★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago
እርቃን መሄድ መብት ከሆነ ለብሶ መሄድ ለምን ወንጀል ሆነ⁉️ #አክሱም❌?⬇️⬇️
https://youtu.be/0CfjlF68Ido?si=wiNtvA2o_v4tl-X3
https://youtu.be/0CfjlF68Ido?si=wiNtvA2o_v4tl-X3
አንዳንዴ ቤተሰቦችክ በየዕለቱ በስራ ምክንያት ተፍ ተፍ ስትል ያለህበትን ከባድ ውጥረት ላያውቁ ይችላሉ
ስራህ ደግሞ የቤትህን ሁኔታ ማወቅ አይፈልግም ሁሌም አንተን ይፈልጋል፣ አንዱ ስራ ሲያልቅ ሌላው ይቀጥላል ሁሌም ስራ አለ
ወዳጆችክ በጫንቃህ ላይ የተጣለውን አዲሱን የስራ ኃላፊነት አይረዱህም
የትዳር ጓደኛህ ሁልጊዜም ፍቅርና መዝናናት ትጠብቃለች ፥ የቱንም ያህል ያለህበትን የስራ ውጥረት ለማስረዳት ብትጥር አትረዳህም
ሲጠቃለል - ከአንተ ውጪ ያለህበትን በትክክል ሊረዳ የሚችል ያለ አይመስልም…..
የሆነ ሆነና መቼም ተስፋ እንዳትቆረጥ
ጉዞህን ልፋትህን ያለመታከት ቀጥል..?
በዚህ ቻናል⬇️?
✔ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
✔ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
✔ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
✔ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️?
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube
Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886
ቴሌግራም⬇️?
https://t.me/ZEKR_MENZUMA
አላህ ለዋለልን ፀጋ አመስጋኞች እንሁን
አሁን ወደ ቤት እየሄድኩ ከሀይሌ ጋርመንት ወደ ሰፈራ የሚሄደውን ታክሲ ለመሳፈር ወደ ታክሲ ተራ ስሄድ በጣም ረጅም ሰልፍ አለ። እና እዚህ ከምሰለፍ ቅርብ ስለምወርድ ለምን ወክ አላደርግም ብዬ በእግሬ ጉዞ ጀምርኩኝ።
ወደ ቶታል አከባቢ ስደርስ ሰዎች ተሰብስበው ተመለከትኩኝ ጠጋ ብዬ ስመለከት አንድ ሰው መንገድ ላይ ወድቋል። በቦታው ያሉ ሰዎች ልያናግሩት ቢሞክሩም ምንም መልስ አይሰጥም፣ የሞተ ሰው ነው የሚመስለው። እዚያ የነበሩ ብዙ ሰዎች ቀስ በቀስ መበተን ጀመሩ። እዚያ የቀረነው ሶስት ሰዎች ትንፋሹን ለማየት ወደ አፉ ጠጋ ስንል ሎሊፖፕ (ባለ ዱላው ከረሜላ) አፉ ውስጥ አለ።
ከዚያ ከንፈሩን ስያንቀሰቅስ ተመለከትንና ጎንበስ ብለን ስንሰማው "ስኳር" "ስኳር" የሚል ድምፅ ሰማን። ከዚህ በፊት የዚህ ዓይነት ነገር አጋጥሞኝ ስለሚያውቅ ወደኋላ ሮጥ ብዬ ተመልሼ ካገኘሁት የጀቡና ቡና ሱቅ ትንሽ ስኳር ለምኜ ተመልሼ ወደ ሰውዬው በመሄድ ወደ አፉ ሳስጠጋለት ስኳሩን መላስ ጀመረ። ከጥቂት ሰከንዶች ብኋላ ሰውነቱ መንቀሳቀስ ጀመረ።
ከደቂቃ ብኋላ ድምፁም ትንሽ መሰማት ጀመረ። አጠገቡ ያለውን ፌስታል በእጁ እየጠቆመ ሚሪንዳ ስጡኝ አለ። ሚሪንዳውን ከፌስታል አውጥቼ ሰጠሁት። ትንሽ ቆይተን ሰውነቱ መፍታታት ሲጀምር አንሰተን በቂጡ አስቀመጥነው።
ከዚያ መውራት ጀመረ "በእጄ ከነበረኝ ብር ላይ እቺን ሚሪንዳና ሎሊፖፕ ገዝቼ እጄ ላይ የቀረኝ አስር ብር ብቻ ነው። በህይዎቴ ከሰው ገንዘብ ለምኜ አላውቅም እናም አስር ብሩ ለታክሲ ስለማይበቃኝ ከገላን ኮንዶሚኒየም በእግሬ ጉዞ ጀመርኩኝ። እየራበኝ ነበር ምግብ የምበላበት ብር ስለሌለኝ ዝም ብዬ ተጓዝኩኝ" አለን።
አስባችሁታል የስኳር በሽታ ያለበት ሰው ምግብ ሳይበላ እየራበው ከገላን እስከ ጋርመንት በእግሩ ሲጓዝ። ደግሞኮ ወደየት ነው መዳረሻህ ስለው ገና አብነት ነው የምሄደው አለኝ። ለታክሲ የሚሆን ብር እንኳን ልንሰጠው ስንል በግድ ነው የተቀበለን። የሰው እጅ ማየት የማይወድ ሰው እንደሆነ በደንብ ያስታውቃል።
ታድያ ስንቶቻችን ነን አላህ ሙሉ ጤና ሰጥቶን በትርፍ ነገሮች የምናማርር? ስንቶቻችን ነን አላህ የመድሃኒት መግዣ ብር ሳያሳጣን አሳመምከን ብለን የምናማረው? ስንቶቻችን ነን ከኛ በላይ ስላሉ ሰዎች እንጂ ከኛ በታች ስላሉት የምናስበው?
"إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ
አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነውና፡፡ ግና አብዛኛዎቹ ሰዎች አያመሰግኑም"
ይላል አላህ በቁርዓኑ ላይ
ወላሂ ብዙዎቻችን አላህ የሰጠንን ፀጋ ብናውቀው ለሰከንድም ባላማረርን ነበር። አላህ ጤና የሰጠህ ወንድሜ ሆይ፣ አላህ ለህክምና የሚሆን ገንዘብ ያላሳጣሽ እህቴ ሆይ፣ አላህ የታክሲ ገንዘብ ያላሳጣን ሰዎች ሆይ እስኪ አልሃምዱሊላህ እንበል።
አልሃምዱሊላህ ረቢል ዓለሚን።
✍️Hassen Hidaya
በዚህ ቻናል⬇️?
✔ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
✔ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
✔ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
✔ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️?
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube
Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886
ቴሌግራም⬇️?
https://t.me/ZEKR_MENZUMA
ኢሬቻ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ"፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
አምላካችን አሏህ መለኮት ነው፥ “መለኮት” ማለት "ሁሉን ነገር የሚሰማ፣ ሁሉን ነገር የሚመለከት፣ ሁሉን ነገር የሚያውቅ፣ ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ በሁሉን ነገር ላይ ቻይ" ማለት ነው። እርሱ በእኔነት የሚናገር ነባቢ እና ሕያው መለኮት ነው፥ አምላካችን አሏህ ብዙ አናቅጽ ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ "እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ"፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ”፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
"እኔንም ብቻ አምልኩኝ" የሚለው ይሰመርበት! "አምልኩኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አዕቡዱኒ" ٱعْبُدُونِ ሲሆን አምላካችን አሏህ ጥንት ለነበሩ ነቢያትም "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት የሚናገር አምላክ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ ”የምናወርድለት” ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
ሰው የተፈጠረበት ዓላማ እና ዒላማ የአምልኮ ሐቅ የሚገባውን አሏህን ብቻ ለማምለክ ነው፥ አንድ ሙሥሊም በጌታው አምልኮን ማንንም ሆነ ምንንም ማጋራት የለበትም፦
51፥56 ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
18፥110 «በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا
"ዒባዳህ" عِبَادَة ማለት እራሱ "አምልኮ" ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ስለ ኢሬቻ ትንሽ እንበል? “ኢሬቻ” ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን “ገልማ” ማለት “ቤተ አምልኮ” ማለት ነው፥ ኢሬቻ ገልማ ውስጥ በጭፈራዎቹ እና በፌሽታዎች የሚከበር በዓል ነው። ኢሬቻን የምትለዋ ቃል የምትወክለው እርጥብ ሣር ወይም አበባ በማቅረብ “መሬሆ” ማለትም “መዝሙር” መዘመሩን ነው፥ "ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" ለምትሉ ስመ ሙሥሊም ይህንን ስትረዱ ምን ይውጣችሁ ይሆን?
“ዋቃ” ማለት እኮ “አምላክ” ማለት ነው፥ "ዋቃ ጉራቻ" ማለት "ጥቁር አምላክ" ማለት ሲሆን "ዋቃ ጉራቻ" እያሉ ለወንዙ፣ ለተራራው፣ ለሐይቁ የሚደረገው የሁሉ አምላክነት”Pantheism” እሳቤ ባዕድ አምልኮ ነው። በዚህ አምልኮ ውስጥ ልመና፣ ምስጋና፣ ስለት፣ ስግደት የመሳሰሉት ይካሄዳሉ፥ ዛፍ ቅቤ በመቀባት መለማመን፣ ማመስገን፣ መሳል፣ መስገድ ባዕድ አምልኮ ካልሆነ ምንድን ይሆን?
እንደውም “ቃሊቻ” የሚለው ቃል የተገኘው “ቃሉ” ከሚለው እንደሆነም ይነገራል፥ “ቃሉ” የተባሉት መሪዎች ከአጋንንት ጋር እየተነጋገሩ ሺርክ እንደሚያደርጉ የዚህ ባዕድ አምልኮ ነጻ የወጡ ሰዎች ይናገራሉ።
ይህንን አምልኮ የሚፈጽሙ ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ሲባሉ እምነቱን የሚመሩት ካህናቱ “ቃሉ” ይባላሉ፥ ፓለቲካውን “ሲርነ ገዳ” ሲባል ፓለቲካውን የሚመሩት መሪዎች ደግሞ “አባ ገዳ” ይባላሉ።
የዚህ ባዕድ አምልኮ ስም "ዋቄፈና" ሲባል ይህንን እምነት የሚከተል ሰው ደግሞ “ዋቄፈታ” ይባላል፥ ይህ እምነት አምልኮውን የሚፈጽመው በተራራ እና በሃይቅ ወዘተ ነው። “ቱሉ” ማለት “ተራራ” ማለት ሲሆን “ቱሉ ጩቋላ(የዝቋላ ተራራ) “ቱሉ ፊሪ” “ቱሉ ኤረር” እየተባለ ወደ ስምንት ተራሮች ላይ አምልኮ ይፈጸማል፥ “ሆረ” ማለት “ሃይቅ” ማለት ሲሆን “ሆረ አርሰዴ” “ሆረ ፊንፊኔ” “ሆረ ኪሎሌ” እየተባሉ ሰባቱ የዋቃ ሃይቆች ላይ አምልኮ ይፈጸማል።
ይህንን የባዕድ አምልኮ በዓል በዓመት ሁለት ጊዜ ይከበራል፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሙሥሊም የሚያከብረው በዓል ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ብቻ እና ብቻ ናቸው፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ”
ይህ እምነት ታሪካዊ ዳራው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3000 ቅድመ ልደት እንደተጀመረ እና ጅምሩ የአንድ አምላክ አስተምህሮት እንደነበር ይገመታል ይነገራል፥ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 2007 ድህረ ልደት በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከኦሮሞ ሕዝብ ወደ 3.3 በመቶ የሚደርሰው ሕዝብ የዚህ እምነት ተከታይ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ይሄ ቁጥር ወደ 3 በመቶ ዝቅ እንዳለ ይነገራል፥ አንዳንዶች ደግሞ፦ “አብዛኛው ዋቄፈናን ከእሥልምና ጋር ወይንም ከክርስትና ጋር ቀይጦ ነው የሚያመልከው” ይላሉ። ይህ ስህተት ነው፥ ምክንያቱም የሚያመልኩት ዋቃ አንድም ቀን እንዴት መመለክ እንዳለበት አልነገራቸውም። ደግሞም “አይናገርምም” ይላሉ፥ እነርሱም ባወጡት ሰው ሠራሽ አምልኮ ያመልኩታል።
ገና፣ ፋሲካ በዓል "ቢድዓህ" ብለህ እየተቃወምክ ኢሬቻ ላይ መሳተፍ እና በዓሉን ማክበር በምን ሞራልህ ነው "ባህል ነው" የምትለው? ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። ሙሥሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩም እና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሓ ወደ አሏህ ተመለሱ! አሏህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ
"እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ" ብሎ የተናገረን አምላክ በብቸኝነት ማምለክ ምንኛ መታደል ነው? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
በዚህ ቻናል⬇️?
✔ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
✔ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
✔ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
✔ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️?
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube
ቴሌግራም⬇️?
https://t.me/ZEKR_MENZUMA
በራስህ ላይ እንዲደርስ የማትፈልገዉን በሌሎች ላይ አታድርግ!!!
በዚህ ቻናል⬇️?
✔ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
✔ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
✔ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
✔ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️?
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube
Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886
ቴሌግራም⬇️?
https://t.me/ZEKR_MENZUMA
«ሙሐመድ ቢራ?» ለምን የለም ? ማለት ጀምረዋል። ቄስ መስሎኝ በጊዮርጊስ ተጉመጥምጦ የሚቀድሰው ! እኛን ካልነካችሁ ለቅሶው አይድምቅም ማለት ነው ?
ነገ ዙልሂጃ 1 ይጀምራል በፆም ብናሳልፈው ተቆጥሮ ማይዘለቅ አጅር እናፍሳለን ነይተን እንፁመው
ከተቻለ ሁሉንም ቀናት ካልተቻለ የተወሰነውን ካልሆነ ሰኞና ሀሙሱን ካልሆነ የመጨረሻ 2 ቀናትን አላህ ይቀበለን
ጨረቃ በመታየቷ የዙልሒጃ ወር ነገ ጁምዓ አንድ ብሎ ይጀምራል! የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ሰኔ 9 ዕለተ እሁድ እንደሚከበር ታውቋል! አስሩን ቀናት በመልካም ስራ እናሳልፋቸው በዱዋ አንረሳሳ
ኡድሂያ የሚያርድ ሰው ደሞ መከልከል ካለባቸው ነገር እንዲከለከል ለምሳሌ ጥፍር :ጸጉር መቁረጥን የመሳሰሉ ከዛሬ ይጀምራል የሰማ ላልሰማ ...
በዚህ ቻናል⬇️?
✔ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
✔ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
✔ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
✔ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️?
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube
Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886
ቴሌግራም⬇️?
https://t.me/ZEKR_MENZUMA
ያስገረመኝ
```````
አሜሪካ ላይ አንድ እጅግ ታዋቂ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አለ። <አንተ አባት አይደለም!> የሚሰኝ ፕሮግራም ነው።
ፕሮግራሙ እንዴት መሠላቹ?
በፕሮግራሙ አንዲት ሴት ትቀርብና አብረዋት ዚና የፈፀሙ ወንዶችን የምትሞግትበት ነው። በዚህም ወንዶቹ የ DNA ምርመራ እንዲያደርጉና ከውርስ ጋር ያለውን ነገር ለመለየትና የልጇ አባት እንዲታወቅ ይደረጋል።
በጣም የደነገጥኩት ግን አንድ ፕሮግራም ላይ አንዲት ሴት ከ18 ወንዶች ጋር እንደተኛች ስትናገር ነው። የሚገርመው 18ቱም የDNA ምርመራ ቢያደርጉም አንዳቸውም አባት መሆናቸውን የሚያሳይ ውጤት አልተገኘም።
በዚህ የመጣም አባቱን ማወቅ ያልቻለው የ11 አመት ጨቅላ ህፃን በየቀኑ የሚያለቅስ ሲሆን ለከፍተኛ የጭንቀት በሽታም ተዳርጓል።
ፕሮግራሙ ወንዶችንም ያቀርባል ፤ ሚስቶቻቸው <<የልጅ አባት ነህ>> በሚል ለሚያቀርቡት ክስ በባሎች ጥያቄ መሠረት አንዳንድ ሚስቶች ለምርመራ የሚቀርቡ ሲሆን ከነሱም አንዳንዶቹ አጭበርባሪ ሆነው ይገኛሉ።
ፕሮግራሙ ከ1991 ጀምሮ የሚታወቅ ሲሆን በ19 ክብረ በአላት ላይ 3500 የሚሆን ፕሮግራም ያቀርባል። በእያንዳንዱ ፕሮግራም ላይ 3 ባለጉዳዮች ይስተናገዳሉ። (አስቡት የከሳሽ ተከሳሹን /የዛኒዎችን/ ብዛት)?
አቅራቢ ጣቢያው NBC የሚባል ነው።
ይህ ፕሮግራም አሜሪካውያንና ምዕራባውያን ምንያህል በስነምግባራቸው ውድቀትና በዘር መጥፋት ጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን በግልፅ ያሳያል።
እንግዲህ ኢስላምን የሚዋጉት እዚህ የወደቀ ደረጃ ላይ ሊያደርሱን ነው። ኢስላም ለሴት ልጅ መብት የነፈጋት ይመስል <የሴት ልጅ መብት> <የፆታ እኩልነት> እያሉ የሚያደነቁሩን ለዚህ ነው። (አላህ ያደንቁራቸውና)
እንደዚ አይነት ፕሮግራሞች በአሜሪካ የሚገኙ ሴቶች (እናቶች) የልጆቻቸውን ትክክለኛ አባት በማጣት ምን ያህል እየተሰቃዩ እንደሚኖሩም ማሳያ ነው።
አላህ ዘርና ክብር እንዲጠበቅ ብሎ ያስቀመጠውን ድንበር በነፃነት ስም እንዲደፈር ማድረግ ድንቁርና እንጂ ሌላ አይደለም።
أُو۟لَٰٓئِكَ كَٱلْأَنْعَٰمِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْغَٰفِلُونَ
እነዚያ (ከሀዲያን) እንደ እንስሳ ናቸው፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ (ከእንስሳም የባሱ ናቸው)
በዚህ ቻናል⬇️?
✔ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
✔ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
✔ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
✔ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️?
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube
Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886
ቴሌግራም⬇️?
https://t.me/ZEKR_MENZUMA
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago