግን “የድኃዪቱን መሬት ካልመለሰች አልፈታትም ብሎ በአቋሙ በመጽናቱ ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ ንግሥት አውዶክስያ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በኑፋቄያቸው ምክንያት አውግዞ የለያቸውን አርዮሳውያን ኤጲስ ቆጶሳትን ሰብስባ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በማይገባ ነገር አውግዞኛልና ፍረዱልኝ አለቻቸው፡፡ እነርሱም በኑፋቄያቸው ምክንያት አውግዟቸው ስለነበር ይጠሉት ነበርና ተሰዶ በግዞት እንዲኖር፣ በዚያም እንዲሞት ፈረዱበት፡፡
ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ሁከት እንዳያነሣ እርሱን በመንፈቀ ሌሊት በፈረስ በሠረገላ አድርጋ ወደ ደሴተ አጥራክያ አጋዘችው፡፡ እርሱም በዚያ በተጋዘበት ሀገር የነበሩትን ሰዎች አስተምሮ ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መለሳቸው፡፡ በወቅቱ በሮም ነግሦ የነበረው ንጉሥ አኖሬዎስ እና ሊቀ ጳጳሱ ዮናክንድዮስ ይባላሉ፡፡ ንጉሡና ሊቀ ጳጳሱም የሊቁን ከመንበሩ መሰደድ ሲሰሙ የሮሙ ንጉሥ አኖሬዎስ ወደ ንጉሥ አርቃድዮስ በፍጥነት ከስደቱ መልሰው የሚል መልእክት ላከበት፡፡ ንጉሥ አርቃድዮስም ያለ ንግሥት አውዶክስያ ፈቃድ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ከስደቱ መለሰው፡፡
ነገር ግን ንግሥት አውዶክስያ ሊቁ ከግዞቱ የተመለሰው ያለ ፈቃዷ ነበርና ሌላ ምክንያት ፈልጋ እንደገና በስደት እንዲጋዝ አደረገችው፡፡ እርሱም በመንገድና በእስራት ደክሞ ስለነበር አጥራክያ እንደደረሰ ብዙ ሳይቆይ ግንቦት 12 ቀን በ407 ዓ.ም. በሰላም ዐረፈ፡፡
ከዚህም በኋላ የሮሙ ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሱ ዮናክንድዮስ የሊቁን ሁለተኛ መሰደድ ሲስሙ ሊቀ ጳጳሱ ዮናክንድዮስ ከስደቱ ካልመለሽው ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበይ ብሎ አወገዛት፡፡ እርሷም ከስደቱ ይመልሱት ዘንድ መልክተኞችን ብትልክም መልክተኞቹ በደረሱ ጊዜ ዐርፎ አገኙት፡፡ እነርሱም አስከሬኑን በድንጋይ ሳጥን ይዘው ከደሴተ አጥራክያ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሱ፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር የሊቁ ቅድስና እንዲገለጥ ፈቃዱ ነውና በንግሥቲቱ ላይ ከባድ ደዌ አመጣባት፡፡
ንግሥቲቱም የምትድን መስሏት ለብዙ ባለ መድኃኒቶች ብዙ ገንዘብ ብትከፍልም ከደዌዋ ግን ሊፈውሳት የቻለ ከቶ አልነበረም፡፡ ከብዙ ድካም በኋላም ለክፉ ሠሪ ደግ መካሪ አይታጣምና አንድ ሰው ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መቃብር ሂዳ ብትማጸን ሊቁ እንደሚያማልዳት ነገራት፡፡
እርሷም ወደ መቃብሩ በመሄድ “የአዛኙ የክርስቶስ አገልጋይ ሆይ እዘንልኝ፤ የሩኅሩኁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ራራልኝ፤” እያለች ጸለየች፡፡ ከዚህ በኋላም በጻድቁ አማላጅነት በእግዚአብሔር ቸርነት ከደዌዋ ተፈወሰች።
"በሰው ላይ የምንመለከተው የእግዚአብሔር መልክ ነው። የእኛ ሰዓሊ ሲስለን እርሱን እንድንመስል አድርጎ ነው፡፡ የእርሱን ውበት በእኛ ውስጥ ይሰራዋል፡፡
በቀለም ፋንታ በተለያየ መንፈሳዊ በጎነት ያሳምረናል፤ የእግዚአብሔር ምስልና መልክም ከምንም ነገር ጋር ስለማይነጻጸር ሰውም ይህ እውነተኛ መልኩ በመሆኑ ከሌሎች ምድራዊ ነገሮች ጋር አይቀላቀልም፣... ተፈጥሯችንን ያስዋበ እግዚአብሔር ከተጠቀመበት ብሩሽ አንዱ #ፍቅር ነው።
ትሕትና
ትሕትና የትንሽት ምልክት አይምሰልህ ፡፡ ታላቁ መስፍን ሙሴ ፣ ታላቁ ጌታ ክርስቶስ ትሑታን ነበሩ ፡፡ ባለጠግነት ትሕትናን ሊያሳጣህ ሲሞክር ጻድቁ አብርሃምና ጻድቁ ኢዮብ ትሑታን እንደ ነበሩ አስብ ፡፡ ሥልጣን ልብህን ከፍ ሲያደርግብህ “ለንጉሥ በቀን ላይ ቀን ትጨምራለህ” በማለት የተናገረውን ዳዊትን አስብ ፡፡ ምንም ብትነግሥ ለራስህ አንድ ቀን መስጠት አትችልምና ፡፡ ደግሞም “ሁሉም ከንቱ” ያለውን ሽቅርቅሩን ንጉሥ ሰሎሞንን ፣ ጠቢቡን ንጉሥ ይዲድያ የተባለውን በማሰብ አለባበስንና እውቀትን ናቀው ፡፡ ጉልበትህ ሊያስታብይህ ሲሻ ሶምሶምን አስብ ፡፡ ኃይልህ ከኃያላን ፣ ሥልጣንህ ከሠለጠኑት ፣ እውቀትን ካወቁት ጋር ቢነጻጸር በጣም ትንሽ ነው ፡፡ በምድራዊ ነገር ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ጸጋም ልትመካ አይገባህም ፡፡ ትምክሕት እጄ ሀብትን ፣ ጽድቄ ጸጋን አመጣልኝ ማለት በመሆኑ ቁጥሩ ከክህደት ነው ፡፡ በጸጋ ሳይሆን በባለጠጋው መመካት ግን ተፈቅዷል ፡፡ ኃጢአትህ እየበዛ ሲመጣ የሌሎች ስህተት እየታየህ ይመጣል ፡፡ ጽድቅ በውስጥህ እየተስፋፋ ሲመጣ የራስህ ደካማነት ይታይሃል ፡፡
ትሕትና በአደባባይ እንደ ለበስከው ነጭ ሸማ ነው ፡፡ ታጌጥበታለህ ፡፡ ትዕቢት ግን ያዋርድሃል ፣ የማያውቅህ ሳይቀር አይቶ ይጸየፍሃል ፡፡ ቁመተ ረጅሞች ሲኮሩ ሰማይን የምታይ ይመስልሃል ፡፡ አጭሮች ሲልመጠመጡ መቃብር የገቡ ይመስላል፡፡ የረጅምነት ውበቱ ዝቅ ማለት ነው ፡፡ ትዕቢተኛ ስትሆን ሰዎች እንከን እንዲፈልጉብህ መንገድ ትከፍታለህ ፡፡ ትሕትና ራስን የማወቅ ውጤት ነው ፡፡ ራሱን በትክክል የሚያውቅ ሊታበይና በሌሎች ሊፈርድ በፍጹም አይችሉም ፡፡ ትሕትና የሌሎችን ክብር ማወቅ ነው ፡፡ ማክበር መከበር ነውና ሌሎችን ስናከብር ትሕትና ታስከብረናለች ፡፡ ትሕትና ሁልጊዜ እንደሚማሩ ሁኖ መኖር ነው ፡፡ ትሕትና በጠፋበት ዘመን ሁሉም ሰው አስተማሪ ይሆናል ፡፡ ሁሉም ሰው ቅዱስ ነኝ በማለት ሌሎችን ያጣጥላል ፡፡ ጆሮ ጠፍቶ አፍ ብቻ የበዛበት ዘመን ዘመነ ትዕቢት ነው ፡፡ እገሌ ክፉ ነው ማለት በተዘዋዋሪ እኔ መልካም ነኝ ማለት ነውና ትዕቢት ነው ፡፡ ትሕትና የሰዎችን ትልቅ ድካም አሳንሶ ፣ ትንሽ ብርታታቸውን አጉልቶ ያሳያል ፡፡ ትሕትና እንዳልኖሩ ሁኖ ከሌሎች ልምድን መቅሰም ነው ፡፡
ከፍ ላሉት ዝቅ ማለት ትሕትና አይደለም ፡፡ ከፍ ያሉትማ ግርማቸው በግድ ያሰግዳል ፡፡ ትሕትና ዝቅ ላሉት የምናሳየው ፍቅርና ክብር ነው ፡፡ ለእግረኛ ቅድሚያ ስትሰጥ አንድ ነገር አስብ ፡- “መኪና ለሰው እንጂ ሰው ለመኪና አልተፈጠረም፡፡” እውነተኛ ትሕትና ለሚያንሱን መታዘዝ ነው ፡፡ ሰው እንደዚህ ሁኖ እንደማይቀር ብናስብ ስንት ሕጻናትን ስንት ድሆችን ባከበርን ነበር ፡፡ ትሕትና የልብ መሰበር ያመጣልና ለዝማሬና ለንስሐ ያበቃል ፡፡ አበባ ካልታሸ አይሸትም ፣ ፍራፍሬ ካልተጨመቀ አይጠጣም ፡፡ ሰውም ትሑት ካልሆነ መልኩ አይወጣም ፡፡ ትሕትና ያወቁትን ያለ ትችት ማስተማር እንጂ አላውቅም ማለት አይደለም ፡፡ እያወቁ አላውቅም ማለት ልግመት ፣ ሳያውቁ አውቃለሁ ማለት ራስን አለማወቅ ነው ፡፡ ያወቁትን በትጋት ማስተላለፍ ትሕትና ነው ፡፡ የተማርከው ሌሎችን ደንቆሮ ብሎ ለመሳደብ ሳይሆን በጨለማ ላሉት ብርሃን ለማወጅ ነው ፡፡ የጋን ውስጥ መብራት ከመሆን የሚያድነው ትሕትና ነውና ስታውቅ ትሑት ሁን ፡፡ ፍሬ ያለው ዛፍ ዘንበል ይላል ፡፡ ቀና የሚሉት ዛፎች ግን ፍሬ የሌላቸው ናቸው ፡፡ በእውነት ካወቅህ ያላወቅከው ስለሚበዛብህ ትሑት ትሆናለህ ፡፡ በአንድ ጥቅስ ጫካ የሚገቡ የአቡጊዳ ሽፍቶች ግን ትዕቢተኞች ናቸው ፡፡ “ድምፅና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል” ይባላል ፡፡ ቁንጫም እንደ ልቡ ይዘላል ፣ ባዶ አዳራሽም ድምፅን ያስተጋባል ፡፡ ጩኸት ማብዛት የባዶ ቤት ምልክት ነው ፡፡ ባዶ ሰው ከቀድሞ የከፉ የሰባት ኣጋንንት ማደሪያ ይሆናልና እባክህ ባዶ አትሁን ፡፡
ትሕትና የልብ ነው ፡፡ የልብ ያልሆነ ትሕትና የአንገት መሰበር ፣ የጉልበት መሸብረክ ብቻ ነው ፡፡ በልብ እየናቁ በአፍ ማክበር እርሱ ትሕትና ማጣት ነው ፡፡ ይልቁንም ትልቁን መንግሥት ፣ መንግሥተ ሥላሴን እየሰበክህ ትሑት ልትሆን ይገባሃል ፡፡ ትልቁን ትሕትና ነገረ ሥጋዌን እየተናገርህ ትሑት መሆን ያስፈልግሃል ፡፡ ተዋሕዶ ማለት ትሕትና ማለት ነው ፡፡ ባለጠጋው መለኮት ከድሃው ሥጋ ጋር የተዋሐደበት ማለት ነው ፡፡ የሥጋ ድህነት ለመለኮት ፣ የመለኮት ብልጥግና ለሥጋ እንዲነገር የፈቀደው ትልቁ የትሕትና ትምህርት ቤት ምሥጢረ ሥጋዌ ነው ፡፡ ምስኪኖችና ጦም አዳሪዎችን ፣ ኃጢአተኞችንና መንገድ የጠፋባቸውን ካላዘንክላቸው በተዋሕዶ አታምንም ማለት ነው ፡፡ የተዋሕዶ ምሥጢር ሲገባህ በቀራጮችና በኃጢአተኞች አታፍርም ፡፡ የወደቀውን ለማንሣት ዝቅ ትላለህ ፣ ወደ ሐኪም ቤት ለማድረስ አህያህን እንደ ደጉ ሳምራዊ ለቀህ እግረኛ ትሆናለህ ፡፡
የስድብ አምሮትህን ለመወጣት “ውሾች” ይላል ቃሉ ፣ የነቀፋ ጥማትህን “ተኩላ” ይላል ወንጌሉ እያልህ ከተወጣኸው ኃጢአትና በቅዱሱ ነገር መበደልህ ነው ፡፡ ውሻ ፣ ተኩላ ያለው ጠባያቸውን ለመግለጥ እንጂ ላንተ ስድብ ለማበደር አይደለም ፡፡ ትሕትና ተፈትኜ አልጨረስኩም ብሎ በራሱ በጣም አይመካም ፡፡ ገና በፈተና ዓለም ያሉ ሰዎችንም በጣም አያመሰግንም ፡፡ እባክህ ወዳጄ ትሑት ሁን ፡፡ የበላይ የበታች ሁሉም ልቡ ጎረምሳ ሁኗልና የሚያስተነፍስ መዓት ሳይመጣ ትሕትናን ገንዘብ እናድርግ ፡፡ ትሕትናን በማጣት ያሳዘንከውን እግዚአብሔር በብዙ ትሩፋት አታስደስተውም ፡፡ ትሕትና የእምነት መጀመሪያ ነውና ፡፡
"ዲያብሎስ በእናንተ ላይ እጅግ ክፉ ነገርን በማምጣት አሳዝኖአችኋልን? እናንተም ኢዮብን አብነት አድርጋችሁ እግዚአብሔር ይመስገን በማለት አሳዝኑት፡፡ ዲያብሎስን ድል ማድረግ ስትሹ ይህን መሣርያ ዘወትር ያዙ፤ ምስጋና፡፡"
"ለበጎ ነው"
"አንድ ንጉስ ከአጃቢው ጋር በመሆን ለአደን ይወጣል። ለአደን ሲወጡ ንጉሱ ወጥመድ እያጠመደ እያለ ወጥመዱ አምልጦት እጁን ቆረጠው። በዚህም አጃቢው በማዘን "አይዞህ ንጉስ ሆይ ሁሉ ነገር ለበጎ ነው!" ይለዋል። በዚህም ንጉሱ በንዴት እየጦፈ "የኔ እጅ መቆረጥ ነው ለበጎ?" ይለውና እስር ቤት አሳሰረው።
ንጉሱ አጃቢው 'ሁሉ ነገር ለበጎ ነው!' ያለው ትዝ አለውና እስር ቤት ሄዶ ስላሰርኩህ ይቅርታ አርግልኝ! ብሎ ታሪኩን አጫወተው። አጃቢውም "ማሰርህ ለበጎ ነበር! እኔም መታሰሬ ጠቅሞኛል።" አለው። ንጉሱ "እንዴት?" አለው አጃቢውም "ባልታሰር ኖሮ ከአንተ ጋር እሄድና አንተ ቆራጣ መሆንህን ሲያውቁ ይለቁህና አኔን ይገሉኝ ነበር" አለው።
ስለዚህ ሁላችንም ስለተደረገልንም ሆነ ስላልተደረገልን እንዲሁም ስለሆነውም ሆነ ስላልሆነው ነገር ሁሉ "ለበጎ ነው" ማለት ይልመድብን፡፡
(fb ላይ ካነበብኩት በድጋሚ የተለጠፈ)
[? ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ ? ?
? ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ
? እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?
? በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል
? የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች](https://t.me/addlist/2Tk_Bck2rFoxMjNk)
ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
#[ዕርገተ_ማርያም (#ነሐሴ_16)
ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር።](https://t.me/beteafework)
ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ።
[የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ።
የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ ። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት ።](https://t.me/beteafework)
ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው ። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው ።
ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳትው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ ።
ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን ።
የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ።
ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው ። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት።
በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው ። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ ።
የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና ።
?#አንድጥያቄ
✟ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለአብርሃም ድንኳን ለኖህ መርከብ ለያዕቆብ መሰላል ለአዳም ምኑ ናት? ✟
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago