በ ግጥም

Description
በግጥም ቻነል ውስጥ:-
◇የተለያዩ ገጣሚያን ግጥሞች?
◇የተመረጡ አባባሎች ?
◇አስተማሪ ፅሁፎች እናም ሌሎች ❤️
እነዚህን ለማግኘት subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ?
ለ አስተያየት :- @sari_na9
Advertising
We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc

7 months, 2 weeks ago

የእጣዬ :ፈንታዬ ፍሬ

ከፍጥረታት ተርታ ፥አድምቆ ከተበኝ
ሰው በሚል ቃል ፥ወደርሱ አቀረበኝ
የእጣዬ ፥ባለቤት
የፈንታዬ ፥ወሳኝ
ከጠብታ ፥አንስቶ
ከመኖር፥ አወሳኝ
.
ከእናቴ ማህፀን ፥ድሎት ከሞላበት
ዘጠኝ ወር ጨርሼ፥ደግሞ ልሰናበት
.
ከማየት ጉጉቷ ፥ከነበራት ብርታት
ታደለች ልታየኝ ፥ከአይኔም አልገታት
አቅፋኝ አይበቃት ፥አይታ አትጠግብ
የጠገብኩ አይመስላት ፥ደሞ ስትመግብ
.
ጥርሴ ሱሷ፥ ያበቀለው ወተት
ልታይ ፈገግታዬን፥ ደግሞ መንከራተት
አፌን ስፈታ፥ የወጣኝ ቃል
ዘላለም ትልቅ ነዉ ፥ ለርሷ ይልቃል
*እማ አልኳት፥ ተስፋዋን ስቀጥል
እኔ የሷ ልጅ፥ የሷ ቅምጥል
.
መራመድ ጀምሬ፥በሩጫ ሳለው
ወድቄ ስቆስል
ህመም ለቅሶዋ፥እንደወጋት ስል
.
ደሞ ደሞ
ከመኖር ቢያስሞጥለኝ
ፍቅር ይዞ ሲያነሳ ሲጥለኝ
ደሞ ደሞ
ከመኖር ቢያስተዛዝበኝ
በ ክፉ :ደጉ ዙሪያዬን ሲከበኝ
.
እንዲህ
እጣዬ አምሮ፥ ፈንታዬን ሳጣጥም
ነፍሴ ተገኘ ፥ሆኖ የግጥም
.
ግጥም ለነፍሴ ፥የመኖሬ አሻራ
ሁሉን የማይበት ፥የምዕናቤ ሸራ
ግጥም ለነፍሴ ፥የማለፊያ ደሴት
ምንም ቢሰማኝ ፥ሀዘን ወይ ሀሴት
.
ግጥም ማለት ለ'ኔ
የነፍሴ ብርሃን፥ ሚታይበት መስኮት
ከምድር አንስቶ ፥ደራሽ ከመለኮት።

@sari_na9
Like &share ❣️

7 months, 2 weeks ago

ፍቅር ጥላ ሲጥል

በገና ቢቀኙ
ሸክላ ቢያዘፍኑ
ክራር ቢጫወቱ…..
ለሚወዱት ምነው
ሙዚቃ ቢያዜሙ
ቃል ቢደረድሩ
ጌጥ ውበት ቢፈጥሩ
ቤት ንብረት ቢሠሩ
አበባ ቢልኩ
ምነው ቢናፍቁ
አገር ቢያቋርጡ
ቢሄዱ ቢርቁ
አመት ቢጠብቁ
ለሚወዱት ምነው?
~~~~~~~
©ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ

7 months, 3 weeks ago

ሚስጥር ነው

እንደ ገደል ዳር ሳር ጸጉሯን አንዠርፍፋ
እንደ ኮቷ ጸዳል መንበሯ ላይ አርፋ
ልትሄድ ነው አትበሉኝ አትርቅም ከራሷ
ቀጠሮም ወጉ ነው ለዛሬው ሞገሷ
ቀኑም ይኳትናል ሌቱ አይልም አልነጋ
በመጭው ንጋት ነው ከልብ የምንረጋ፤

አንቺ እንደ ተራራ እኔ እንደ ወዲያ ሃገር
ከአንቺ ተቁሞ ነው መኖሬ የሚነገር
አንቺ እንደ ንፋሱ እኔ ህያው ሳሚ
በባዶ ሰማይ ላይ ቆሜ አንችን አላሚ
አንቺ እንደ መስከረም እኔው ደግሞ አበባ
ውበት ያለ አንዳችን ለስምረት አይጠባ
አይቶ መመኜትን ለልብ ማን አደለው?
ለምን? አትበሉኝ
እንዴት? አትበሉኝ
አድሮ ያልተፈታ እሱ እኮ ሚስጥር ነው፤

የሚልሽ አለና ማምሻውን ጠብቆ
ምን ያደርጋል ግምጃ ሻሽና ጥብቆ
በዓይን አይመረመር
በልብ አይሰፈር
ይሄ ሁሉ ቅኔ ይሄ ሁሉ ምስጢር
በወራት በአዝማናት አልፎ ‘ማይሰፈር
ለመለኮት ህጸጽ ለሰው ህያው ክብር
ለድኅነት ነውና ጾም ጸሎቱ
በምስጢር ጀምሬው ተዓምር ሆነ ቤቱ።

7 months, 3 weeks ago

[ሠለስቱ ...]
_
፩.
[አምሳለ ጠርሙስ ገላ
በውስጡ ትንኝ ነፍስ ይዟል]
______
ጠርሙስ መውደቁ
ገላ መድቀቁ
አይቀርምና...፤
ስጋ ሲፈርስ ገላ ሲሰበር...
ነፍስ መብረሯ...
እርግጥ ነውና.....፤
(ከሞት ባሻገር አለ ጎዳና።)
ለእግዜርስ ይሄ መች ይጠፋዋል!?
“ሁለት” ያሉትን አንድ ያደርገዋል ።
(አንድ ያደርገዋል “ሁለት” ያሉትን...)
የሠው ሠውነትን....
ስጋና መንፈስን...
(ታቦትወ መቅደስን)
ባንዲት ቀጭን ገመድ
ፈትሎ ሲያስተሳስር ፤
ትንኝ ነፍስ ያኖራል...
ከጠርሙስ ገላ ስር ።

፪.
[መሽቶ ነበር ...
ሞት አማረኝ.... ]
____
ደቂቅ ክንፋም ትንኝ ነፍሴ...
ጠርሙስ ገላ ተከድኖባት ፤
(ብርጭቆ ስጋ ተዘግቶባት ...)
መውጣት አምሯት ትጮኻለች ፤
ከጠርሙሱ ግድግዳ ጋር
ወዲያ ወዲህ — ትጋጫለች ፤
"ስበርልኝ ይሄን ስጋ
ልውጣ ልብረር " — ትለኛለች ።

"ምን አገባኝ ስለ ሲኦል ?!
ምን ጨነቀኝ ስለ ኋላ ?!
በ`ሳት መሀል መቀመጡ
(መች ይብሳል ከዚህ ኑሮ)
መች ይብሳል ከዚህ ገላ!?
ስበርልኝ
ከስክስልኝ
ልውጣ ልብረር ሆዴ ይሙላ "

፫.
[ዝም እላለሁ....
እንዳልሰማሁ...]
___
መታሰርን ጠልታ
(ነጻነቷን ሽታ...)
"ልብረር ልውጣ ልውጣ
ልቀቀኝ እባክህ? "
— ብትል ትንኝ ነፍሴ ፤
(አ ል ፈ ቀ ድ ኩ ላ ት ም
አ ል ሰ በ ር ኩ ላ ት ም )
— ሳሳሁ ለጠርሙሴ ።
?
___
BekAlu ShuMye

7 months, 3 weeks ago
በ ግጥም
7 months, 3 weeks ago
በ ግጥም
7 months, 4 weeks ago
በ ግጥም
8 months ago
8 months ago
በ ግጥም
9 months, 4 weeks ago

◇•○ስውር~ልብ○•◇
☆ክፍል~3☆
✍️ ፀሀፊ:ቃል
እንደገባው የአልማዝ ፈርጥ የመሰሉ ክብ ክብ የሰሩ ብርሃኖች መሬት ላይ አየሁ ።ብርሃኑን ተከትዬ ወደ ላይ ቀና ስል ቆርቆሮው ከማርጀቱ የተነሳ ወንፊት ሆንዋል። ወደ ጎን ስመለከት መሬቱ ላይ ትንሽዬ ጣል የተደረገች ፍራሽ ላይ እድሜያቸው የገፋ እና እና በሽታ ያደከማቸው አዛውንት ተቀምጠዋል። ፀጉራቸው ሉጫ ሲሆን ንጣቱ ጥጥን ያስንቃል።

የደረቡት ጋቢ ወደ ቡናማነት ተቀይሮ መልኩን ለቋል። አንሷላዋም በጣም ከማገልገሏ ብዛት አፍ ቢኖራት' በቃኝ' ትላለች። ግርግዳውን ሳየው ከመሰነጣጠቁ የተነሳ ለሌሎች ጥቃቅን ነፍሳት የሚያከራዮት ነው የሚመስለው። ይሄን እያሰብኩ እንደ ህፃን እየቦረቀ 'ድክ ድክ ' የሚል አይጥ 'ዱብ' ሲል እውነትም እያልኩ ፈገግ አልኩ።

የሰላም አባት ነቅተውብኝ መሰለኝ። እርሳቸውም ፈገግ እያሉ "እ ጓሮ ታገኝያታለሽ ግቢ " ሲሉኝ ከገባውበት ሰመመን ቀሰቀሱኝ። እኔም ድንግጥ አልኩና እየተርበተበትኩ "ሰላም ሰላም " እየተጣራው ወደ እሷ ሄድኩ ።እሷም ካለ ወትሮዬ እነርሱ ቤት በመሄዴ ግራ እየተጋባች " ከየት ተገኘሽ" አለችኝ። እኔም ጥቁር እንግዳ መሆኔ ገባኝ እና ምን እንደምላት ግራ ገባኝ ።ከዛ ግን የሆነ ነገር ትዝ አለኝ ።
????? &?????❤️

We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc