Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

Mm

Description
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

1 month ago

ይቅርታ አንዳንዴ የምንዘገየው በወረፋ ምክንያት በመሆኑ ትንሽ ይጠብቁን

https://t.me/drabufewzan2

1 month ago

#ስትሮክ

#ስትሮክ ምንድን ነው?

🖋 የራስ ቅል (ጭንቅላት)ውስጥ ደም ሲፈስ
🖋 ወደ ጭንቅላት ውስጥ የጓጎለ ደም ሲገባ
🖋 ወደ ጭቅላት የሚገባው ደም ሲቋረጥ ነው።
እንደ አጠቃላይ ስትሮክ ማለት ከላይ በተጠቀሱት ምክናየት አንጎል ሲጠቃ ነው።

🖋 ሁለት አይነት ስትሮክ አለ

📌 1ኛው ኢስኬሚክ(Ischemic) ስትሮክ የሚባል ነው።

ይህ አይነቱ ስትሮክ በሰውነት ውስጥ ባሉና በተለያዩ የደም ቱቦዎች ውስጥ ደም ይጒጉልና ከዚያም ወደ አንጎል በመሄድ የአንጒል ህዊሳትን ሲያውክና ሲያውክ የሚፈጠር ነው። ይህም የአንጎል ህዋሳት ግልኮስና ኦክስጅን እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል። 80% የሚሆነው ስትሮክ በዚህ ምክናየት ይከሰታል።

📌 2ኛው ሄሞረጅክ(Hemorragic) ስትሮክ የሚባል ነው።

ይህ ደግሞ ቀጥታ አንጎል ውስጥ ደም ሲፈስ የሚከሰት ነው።ምክናየቱ ደግሞ ከፍተኛ የደም ግፊት፡ የደም ቱቦዎች መሳሳትና መቅጠን ነው።

#ዋና ዋና የስትሮክ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

  1. የእጅ፡ የእግርና የፊት መደንዘዝና መስነፍ
  2. እይታን ማጣት
  3. መናገር አለመቻል
  4. ሌሎች የተናገሩንንም መረዳት አለመቻል
  5. ድንገተኛና ከባድ የራስ ምታት
  6. የሰውነትን ሚዛን መጠበቅ አለመቻል

#ስትሮክን መከላከል ይቻላል?

አዎ 50% መከላከል ይቻላል።

#ለስትሮክ የሚያጋልጡ ነገሮች

  1. ከፍተኛ የደም ግፊት
  2. የልብ ችግር(ሁሉም አይደለም)
  3. ከቁጥጥር ያለፈ የስኳር በሽታ
  4. የኰሌስትሮል መጠን መጨመር
  5. ማጤስ
  6. መጡኑ የጨመረ የአልኮል መጠጥ
  7. ውፍረት
  8. ጭንቅላትንና ልብን የሚመግቡ የደም ቱቦዎች ላይ ችግር ካለ።
  9. ወንድ መሆን፡ እድሜ ከ65በላይ ከሆነ፡ በቤተሰብ ካለና ጥቁር መሆን የመጠቃት እድል ከሌሎች አኳያ ይጨምራል።

❗️ ስትሮክ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት።

  1. Major Stroke የሚባል፡ ለማከብ አስቸጋሪ የሆነና ወድያው ገዳይ የሆነ ነው።
  2. Minor Stroke የሚባል፡ የሚታከምና በህክምና ለውጥ ማምጣት የሚቻልበት አይነት ነው።

🔺አስታውሱ

በህይዎተዎ ሳያውቁት አንድ ጊዜም ይሁን ከዚያ በላይ እራሰዎን ስተው የመውደቅ አጋጣሚ ከገጠመዎት በስትሮክ የመመታት እድሉ ሊኖረዎት ስለሚችል እራሰዎን ለሀኪም ያሳዩ።

መልካም ቀን

#ዶክተር ከድር ነኝ
#በህክምና ስነምግባር ሚስጥርዎን ጠብቀን እናማክራለን!
#በርቀት መታከም ለሚችል በሽታ በርቀት እናክማለን!
#ስለጤናዎ ማማከር ሲፈልጉ በውስጥ መስመር ይፃፉልን
👇👇👇👇👇
@Drabufewzan1

#ሸር በማድረግ ቻናላችን ያስተዋውቁ

https://t.me/drabufewzan2

1 month ago

በህይወትህ አርፋጅ አትሁን።

በህይወቱ የሚያረፍድ ሰው ብዙ ነገሮችን መስዋት ያደርጋል።

ስለዚህ በህይወትህ አታርፍድ።

የመለወጥ ጊዜው አሁን ነው!

ለመቀየር ጊዜው አሁን ነው።

ስራህን ለማስተካከል ጊዜው አሁን ነው።

ከቤተሰብ ጋር ያለህን ችግር ለማስተካከል ጊዜው አሁን ነው።

አሁን ላይ ማድረግ ያለብህን ካደረክ በህይወትህ አታረፍድም።

https://t.me/drabufewzan2

1 month ago

የኩላሊት ጠጠር ህመም

👉የጠጠር ህመም በብዛት ከሚከስቱ ህመሞች መካከል አንዱ ነው። የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው በጣም ከፍተኛ ህመም የሚፈጠር ህመም ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ግን ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል። የጠጠር ህመም የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሊፈጥርና የኩላሊትን ስራ ሊያውክ ይችላል። ስለዚህም የመከላከያና የህክምና መንገዶችን ማወቅ ተገቢ ነው።

የኩላሊት ጠጠር ምንድን ነው?

🔴 የኩላሊት ጠጠር ጠንካራ የሆነ በኩላሊት ወይም በሽንት ማስተላለፊያ አካላት ውስጥ የሚፈጠር ጠጠር ነው። በሽንት ውስጥ የጠጣር ነገሮች ወይም እንደ ካልሲያም ኦክሳሌት፣ ዩሬት ወይም ፎስፌት ያሉ ቅንጣቶች መብዛት ምክኒያት እንደሆነ ይታመናል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቅንጣቶች በሽንት ውስጥ ተከማችተው ቀስ በቀስ በመጠን ከጨመሩ በኋላ በረጅም ጊዜ ጠጠር ይፈጥራሉ።

ምንም አይነት እክል በማይኖርበት ጊዜ ሽንት ውስጥ ቅንጣቶች እንዳይሠባሠቡ የሚያደርጉ ንጥረ ነገሮች አሉ። የነዚህ ንጥረ ነገሮች መዛባት በኩላሊት ጠጠር መፈጠር አስተዋፅዖ ያደርጋል። የሽንት ማስተላለፊያ አካላት ውስጥ የሚፈጠር የጠጠር ህመም የሀሞት ከረጢት ውስጥ ከሚከስተው የሀሞት ጠጠር የሚባለው ህመም የተለየ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው።

🔴 የሽንት ማስተላለፊያ ጠጠሮች ምን አይነት መጠን ፣ ቅርፅና ቦታ ይኖራቸዋል?

ጠጠሮች በመጠንና ቅርፅ ይለያያሉ። መጠናቸው ከአንዲት ፍሬ አሸዋ እስከ ቴኒስ መጫወቻ ኳስ ሊለያይ ይችላል። ቅርጻቸውም ለስላሳ ገጽ ያላቸው ድቡልቡልና ሞላላ ሊሆን እንደሚችሉ ሁሉ በጣም ሻካራና በወል የማይታወቅ ቅርፅ ያላቸው ሊሆን ይችላል። ለስላሳ ገፅ ያላቸው ጠጠሮች የሚፈጥሩት ህመም ቀነስ ያለና ለመወገድ ብዙ የማያስቸግሩ ናቸው። በአንፃሩ ሻካራ ጠጠሮች የሚፈጥሩት ህመም ከፍተኛ ሲሆን በቀላሉ መወገድ የማይችሉ ናቸዉ። ጠጠር በየትኛውም የሽንት ማስተላለፊያ አካል ውስጥ ሊከሰት ቢችልም አብዛኛውን ጊዜ በኩላሊት ተፈጥሮ ወደላይኛው የሽንት ቧንቧ (ዩሬተር) አልፎ ጠባቡ ቦታ ላይ ይቀረቀራል።

ኩላሊት ጠጠር እንዲፈጠር አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ነገሮች ምንድን ናቸው?
♦️ በቀን የሚወስደው የፈሳሽ መጠን ማነስ
♦️ በቤተሰብ ውስጥ የጠጠር ህመም መኖር
♦️ አመጋገብ: እንስሳት ተዋፅዖ ፣ ሶዲየም፣ በዝቅተኛ መጠን አትክልት እና ሲትረስ መወሰድ

🟥75 በመቶ የኩላሊት ጠጠርና የ የ 95 በመቶ በፊኛ ውስጥ የሚፈጠሩ ጠጠሮች ወንዶች ላይ የሚፈጠሩ ናቸው።
🔺ከ 20-70 የዕድሜ ክልል ያሉ ወንዶች ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ነው።
🔺የአልጋ ቁራኛ አልያም እምብዛም የማይንቀሣቀስ ሰው
🔺ሞቃታማ በሆነ አካባቢ መኖር
🔺ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እንዲሁም፤ የሽንት ፍሰት መዛባት
🔺እንደ ታይሮይድ እና ሲስቲንዩሪያ ያሉ ህመሞች
🔺ለመሽናት የሚያግዙ መድሀኒቶች እና የጨጓራ አሲድ የሚቀንሱ መድሀኒ ቶች

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

🔴 እንደ ጠጠሩ ቦታ መጠንና ቅርፅ የሚለያዩ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ፡-

🔺በሆድ አካባቢ የሚሰማ ህመም
🔺ምንም ምልክት አለመታየት
🔺ቶሎ ቶሎ ሽንት መምጣት እና አጠዳፊ የሽንት ፍላጐት መኖር የሽንት ፊኛ ዉስጥ ጠጠር መኖሩን አመላካቾች ናቸዉ።
🔺ጠጠር በሽንት ማስወገድ
🔺ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
🔺ደም የቀላቀለ ሽንት
🔺በሚሸኑ ጊዜ ማመም ወይም ማቃጠል
🔺የታቸኛው የሽንት ማስተላለፊያ ቱቦ ላይ የተቀረቀረ ጠጠር ካለ ሽንት መፍሰስ ከጀመረ በኋላ በድንገት ማቋረጥ ሊኖር ይችላል
🔺አንዳንድ ጊዜ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና የሽንት ቧንቧ መዘጋት ሊያገ ጥምና ቋሚ ወይም ጊዜያዊ የኩላሊት ስራ መዛባት ሊያጋጥም ይችላል

በጠጠር ምክንያት ምን አይነት የሆድ ህመም ሊከሰት ይችላል?
የህመሙ ቦታና ክብደት እንደ ቦታው ፣ እንደ አቀማመጡ እና እንደየሰዉ ይለያያል። የጠጠሩ መጠን ከህመሙ መጠን ጋር አይገናኝም። ትንንሽ ሆነው ሻካራ የሆኑ ጠጠሮች ትልልቅ ሆነው ለስላሳ ከሆኑ ጠጠሮች የባሰ ህመም ያስከትላሉ።
የጠጠር ህመም ፤በዉል ከማይታወቅ የጎን ህመም እስከ ከባድ የህመም ደረጃ ሊደርስ ይችላል። ህመሙ በአቋቋም ወይም አቀማመጥ እና በእን ቅስቃሴዎች ሁኔታም ሊባባስ ይችላል። ከደቂቃዎች እስከ ሠዓታት የሚዘ ልቅ ህመም ይፈጠርና ከዚያም ህመሙ እየቆየ ጋብ የሚል ይሆናል። ይህ ዓይነት ህመም ከጠጠር ጋር የተያያዘ ምልክት ነው በአብዛኛዉ።
ህመሙ ጠጠሩ ባለበት ጎን በብዛት የሚኖር ይሆናል። በአብዛኛው ከእም ብርት በታች ና የጎን ሆድ ወደ መራቢያ አካላት አካባቢ የሚሰራጭ ህመም ከማቅለሽለሽና ማስመለስ ጋር የጠጠር ህመም መለያ ምልክቶች ናቸው።
ፊኛ ውስጥ ያለ ጠጠር፤ ከእምብርት በታች ህመም እና ወንዶች ላይ በሽንት አወጋገድ ወቅት፤ ብልት ጫፍ ላይ ህመም ሊፈጥር ይችላል።
ጠጠር የሽንት ማስተላለፊያ አካላት ዉስጥ ሲቀር የሚፈጥረው ድንገ ተኛ ህመም ፋታ የሚሰጥ ባለመሆኑ በዚህ ሰዓት ወዲያውኑ ሀኪም ዘንድ መቅረብ ግድ ይሆናል።

የኩላሊት ጠጠር ኩላሊትን ምን ድረስ ይጎዳል?

🔴 በኩላሊት ወይም በላይኛው ሽንት ማስተላለፊያ (ዩሬተር) ውስጥ የተቀረቀረ ጠጠር ሽንት እንደልብ እንዳይተላለፍ ያደርጋል። እንደዚህ ያለ የማስተላለፊያ መደፈን ፤ ከኩላሊት ሽንትን ተቀብለው ወደላይኛው ሽንት ማስተላለፊያ (ዩሬተር) የሚወስዱ ትንንሽ ቧንቧዎች በፈሳሽ ብዛት እንዲወጠሩ እና ከጊዜም ብዛት የኩላሊት ስራ መዳከም እንዲመጣ ያደርጋል።

የኩላልት ጠጠር መከላክያ መንገዶች ምንድን ናቸው?
ህክምናውስ??

#ዶክተር ከድር ነኝ
#በህክምና ስነምግባር ሚስጥርዎን ጠብቀን እናማክራለን!
#በርቀት መታከም ለሚችል በሽታ በርቀት እናክማለን!
#ስለጤናዎ ማማከር ሲፈልጉ በውስጥ መስመር ይፃፉልን
👇👇👇👇👇
@Drabufewzan1

#ሸር በማድረግ ቻናላችን ያስተዋውቁ

https://t.me/drabufewzan2

1 month, 1 week ago

ወድ የቻናላችን ቤተሰቦች ዛሬ ይዘንላቹ የቀረብነው በሆዳችን ክፍል ህመማችንን ለመለየት የሚረዳን ፅሁፍ ነው ተከታተኩን።

በሆድ ክፍል ህመምን የመለየት ዘዴ

👉 ዘጠኝ አይነት የሆድ ክፍሎች በእነሱ እንዴት ህመማችንን መለየት እንችላለን?
1. የቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል
• የጉበት ህመም
• የሆድ ቁስለት
• የሃሞት ጠጠር
• የቀኝ ኩላሊት ህመም

  1. የላይኛው የመሃል የሆድ ክፍል
    • የጨጓራ ህመም
    • የምግብ አለመፈጨት
    • የሆድ ቁስለት
    • የጣፊያ ኢንፌክሽን
    • የጉበት ህመም

  2. የግራ የላይኛው የሆድ ክፍል
    • የሆድ ቁስለት
    • የአንጀት ቁስለት
    • የግራ ኩላሊት ህመም
    • የሃሞት በሽታ
    • የጣፊያ ህመም

  3. የቀኝ የጎን መሁለኛው የሆድ ክፍል
    • የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
    • የሆድ ድርቀት
    • የኩላሊት ጠጠር

  4. የእንብርት አካባቢ የሆድ ክፍል(center)
    • ትርፍ አንጀት
    • የአንጀት መታወክ
    • የእንብርት መቁሰል
    • የጣፊያ ህመም

  5. የግራ ጎን መሃለኛው የሆድ ክፍል
    • የኩላሊት ጠጠር
    • የአንጀት መታወክ
    • የአንጀት ኢንፌክሽን

  6. የቀኝ ጎን የታችኛው የሆድ ክፍል
    • ትርፍ አንጀት
    • የሆድ ድርቀት
    • የማህጸን አካባቢ ህመም
    • ትንሹን እና ትልቁን አንጀት የሚያገናኘው ህዋስ ህመም

  7. የሆድ ታችኛው መሃለኛው ክፍል
    • የፊኛ ኢንፌክሽን
    • የማህጸን አካባቢ ህመም
    • የትልቁ አንጀት ህመም

  8. የግራ ጎን የታችኛው የሆድ ክፍል
    • የትልቁ አንጀት ህመም

#ዶክተር #ከድር ነኝ
#በህክምና ስነምግባር ሚስጥርዎን ጠብቀን እናማክራለን!
#በርቀት መታከም ለሚችል በሽታ በርቀት እናክማለን!
#ስለጤናዎ ማማከር ሲፈልጉ በውስጥ መስመር ይፃፉልን
👇👇👇👇👇
@Drabufewzan1

#ሸር በማድረግ ቻናላችን ያስተዋውቁ

https://t.me/drabufewzan2

1 month, 1 week ago

Rabies 'የእብድ ውሻ በሽታ' መከላከያ መንገዶች

ምንድነው?
💡ሬቢስ በተባለ ቫይረስ በተያዘ እንስሳ አማካኝነት ወደ ሰው በንክሻ ወይም በመ'ቧጨር የሚተላለፍ ሲሆን; ይህም የተጎጂውን ዋነኛ ነርቮች በማጥቃት ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ ነው።

💡በተለምዶ የእብድ ውሻ በሽታ ይሰኛል; ይህም ዘጠና በመቶ በላይ በሽታው የሚከሰተው ቫይረሱን በተሸከሙ ውሾች አማካኝነት በመሆኑ ነው።

አንድ ሰው በውሻ ከተነከሰ ምን ያድርግ?

💡 በመጀመሪያ ተጠቂው ወደ ጤና ተቋም ማቅናት ይኖርበታል።
ይህን ማድረግ ያልቻለ ሰው ግን:-

  1. ቁስሉን በውሃና በሳሙና ማጠብ; ለ15ደቂቃ ቁስሉ ላይ ውሃ ማፍሰስ

  2. በመቀጠል በፖቪዶን አዮዲን ማፅዳት(ቫይረሱን የመግደል ባሕሪ አለው)

{ቁስሉን በዚህ መልኩ በማፅዳት በቫይረሱ የመያዝ እድልን 90% በላይ መቀነስ ይቻላል}

  1. ውሻውን በማሰር ቢያንስ ለ10 ቀን ያክል መከታተል።
    (ክትባት የወሰደ ከሆነ; ያንን ማረጋገጥ ያስፈልጋል)

  2. ጤና ተቋም በመቅረብ የክትባት አማራጮችን መማከር; የቴታነስ መድሃኒት መውሰድና የቁስሉን ሁኔታ መከታተል ያስፈልጋል።

#ዶክተር #ከድር ነኝ
#በህክምና ስነምግባር ሚስጥርዎን ጠብቀን እናማክራለን!
#በርቀት መታከም ለሚችል በሽታ በርቀት እናክማለን!
#ስለጤናዎ ማማከር ሲፈልጉ በውስጥ መስመር ይፃፉልን
👇👇👇👇👇
@Drabufewzan1

#ሸር በማድረግ ቻናላችን ያስተዋውቁ

https://t.me/drabufewzan2

1 month, 1 week ago

የስኳር ህመም አለብዎ?
እንግዲያውስ ክትትልዎ ላይ እነዚህን የሲዳሲ አቅጣጫዎች ልብ ይበሉ

🟥 የስኳር በሽታ በየቀኑ ራስዎ ላይ ቸክ ከሚዬደርጉት እስከ አመታዊ ምርመራዎችና ክትትልና ይፈልጋል።

👉 በየቀኑ

🔴በየቀኑ በሀኪምዎ በተነገረዎት ድግግሞሽ መሰረት ስኳርዎን ይለኩ። ፅፈው በማስቀመጥ በቀጣይ ቀጠሮዎት ውጤቱን ለሀኪዎት ያሳዩ
🔴በየቀኑ የእግርዎን ታች ክፍል ይመልከቱ። ይህን ማድረግ ከከበድዎ መስታውት ይጠቀሙ ወይም የቤተሰብ አባል በዚህ እንዲያግዝዎት ያድስጉ።
የቆዳ መሰንጠቅ፣ ማበጥ፣ መቅላት፣ መቁሰል፣ ውሀ መቋጠር፣ቆዳ ወይም ጥፍርዎ ላይለውጥ መኖሩን ይመልከቱ።
🔴 በየቀኑ የስኳር መድሀኒትዎን ይውሰዱ።(ጤነኝነት ቢሰማዎትም)

👉 በየሶስት ወሩ

🔴 Hb A1c
የስኳር ህክምና ለውጥ ሲያደርጉ ወይም የስኳር የሚፈለገው መጠን ላይ ካልደረሰ ይህ ምርመራ የ3 ወር ስኳር መጠንን የሚያሳይ ስለሆነ በየ 3 ወር ይሰራል
🔴 ደምዎት ይለካል
🔴 ክብደትዎት ይለካል
🔴 ሀክምዎት ይመረምርዎታል።

👉 በየ ስድስት ወሩ

🔴 የጥርስ ማስፀዳትና ክትትል ይኑርዎት
(በተለይም ሀኪምዎት ይህን ምክር ከሰጠዎት።)
⭕️ ጥርስ ሀኪምዎ ጋር በሄዱ ሰዓት ስኳር በሽታ እንዳለብዎ መንገር አይዘንጉ
🔴 Hb A1c
ጥሩ የስኳር መጠን ላይ ከሆኑ በዚህ ሰዓት ያሰሩ።
🔴 የዶክተር ክትትል
ጥሩ የስኳር መጠን ላይ ከሆኑ ዶክተርዎት በዚህ ሰዓት ምርመራዎችን ያድርግልዎት
🔴 ደም ይለኩ
🔴 ክብደት ይለኩ

👉 በየዓመቱ

🔴 የኩላሊት ምርመራ ያድርጉ
🔴 የኮሌስትሮል ምርመራ ያሰሩ
🔴 የዓይን ምርመራ ያድርጉ
🔴 የጆሮ ምርመራ ያድርጉ
🔴 እግርዎት በደምብ ይመርመር

👉 በህይወት ዘመንዎ አንዴ

🔴 ሄፓታይተስ ቢ(የጉበት ቫይረስ)
🔴 የሳምባ ነቀርሳ ክትባቶችን ይውሰዱ

👉 እንዳስፈላጊነቱ

🔴 የአእምሮ ጤናና ሌሎች ምርመራ ሀኪምዎ ጋር ተነጋግረው ያድርጉ።

ማሳሰቢያ፦
👉የስኳር በሽታ በተለይም ሁለተኛው ዓይነት ብዙ ችግሮችን ሲያመጣ ምልክት ስለማያሳይ ጣንነዕ ቢሰማዎትም ምርመራዎች ላይ አይዘናጉ
👉ምርመራዎትን ከሀኪምዎ ጋር በመነጋገር ያድርጉ
👉አንዳዶች በእድሜና ሌሎች ምክንያቶች ቀደም ብለው ሊሰሩ ወይም ሊገዩ፣ ሊጨመሩ እና ሊቀነሱ ይችላሉና የሚከታተልዎትን ሀኪም ምክር ይቀበሉ።

#ዶክተር #ከድር ነኝ
#በህክምና ስነምግባር ሚስጥርዎን ጠብቀን እናማክራለን!
#በርቀት መታከም ለሚችል በሽታ በርቀት እናክማለን!
#ስለጤናዎ ማማከር ሲፈልጉ በውስጥ መስመር ይፃፉልን
👇👇👇👇👇
@Drabufewzan1

#ሸር በማድረግ ቻናላችን ያስተዋውቁ

https://t.me/drabufewzan2

3 months, 1 week ago

የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን (Vaginal Candidiasis) ችግር

👉 ይህ ችግር የተለመደና Candidia በሚባል ፈንገስ ምክንያት የሚከሰት ሲሆን፡፡

👉 ከ4 ሴቶች በ3ቱ ላይ በዕድሜ ዘመናቸው ቢያንስ አንዴ ይከሰታል፡፡

👉 ይህም የአባላዘር በሽታ አይደለም።

👉 በሴቶች ማህፀን ይህንና ሌሎች ኢንፌክሽኖችን የሚከላከሉ የተፈጥሮ ፈንገስ እና የባክቴሪያ ሕዋሳት ሲኖሩ ቦታው ላይ እነሱ ካሉ አሲድ በማመንጨት ሌሎች ፈንገስ እና ባክቴሪያዎችን ይከላከላሉ።
ሆኖም ብዙ ምክንያቶች እነዚህን ጠቃሚ የፈንገስና የባክቴሪያ ክምችት በመቀነስ ለሌሎች ጎጅ ተህዋስያን ተጋላጭ ያደርጋሉ።

👉 ቀላል በሚባል ሕክምና  ይድናል፡፡

👉 ነገር ግን  በዓመት ውስጥ ከ4 እና ከዛ በላይ የሚከሰት ከሆነ ረዘም ያለ የህክምና ጊዜ ይፈልጋል ፡፡

🔴 ምልክቶቹ፡

⭕️ የማህፀን ማሳከክ፣
⭕️ የማህፀን አካባቢ መቅላት እና ቁስለት
⭕️ በግንኙነት ጊዜ ህመም
⭕️ ሽንት ሲሸና ማቃጠል
⭕️ ነጭ ወፍራም ሽታ የሌለው የተቆራረጠ እርጎ መሳይ የማህፀን ፈሳሽ

👉ችግሩ ካልታከም ለከፋና ወደሌላ ቦታም ለሚሰራጭ ኢንፌክሽን ይዳርጋል

👉ችግሩ ታክሞም ብዙ ጊዜ ደግሞ ይመጣል ። ይህ እንዳይሆን መከላከያው ምንድን ነው?
🟥 የማህፀን ፈንገስ ኢንፌክሽን በምን ምክንያት ይከሰታል?
🟥 ጤናማ ባክቴሪያና ፈንገስን የሚቀንሱ አጋላጭ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
🟥 ህክምናውስ???

#በህክምና ስነምግባር ሚስጥርዎን ጠብቀን እናማክራለን!
#በርቀት መታከም ለሚችል በሽታ በርቀት እናክማለን!
#ስለጤናዎ ማማከር ሲፈልጉ በውስጥ መስመር ይፃፉልን
👇👇👇👇👇
@Drabufewzan1

https://t.me/drabufewzan2

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago