Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

Description
🔨እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይናኖች
💻ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን
📙መፅሃፍቶች
🎬ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል

📨ሃሳብ እና ኣስተያየት @ETCONpBOT ፃፉልን

📌ጨረታ ና ስራ @ETCONpWORK
📃 ለ መወያያ @COTMp

📍ዲጂታል ቤተ መፅሃፍ:- @ETCONpDigitalLibrary_Bot
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 5 days, 11 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month ago

ጥራት ያላቸው የቤት ዕቃዎችንና የቤት ማስዋቢያ ቁሳቁሶችን ከእኛ ይግዙ። አድራሻ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ 376 ያገኙናል። ባሉበት ሆነው ማዘዝ ይችላሉ። 0944222324

Last updated 23 hours ago

3 months ago

👉በመዲናዋ የሚገኙ ከ30 ሺህ በላይ ግንባታዎች ላይ የጥራትና ቁጥጥር ሥራ እየተሠራ ነ

🌟በመዲናዋ በሂደት ላይ የሚገኙ ከ30ሺህ በላይ ግንባታዎች ላይ የጥራት ደረጃና የደህንነት ቁጥጥር እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

🚧በየመንገዱ የተሰቀሉ ከ45ሺህ በላይ ሕገወጥ ማስታወቂያዎች ተነስተው ወደዲጂታል ሥርዓት እንዲገቡ አቅጣጫ ተቀምጧል።

▶️የባለስልጣኑ የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ከማል ጀማል (ኢ/ር) ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ በአጠቃላይ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ማዕከል በተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት አማካኝነት ከ30ሺህ በላይ ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛል።

▶️ግንባታዎቹ ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በተቋም ደረጃ ልዩ እቅድ ተዘጋጅቶ ክትትል እየተደረገ ነው ያሉት ኢንጂነር ከማል፤ የግንባታ ጥራትና ደህንነት ጥንቃቄዎችን ከግምት ውስጥ ባስገባ መንገድ የፍቃድ አሰጣጥና የክትትል ሥርዓቱ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማና በማዕከል ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። የህንጻ ግንባታዎች በተዘጋጀላቸው ዲዛይንና ቦታ ላይ መከናወናቸውን የሚከታተል ክፍል መኖሩንና፤ ማንኛውም አልሚ የግንባታ ደህንነት መሟላቱን አረጋግጦ ህንጻውን ማጠናቀቅ እንዳለበት አመላክተዋል።

ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተሠራ ባለው ሥራ የማስታወቂያ፣ የመሰረተ ልማትና የሌሎችንም ግንባታዎች ለመቆጣጠር በልዩ ሁኔታ ከጥቅምት ወር ጀምሮ እቅድ ወጥቶ ከማዕከል እስከ ወረዳ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል። በዋና ዋና መስመሮች የከተማ ገጽታን የሚያበላሹ የአጥር ግንባታዎች እንዲስተካከሉ፣ የህንጻ ሽፋኖች ደረጃቸውን እንዲጠብቁና በግንባታ ወቅት የሰራተኞች ደህንነት እንዲጠበቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

🖱ኢንጂነር ከማል እንዳመለከቱት፤ የህንጻ ሽፋን፣ የአጥር ደረጃ፣ የግንባታ ግብዓትና ተረፈ ምርት በመንገድ ላይ የሚያስቀምጡና በህንጻ ደህንነት ላይ ችግር የተገኘባቸው አልሚዎች፣ የግንባታ አማካሪዎችና ኮንትራክተሮች ላይ የማስተካከያ ርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።

የግንባታ ግብዓቶች በእግረኛ መንገዶች ላይ በሚያስቀምጡ በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ያደረሱ ሦስት ሺህ የሚጠጉ አካላት ላይ ርምጃ በመውሰድ ግብዓቶቹን የማንሳት ሥራ ተከናውኗል ሲሉ አስረድተዋል።

በተጨማሪ የከተማዋን ውበት በማበላሸት በየመንገዱ የተሰቀሉ ከ45ሺህ በላይ ማስታወቂያዎች እንዲነሱና በዋና ዋና መንገዶች ላይ በዲጂታል ማስታወቂያዎች እንዲተኩ መደረጉን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

🚧በመንገድ ዳር በተለያዩ ተለጣፊና ተንጠልጣይ መንገዶች የሚሰቀሉ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ማስታወቂያዎች ህጋዊነታቸው ያልተረጋገጡና የመንገድ ደህንነት ህግን ያላከበሩ በመሆናቸው በቀጣይም የማስተካከሉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በከተማዋ ዋና ዋና አካባቢዎች የተሰቀሉ ዲጂታል የማስታወቂያ ቦርዶች ዘመናዊነትን የተላበሱና በውበትም የተመረጡ በመሆናቸው ማንኛውም ማስታወቂያ ያለው አካል ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመነጋገር ወደዘመናዊ ሥርዓቱ መግባት እንደሚችል አስረድተዋል።

Via ኢ ፕ ድ

@etconp

3 months ago

👉WHAT IS QUANTITY SURVEYING

➡️Quantity surveying means generally materials take off preparation and measuring of quantities Such as length,Area,Volumes and Pcs for Construction projects

🏷Quantity Surveying can be cover different tasks like

*⃣preparation of specification.

*⃣Taking measurements of Construction works.

*⃣preparation of approximate cost estimate at the very early stage of the project.

*⃣preparation of detail cost estimate at different stages.

*⃣Valuation of property.

🏷PURPOSE OF QUANTITY SURVEYING

Assist the client to have an accurate estimate of volume of work as well as the required budget.

to assist in the accurate preparation of tenders,by providing uniform Measuring of quantity.

To give an accurate checklist of work accomplished.

To assist in the certification of payments.

To give insight into the required variation work amounts.

#QuantitySurveying

@etconp

3 months, 1 week ago
3 months, 1 week ago
3 months, 1 week ago

👉ውድ የ ቻናላችን ቤተሰቦች

ለ ኮንስትራክሽን እቃ አቅራቢዎች እና ተያያዥ ስራ ወይም ድርጅት ያላቹ

⭐️ዛሬ አንድ የምስራች ይዘን መጥተናል ይህም ለ ሁሉም የግንባታ ግብዓት ዕቃ ማቴሪያል አቅራቢዎች እና ተያያዥ ስራ ያላቹ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ነፃ የ ማስታወቂያ አገልግሎት ለመስጠት አስበናል ስለዚህ ይህን ሀሳብ የምትስማሙ በ @Philemona7 ልታገኙን ትችላላቹ።

🙏እናመሰግናለን🙏

@etconp

3 months, 1 week ago

👉**በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለሚሰማሩ ለውጭ ኣገር ዜጎች ስራፈቃድ ለማውጣት የድጋፍ ደብዳቤ የሚሰጥበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመርያ ቁጥር 29/2012

🖱የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር**

@etconp

3 months, 2 weeks ago

👉በከተማዋ 30 የእግረኛ ማቋረጫ ተሻጋሪ ድልድዮችና መተላለፊያዎች ሊገነቡ ነው

🚧በአዲስ አበባ በቀላል ባቡርና በቀለበት መንገዶች 30 የእግረኛ ማቋረጫ ተሻጋሪ ድልድዮችና መተላለፊያዎች ሊገነቡ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።

ተሻጋሪ ድልድዮቹና መተላለፊያ መስመሮቹ ከመሬት በላይ እንዲሁም በመሬት ውስጥ እንደሚገነቡም ተገልጿል።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እያሱ ሰለሞን ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለሥልጣኑ የከተማዋን አጠቃላይ የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ፣ ቀልጣፋና ደኅንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ በርካታ የመንገድ ግንባታ ሥራዎች እያከናወነ ይገኛል።

ከሚከናወኑ የመንገድ መሠረተ-ልማቶች መካከልም የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ እድገት መሠረት ያደረገ የእግረኛ ማቋረጫ ተሻጋሪ ድልድዮችና መተላለፊያዎች ግንባታ ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በሚያልፍባቸውና ውስጠኛው ቀለበት መንገድ ተብለው በሚጠሩ ቦታዎች ላይ መሸጋገሪያ ድልድዮችና መተላለፊያዎች ባለመኖራቸው እግረኞች ለትራፊክ አደጋ እየተጋለጡና መንገድ ለማቋረጥ ረዥም ርቀት ለመጓዝ እንደሚገደዱ ተናግረዋል።

ይህን ታሳቢ በማድረግ አሁን ላይ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች 30 የእግረኛ ማቋረጫ ተሻጋሪ ድልድዮችና መተላለፊያ መስመሮች ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

▶️ተሻጋሪ ድልድዮቹና መተላለፊያ መስመሮቹ የቀላል ባቡርና የቀለበት መንገዶችን ተከትሎ ከመሬት በላይ እንዲሁም በመሬት ውስጥ እንደሚገነቡ ጠቁመዋል።

▶️የዲዛይን ሥራው "አድቫንስድ ኢንጂነሪንግ ሶሉዩሽን" በተባለ የውጭና "ታክት" በተሰኘ አገር በቀል አማካሪ ድርጅት አማካኝነት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የዲዛይን ሥራው 23 ሚሊየን ብር የሚጠይቅ እንደሆነም አስረድተዋል።

▶️የእግረኛ ተሻጋሪ ድልድዮቹ ሐናማርያም፣ ኃይሌ ጋርመንት፣ ሳሪስ ሐኪም ማሞ ሰፈር፣ አደይ አበባ፣ ጉርድ ሾላ፣ አውቶቡስ ተራና አብነት አካባቢ እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች የሚገነቡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

▶️በተሻጋሪ ድልድዮችና መተላለፊያ መስመሮች አካባቢ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንደሚገነቡ ገልፀዋል።
የዲዛይን ሥራው በፍጥነት ተጠናቆ ወደ ተግባር ለማስገባት በቀጣይ ተያያዥ ሥራዎች በትኩረት ይሠራሉ ብለዋል።

🖱የሚገነቡት የእግረኞች መሸጋገሪያ ድልድዮችና መተላለፊያዎች የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ ባሻገር መንገድ ለማቋረጥ ረዥም ርቀት መጓዝን እንደሚያስቀሩ ጠቅሰዋል።

Via ኢዜአ

@etconp

3 months, 2 weeks ago

👉10 Basic Rules For Design Of Column:

🚧1. Minimum size of Column 225mm x 225mm (9"x9")

🚧2. Choose Square Column, if load acts at axis.

🚧3. Choose Rectangular Column, if load acts at eccentric
axis of column.

🚧4. Lapping Length for Column is 48d.

🚧5. Minimum 4 No's of Longitudinal Bars requised
for Square & Rectangular Column and 6 Nos for
Circular Column.

🚧6. Minimum dia of Longitudinal Bar is 12 mm and
Min. Dia. of Lateral Tie is 6 mm.

🚧7. Longitudinal Bars should be Duck Leg to link foundation.

🚧8. Minimum Area of Reinforcement percentage is
0.8% & Maximum is 6% of Column Cross-section

🚧9. C-20 Grade Concrete & Fe-500 Steel used
for Column.

🚧10. Spacing between Ties not greater then 100mm for Zone-A and not greater then 150mm for
Zone-B

@etconp

3 months, 2 weeks ago

👉ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከኮሪያ ሪፐብሊክ መንግስት በተገኘ የ30 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ የከተማ መሬት መረጃን ለማዘመን የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊያደርግ ነው

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከኮሪያ ሪፐብሊክ መንግስት በተገኘ የ30 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ የከተማ መሬት መረጃን ለማዘመን የሚያስችል ፕሮጀከት WAVUS JV ከተባለ ከሀገሪቱ መንግስት ኩባኒያ ጋር የኮንትራት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር  ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በፊርማ ስነ-ሥርዓቱ ወቅት ኢትዮጵያና የደቡብ ኮሪያ ሪፕብሊክ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ግንኙነታቸው የዳበረ ታሪካዊና ባህላዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያና የኮሪያ ሪፐብሊክ ግንኙነት በዲፕሎማሲው እና በልማት ላይ የተመሰረተ ብቻ ሳይሆን በደምም የተሳሰረ በመሆኑ ስምምነቱ ይህንን የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ትስስር የበለጠ ያጠናክረዋል፡፡

በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ውስን የሆነውን የመሬት ሀብት በዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርአት በመታገዝ ለዜጎች ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት ወቅቱ የሚጠይቀው ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡

ለሚቀጥሉት አራት አመታት በአራት ከተሞች ተግባራዊ የምናደርገው ይሄው ፕሮጀክት በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ በየደረጃው የሚገኙ የከተማ አመራሮች ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱን የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ  አቶ ፈንታ ደጀን እና WAVUS JV ካምፓኒ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ኪም ሀክ ሱንግ ተፈራርመዋል፡፡

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር የመሬትና የካዳስተር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ብዙዓለም አድማሱ ፕሮጀክቱ በአዳማ፣ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሰዶ እና በባህርዳር ከተሞች ለአራት ዓመታት ያህል እንዲሚከናወን አብራርተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በድጅታላይዘሼን፣ በመሬት መረጃ አያያዝ ስርአት፣ በዳታ ማዕከል ግንባታ፣ በአቅም ግንባታ እና መሰል የዘርፉ ስራዎች ላይ እንደሚያተኩር አቶ ብዙዓለም  አስገንዝበዋል፡፡

@etconp

5 months, 2 weeks ago
Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 5 days, 11 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month ago

ጥራት ያላቸው የቤት ዕቃዎችንና የቤት ማስዋቢያ ቁሳቁሶችን ከእኛ ይግዙ። አድራሻ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ 376 ያገኙናል። ባሉበት ሆነው ማዘዝ ይችላሉ። 0944222324

Last updated 23 hours ago