Great_Abyssinia

Description
የታላቋ አቢሲኒያ መንደርደሪያ
.
.
.
ያላችሁን መልዕክት ጥያቄ በ @Tekit_leEthiopia_bot እና @Great_Abyssinia ማድረስ ይችላሉ
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

1 day, 8 hours ago

ስንቶቻችሁ ናችሁ ድሮ የተከፈተ ግሩፕ እንደሚሸጥ የምታውቁት በፍጥነት የዋጋ ቅነሳ እየተደረገ ስለሆነ ያላችሁ ሰዎች በውስጥ መስመር @Great_Abyssinia ፃፉልኝ

Old group ያለው ማለትም የቆየ Group ያላችሁ እየገዛን ነው እንዳያመልጣችሁ ግዜው ሳያልፍ ሽጡት::

ማሳሰቢያ‼️

1, old group ሲያመጡ  history clear እንዳያረጉበፍፁም ‼️

2, members ብዛት ለውጥ የለውም
    ዋናው groupፑ old text ይኑረው.

በነዚህ አመት ላይ የተከፈተ👇 :
2023 (first 8 months)
2022 - 💸💸
2021 - 💸💸
2020 - 💸💸
2019-16 - 💸💸
ያላችሁ

ከላይ በጠቀስኳቸው አመት ላይ የተከፈተ ግሩፕ ያላቹ በውስጥ በመምጣት መሸጥ ትችላላችሁ።
@Great_Abyssinia
Inbox

1 day, 16 hours ago

የማይቻል ነገር የለም

የሆነ ሰው እስኪችለው ድረስ የማይቻል ይመስል ነበር የማይቻለውን ብዙወች ችለዋል ከነዚህ ውስጥ ማሚቱ ጋሸ አንዷ ነች ማሚቱ ወደ ዶ/ር ካትሪን ሀምሊን  የፌስቱላ በሽተኛ ሁና ለመታከም ነበር የሄደችው ከበሽታዋ ስትፈወስ አንዳንድ ስራወችን በማገዝ አገለግላለሁ ብላ በረዳትነት እያገለገለች ቀጠለች ዶ/ር ሀምሊን ስታክም ታያለች ትከታተላለች በመጨረሻም ያለምንም የህክምና እውቀት የቀዶ ጥገና ስፔሻል ሆነች በቁጥር የማታውቀውን ብዙ ቀዶ ህክምና አድርጋ ለብዙ ሴቶች ፈውስ ሁናለች በእንግሊዝና በአሜሪካ እውቅናን አግኝታለች የማይቻለውን ነው የቻለችው።ራይት ብራዘር   አውሮፕላን በሌለበት ዘመን ከመሬት ተነስተው አውሮፕላንን በሰማይ ላይ ማብረር ችለዋል አየህ የሆነ ሰው እስኪችለው ድረስ አይቻልም ነበር አይቻልም ያልከው ነገር አንተን እየጠበቀ ቢሆንስ? እችላለሁ በል ለአእምሮህ እንደምትችል ደጋግመህ ደጋግመህ መንገር አለብህ እንደምትችል ከነገርከው እምነቱ ይሆናል አእምሮህ እስኪያምን ጊዜ ይወስዳል አእምሮህ እንደምትችል ያመነ ቀን ተዐምር እስኪመስልህ ድረስ ህይወትህን ትቀይራለህ።

የተዋበ ሳምንት ይሁንላችሁ!

SHARE  #LIKE  #JOIN
👇👇👇👇
🎁  https://t.me/TekitLeHagerachin

በመሰልጠን ሕይወቱን መቀየር የሚፈልግ "ራሴ ላይ ለመሥራት ወስኛለው" ብሎ ይላክልኝ።
👇👇👇
@Great_Abyssinia
@Great_Abyssinia

5 days, 17 hours ago

አባት የመጀመርያም የመጨረሻም የሆነ ብቸኛ ልጁን ሊድር ድል ያለ ሰርግ ደግሶ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆቹን ጠርቶ የምሳ ግብዣውን እየተዟዟረ ይመለከታል።

‹‹ማን ቀረ ማን መጣ›› የሚለውን በትኩረት እየተመለከተ ሳለ የቅርብ ጎረቤቱን ከእይታው ያጣዋል። ግራ በመጋባት እየተዟዟረ ቢመለከትም ጎረቤቱንም ሆነ የጎረቤቱን ልጆች ሊያይ አልቻለም።

‹‹የልብ ወዳጄ በዛሬ ቀን እንዴት ከጎኔ ይጠፋል›› እያለ በንዴት ስሜት በመብሰልሰል ላይ ሳለ ድንገት የጎረቤቱ ልጅ ብቅ አለና በፍጥነት ትንሽ ምግብ ቀማምሶ ትቶ ወጣ።

ይህን ትዕይንት የተመለከተው ደጋሽ በንዴት ተብከነከነ። የአባቱ በደስታው ግዜ አለመገኘት ሳያንሰው ልጁ መጥቶ በምግቡ አላግጦ መውጣቱ አበሳጨው።

በዚህ መሀል የሙሽራው አጃቢዎች ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት ጉዞ ሊጀምሩ መኪናቸውን ማንቀሳቀስ ሲጀምሩ ምግቡን ቀማምሶ በፍጥነት የወጣው የጎረቤቱ ልጅ ሙሽራውን ለማጀብ ከግቢ መኪናውን ይዞ ይወጣል።

አባት ተበሳጨ፣ ንዴቱን መቆጣጠር ቢያቅተው በቁጣ መንፈስ ተሞልቶ ወደ ጎረቤቱ ልጅ በመሄድ፦‹‹አባትህ ጎረቤቴ ሁኖ ደስታዬ ላይ አልተገኘም፣ ታላላቅ ወንድሞችህም እንደዝያው፤:ታድያ አንተ ምን አስበህ ነው በምግብ አላግጠህ ትተህ የወጣኸው? አሁን ተመለስ ያንተን አጃቢነት አንፈልግም›› ብሎ መለሰው። ልጁም እቤቱ ገባ፤ ሰርገኛዎችም ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት አቀኑ።

በመጨረሻም አጃቢዎች ሙሽሮችን ይዘው ወደ ቤት በመግባት የደስታቸው ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ቀኑ ሲጨልም ሁሉም ተበታትኖ ሰርግ ቤቱ በሙሽሪት እና በሙሽራው ጭር አለ።

አባት አሁንም በጎረቤቶቹ ንዴት እየተብሰለሰለ ነው። ድንገት ከመሸ ያለ ወትሮው የጎረቤቱ ጊቢ ተከፈተ። የሙሽራው አባት እየተመለከተ ነው።

የጎረቤቱ ልጆች በትከሻቸው አንዳች ነገር ተሸክመው ከቤታቸው ሲወጡም ተመለከተ። ፍፁም ዝግታ እና እርጋታም በሚስተዋልበት እርምጃ ልጆቹ ይራመዱ ጀመር።

የሙሽራው አባት ጠጋ አለ። ፦‹‹ምንድነው?ማንን ነው የተሸከማችሁት ›› ሲልም ጠየቃቸው።

‹‹አባታችን ጠዋት ሞቶ ነው፤ ሲሞትም በሱ ለቅሶ ምክንያት ያንተ ደስታ እንዳይስተጓጎል መሞቱን ከሰርግህ በፊት ለማንም እንዳንናገር እና ድምፅ አውጥተን እንዳናለቅስ ተናዞልን ነበር። ለዝያ ነው ድግሱ ላይ መገኘት ያልቻልነው። ›› በማለት አባታቸውን የተሸከሙት ልጆች ጉዳያቸውን አስረዱ።

ደጋሽ ተፀፀተ፦ ‹‹እኔ በሱ ቦታ ብሆን ይህን የማድረግ አቅም አይኖረኝም ነበር›› ሲልም የቁጭት እንባ ያነባ ጀመር።

በህይወታችን ችላ ያሉ እየመሰሉ በቁስላቸው ደስታችንን ላለማበላሸት ሲሉ ከአከባቢያችን የሚርቁ ሰዎች አሉና ልብ ያለው ልብ ይበል።

SHARE  #LIKE  #JOIN
👇👇👇👇
🎁  https://t.me/TekitLeHagerachin

በመሰልጠን ሕይወቱን መቀየር የሚፈልግ "ራሴ ላይ ለመሥራት ወስኛለው" ብሎ ይላክልኝ።
👇👇👇
@Great_Abyssinia
@Great_Abyssinia

1 week, 3 days ago

እንኳን ለከተራ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ

2 weeks, 5 days ago

ምን አይነት ሕዝብ ነው?
የተቃኘ እይታ

የተቃኘ እይታ ማለት የአንድን ሁኔታ ጥሩነትም ሆነ መጥፎነት በጥቅሉ ከመገመትና ቀድሞውኑ በአንድ አቅጣጫ በተዘጋ እይታ ለማየት ከመዘጋጀት ይልቅ ግራና ቀኙን ባመዛዘነ እይታ ለመመልከት መዘጋጀት ማለት ነው፡፡

አንድ በእድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ወደፊትና ወደኋላ እንዲወዛወዝ የተሰራውን ወንበራቸውን እንደ ልማዳቸው ወደደጅ አውጥተው የልጅ ልጃቸውን በጉልበታቸው ላይ አስቀምጠው ከተማ መሃል ባለው ቤታቸው ደጃፍ ላይ የሚጫወቱትን ልጆች ያያሉ፡፡ በአንድ ጎኑ የልጆቹ ጨዋታ ደስ ይላቸዋል፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ብዙም የሚሰሩት የሌላቸው ጡረተኛ ስለሆኑ በዚያ ተቀምጦ ጨዋታውን በማየት ጊዜን ማሳለፍ የየቀን ልማዳቸው ነው፡፡  እነዚህ ልጆች በጨዋታ መሃል ሲጣሉ እኝህ አዛውንት ካሉበት ሆነው ከፈ ባለ ድምጽ በማድረግ ያረጋጓቸዋል፡፡ ልጆቹ ስለሚታዘዟቸው ደስታቸው ይህ ነው አይባልም፡፡

የዛሬዋ ቀን ትንሽ ለየት ትላለች፡፡ ከየት መጡ የማይባሉ ጎብኚዎች (ቱሪስቶች) እጅግ የገዘፉ የጉዞ ሻንጣዎቻቸውን በጀርባቸው ላይ አዝለው በከተማዋ ላይ ፈስሰዋል፡፡ በዚያ ከሚያልፉት ቱሪስቶች መካከል አንዱ በመንገድ ላይ በድርቅና ከተዋወቀው “የመንደር” አስተርጓሚ ጋር ወደሳቸው ቀረበና ጥያቄ ሊጠይቃቸው እንደሚፈልግ ገለጸላቸው፡፡

ፈቃዳቸውን ካገኘ በኋላ እንዲህ አለ፣ “ይህች ከተማ ምን አይነት ከተማ ነች? ለመሆኑ ሕዝቧስ ምን አይነት ሕዝብ ነው? ክፉ ነው ወይስ ደግ?” አላቸው፡፡ ሽማግሌው መልሰው፣ “አንተ የመጣህባት ከተማ ምን አይነት ከተማ ነች? ሕዝቡ ክፉ ነው ወይስ ደግ?” በማለት ጥያቄውን በጥያቄ መለሱለት፡፡ ቱሪስቱ በመመለስ፣ “እኔ የመጣሁባት ከተማ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ ደግና እጅግ መልካም ነው” አላቸው፡፡ ሽማግሌውም፣ “እዚህም እንዲሁ ነው፣ ሁሉም ሰው ደግና እጅግ መልካም ነው” አሉት፡፡ 

ቱሪስቱ ምስጋናውን አቅርቦ ገና ከመሄዱ እሱ ከመጣበት ከተማ የመጣ ሌላ ቱሪስት ወደ እሳቸው ቀረበ፡፡ እነዚህ ቱሪስቶች ከሃገራቸው ከመነሳታቸው በፊት ያንን ብቸኛ ጥያቄ ጠይቁ ብለው ቃለ-መሃላ ያስገቧቸው ይመስል ይህኛውም ቱሪስት ያንኑ ጥያቄ አዛውንቱን ጠየቃቸው፡፡ “ይህች ከተማ ምን አይነት ከተማ ነች? ለመሆኑ ሕዝቧ ክፉ ነው ወይስ ደግ” አላቸው፡፡ ሽማግሌውም ልክ ለቀደመው ቱሪስት እንደመለሱት፣ “አንተ የመጣህባት ከተማ ምን አይነት ከተማ ነች? ሕዝቡ ክፉ ነው ወይስ ደግ?” በማለት ጥያቄውን በጥያቄ መለሱለት፡፡ ቱሪስቱ በመመለስ፣ “እኔ የመጣሁባት ከተማ ያለው ሰው ሁሉ ጨካኝና እጅግ ክፉ ነው” አላቸው፡፡ ሽማግሌውም፣ “እዚህም እንዲሁ ነው፣ ሁሉም ሰው ጨካኝና እጅግ ክፉ ነው” አሉት፡፡

የአያቷን ምላሽ በመገረም ትሰማ የነበረችው ልጅ፣ “አባባ፣ ሁለት ሰዎች አንድ አይነት ጥያቄ ጠይቀውህ የተለያዩ መልሶችን እንደሰጠሃቸው አውቀሃል” አለቻቸው፡፡ አያት እንዲህ አሉ፣ “አውቃለሁ፡፡ አየሽ ጉዳዩ እንዲህ ነው፣ ሰው በሄደበት ቦታ ሁሉ ለማየት የተዘጋጀውን ነው የሚያየው፡፡ የከተማው ሰው ሁሉ ክፉ ነው ብሎ አምኖ ከመጣ ያንኑ እየመረጠ ያያል፣ ሰው ሁሉ ደግ ነው ካለ ደግሞ ያንኑ እየለቀመ የማየት ዝንባሌ አለው፡፡ ለእነዚህ ቱሪስቶችም የመለስኩላቸው ይህንኑ ነው፡፡ ከአንድ አይነት ከተማ መጥተው አንዱ የሃገሩን ሕዝብ ደግ ሲል ሌላኛው ደግሞ ያንኑ ሕዝብ ክፉ ሊሉ የበቁት ከአመለካከታቸው የተነሳ ነው፡፡”

የእኚህ አዛውንት አባባል እውነትነት አለው፡፡ የእይታችን ዝንባሌ በሄድንበት ሁሉ የምንመለከተውን ነገር የመወሰን ኃይለኛ ጉልበት አለው፡፡ አንድን ነገር በተዛባ እይታ መመልከት አጅግ አሳዛኝ ውጤትን ያስከትላል፤ የሌለውን እውነታ እንድንመለከትና በተሳሳተ ግምት ውስጥ እንድንኖር ተጽእኖን ያደርግብናል፡፡ በእርግጥም ከዝንባሌአችን የተነሳ ያየናቸውና ያተኮርንባቸው ሁኔታዎች ቢኖሩም እንኳ አመለካከታችን ሁኔታዎቹን ስለሚያጎላቸው ነገሮቹ ሊሻሻሉ ይችላሉ የሚል ተስፋ እንዳይኖረን ያደርገናል፡፡

የምንኖርበት ሕብረተሰብ መልካም ሕብረተሰብ ነው!!! ምድሪቱም መልካም ነች!!! እኛም መልካም መልካሙን እናስብ!!! በጎ በጎውን እንናገር !!!

“እይታ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡

#SHARE #LIKE #JOIN
????
@tekilehagerachin
በመሰልጠን የሕይወቱን ዓላማ አውቆ መኖር: ራሱን በስልጠና መገንባት የሚፈልግ ሰው "መሰልጠን እፈልጋለው" ብሎ ከታች ባለው ቴሌግራም ይላክልኝ።
???
@Great_Abyssinia
@Great_Abyssinia
@Great_Abyssinia

1 month, 2 weeks ago

ሕይወታችንን በአወንታዊ መልኩ ለመቀየር የህሊና ውቅራችን መቀየር አለበት። እኔ ባለፉት 3 ዓመታት የህሊና ውቅሬን በመቀየር ብዙ የሕይወት ስኬቶችን አሳክቻለው። ይሄንን የህሊና ውቅር ምሥጢር ተረድተው በሕይወታቸው አዲስ ለውጥ ማስመዝገብ የሚፈልጉ ሰዎችን በሳምንት ሰኞና ሐሙስ ከ2-4 ሰዓት መድቤ በነፃ ለማገልገል፡ ለማማከር ዝግጁ ነኝ። ለስኬት የተዘጋጃችሁ መለወጥ የምትፈልጉትን የሕይወት ክፍልና ጥያቄዎቻችሁን…

3 months ago

ጥቅምት እኩሌታ

ዳግማዊ ምኒልክ "ዘመቻዬ በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ።" የሚል የክተት አዋጅ በማወጅ በዓድዋ ጦርነት ድል ያደረገ ሰራዊታቸውን በወረኢሉ ያሰባሰቡት ከዛሬ 129 ዓመታት በፊት ነበር፡፡

ወረኢሉ በደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን ከደሴ ከተማ 91 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ታሪካዊ ከተማ ናት፡፡ ወረኢሉ ቀደም ባለው ጊዜ የብዙ ነገሥታት መናገሻ እና የቤተ አማራ ማዕከል እንደነበረ በታሪክ የታወቀ ሲሆን ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊትም አካባቢው ዋስል ከተማዋ ደግሞ ምድረ ሀጓ ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡

በታሪካዊው የዓድዋ ጦርነት ክተተት አዋጅ መሰባሰቢያነቷ ጥቅምት እኩሌታ እና የካቲት ወራት በደረሱ ቁጥር የምትታወሰዋ ወረኢሉ የበርካታ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ የመስህብ ሀብቶች መገኛ ናት፡፡ በቅርስ ክምችት ሀብቱ የሚታወቀው የደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፣ የዳግማዊ ምኒልክ እና አድዋ የዘመቱ የጦር መሪዎች ሰፈሮች፣ የራስ ሀብተ ማርያም የቀብር ቦታ የሚገኙት በወረኢሉ ከተማ ነው፡፡ በዙሪያዋም ታሪካዊው የመካነ ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ፍርስራሽ፣ የባቄላ መስጅድ፣ አባሻረው የአርኪዮሎጅ ስፍራ፣ የአጼ ዳስ ዋሻ፣ ወይብላ ማርያም፣ የአጼ ገላውዲወስ ቤተ መንግስት ፍርስራሽ ሕንፃ እና የቅዱስ ሚካኤልን ቤተ ክርስቲያ ይገኛሉ፡፡

3 months, 1 week ago

የገንዘብህ መጠን ሲጨምር የመስጠት ፍላጎትህ አብሮ ሊጨምር እንጂ ሊቀንስ አይገባም!
የሰበሰብከው ገንዘብ ምድር ላይ እንጂ በሰማይ ቤት አይሰራልህም! ....!
የድህነት - የየለኝም አዕምሮ - poverty Mentality ካለህ በከፈልክ ቁጥር የሚያልቅ
- በሰጠኸው ልክ የምትደኸይ ይመስልሀል!
ለዛ ነው የሰበሰብከው ብር ደስታን- ያካበትከው ንብረት ሀሴት ሳይሆን ጠላት ይዞ ቤትህ የሚመጣው!
ስለዚህ #ስጥ
እህታችሁ ሀና...

3 months, 2 weeks ago

ደስታ ቢራቢሮ ሲሆን፤ ለመያዝ ብንሞክር የማይጨበጥ....ነገር ግን ፀጥ ብለን ስንቀመጥ ከአጠገባችን ብልጭ የሚል ነው።

?ለደስተኝነት አንድ መንገድ ነው ያለው። እሱም ከምኞታችን አቅም በላይ በሆኑ ነገሮች ላይ መጨነቅን ማቆም ነው። እጅህ ላይ ያለው ካላስደሰተህ እርግጠኛ ሁን ሊመጣ ያለውም አያረካህም። በበርሃ አበባ ሳትፈነድቅ በገነት ውበት አትመሰጥም። የፍላጎት ስሌትህን ወደ ጎን አርገውና፣ ስለ ንጋት ፀሀይዋ መሞቅ ፣ ስለ ቀኑ ብራነት፣ በነፃ ስለምትተነፍሰው ውድ አየር፣ ደክሞህ እንኳ ሰለማይደክማት ልብህ፣ በዙሪያህ ስላሉት ወገኖች፣ ይህንን ማንበብ  እንኳ ስላስቻለህ አይንህ ስታስብ ...
.
.
.
በደንብ ስታጤን ... በእርግጥ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ብዙ እንደሆነ ትረዳለህ ፡፡ ያኔ እድለኝነት ይሰማሀል፡፡ ያኔ እንዳልጎደልክ ይገባሀል .... ያኔ አመሰጋኝ ትሆናለህ....

? የራስህ አመለካከት ሲጠራ ደስታህና መልክህ እንደፀሓይ ያበራል። በቁስ ያልተደገፈ ደስታ ውስጥህን ይሞላዋል፡፡ ነገ ራሱ የብዙ ዛሬዎች ድምር ነውና ለደስታህ ቀጠሮ አትያዝለት ...
የደስታህ ጊዜ አሁን ነው።

5 months, 3 weeks ago

"እኔ ፍርሃት ተፈጥሯዊ እንደሆነ እየተቀበልኩ እና ህልሜን ለማሳካት ወደ ፊት የሚወስዱኝን እርምጃዎች በድፍረት እየወሰድኩ ነው "

የ180 ቀን 37ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 143  ?*? ቀን ብቻ*

መርህ ቁጥር 15
ፍርሃቱ ይሰማህ እና ለማንኛውም ተግባር ውስጥ ግን ግባ

ካለህበት ወደ ምትፈልግበት  በምታደርገው ጉዞ  ወደፊት  በሄድክ ቁጥር ፍርሃትህን ልትጋፈጥ ይገባል። ፍርሃት ተፈጥሯዊ ነው። አዲስ ፕሮጀክት ስትጀመር፣ አዲስ መንገድ ስትከተል፣ አዲስ መድረክ ላይ ስታሰለጥን ወይም ወደ ፊት እራስህን ስታቀርብ ብዙውን ጊዜ ፍርሃት ያጋጥምሃል። በሚያሳዝን መልኩ ብዙ ሰዎች ፍርሃት ህልማቸውን ለማሳካት የሚያስፈልገውን አስፈላጊ እርምጃ ከመውሰድ እንዲያግዳቸው ያደርጋሉ። ስኬታማ ሰዎች በሌላ በኩል ሁላችንም እንደሚሰማን ፍርሃት ይሰማቸዋል ፤ ነገር ግን የሚፈልጉትን ከማድረግ፣ ከማግኘት እና ከመሆን እንዲያግዳቸው አይቀዱም።

ፍርሃት የሆነ የምንቀበለው፣ የምናልፍበት እና አብሮን በመንገዳችን የሚከተለን ነገር እንደሆነ ተረድተዋል።

ፍርሃት ማድረግ ያለብህን ከማድረግ አያግድህ ! 

ቃል ህይወት ነውሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ይፈጥራል ፣ ከዛም ተግባርን ያስጀምራል
ስለዚህም ሃሳቡን ከገዛን ይሄን አዎንታዊ ማረጋገጫ ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)
"እኔ ፍርሃት ተፈጥሯዊ እንደሆነ እየተቀበልኩ እና ህልሜን ለማሳካት ወደ ፊት የሚወስዱኝን እርምጃዎች በድፍረት እየወሰድኩ ነው "

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago