BekAlu ShuMye??

Description
For more..... https://www.facebook.com/profile.php?id=100084623820161&mibextid=ZbWKwL
We recommend to visit

Telegram stands for freedom and privacy and has many easy to use features.

Last updated 1 month, 2 weeks ago

Roxman
Roxman
12,975,749 @developer

Sharing my thoughts, discussing my projects, and traveling the world.

Contact: @borz

Last updated 1 month, 3 weeks ago

Official Graph Messenger (Telegraph) Channel

Download from Google Play Store:
https://play.google.com/store/apps/details?id=ir.ilmili.telegraph

Donation:
https://graphmessenger.com/donate

Last updated 7 months, 1 week ago

hace 5 meses

መውደድ ወዳጅ ሲያጣ

@Bekalushumye

hace 6 meses, 1 semana

[ድፍን ድርሰት*]

?
____
¹
ትልሙንና ህልሙን —···
(በመቼት በሴራ) እያጠላለፈው ፤
ወጉን ትረካውን (በቀናቶች ክፍል)
(በገፁ በአንቀፁ) እየሸራረፈው ፤
ዓለምን በቃሉ....
(በፈጠራው ቀለም) ነክሮ የነደፈው
ደራሲው ፈጣሪ (ስለሁለታችን)
ስለ እኔ ስላንቺ — ምን ይሆን የፃፈው?
²
አፈር ከሞላበት (አመድ ከለበሰው)
(ከመጣው ከሄደው) ከተመላለሰው
ከአምና ከዘንድሮ (ከዛሬ ከድሮ)
የተከመረውን (ጥራዝ እያወጡ )
(ሕይወትን ዘርግተው) ቢገልጡ ቢገልጡ ፤
የእግዜር ድፍን ድርሰት አይገኝም ጭብጡ ።
³
(“አትመጪም ወይ?” ስልሽ...)
—··· “እመጣለሁ” ብትይ ፤
(ለመንገድ የሚሆን....)
—··· ስንቅ ብታስከትይ ፤
ልብሽ ቢሰናዳ —·· እግርሽ ቢበረታ፤
(የጎዳናው ቀያሽ የመንገዱ ጌታ....)
ደራሲው ፈጣሪ — ·· የመቼት የቦታ ፤
ምን እንደሚበጥስ
ምን እንደሚቀጥል...
ማንን እያነሳ
ማንን እንደ ሚጥል....
አውቄው አላውቅም ገምቼው ቀድሜ
የታል ስለ ነገ ፍፁም ድምዳሜ?
ስንት ነው በምድር የተሰጠኝ ዕድሜ?

(ማን ይሄን አወቀ? አሁንስ ማን ያውቃል‽)
“እመነኝ” ብትይኝ አፍሽ ቢያወጣ ቃል ፤
(ጠዋት "ለምለም" ያልነው
ባመሻሽ ይደርቃል)
ስውር ደራሲያችን የላይኛው አካል
ነባሩን ቀይሮ አዲስ ይተርካል ።
ይለየን ይሆናል...
(ያርቀን ይሆናል) በጊዜ – በቦታ ፤
ከቃል የበለጠ — ጌታ ነው “ሁኔታ” ።
(ይሆኑታል እንጂ...)
ይኖሩታል እንጂ ....
“ይግባኝ” አይባልም — እንዲህ ያለ ፍርጃ
አንቺን አምንሻለሁ — እግዜሩን ግን እንጃ ።
___
?*@Bekalushumye

hace 6 meses, 2 semanas

*··— ዲያቢሎስ ሀገሩ የት ነው ? .........
“የሠው ልብ” አይደለምን !? —··

___
“??? ??? ?????” የተሰኘ ፊልም ላይ ያለ አንድ ገፀ - ባህሪ እንዲህ ሲል ይደመጣል....

«?? ??? ?????? ?? ??? ?????? ???...
??? ????? ?? ???? ?? ??? ????? ?? ??????
?? ?????? , ??? ?? ???? ?? ????????? ???? ???? ?????? ????? ??? ????? ?????.»

ትላንት ያንን አሠቃቂ ድርጊት ከሰማሁ በኋላ ቀኑን ሙሉ ሲመላለስብኝ የነበረ ሃሳብ ነው — ይሄ። ዓለምን ጠላሁ ፤ ራሴን ደግሞ ፈራሁ ። ውስጣችን ጥልቅ ውቅያኖስ ነው አይደል!? ሆዳችን ከሀገራችን ይሰፋል ። እና በዚያ ውስጥ ማን ያልፋል? የልባችን ክፍሉ ምን ያህል የእኛ ነው? ከገላችን ውስጥ ከእኛ ሌላ ማን ይኖራል? በጥልቅ ዝምታ እና ብቸኝነት መሀል ወደ ጭንቅላታችን የሚመጡ ሃሳቦች የማን ናቸው? በደም ስራችን ስር ከደማችን ሌላ ምን ይመላለሳል? በራሳችን ባለቤትነት ምን ያህል እርግጠኞች ነን? ትከሻችን ላይ ተፈናጥጦ የሚጋልበን እርኩስ መንፈስ ቢኖርስ?
ወይም በውስጣችን ውቅያኖስ ስር እየተርመሰመሰ የሚያዝዘን ጋኔል? ? ????? ??? ????? ?????? ??.
ወደ ልባችን ገብተን ማን አብሮን እንደሚኖር እንፈትሽ እስኪ...ደቂቃ በማትሞላ ቅጽበት ስር በልባችን ጎዳና በኩል ሽው ብላ የምታልፈውን እንግዳ ስሜትና ሃሳብ ጉሮሮዋን አንቀን እንመርምራት—···“ከየት ነሽ ?” ፡ “የማን ነሽ?” ፡ “ማን አመጣሽ?” እንበላት ። አጠገባችን ወዳሉ ሰዎች ከመዞራችን በፊት ወደ ራሳችን እንመልከት ። ዲያቢሎስ ገላና መልካችንን ለብሶ አብሮን መኖር ከጀመረ ከራርሟልና ለድርጊቶቻችን ማን ኃላፊነት እንደሚወስድ አናውቅም።
በዕውቀቱ ስዩም በአንድ ግጥሙ ላይ....
“...ሰይጣን ይሉት ነገር፥ የተጭበረበረ
ዋዛ ነው ቧልት ነው ፥ ብዬ አስብ ነበረ
ይሄው እውነት ሆኖ፥ ዋዛና ተረቱ
ባይኔ በብረቱ
ዲያቢሎስን አየሁት፥ በሸሚዝ ዘንጦ
እልፍ ግዳይ ጥሎ ፥ ቸብቸቦ ጨብጦ
” ይላል ።

ዲያቢሎስ ሸሚዝ ይለብሳል ። ዲያቢሎስ ያስቀድሳል ። ዲያቢሎስ ሶላት ይሰግድ ይሆናል ። መልኩም እንደእኔና እንደእናንተ ያለ ነው ።
ተረት የሚመስለን ጭራቅ ሰባት ቅል ራስ እና ሀያ ረጃጅም ጥፍሮች የሉትም ። ቆንጆ ነው ። መልከመልካም ። ምናልባት ግጥምና ወግ ይጽፋል ። ኳስ ያያል ። የፌስቡክ አካውንትም አለው ። “#ፍትሕ ለምናምን” ብሎ ይፖስታል ።
አስባለሁ ያቺን ለጋ ህፃን ደፍሮ የገደለው ዲያቢሎስ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ወንጀል ሲሰማ ከሰው ለመምሰል ብሎ “እንዴት ያለ ዘመን ላይ ደረስን? ” ብሎ ይሆናል ። ቦታው ላይ ሲቆም ግን ያደረገውን አደረገ ። እኛ ነገ አንደግመውም ወይ?
ሰው ብቻ ነን ወይ የምር?

ቅዱስም...ንጉሥም....እርኩስም....*?
_
@Bekalushumye

hace 7 meses, 3 semanas

*[ስለ ልብሽ.....]
__
[ ፩ ]

¹
በዕድሜ ጎዳና ላይ
ብዙ መንገድ ሄደሽ ፤
ገደል ጉራንጉሩን
ተራራውን ወርደሽ ፤
ሽቅብ ያለፍሽውን
ቁልቁል ተመልሰሽ ፤
ባገኘሻት አፍታ —
ደረትሽን ዳብሰሽ.....
(ድለቃ - ሙዚቃ) ትርታ — ስታጪ ፤
“ልቤ ሞቷል” ብለሽ አትደናገጪ ።
_
ባይጮኽ እንደ'ኛ
ትርታ ቅኝት.....
ድቤ (ከበሮ) ባይሆን አጀቡ ፤
(ልብሽ ልብ አለው....)
ያንጎራጉራል እሱም በልቡ ።
(ሰምቼዋለሁ ....!)
እሰማዋለሁ....
ጊዜ ጌታው በቀለሙ
በቀኑ ላይ ፅልመት ሲስል
ጨለም መሸት ደንገዝ ሲል
በሌሊቱ በድቅድቁ
ሁሉም ሲተኙ ሲወድቁ
(አንቺም ..)
ተኛሁ ብለሽ ካረፍሽበት ...
እንደ መንፈስ ስውር ጥላ
በዘጋሽው በር አልፌ ፤
(እገባና....)
ደረትሽ ላይ ተለጥፌ ፤
(“የለም ጠፍቷል
ሞቷል” ያልሽው)
ዳብሰሽ ዳብሰሽ
ያልሰማሽው....
ያልተጨመረበት ድቤ
ያልታጀበ በከበሮ ፤
የልብሽን ለስለስ ያለ
የለሆሳስ እንጉርጉሮ ፤
ደስስ እያለኝ እሰማለሁ ....
(ሌሊት ሌሊት እመጣለሁ ።)
²
ዘምቶ ባይዋጋ ....
ባይሆን ፊታውራሪ ፤
«ጊዜ `ሚጠብቅ ሰው
ይባላል ወይ ፈሪ !?»
(እንዳለው አዝማሪ......)
የሚመስል ዘፈን እያንጎራጎረ ....
ተኝቶ (ድምፁን አጥፍቶ)
በዘዴ ሲያልፈው ወጀቡን ፤
ላይ ላዩን በረሃ መስሎ
ውስጥ ውስጡን አውቆ ማበቡን ፤
ማን አየው የልብሽ ልቡን !?
_
ያለም ሁካታ ሸፍኖት
ጫጫታው ጆሮውን ደፍኖት
ልብሽን ሳይሰማው ቢቀር
ውስጥሽም እየታለለ ፤
«ልብ አልባ ኦና !
ባዶ ነኝ » አለ ?!
ካንቺም ወዲያ “ሙሉ” የለ !!
ካንቺም ወዲያ “ልባም” የለ !!

[፪]

በዕድሜ ጎዳና ላይ
ብዙ መንገድ ሄደሽ ፤
ገደል ጉራንጉሩን
ተራራውን ወርደሽ ፤
ሽቅብ ያለፍሽውን
ቁልቁል ተመልሰሽ ፤
ባገኘሻት አፍታ —
ደረትሽን ዳብሰሽ ፤
የራቀብሽ ድምፁ
ያጣሽው ትርታ ፤
ይጠራሽ ይሆናል
የማታ የማታ ።
(አሁን ግን ይብቃሽ!)
አትድቂ ደረት — አቁሚ ለቅሶ ፤
(አውቆ በዘዴ ድምፁን ቀንሶ ...)
ቀን ጠበቀ እንጂ — ቀን ሊያወጣልሽ
ልብሽ ዝም ሲል — “ሙት” አይምሰልሽ ።
___*@Bekalushumye

hace 8 meses, 2 semanas


ፍቅርንስ ያፍቅሯት ጌቶች ....
(መውደድ በእነሱ ያምራል )
በልዑላኑ — በሀያላኑ —
በንጉሦቹ ፤
(በፈላጭ በቆራጮቹ )
ጊዜም ስልጣንም ባላቸው ፤
ሁሉን በሚቻላቸው ።

(እንደ እኔ አይደሉም እነሱ....)

የልብን መሻት ይሞላሉ ....
እንባን ማበስ ይችላሉ ....
(ለሚጠሉት ባይሆን እንኳን )
ለሚወዱት ይደርሳሉ ።

(ለምን ወደድኩሽ እኔ ግን?)

“መውደድ” (የንጉሥ ዘመድ)
በባሪያ ልብ ምን ይሰራል?
ላፈቀሩት ካልደረሱ ....
ማፍቀር ብቻ ምኑ ያምራል?

ባይሽም በእሳት መካከል
ባለጊዜ ሲያንገላታሽ
ቢሰማኝ ጩኸት እሪታሽ
አድንሽ ዘንድ ....
(አተርፍሽ ዘንድ )
አቅመቢስ ነኝ ድኩም ባሪያ
ስስ ጉልበቴ አንሶብኛል ፤
ታዲያ ....
(“ደረስኩልሽ” ማለት አቅቶኝ)
“ወደድኩሽ” ብል ያምርብኛል?

ለወደዱት አካል ለወደዱት ገላ ....
ለመድረስ የሚችል ከሌለበት አቅም
ያሳምማል እንጂ መውደድ ምን ሊጠቅም?
ካላበስኩልሽ እንባሽን
ካላከምኩት ህመምሽን
ካላተረፍኩት....
ቆሜ ካየሁት ልብሽ ሲሰበር ፤
ባልወድሽ ይሻለኝ ነበር ።

²
ፍቅርንስ ያፍቅሯት ጌቶች....
(መውደድ ያምራል በእነሱ ፤)
ቀላል ነው እንባ ማበሱ ፤
(ላፈቀሩት ሰው መድረሱ ። )

ጌታም ራሱ ሁሉን የሚችል....
(የማርያም ልጇ) የዓለም ንጉሥ ነው
ስለመውደዱ ተሰቅሎ ያልፋል ፤
ደሙን አፍስሶ ፍቅሩን ያተርፋል ፤
ሞቱ እንኳን ሚዛን ይደፋል ።

(ታውቂያለሽ ይሄንን)
የንጉሥ ነው እንጂ
የጌታ ነው እንጂ
ምንም ለውጥ የለውም
(ተዓምር አይፈጥርም ) የአንድ ባሪያ መጉደል
እኔ ብሞትልሽ አትተርፊም አይደል !?
_*@Bekalushumye

hace 8 meses, 3 semanas


“ግፋ” ብለኸው — እግርህን
እያፈስስከው — ላብህን
ስታሯሩጣት — ወደ ፊት...
(ስትከተላት ህልምህን ...)
አሁን ግን በቃህ — ደክሞሃል
አየሁህ መንገድ — ወድቀሃል ።

“በርታ - ተነስ” — አልልህም
“” ደግመህ ሩጥ” — አልልህም
(“ውደቅ እረፍ” — ግዴለህም ።)

♟️

ያቺን ብሩህ ጊዜ...
(ያቺን ፍፁም ደስታ....)
ሮጠህ ብታጣት፤
ወድቀህ ፋታ ስጣት ።
(ወይም ደግሞ ቆመህ
በሩቅ ተመልከታት....)
ወዴትም አትሄድም....
ክብ ነው መሮጫው.....
(ምድርስ ክብ አይደለች?!)
ት ደ ር ስ ል ሃ ለ ች — ባትደርስባትም ፤
ወደ ፊት መሄድ ነው — እርምጃ መግታትም።
---
(አትልፋ ደጋግመህ ....)
እጅ ስጥ ግዴለም — “በቃኝ” በል አንዳንዴ ፤
ተስፋ ካልቆረጡት — ይቀጠላል እንዴ ?!

♟️

[ተራራ ሲገፉ....
ወደ ላይ ሲከንፉ...
ሰማይ የፈለጉት...
መሬት ወድቆ እንደሆን
መች ያስተውሉታል !?
(ዕድሜ ይስጠው ድካም)
ሲሮጡ ያጡትን — ሲያርፉ ያገኙታል ። ]
——
²
አንተም ወዳጄ ምስኪኑ እረኛ ፤
(ፍሬ ለማውረድ....)
መዝለልህ ይብቃ....
ዛፉ ስር ተኛ ።

(መተው መልካም ነው....)
“አልቻልኩም” ማለት ያስችልልሃል ፤
(ሽቅብ ወደ ላይ ስትንጠራራ...)
ያልደረስክበት ጣፋጩ ፍሬ....
ሲበስል መሬት — ይወድቅልሃል ።

“ተነስ” — አልልህም...
“ሩጥ” — አልልህም....
“እረፍ” — ግዴለህም ።
_@Bekalushumye ታህሳስ ፪ — ፳፲፮ ዓ.ም*

hace 1 año, 7 meses

___
ኣውቃታለሁ እኮ.....
ንትም ስትፈጠር መልዐክ ነበረች ፤
ዛሬ ግን ስትመጣ....
(ክንፏን ሰይፏን ጥላ)
ሠው መምሰል ሞከረች ።
(ዝቅ ልትል ጣረች .... )
አልተሳካላትም !
እንደኔ ሠው መሆን አልሰመረላት
`ም ።

(ብቻ ግን ገረመኝ.....)
ጉሙ ተጠረገ — ጭልም ያለው በራ ፤
ዓይኔ ተገለጠ — ከመምጣቷ ጋራ ።
(የጠቆረው ሁሉ — እያየሁት ፈካ ፤)
እሾህ የመሰለኝ — አበባ ነው ለካ !?
("ለካ.." ማለት ጀመርኩ.....)
ለካ ፀሐይ ውብ ነበረች......
ለካ ዝናብ እርጋታ አለው.....
ወፍ ስትዘምር ድምጿ ያምራል.....
ለምለም ነበር ሳር ቅጠሉ ፤
(እንዴት እንዴት እስከ ዛሬ —
አልታየኝም ይሄ ሁሉ?! )

ለካስ ለካስ እግዜር አለ....
(ለካስ ለካስ እግዜር አለ....)
ለቅጽበት ሰማሁት ድምጹን ፤
(በፊቷ በኩል ውልብ ሲል...)
ኣየሁት ሞገሳም ገጹን ።

ይሄው መጣች!
(ይሄው መጣች!)

ተቀደደ መጋረጃው...
ጎህ ለበሰ ጥቁር ግምጃው...
ተራራው ተገፈተረ ....
ጽልመቱ ጠፋ በረረ ፤
(ይሄንን ታምር እንዳላይ)
መቅረቷ ጋ`ርዶኝ ነበረ ።
×
|ሓምሌ ፫ --------|~~@Bek~~alushumye

hace 1 año, 7 meses

[ሙሾ ለውቢት.....]

ዘመድ ...ዘመድ..ጓደኞቿ---
ወዳጅ.. ወዳጅ... አዝማዶቿ
(የሚያውቋት ሰዎች በሙሉ...)
"ሞተች "
"ሞተች"
"ሞተች " አሉ ።
(ዋይታና ዕምባ ቀላቀሉ ።)
አለቀሱ አለቀሱ ፤
ፈራ.. ፈራ...ፈራረሱ....
(አመድ አፈር ነሰነሱ)
ጥቁር ሸማ ማቅ ለበሱ ።

ደግሞ ገላዋን ከፍነው....
(በሆነ ጨርቅ አፍነው)
እየጮኹ---( "እሪ" እያሉ ፥)
ጉድጓድ ይቆፍራሉ ።

ለምን ..ለምን... ለምን ነበር?
(ስትገንዟት ዝም አልኳችሁ...)
አሁን ደግሞ ልትቀበር ?!
ኧረ አይሆንም
ኧረ አይሆንም
ውበቷ በምስጥ አይበንም
አካሏ በትል አይተንም ።

(አይሆንም አይደረግም !)
አጥንቷን አፈር ሊበላው?!
ገላዋ ፈርሶ ሊያዘግም?!

(ወደ መሬት ጥላችሁ....)
ውበቷን አፈር ልትጭኑት?!
አካሏን ድንጋይ ልትከድኑት?!
(ህም...!)
በሉ ጉድጓዱን ድፈኑት ።

ይቅር አፈሩን መልሱ.....፤
ቅበሯት ከደመናው ላይ
ይሻላል አየር ከየብሱ ፤
(ገላዋን አፈር ቢነካው....)
ምን ይላል እግዜር ራሱ !?

{}
@Bekalushumye
| ~~የካቲት 6--2014 ዓ.ም~~
በቃሉ ሹምዬ |

hace 1 año, 7 meses

*[ል ክ ፍ ት...]
.
አዉቃለሁ ጠልተሽኛል፣
አትወጂኝም ይገባኛል፣
መቼስ አንዴ ለክፈሽኛል...
(መቼስ አንዴ ታምሜያለሁ...)
ዛሬም አንቺን አስባለሁ።

(አዎ...)
ከሄድሽ በሁዋላ...
(ምወዳቸዉ ሴቶች)
ማደንቃቸዉ ሴቶች
(ከኔ ጋር ያደሩ)
ከኔ ጋር የዋሉ፣
በጥቂቱም ቢሆን...
አንችን ይመስላሉ።
.
ተመልከቻት እሷን፣
ዉብ አረማመዷን
እግር አነሳሷን፣
ያ'ነጋገር ስልቷን
ደግሞ አለባበሷን።
"ቁርጥ ራስሽን!"
(ማለት ቢያስቸግርም፣)
የሆነ ነገሯ...
እንዳ`ንቺ እንደሆነ
አልጠራጠርም።
(እያት ደግሞ ያቺን...)
ካ'ፍንጫዋ በታች|
ያለዉ ከፊል ገጿ፣
ከንፈርና ጥርሷ|
የንግግር ድምጿ።
ደግሞ ሳቅ ስትል...
የጉንጯ ስርጉዳት፣
ያንቺን በመምሰሉ
ነፍሴን ሲያሻፍዳት፣
ልቤን ሲያሟሽሻት...|
አየሽኝ?| አየሻት?


(እናልሽ...)
ከብዙ ሴቶች ላይ
ጥቂት አንችነትን...
እያነፈነፍኩኝ፣
ያቺንም..|ያቺንም...
"ወደድኩዋት" ስላልኩኝ፣
ባ'ገር በመንደሩ| "ሴሰኛ" ተባልኩኝ።
ሰማሽልኝ ስሜን?
ልክፍቴን ህመሜን?
ስራብሽ ስጠማሽ..|
በሰዉ አፍ መክረሜን?
አየሽልኝ ህልሜን..?
(አንቺን ባላገኝሽ)
ካ'ምሳያሽ ጋራ ነኝ|
እድሜ ዘላለሜን።*
{}
@Bekalushumye
~~ሚያዚያ 17--2014 ዓ.ም~~
በቃሉ ሹምዬ

We recommend to visit

Telegram stands for freedom and privacy and has many easy to use features.

Last updated 1 month, 2 weeks ago

Roxman
Roxman
12,975,749 @developer

Sharing my thoughts, discussing my projects, and traveling the world.

Contact: @borz

Last updated 1 month, 3 weeks ago

Official Graph Messenger (Telegraph) Channel

Download from Google Play Store:
https://play.google.com/store/apps/details?id=ir.ilmili.telegraph

Donation:
https://graphmessenger.com/donate

Last updated 7 months, 1 week ago