Psych For Bahirdar

Description
A group of psychology majors (Friends) trying to shed light on issues we as a society have neglected. We’re here to listen and be there if needed.
You’re welcome to join us on our journey.
Advertising
We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 6 days, 8 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 month, 3 weeks ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 2 months ago

1 year, 6 months ago

sometimes illogicality...

በህይወታችን በጣም ቦታ ምንሰጣቸው ነገሮች ይኖሩን እንዲው(illogical) ሆነን ስለተቀበልናቸው አይመስላቹም፤በእያንዳንዱ ነገር ምክንያታዊ (logical)ልንሆን ብንሞክር ያለንን እምነት፣ወዳጅነት፣እንዲሁም ህይወታችንን ዋጋቢስ እናደርጋታለን ።

ለዛም ነው ብዙ ጊዜ እንዲሁ በዘፈቀደ (arbitrary) መሆንን የመረጥነው ይቺ ዓለም አንድ አንዴ ከስሌት ውጪ ሆነን ስንኖራት ነው ዋጋ ያላት ሆና ምትታየን፤ታዲያ በእያንዳንዱ ነገር logical ብንሆን ደስታችንን በእርግጠኝነት እናጠፋዋለን:: አስቡት በጓደኝነታችን መሀል ብዙ ክብር ,ግዜ,ቁስ, እናም ቅድሚያ የሰጠነው ሰው የኛን ያህል መልሶ ባይሰጠን እና benefit-cost calculate እያደረግን ብንኖር ምን ሊሆን እንዳለ እና ብዙ ጓደኝነትን ልናጣ እንደምንችል ::

አንድ አንዴም ዓለምን logical ሆናቹ ስትመለከቱ ዳኛ የሌለበት የወንበዴዎች መንደር ወይም በበረሃ ደክሞት ምልክት ሳያስቀምጥ አንቀላፍቶ ሲባንን አቅጣጫ እንደጠፋበት ምስኪን ስደተኛ አይነት ስሜት ይሰማቸዋል።

አስተውሉ ምዛናዊ ባልሆነች ምድር እየኖርን ነገሮች ምዛናዊ እንደሆኑ መጠበቅ በራሱ ሰተት እንደሆነ

እንተው ሁሌ logical መሆንን..
እንዲሁ እንሳቅ
እንዱሁ እንወደድ
እንዱሁ እናፍቅር
እንዲሁ እናምልክ

Logical ልክ አይደለም ማለት ስህተት ነው ማለት አይደለም

ምክንያቱም ዛሬ ልክ መስሎ ያልታዩን ነገሮች በ ጊዜ ሂደት ይፈቱልናል።

✍️ @fekaduberhanu

1 year, 6 months ago

ሰላም??

እንዴት ቆያችሁ?

Random thoughts with Fikadu??**

1 year, 7 months ago

እንደ ማጠቃለያ...

ውጫዊ እና ውስጣዊ ሁለቱም በራሳቸው መንገድ ጥሩ ናቸው, እና ምንም "የተሻለ" ወይም "የከፋ" ስብዕና አይነት የለውም። ነገር ግን ሁለቱም balance ቢጠብቁ የተሻለ ነው አንዱ ብቻውን ሚዛን ሲደፋ ልክ አይመጣም ለምሳሌ ከሰዎች ጋር ማውራት፣ መደሰት plus ደግሞ እንደ ማዳመጥ እና ማሠላሰል ያሉ ውስጣዊ ባህሪያትን አንድ ሠው ሁለቱንም ሊይዝ ይችላል። ይሄን Ambivert ወይም extrovert-introvert እንለዋለን።

✍?Kalkidan Tesfaye✍?****

1 year, 7 months ago

Carl Jung’s Theory of Personality

እስኪ ዛሬ ስለ introvert እና extrovert ሠዎች ደግሞ ትንሽ እናውራ በዛውም በየትኛው personality type እንደምትገኙ ማወቅ ትችላላችሁ

INTROVERT

የሆኑ ሠዎች ከውስጥ ማንነታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በራሳቸው አለም፣ ስሜት፣ሀሳብ ውስጥ መኖር ሚፈልጉ እና ዓለማቸውን በተለያዩ መንገዶች ለማየት ጊዜ እየወሠዱ በጥልቀት ማብሠልሠል የሚዘወትሩ ናቸው። Introvert ሠዎች በማንበብ፣ በመፃፍ ፣በማሠላሠል መደሰትን የሚመርጡ እና ትንሽ የቅርብ ጓደኞች ያላቸው ብቻቸውን በመሆን ስሜትን በግል የመግለፅ ዝንባሌ በጸጥታ እና በትልቅ ቡድን ወይም በማያውቋቸው ሰዎች አካባቢ ሃሳባቸውን ከማውራት ይልቅ በጭንቅላታቸው ውስጥ የሚያብሠለስሉ ናቸው ።

እራስን ለመፈተሽ እና ለማየት እንኳን አንዳንድ ጊዜ ጥቅም ቢኖረውም, አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ውስጣዊ ነጸብራቅ ውስጥ የመሳተፍ ከፍተኛ ዝንባሌ በመኖሩ ምክንያት እንደ ድብርት ያሉ የአእምሮ ሕመሞች የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው።

EXTROVERT

የሆኑ ሠዎች ደግሞ በተቃራኒው ከውጭው ዓለም ጋር ተግባቢ እና መስተጋብር የመፍጠር ችሎታቸው ላይ ነው።በማህበራዊ ህይወት ውስጥ ወጣ ገባዎች ከሌሎች ጋር ማውራት፣ ሀሳባቸውን በቃላት በመግለጽ እና ከውጭው አለም ጋር መገናኘት ያስደስታቸዋል። Extroverts ብቻቸውን መሆን የማያስደስታቸዉ እና ብዙ ጓደኞች ያሏቸው ፣በማህበራዊ ህይወት መደሰትን የሚመርጡ ፣ ትኩረትን የሚፈልጉ ፣ ተግባቢ፣ በቡድን ስራ የሚደሰቱ፣ ከመፃፍ ይልቅ ማውራትን ይመርጣሉ።

ማህበራዊ ኑሮ እና ተግባቦት ጥሩ ነገር ቢሆንም አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት extroverts የተሻለ ምርጫ ማድረግ [decision making] ላይ ደካማ ሊሆኑ ይችላሉ ይህም የሌላው ሠው ሀሳብ influence ስለሚያደርጋቸው ነው።

1 year, 7 months ago

"ከ PSYCH ገጾች"

?A NEW SEGMENT?

1 year, 8 months ago

This week’s Random Thoughts, with Helina.

አንዳንዴ በሚወዱን ሠዎች ዙሪያ ስንሆን ምንም መሆን የምንችል ይመስለናል...
ምንም ነገር ብናደርግ የሚቀበሉን ወይም የማይርቁን.....ነገር ግን መውደዳቸው የኛን የትኛውንም ባህሪ መቀበል የሚያስችል አቅም እንዳላቸው አያረጋግጥም።

ሠዎች እንደወደዱን ከማረጋገጣችን በፊት ራሳችንን የተሻለ ለማድረግ እንደምንሞክረው ሁሉ ካረጋገጥን በኃላም ራሳችን ላይ መስራት አለብን።
የወደዱን እናት አባት እህት ወንድም ጓደኛ ፍቅረኛ ወይም ልጃችን ሊሆኑ ይችላሉ...መውዳቸው እንዲፈትናቸው አናድርግ::

በሕይወታችን ፈልገንም ሳንፈልግም ወደ ሕይወታችን ገብተው በጥሩም በመጥፎም የወጡ ሠዎች ይኖራሉ::

ጥሩ ያልናቸውን ተቀብለን መጥፎ ያልናቸውን ደግሞ ምናልባትም አዝነንባቸው...ጠልተናቸው ላለማስታወስም እየሞከርን ይሆናል።

ነገር ግን ስሜታችንን ትንሽ ረገብ አድርገን ብናይ እያንዳንዳቸው በትንሹ አንድ ጥሩ ነገር ሰጥተውን አልፈዋል...ለወደፊቱ ህይወታችን የሚገጥሙንን መሰናክሎች የምናቀልበት በትንሹ አንድ ነገር አለ።

ስለዚህ ወሰዱብን ከምንለው በላይ ሰጥተውን የሄዱት ይበልጥ ይሆናል እና...እንፈልገው።

1 year, 9 months ago

Random Thoughts with Kalkidan Tesfaye.
መቼስ በህይወት ስንኖር መለወጥ እና ማደግ የማይፈልግ ሠው ያለ አይመስለኝም።

በዚህ ሂደት ውስጥ አንድ የማንረዳው ነገር ቢኖር አሁን ያለንበት ደረጃ፣ ዉሎ፣ ሙድ(mood)፣ ባህሪ ፣ተግባቦት እና አጠቃላይ ማንነታችን የአስተሳሰባችንን ልክ እንደሚያሳይ ታምናላችሁ?
ለምን ካልን ሠው እንዲው አሁን ያለውን ማንነት ስላላመጣው በድግግሞሽ ተግባር ባህሪን ስላመጣን ከዚያም በፊት በስሜት(feeling) ክፍል feel ስለሚደረግ ከዚያም ቀድሞ ሀሳብ ደግሞ ስላለ።

እንዴት ካልንም አንድ ሀሳብ ወደ አዕምሮአችን ክፍል ውስጥ ገብቶ አብሰልስለነው (thought process) ከዚያም ደግሞ ያሰብነው ሃሳብ የሚፈጥርብን ስሜት (feeling)
ተቀይሮ በ behaviour ደግሞ ስለሚገለጥ ነው። ስናጠቃልለው ስሜቶቻችን ምላሽ እንዲሰጡ አትፍቀዱ ባይሆን ግን ጠይቁ በምን ምክንያት ይሄ ስሜት ፣ተስፋ መቁረጥ፣ ንዴት እና ብስጭት፣ ትዕግስት ማጣት፣የmood መቀያየር፣ድብርት መጣ?

ከዛስ እነዚህ በsocial life በ Academic performance እና በሌሎችስ ላይ እየጎዳን ነው? ስሜትን ለመቀየር ከመታገል ይልቅ እውነታውን ማየት እና መለወጥ የማንችለው እውነት ከሆነ ደግሞ መቀበል ለእድገት በር ከፋች ነው።
ለራሳችሁ ታማኝ ከሆናችሁ ያላቹበትን ቦታ እና negative አስተሳሰብ ቁልጭ አድርጎ ያሳያቿል ግን እውነትን የማትፈልጉና አሁን ያላቹበትን status ሌላን አካል ተጠያቂ እያደረጋቹ ለራሳችሁ ባህሪ ሀላፊነት የማትወስዱ ደግሞ ከሆነ ስሜትን ሳይመረምሩ እያመኑ በፀፀትና እንደነበሩ ለውጥ በሌለው ኑሮ ህይወት ትቀጥላለች::

ግን ከየትኛው ወገን ነን?

1 year, 9 months ago

አስተያየት እና ጥያቄዎች ካሏችሁ??

@PsychForBahirdar_bot

1 year, 9 months ago

ሰላም??

ህይወትን (ነገሮችን) በቁጥጥሬ ስር ማዋል እችላለሁ ብላችሁ ታስባላችሁ?

ቢሆን ቆንጆ ነበር...ሁሉም ሰው ቀለል ያለ እና ውጥረት የማይኖርበትን ኑሮ እንዲኖር::

መወለድ...ማደግ...ትምህርት መማር...ስራ መያዝ (ያው በህይወት ለመቆየት ሲባል)...ቤተሰብ መመስረት ወይም ደግሞ የእኔ የምንለውን ሰው መፈለግ...ጊዜው ሲደርስ ደግሞ የገነባነውን በሙሉ ደህና ሰንብት ብሎ መሞት::

መቼም አይ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን እምቢ ብዬ መቆጣጠር እችላለሁ የሚል አይኖርም...እንደው ምናልባት የትምህርቷን ጉዳይ::

እና ምን ተሻለ? እሺ ማለት ወይም acceptance!

ልንለውጥ የምንችላቸውን እና የእኛን ትጋት ለሚጠይቁ ነገሮች ለፍቶ እንደሚሆኑ ማድረግ መልካም ነው...የማይለወጡትን እና የህይወት ገጽታዎች የሆኑትን ነገሮች ደግሞ እንዳሉ ምን ባደርግ የተሻለ ይሆናል? ብሎ መፍትሄ ፈልጎ ወደ እሺታው መሄድ ይመረጣል::

ሁሉም control አይደረግም እንግዲህ?

We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 6 days, 8 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 month, 3 weeks ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 2 months ago