"ደዕወቱ አስ ሰለፍያ!"

Description
የተለያዩ ኢስላማዊ ወሳኝ ትምህርቶች ይተላለፉበታል

https://t.me/+6SaOWBkUxRBhNTlk
Advertising
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc

5 months, 3 weeks ago

ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል አላህ ለቀጥተኛው መንገድ ይምራውና ሸይኽ አብዱል ሓሚድን ቪድዮ ያነሳቸው አካል ቪድዮውን ያነሳቸው ፊት ለፊት ነው የሚባለው ጭራሽ ዝም ብንል ተጋኖ እየተናፈሰ ይገኛል።
እውነት ፊት ለፊት ነው ያነሳቸው?? እስኪ ስለ ጉዳዩ እናንሳ።
ቪድዮው ላይ በግልፅ የሚያሳየው ሸይኹ በሀይለኛ እየተግተረተሩ ስለ ትልቅ ጉዳይ ስለ ሳዑዲያ እያብራሩ ባሉበት በፍፁም እንዳላዩት በሚጠቁም መልኩ በጎን በኩል ያነሳቸው እንጅ ፈፅሞ ፊት ለፊታቸው መሆኑን የሚጠቁምና በየ ሀገሩ እየዞሩ እንደሙሽራ እየተዘጋጁ እንደሚነሱ ሰዎች አይደለም።
ቅጥፈቱ ከቀጠለና አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በግልፅ እናስተላልፈዋል።
t.me/Abdurhman_oumer

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman\_oumer

ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል አላህ ለቀጥተኛው መንገድ ይምራውና ሸይኽ አብዱል ሓሚድን ቪድዮ ያነሳቸው አካል ቪድዮውን ያነሳቸው ፊት ለፊት ነው የሚባለው …
5 months, 3 weeks ago
አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ የተከበራችሁ እህት ወንድሞች …

አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ የተከበራችሁ እህት ወንድሞች እናት አባቶች መላው ሙስሊም ሰለፍዮች አልሐምዱሊላህ ( የምስጋና አይነቶች ሁሉ ለአላህ የተገባው ነው። ) “የሰለፍያ እውነታ!” መጽሐፍ አረብ ኢምሬት በሀገረ ዱባይ ገብቷል። በመሆኑም በሚከተሉት አድራሻዎች ማግኘት ትችላላችሁ።

ቻርጃ
0559947371
00251991438034

ቻርጃ
+971543818063

አቡ ዳቤ
+971523592631

ዱባይ
+971521648502
*_____

የቴ*ሌግራም ቻናል
t.me/Abdurhman_oumer/8311

5 months, 3 weeks ago

የሱና ሰዎች በዲን በኩል ባለው ጉዳይ ያን ሁሉ ሲታገሉ
በነሱ ላይ ከግላቸው ጋር ተያይዞ ሲቀጠፍባቸው ለምን ቀዝቀዝ ይላሉ?
1.ዋናውና የመጀመሪያው ምንምኳ እነሱን ለማጠልሸት አነሳሹ ነገር የያዙት ሀቅ ቢሆንም የግላቸውም ጉዳይ ስለተቀላቀለበት የተወሰነ ቀነስ ማድረጋቸው የሱና ሠዎች ለነፍሳቸው የሚበቀሉ አለመሆኑን ያሳያል።
2.ለነፍሳቸው የማይበቀሉ ከሆነ እውነትን በውሸት በመቀላቀል የተዘመተባቸውን ዘመቻ አላህ በቂያቸው ነው ከዚህ ቀደም ለአላህ ብለው እንደታገሉት የራሳቸውን ጉዳይ ወደ አላህ በማስጠጋታቸው አላህ ይረዳቸዋል።
3.እንደ ሌሎች ለጥቅም ለቁጥር አይደለምና የሚኖሩት።
4.ያሉበት መንገድ የታወቀ በመሆኑ ስለ ራሳቸው መናገር ስለማይጠበቅባቸው ነው። በዚህም የሱና ሠዎች ያሉበትን መልካም አካሄድ ጠንቅቆ ያወቃቸውና በማስመሰል ለብ ለብ አድርጎ አብሽር ማሻ አላህ ጎበዝ ናችሁ ከእናንተ ጋር ነኝ ወ ዘ ተ . . . የሚለው ፈተና ሲፈጠር ሲዋልል የሚለይበት ነው።
5.በየ ስርቻው ያለው ሁሉ ሲዘልፋቸው የሚባልባቸው ሁሉ እውነትና እውነት ለዲን የታሰበበት ቢሆን ኖሮ ተጨንቀው ተጠበው ቦታ ይሰጡት ነበር።
6.ሌሎቹ እነሱን ለማጠልሸት ሲሮጡ ሲደክሙ የሱና ሰዎች ግን አሁንም ከባዱ ጥረታቸውና ትግላቸው ዲኑንን አስመልክቶ ባለው ዙሪያ ነው።
t.me/Abdurhman_oumer

5 months, 4 weeks ago

ይሄው የሸይኽ ሙሳ አልቀጧን ተጨባጩን የዳሰሰ ማብራሪያ ለራሳቸው ላኩላቸው

በርግጥ እነሱ አንድ ሠው ወይ ካለበት አቋም ካልዘቀጠ ባጢል ካላገሳና በሰለፍዮች ላይ በቅጠፈት ካላጠለሸ እርካታ አያገኙም።

መርከዝ ኢብኑ መስዑዶችን እንዲሁም ነሲሐ ቲቪያቸውን፣ ዶክተር ጀይላንን እንዲሁም ሌሎች ኢኽዋኖችን በተመለከተ፣

#በሸይኽ_ሙሳ_አህመድ

#ከዓረበኛው_ድምፅ_ወደ_አማረኛ_ትርጉም
.  .... ?
የቢድዓ ባለቤቶች ጋር መተባበር ፈፅሞ አይቻልም።
ይህ የሰለፍያን ጥሪ ማቅለጥ ነው።
ሙመይዓዎች በሰለፍያ ጥሪ ላይ አደጋ ከሆኑ ሰዎች ሁሉ አደጋዎቹ ናቸው።
እነዚያ የሱና ባለቤቶችን ጥሪ እና ሱናን የሚያቅለጠልጡ ናቸው።
ከቢድዓ ባለቤት ጋር መተባበር ሀራም(እርም) / ክልክል ነው። ፈፅሞ አይቻልም።
እነዚያ መስለሀ (ጥበብ/ጥሩን ነገር በመሻት) እና መስጅዶቻችንን ለመጠበቅ ብለው ነው ሚሞግቱት/የሚያስቡት!!
መስጅድኮ የሰለፍያን ጥሪ ለማስፋፋት የሚያግዙ ናቸው።
ከመስጅዶች ውስጥ የሰለፍያ ደዕዋ የተራቆተች ከሆነች የመስጅድ ጥቅም ምንድን ነው??
የት ነው መሰለሀ? (ጥሩን ነገር መሻት/ጥበብ?)
እነዚህ ሰዎች ሁል ጊዜ የደዕዋ መስለሀ መስለሀ ይላሉ!!
እነዚህ ሰዎች የዳዕዋን ጥበብ በሷ ላይ  መደገደፊያ አድርገዋል፣በዚች ሰበብ በሰዎች ላይ ሀቅን ይሸፍኑባታል።
የቀደምቶች መንገድ ደግሞ (ለራስ) ጥሩን በመፈለግ፣ስሜትን ለማርካት፣ ለአሰተያየቶችም ተብሎ አትወገድም/ክፍተት አይፈጠርባትም።
የሰለፍያ (የሰለፎች መንገድ) ጥሪ የራሷ የሆነ መስፈርት፣ጅማሮና፣የራሷ አንኳር ነጥቦች አሏት!!
ስለዚህም፦ በኢስላም ታሪክ ከድሮም ጀምሮ እስከ አሁን እሰካለንበት ዘመን ድረስ ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር መተባበር ተከስቶ አያወቅም።
ማንኛይቱም ስብስብ ከእንዲህ አይነቱ የዘቀጠ ተግባር  ራሷን አታስገባም። የጥሪዋ መጨረሻ ሙመይዕ ሆና ብትወጣ እንጅ!!
ከዛም በቀጣዩ የሱና ባለቤቶችን ከሱና ባለቤቶች ያርቃሉ።
አንተ በኢኽዋን ላይ ካልተናገርክ፣ከቢድዓ ባለቤቶች ካላስጠነቀክ፣ከተብሊግ ካላስጠነቀክ ከሌሎችም ከጠማማ ቡድኖች ካላስጠነቀቀክ የት ላይ ነው በጥበብ መጣራት?/ጥሩን ነገር መሻት፣ አንተ ሚስኪን??
ይህ ውድመት/ድምሰሳ ነው። ከኢኽዋን ወይም ከሱሩርያ ውድመቶች/ጥፋቶች ውስጥ የሆነ ጥፋት/ማጥፋት ነው።
እኛ ድሮም ዶክተር ጀይላኔ የወጣለት ሱሩርያ መሆኑን እንሰማ ነበር።
በሰለፍያ ጥሪ ላይ ጉዳት ከሆኑ ሰዎች በጣም ከባዱ ነው።
ምክንያቱም ብዙ ሰዎች እሱ ዓሊም የሀዲስ ሥር መሰረት የሚውያቅ ምናምን ብለው ይገምቱታልና።
ሥንትና ሥንት ሰዎች አሉ ከሱ የበለጡ በዒልም የሀዲስን ሥር መሰረት የሚያውቁ ሆነው ግን ቢድዓ ላይ የወደቁና ራሳቸው ጠመው ሰዎችንም ያጠመሙ!??
ጀይላን ድሮ ጀምሮ ሳዑዲ ላይ በገንዘብ እና በሌሎችም ነገሮች ማን እንደሚረዳው አውቅ ነበር።
እነሱም በሳዑዲ ውስጥ የሚገኙ ታላላቅ ሱሩሪያዎች ነበሩ።
ስለዚህም፦ እሱ የሰለፍዮች ዋና ጠላት እንደሆነ ነው ሚታሰበው!! ከሱ መጠንቀቅና ማስጠንቀቅ ተገቢ ነው!!
ሙሐመድ ሓሚድን የሚባለው ራሱን ሰለፍይ ቢል እንኳ ይህ ታላቅ ኢኽዋንይ ነው።
ሲጀመር ማንኛውም የቢድዓ ባለቤት እኔ የቢድዓ ባለቤት ነኝ!! እኔ ሂዝብይ (ከሱና ውጭ ጭፍራ የመሰረትኩ) ነኝ አይልም።
ሰለፍዮችን እንደሚሳደብና እንደሚተች እሱን የሚያቁት ከፊል ወንድሞች ነግረውኛል።
ነገር ግን ሰዎችን አትሳደቡ አትተቹ ይላሉ። ራሳቸው ሰለፍዮችን የሰለፍያ ዓሊሞችን ለመተቸት/ማነወር ከሰዎች ሁሉ የበረቱ ናቸው።
ዶክር ጀይላን ሸይኽ መሐመድ አማነል አልጃሚዕን አላህ ይማራቸውና እሳቸውን ሳይቀር ያነውራል።
እሳቸውንም ሲያነውርም እንድህ ይላል
ዑለማን በማነወሩ አላህ በነቀርሳ በሽታ ፈተነው ይላል።
ይህ ሰው (ጀይላኔ) የታወቀ ነው።
ጎደኛችን የነበሩና የሸይኽ አህመድ አሽንቂጢ ተማሪ ሸይኽ አህመድ ሙነወር አላህ ይዘነላቸውና
ዶክተር ጀይላኔ በደንብ ያውቁት ነበር። ስለሱ ሲጠየቁ እንዲህ አሉ ይሄ የወጣለት ሱሩርይ ነው ተጠንቀቁት ብለዋል።
እሳቸው በጣም ይጠሉትና ከሱ ያስጠነቅቁ ነበር ምክንያቱም ሰውየው መቀያየር የሚያበዛ በጣም ተንኮለኛ ሰው ነው።
ኢኽዋን ጋር ሲሆን ኢኽዋን፣ ሱሩርይ ጋር ሲሆን ሱሩርይ፣ ሰለፍዮች ጋር ሲሆን ሰለፍይ ይህ በጣም አደጋ ነው።
አላህ ጀዛቸውን ይከፈላቸውና ከፊል ወጣቶች የተናገረውን  አሰምተውኝ። #ሱፍያን_ሱፍያ ብለን አንጠራትም። ግን #ነፍስን_ማጥራት በሚል (ለወጣቱ) እናስተዋውቃታለን። #አሻዒራን ደግሞ #የሱና_ባለቤቶች ብለን (ለወጣቱ) እናስተዋውቃለን ይላል።
ተመልከቱ የዚህን ሰውየ ተንኮልና አደጋውን።
ይሄን ታላቅ ሸፋፋኝ ተመለከታችሁት እሱ በሃበሻ  ሰለፍዮች ላይ ታላቅ አደጋ ነው።
ምክንያቱም ብዙ ሰዎች በሱ ይሸነገላሉና።
በሱና ባለቤት ላይ ታላቅ አደጋ ማለት ጀይላኔና መርከዝ ኢብኑ መስዑድ ናቸው።
መርከዝ ኢብኑ መስዑዶችን በፊት ሰለፍያ እንደሆኑ እንገምታቸው ነበር። ግን ዛሬ ላይ ኢኽዋን ጋር ቃል ተግባብተዋል ሥለ ኢኽዋን አይናገሩም።
በጣቢያቸው በነሲሀ ቲቪ ላይ ከቢድዓ ባለቤቶች ሲያስጠነቅቁ አትሰሟቸውም። ምንም ሥማቸውን አይጠቅሱም።
ነገር ግን ሀገሪቱ በቢድዓ ባለቤቶች የተሞላች ነች። በሱሩሩያ፣በተክፊር በሌሎችም የጥመት ባለቤቶች የተሞላች ነች!!
ነገር ግን አንድት ቃልና ፊደል ሲናገሩ አትሰሙም።
ይሄም እነሱ ከጠንካራዋ/ከቀጥተኛዋ አካሄድ ማፈንገጣቸውን ያመለክታል።
ሥለዚህም፦ በድጋሜ እነሱም በሱና ባለቤት ላይ አደጋ ናቸው።
ምክንያቱም ይህ ነሲሀ ጣቢያቸውን
ከማንኛውም ቤት ገብቶ ታገኘዋለህ። ሰዎች በሱ (በነሲሀ) ጥሩ አለው ብለው ይገምታሉ!!
ነገር ግን እነሱ በሌላ በኋላ ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር ባንድ ተሳስረዋል። ደዕዋን ገድለዋል፣ደዕዋን አቅልጠዋል፣ ወደ ገንዝብም ተዘንብለዋል።
ይህ ነው ያለው!!
አላህን (ከእንዲህ አይነት ተግባር) ሰላምና ደህንነት እንጠይቀዋል።

እኔ በማውቀው ልክ እነዚህን ሰዎች መጠንቀቅ ተገቢ ነው። በተለይ ጀይላኔን(ተጠንቀቁት) አህለ ሱናን የሚያወድምና ሀቅን በመሸፈን (ደራሽ የሌለው) ከትልልቅ ሸፋኞች ውስጥ ነው። ለኛም ለሱም መምራትን አላህን እጠይቀዋለሁ።

#የሸይኹን ድምፅ ለማግኘት
?
t.me/Abdurhman_oumer/953#ትርጉም
አብዱረህማን ዑመር
t.me/Abdurhman_oumer/8309
t.me/Abdurhman_oumer/8309

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

ሸይኽ ሸይኽ ሙሳ በመንሀጅ ጉዳይ

5 months, 4 weeks ago

ከሳምንታት ጀምሮ የሚራገብ አንድ ቅጥፈት አለ ። ይኸውም ከሸይኽ ዐ/ሐሚድ ቪዲዮ ጋር የተያያዘ . . .. ነው።
    የሚራገበውን ቪዲዮ በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ ተመልከቱት : –
https://drive.google.com/file/d/1ZLzI1YvFqLn3L5DjFSxicXTpAufx0-ti/view?usp=drivesdk
?ይህ ቪዲዮ ከዛሬ ሁለት አመት በፊት እኔና ሸይኽ ዓብዱል ሐሚድ ኢብራሂመል ሙሐይሚድ ከሚባል ከሳውዲ ከመጣ እንግዳ ጋር ወደ ሸይኽ ዓብዱል ከሪም ዚያራ ሄደን ነበር ። ሸይኽ ዓብዱል ሐሚድ አምቡዬ ላይና ሊሙ ላይ በሸይኽ ዓብዱል ከሪም መስጂዶች ላይ ዳዕዋ ያደርጋሉ ። በተለይ አምቡዬ ላይ ሁለት ቀን ሰፋ ያለ ዳዕዋ አድርገዋል ። መጨረሻ ላይ ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሳውዲ ዑለሞችና መሪዮች ዳዕዋ ሲያደርጉ እንግዳው በሞባይሉ ቀርፆ በራሱ ግሩፕ ላይ ለቀቀው ። አንድ ወንድም ከሱ ግሩፕ ወደራሱ ሼር አደረገው ። የተለያዩ ወንድሞች የሸይኽ ቪዲዮ ተለቆ አየን ብለው ደወሉ ። ለሸይኽ ተነገራቸው እሳቸውም አላህን ፈርቶ እንዲያጠፋው ንገሩት አሉ ተነገረው ወዲያው አጠፋው ።
     አሁን የሚራገበው ቪዲዮ ታሪክ ይህ ነው ።

ኡስታዝ ባህሩ ተካ (ሃፊዘሁላህ)
t.me/Abdurhman_oumer/8308

5 months, 4 weeks ago

የአኗር መስጅድ ቂያስ. ..
አንዱ የማቅለጫ ስልት

ሱናውን እርግፍ አድርገው ለመተው የፈለጉ ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር አብረው ሲርመጠመጡ ለመኖር ያለሙ ሠዎች አንዱ የስሌት ካርዳቸው አኗር መስጅድን ነው። ይህ ገና መጀመሪያም ኢልያስ አህመድ ለተመዩዑ ቦታ ሲያምቻች ያቀረበው ቂያስ ነበር። ጉዳዩን ለሚያጤኑት አኗር መስጅድን ለሚያውቁት ብቻ የሚተው ይሆናል። በእርግጥ ቀላል የሚባሉ ኸልቆች አይደሉም አኗር መስጅድን የሚያውቁት። እንደት ተብሎ ነው እንደ ገበያ የሰፋና ቁጥጥሩ ለየት ያለ የአኗር መስጅድ ሩቅ ጫፍ ላይ ተቀምጦ የሚያስተምር ሠውና የቢድዓ ባለቤቶች መድረክ አምቻችተውለት ከሚያስተምረው እኩል የሚሆነው?? አኗር መስጅድ ምንምኳ መሪዎቹ የወጣላቸው አሻኢራ አህባሽ ሱፍያ ወዘተ ከሚባሉት ቢሆኑም አንድ የሱና ሠው አቋሙ በተጠበቀ መልኩ ምንም አይነት መነካካት ቀርቶ ከናካቴው ከእነኝህ አካላቶች ጋር ሳይተዋወቅ ከመስጅዱ ሩቅ ጫፍ ላይ ወይም በረንዳ ላይ ሆኖ አስተምሮበት ሊወጣ የሚመች መስጅድ ነው። ምናልባትም  ኢማሞቹ ሶላት ተከትለዋቸው ለመስገድ ብቁ ካልሆኑ (ግልፅ ኩፍር የሚስተዋልባቸው ከሆኑ) ያ የሱና ሠው ከዛ መስጅድ ጫፍ ላይ ቢያስተምርም ከነሱ ጋር እንኳን ግንኙነት ሊኖረው ቀርቶ ተከትሏቸውኳ አይሰግድም። ያለው ተጨባጭ ይህ ሆኖ ሳለ ለጥ ብለው ሊተኙ ያሰቡ ሰዎች ግን በማንኛውም ጉዳይ ሀቂቃን በሀቂቃ ሳይሆን ማመዛዘን የሚፈልጉት ይሄም እንዲህ ሆኗል ይሄንስ ምን ልታደርጉት ነው እያሉ በማወዛገብ ለመገላገልና ሠው ሲወዛገብ እንደፈለጉ እንዲሾፍሩ ለነሱ እንዲያመቻቸው ስምን በስም ነው እያመሳሰሉ ስሌት የሚሰሩት።
ድንቄም የሒክማ ሠው “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል!” እንዲሉ እኛ ከሱና ከወጣን አይቀር ሠውን ውንብድብድ እናድርገው የሚል አላማ አንግበው ተነስተው ዘወር ብለው ቅልስልስ እያሉ ሒክማ የተላበሱ መልካም መስለው ይቀርባሉ።
  በመሆኑም በአኗር መስጅድና መሰል የሆኑ ምንም ንክኪና ሙድሀና እንዲሁም ተልቢስ ሳይኖር ማስተማር የሚቻልባቸው ቦታዎች . . .
እና
በኛ አካሄድ አይነት የምትፈሱ ከሆነ ኑ መድረክ ላይ ተቀመጡ ከዛ ውጭ ከሆነና በኛ አካሄድ ካልሄዳችሁ መስጅድ ጫፍ በረንዳ ላይ መማር ማስተማር ቀርቶ ከፍ ሲልም ሰብሰብ ብላችሁ መቀመጥ አትችሉም የሚባልባቸው መስጅዶችና ቦታዎች እኩል አይወሰዱም።
ይሄን ሳነሳ እንደ ጥቅል በነጥቡ ዙሪያ ለመዳሰስ እንጅ ዋቂዕየን (እዛ ያለውን ሁኔታ) እነገሌ የሚያስተምሩት በዚህ መልክ በተገቢው ልክ ነው እነገሌ ደግሞ እንዲህ ናቸው ወደሚለው ዝርዝር ለመግባት አይደለም። ያን ዝርዝራዊ ሁኔታ ለመናገር በአኗርም ሆነ በመሰል ቦታዎች የሚያስተምሩ ሰዎችንና የሚሰጡ ትምህርቶችን የሚከታተልን ሠው የሚመለከት ጉዳይ ነው። በተቻለ ግን መሆን ያለበት ነው የተወሳው።
t.me/Abdurhman_oumer

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman\_oumer

የአኗር መስጅድ ቂያስ. ..
5 months, 4 weeks ago

ሙስሊም ሆይ ከጫት ራቅ ጎጅ ልምድ የሆነውን ይሄን አደገኛ እፅ በምንም አይነት መልኩ እንዲትጠቀመው የሚያዝም ሆነ የሚያነሳሳ ማንነት የለህም።
በርካታው ሙስሊም ህዝብ በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ላይ ይገኛል። የተፈጠረው ለትልቅ አላማ አላህን ዲኑን የተላከለትን መልእክተኛ ሊያውቅ ሀይማኖቱን ሊማር ሆኖ ሳለ ይህ ለልዩ አላማ ተመርጦ የነበረ ህዝብ ግን ልክ እንደ ሌሎቹ በተለያዩ አጉል ሱሶችና በተለያዩ ከዲኑ በሚያርቁ ሚዲያዎች ተጠምዶ ይስተዋላል።
በተለይ ደግሞ ጫት የተሰኘውን ጎጅ እፅ ልክ ከሀይማኖቱ ድጋፍ ያለው አስመስሎ በተለየ መልኩ የተለየ ባህል ልምድ አድርጎ ይዞት ይገኛል። ይሄ አስተሳሰብ በተለይ በአንዳንድ አካባቢዎች እንደ ዝና ተደርጎ በመታሰቡ የማይቅም እንግዳ ተደርጎ እስከሚታሰብ ድረስ በከባድ ሁኔታ ለትውልድ ሲያወርሱትና ሲያስፋፉት ይስተዋላል። በእነኝህ መሰል አካባቢዎች ሴት ወንዱ ትልቅ ትንሹ ሁሉም ሊባል በሚቀርብ መልኩ ልክ እንደመሰረታዊ ነገሮች እንደ ምግብና መጠጥ የዘወትር ክንዋኔው አድርጎት ይገኛል። በዚህም የተነሳ በእነኝህ መሰል አካባቢዎች በየ ቦዩ ስር አብዶ ራቁቱን ወድቆ የሚገኝ ህዝብ በርካታ ሆኖ እናገኛል። ትልቅ አደራ የተሸከመ ትልቅ አላማ ያነገበ ትልቅ ቁም ነገር የሚጠበቅበት አላህ ያላቀውና የመረጠው የሙስሊም ማህበረሰብ በዚህ መልክ ሌላ ጉድ ውስጥ ገብቶ ሲገኝ ምን ያህል ውድመት ነው??
ሙስሊም እንኳን የአንድ አካባቢ ባህል ልምድ ተደርጎ የተያዘ ነገርን ቀርቶ በዓለም ደረጃ ልምድ ተደርጎ ቢያዝ መጥፎ ልምድን ሀይማኖቱ አጥብቆ ይኮንነዋልና ታሪክ ቀያሪ ነው መሆን ያለበት።
t.me/Abdurhman_oumer

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman\_oumer

ሙስሊም ሆይ ከጫት ራቅ ጎጅ ልምድ የሆነውን ይሄን አደገኛ እፅ በምንም አይነት መልኩ እንዲትጠቀመው የሚያዝም ሆነ የሚያነሳሳ ማንነት የለህም።
5 months, 4 weeks ago

እንደ አጠቃላይ እይታ የሀረርና የድሬዳዋ ህዝብ ከዘረኝነትም ሆነ ከሌላ ፀብ አጫሪነት ብዙ ርቀት ያለው ከኦሮሚያ ክልል አልፎ ለኢትዮጵያ ጥሩ ተምሳሌት ተብለው ከሚጠቀሱ ቦታዎች ተርታ የሚሰለፍ ቅቤ የሆነ መልካም ህዝብ ነው። ሆኖም ይህ መልካም የሆነ አዎንታዊ ባህሉ የተጠበቀ ሆኖ ሳለ በሌላ በኩል ደግሞ አደገኛ ጎጅ እፅ በሆነው በጫት ሱስ ባህል ተጠቅቶ ይገኛል። ይሄን መልካም ማህበረሰብ ለብዙ አመታት የኖረበትን ይሄንም ጎጅ ሱስ አውጥቶ እንዲጥል ከባድ ርብርብ ያስፈልጋል።
ይሄን ለማሳካት በዋናነት ማንኛውም የዚያ አካባቢ ኗሪ ሁሉም እያንዳንዱ ከራሱ ከቤተሰቡ ከቅርብ ወዳጁ ጀምሮ የመቅረፍ ዘመቻ “ሀ” ብሎ ሊጀምር ይገባዋል።
ሀረርና ድሬደዋ ጉዳዩም ይበልጥ ጎልቶ ስለሚስተዋል እንደ ምሳሌ ተጠቀሰ እንጅ ለሌሎች ተመሳሳይ ቦታዎችም ይሄ ይመለከታል።
t.me/Abdurhman_oumer

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman\_oumer

እንደ አጠቃላይ እይታ የሀረርና የድሬዳዋ ህዝብ ከዘረኝነትም ሆነ ከሌላ ፀብ አጫሪነት ብዙ ርቀት ያለው ከኦሮሚያ ክልል አልፎ ለኢትዮጵያ ጥሩ ተምሳሌት …
6 months ago

የቢድዓ ሠዎች የሰለፍዮችን ሀሳብ እስከ ዱንያዊ ጥቅማጥቅሞችና ዱኒያዊይ ጉዳዮች ድረስ እንደሆነ በማሰብ የተለያዩ ጥረቶችን ያደርጋሉ። ራሳቸው ተሳስረው የሱና ሠዎችን መስጅድ ለማስቀማት እየተጣጣሩ ምድር ላይ የሱና ብርሀን የሚፈነጥቅባቸውን የሱና ሰዎች የሚያስተምሩባቸውን መስጅዶችና መድረሳዎችን ምንጫቸውን ለማድረቅ ለማኮላሸት ቀን ከሌት እያለሙ ሳለ
ዘወር ብለው መፍትሔ ጠቋሚ መስለው ችግሩን በሌሎች ለማዞር መስጅዶቻችሁ እንዳይወሰዱባችሁ የሆነ ነገር እንዳይሆንባችሁ የሆነ ነገር እንዳታጡ የሱና ጥሪያችሁን አቁሙ ያላችሁበትን ጠንካራ አቋም ቀይሩ የተበላሸውን አካሄድ ተቀበሉ ወደሚል ውስወሳ ያመላክቷቸዋል።
መስጅድ መድረሳ የሱና አስተምህሮት የማይካሄድበትና ማለዘብ በሚሉት ዘመቻ በጥሩ ሁኔታ ተፋፍሞ ፈክቶ የነበረው የሱና አስተምህሮት አበባው ከጠነዘለ በውስጡ ያሉት ጀግኖች አቋማቸውን ቀይረው አሞታቸው ሞቶ ከአሟሚዎች ጎራ ተመድበው እነሱ የሚሉትን አይነት የሚሉ ከሆነ መስጅዶች የዲን ሳይሆን የዱኒያዊይ አላማ ማካሄጃ ሆነዋል ማለት ነው።
ስለሆነም ከተፈላጊው የዲን አስተምህሮት ከተራቆተና የቢድዓ ባለቤቶች የሚሄዱበትን አካሄድ የተከተለ እንዲሆን በትክክል ዲናቸውን የተገነዘቡ የሱና ሰዎች አሳልፈው አይሸጡም።
የአላህ ውሳኔ ሆኖ የጥመት ሠዎች በቅጥፈት በጉልበት በግፍ በጫና አድርገው ቢወስዱትኳ የሱና ሰዎች የሚጠበቅባቸውን እስካደረሱ ድረስ ከአላህ ዘንድ ተጠያቂ አይሆኑም። የእነኝህን በሽተኞች ምክር (ውስወሳ) ሰምተው አሳልፈው ከሰጡ ግን ያን ጊዜ ነው ኪሳራ።
መስጅድ ሀቅ ሱና ተውሒድ ሺርክ ቢድዓ የሺርክ የቢድዓ ሰዎች ሁኔታ በተቻለው አጋጣሚ ፍርጥርጥ ተደርጎ ካልተነገረበት ከቆመለት አላማ ከዋናው አስኳል ውጭ ሆኗል።
የአላህ ቤት ላይ ከአሁን ቀደም የሰማችኋቸው ሁሉ የቢድዓ ባለቤቶች አካሄዶች የሚራመድባቸው ከሆኑ

እንዲሁም አዲስ የምንሰማው . . .
የአላህ ቤት ላይ እገሌ የሚባለውን ሠውየ ሥም አስመልክቶ በቁርአን ስለሌለ ማንኛውም ሠው የሠራውን ቢሰራ በሱ ላይ ሁክም በመስጠት ረገድ ሁሉም አንድ አይነት አቋም ይኑረው አይባልም። ኢጅቲሀድይ የሚገባበት ርዕስ ነው ሲባል መስማት ከዚህ በላይ ሞት ምን እንጠብቃል በአላህ!?
እንደሚታወቀው አብዱላህ አል ሀረርሪ ጀህም ኢብኑ ሶፍዋን ኢብኑ ዓረቢ ሀሰን አል በናእ ሰይድ ቁጥብ ሙሀሙድ አልሀዳዲና (መሰል አካሄዶቹን የሚያንሸራሽሩ) ዩሱፍ አል ቀረዷውይ ዑመር ኮምቦልቻ ዑመር ገነቴ አቡበክር ሱለይማን ጀይላን ኸድር ሙሐመድ ሀሚድን ኢልያስ አህመድ ሌሎችም ማንኛውም የኩፍርም ሆነ የቢድዓ ባለቤት ሥም በቁርአን የለም።
   በቁርአን ሥማቸው የተጠቀሱት ምናልባት አቡ ለሀብና መሰል በጥንት ነብያቶችም ዘመን የነበሩ ጥቂት መጥፎ ሰዎች ብቻ ናቸው። ታዲያ ከነዛ ውጭ ያሉት ሁሉ ከጥንት ጀምሮ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ ያሉ የዲን አስተምህሮትን አዛቢዎች ስማቸው ቁርአን ላይ አልተጠቀሰምና የፈለገ አካል መጥፎ ናቸው ሲል የፈለገ አካል ተነስቶ ጥሩ ናቸው ቢል የሚያጣላ አይደለም የሚል  ይሄ አይነት ህፃን ልጅ የማይናገረው ንግግር ነው እየተሰራጨ ያለው።
ታዲያ ይሄም ግልፅ ስናደርግ እንደ ጅል የማይገናኝ ረብሻ ለመፍጠር እንደሚቋምጡ ሠዎች ጎራጉረን ያወጣነው ሳይሆን ራሳቸው ደረታቸውን ነፍተው ወደውትና ፈቅደውት 100% አምነውበት በአደባባይ ለህዝብ ያሰራጩት ጥመት ነው።
በዚህ ዙሪያ ዓረበኛ ለምትረዱ የሸይኽ ሁሰይንን ምላሽ በሊንኩ ታገኙታላችሁ።
?
https://t.me/Abdurhman_oumer/8294

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

الجهالات العجيبة عند المميع محمد سعيد السلطي . أولا : أثبت محمد سعيد وجود الجرح والتعديل وقرّر أن علم الجرح والتعديل من الأصول وكان قد نفى كون الجرح والتعديل من الأصول لأن مسألة الجرح والتعديل لم تُذكر في أصول السنة للإمام أحمد وغيره من كتب العقائد وهذا…

6 months ago

ሙመይዓዎች ከየት እስከየት

? በኡስታዝ ባህሩ ተካ حَفِظَهُ الله
? ዕለተ ቅዳሜ ግንቦት 18 ቀን 2016 E.C የወራቤ ዩኒቨርስቲ ሰለፍይ ጀመዓዎች ባዘጋጁት የ ???? ?? ፕሮግራም ላይ የቀረበ ሙሐደራ!
https://t.me/Abdurhman_oumer/8297

We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc