★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks, 1 day ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago
ይቅርታ አንዳንዴ የምንዘገየው በወረፋ ምክንያት በመሆኑ ትንሽ ይጠብቁን
#ስትሮክ ምንድን ነው?
? የራስ ቅል (ጭንቅላት)ውስጥ ደም ሲፈስ
? ወደ ጭንቅላት ውስጥ የጓጎለ ደም ሲገባ
? ወደ ጭቅላት የሚገባው ደም ሲቋረጥ ነው።
እንደ አጠቃላይ ስትሮክ ማለት ከላይ በተጠቀሱት ምክናየት አንጎል ሲጠቃ ነው።
? ሁለት አይነት ስትሮክ አለ
? 1ኛው ኢስኬሚክ(Ischemic) ስትሮክ የሚባል ነው።
ይህ አይነቱ ስትሮክ በሰውነት ውስጥ ባሉና በተለያዩ የደም ቱቦዎች ውስጥ ደም ይጒጉልና ከዚያም ወደ አንጎል በመሄድ የአንጒል ህዊሳትን ሲያውክና ሲያውክ የሚፈጠር ነው። ይህም የአንጎል ህዋሳት ግልኮስና ኦክስጅን እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል። 80% የሚሆነው ስትሮክ በዚህ ምክናየት ይከሰታል።
? 2ኛው ሄሞረጅክ(Hemorragic) ስትሮክ የሚባል ነው።
ይህ ደግሞ ቀጥታ አንጎል ውስጥ ደም ሲፈስ የሚከሰት ነው።ምክናየቱ ደግሞ ከፍተኛ የደም ግፊት፡ የደም ቱቦዎች መሳሳትና መቅጠን ነው።
#ዋና ዋና የስትሮክ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
#ስትሮክን መከላከል ይቻላል?
☘ አዎ 50% መከላከል ይቻላል።
#ለስትሮክ የሚያጋልጡ ነገሮች
❗️ ስትሮክ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት።
?አስታውሱ
በህይዎተዎ ሳያውቁት አንድ ጊዜም ይሁን ከዚያ በላይ እራሰዎን ስተው የመውደቅ አጋጣሚ ከገጠመዎት በስትሮክ የመመታት እድሉ ሊኖረዎት ስለሚችል እራሰዎን ለሀኪም ያሳዩ።
መልካም ቀን
#ዶክተር ከድር ነኝ
#በህክምና ስነምግባር ሚስጥርዎን ጠብቀን እናማክራለን!
#በርቀት መታከም ለሚችል በሽታ በርቀት እናክማለን!
#ስለጤናዎ ማማከር ሲፈልጉ በውስጥ መስመር ይፃፉልን
?????
@Drabufewzan1
#ሸር በማድረግ ቻናላችን ያስተዋውቁ
በህይወትህ አርፋጅ አትሁን።
በህይወቱ የሚያረፍድ ሰው ብዙ ነገሮችን መስዋት ያደርጋል።
ስለዚህ በህይወትህ አታርፍድ።
የመለወጥ ጊዜው አሁን ነው!
ለመቀየር ጊዜው አሁን ነው።
ስራህን ለማስተካከል ጊዜው አሁን ነው።
ከቤተሰብ ጋር ያለህን ችግር ለማስተካከል ጊዜው አሁን ነው።
አሁን ላይ ማድረግ ያለብህን ካደረክ በህይወትህ አታረፍድም።
የኩላሊት ጠጠር ህመም
?የጠጠር ህመም በብዛት ከሚከስቱ ህመሞች መካከል አንዱ ነው። የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው በጣም ከፍተኛ ህመም የሚፈጠር ህመም ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ግን ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል። የጠጠር ህመም የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሊፈጥርና የኩላሊትን ስራ ሊያውክ ይችላል። ስለዚህም የመከላከያና የህክምና መንገዶችን ማወቅ ተገቢ ነው።
የኩላሊት ጠጠር ምንድን ነው?
? የኩላሊት ጠጠር ጠንካራ የሆነ በኩላሊት ወይም በሽንት ማስተላለፊያ አካላት ውስጥ የሚፈጠር ጠጠር ነው። በሽንት ውስጥ የጠጣር ነገሮች ወይም እንደ ካልሲያም ኦክሳሌት፣ ዩሬት ወይም ፎስፌት ያሉ ቅንጣቶች መብዛት ምክኒያት እንደሆነ ይታመናል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቅንጣቶች በሽንት ውስጥ ተከማችተው ቀስ በቀስ በመጠን ከጨመሩ በኋላ በረጅም ጊዜ ጠጠር ይፈጥራሉ።
ምንም አይነት እክል በማይኖርበት ጊዜ ሽንት ውስጥ ቅንጣቶች እንዳይሠባሠቡ የሚያደርጉ ንጥረ ነገሮች አሉ። የነዚህ ንጥረ ነገሮች መዛባት በኩላሊት ጠጠር መፈጠር አስተዋፅዖ ያደርጋል። የሽንት ማስተላለፊያ አካላት ውስጥ የሚፈጠር የጠጠር ህመም የሀሞት ከረጢት ውስጥ ከሚከስተው የሀሞት ጠጠር የሚባለው ህመም የተለየ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው።
? የሽንት ማስተላለፊያ ጠጠሮች ምን አይነት መጠን ፣ ቅርፅና ቦታ ይኖራቸዋል?
ጠጠሮች በመጠንና ቅርፅ ይለያያሉ። መጠናቸው ከአንዲት ፍሬ አሸዋ እስከ ቴኒስ መጫወቻ ኳስ ሊለያይ ይችላል። ቅርጻቸውም ለስላሳ ገጽ ያላቸው ድቡልቡልና ሞላላ ሊሆን እንደሚችሉ ሁሉ በጣም ሻካራና በወል የማይታወቅ ቅርፅ ያላቸው ሊሆን ይችላል። ለስላሳ ገፅ ያላቸው ጠጠሮች የሚፈጥሩት ህመም ቀነስ ያለና ለመወገድ ብዙ የማያስቸግሩ ናቸው። በአንፃሩ ሻካራ ጠጠሮች የሚፈጥሩት ህመም ከፍተኛ ሲሆን በቀላሉ መወገድ የማይችሉ ናቸዉ። ጠጠር በየትኛውም የሽንት ማስተላለፊያ አካል ውስጥ ሊከሰት ቢችልም አብዛኛውን ጊዜ በኩላሊት ተፈጥሮ ወደላይኛው የሽንት ቧንቧ (ዩሬተር) አልፎ ጠባቡ ቦታ ላይ ይቀረቀራል።
ኩላሊት ጠጠር እንዲፈጠር አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ነገሮች ምንድን ናቸው?
♦️ በቀን የሚወስደው የፈሳሽ መጠን ማነስ
♦️ በቤተሰብ ውስጥ የጠጠር ህመም መኖር
♦️ አመጋገብ: እንስሳት ተዋፅዖ ፣ ሶዲየም፣ በዝቅተኛ መጠን አትክልት እና ሲትረስ መወሰድ
?75 በመቶ የኩላሊት ጠጠርና የ የ 95 በመቶ በፊኛ ውስጥ የሚፈጠሩ ጠጠሮች ወንዶች ላይ የሚፈጠሩ ናቸው።
?ከ 20-70 የዕድሜ ክልል ያሉ ወንዶች ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ነው።
?የአልጋ ቁራኛ አልያም እምብዛም የማይንቀሣቀስ ሰው
?ሞቃታማ በሆነ አካባቢ መኖር
?ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እንዲሁም፤ የሽንት ፍሰት መዛባት
?እንደ ታይሮይድ እና ሲስቲንዩሪያ ያሉ ህመሞች
?ለመሽናት የሚያግዙ መድሀኒቶች እና የጨጓራ አሲድ የሚቀንሱ መድሀኒ ቶች
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
? እንደ ጠጠሩ ቦታ መጠንና ቅርፅ የሚለያዩ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ፡-
?በሆድ አካባቢ የሚሰማ ህመም
?ምንም ምልክት አለመታየት
?ቶሎ ቶሎ ሽንት መምጣት እና አጠዳፊ የሽንት ፍላጐት መኖር የሽንት ፊኛ ዉስጥ ጠጠር መኖሩን አመላካቾች ናቸዉ።
?ጠጠር በሽንት ማስወገድ
?ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
?ደም የቀላቀለ ሽንት
?በሚሸኑ ጊዜ ማመም ወይም ማቃጠል
?የታቸኛው የሽንት ማስተላለፊያ ቱቦ ላይ የተቀረቀረ ጠጠር ካለ ሽንት መፍሰስ ከጀመረ በኋላ በድንገት ማቋረጥ ሊኖር ይችላል
?አንዳንድ ጊዜ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና የሽንት ቧንቧ መዘጋት ሊያገ ጥምና ቋሚ ወይም ጊዜያዊ የኩላሊት ስራ መዛባት ሊያጋጥም ይችላል
በጠጠር ምክንያት ምን አይነት የሆድ ህመም ሊከሰት ይችላል?
የህመሙ ቦታና ክብደት እንደ ቦታው ፣ እንደ አቀማመጡ እና እንደየሰዉ ይለያያል። የጠጠሩ መጠን ከህመሙ መጠን ጋር አይገናኝም። ትንንሽ ሆነው ሻካራ የሆኑ ጠጠሮች ትልልቅ ሆነው ለስላሳ ከሆኑ ጠጠሮች የባሰ ህመም ያስከትላሉ።
የጠጠር ህመም ፤በዉል ከማይታወቅ የጎን ህመም እስከ ከባድ የህመም ደረጃ ሊደርስ ይችላል። ህመሙ በአቋቋም ወይም አቀማመጥ እና በእን ቅስቃሴዎች ሁኔታም ሊባባስ ይችላል። ከደቂቃዎች እስከ ሠዓታት የሚዘ ልቅ ህመም ይፈጠርና ከዚያም ህመሙ እየቆየ ጋብ የሚል ይሆናል። ይህ ዓይነት ህመም ከጠጠር ጋር የተያያዘ ምልክት ነው በአብዛኛዉ።
ህመሙ ጠጠሩ ባለበት ጎን በብዛት የሚኖር ይሆናል። በአብዛኛው ከእም ብርት በታች ና የጎን ሆድ ወደ መራቢያ አካላት አካባቢ የሚሰራጭ ህመም ከማቅለሽለሽና ማስመለስ ጋር የጠጠር ህመም መለያ ምልክቶች ናቸው።
ፊኛ ውስጥ ያለ ጠጠር፤ ከእምብርት በታች ህመም እና ወንዶች ላይ በሽንት አወጋገድ ወቅት፤ ብልት ጫፍ ላይ ህመም ሊፈጥር ይችላል።
ጠጠር የሽንት ማስተላለፊያ አካላት ዉስጥ ሲቀር የሚፈጥረው ድንገ ተኛ ህመም ፋታ የሚሰጥ ባለመሆኑ በዚህ ሰዓት ወዲያውኑ ሀኪም ዘንድ መቅረብ ግድ ይሆናል።
የኩላሊት ጠጠር ኩላሊትን ምን ድረስ ይጎዳል?
? በኩላሊት ወይም በላይኛው ሽንት ማስተላለፊያ (ዩሬተር) ውስጥ የተቀረቀረ ጠጠር ሽንት እንደልብ እንዳይተላለፍ ያደርጋል። እንደዚህ ያለ የማስተላለፊያ መደፈን ፤ ከኩላሊት ሽንትን ተቀብለው ወደላይኛው ሽንት ማስተላለፊያ (ዩሬተር) የሚወስዱ ትንንሽ ቧንቧዎች በፈሳሽ ብዛት እንዲወጠሩ እና ከጊዜም ብዛት የኩላሊት ስራ መዳከም እንዲመጣ ያደርጋል።
የኩላልት ጠጠር መከላክያ መንገዶች ምንድን ናቸው?
ህክምናውስ??
#ዶክተር ከድር ነኝ
#በህክምና ስነምግባር ሚስጥርዎን ጠብቀን እናማክራለን!
#በርቀት መታከም ለሚችል በሽታ በርቀት እናክማለን!
#ስለጤናዎ ማማከር ሲፈልጉ በውስጥ መስመር ይፃፉልን
?????
@Drabufewzan1
#ሸር በማድረግ ቻናላችን ያስተዋውቁ
ወድ የቻናላችን ቤተሰቦች ዛሬ ይዘንላቹ የቀረብነው በሆዳችን ክፍል ህመማችንን ለመለየት የሚረዳን ፅሁፍ ነው ተከታተኩን።
♦♦በሆድ ክፍል ህመምን የመለየት ዘዴ♦♦
? ዘጠኝ አይነት የሆድ ክፍሎች በእነሱ እንዴት ህመማችንን መለየት እንችላለን?
1. የቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል
• የጉበት ህመም
• የሆድ ቁስለት
• የሃሞት ጠጠር
• የቀኝ ኩላሊት ህመም
የላይኛው የመሃል የሆድ ክፍል
• የጨጓራ ህመም
• የምግብ አለመፈጨት
• የሆድ ቁስለት
• የጣፊያ ኢንፌክሽን
• የጉበት ህመም
የግራ የላይኛው የሆድ ክፍል
• የሆድ ቁስለት
• የአንጀት ቁስለት
• የግራ ኩላሊት ህመም
• የሃሞት በሽታ
• የጣፊያ ህመም
የቀኝ የጎን መሁለኛው የሆድ ክፍል
• የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
• የሆድ ድርቀት
• የኩላሊት ጠጠር
የእንብርት አካባቢ የሆድ ክፍል(center)
• ትርፍ አንጀት
• የአንጀት መታወክ
• የእንብርት መቁሰል
• የጣፊያ ህመም
የግራ ጎን መሃለኛው የሆድ ክፍል
• የኩላሊት ጠጠር
• የአንጀት መታወክ
• የአንጀት ኢንፌክሽን
የቀኝ ጎን የታችኛው የሆድ ክፍል
• ትርፍ አንጀት
• የሆድ ድርቀት
• የማህጸን አካባቢ ህመም
• ትንሹን እና ትልቁን አንጀት የሚያገናኘው ህዋስ ህመም
የሆድ ታችኛው መሃለኛው ክፍል
• የፊኛ ኢንፌክሽን
• የማህጸን አካባቢ ህመም
• የትልቁ አንጀት ህመም
የግራ ጎን የታችኛው የሆድ ክፍል
• የትልቁ አንጀት ህመም
#ዶክተር #ከድር ነኝ
#በህክምና ስነምግባር ሚስጥርዎን ጠብቀን እናማክራለን!
#በርቀት መታከም ለሚችል በሽታ በርቀት እናክማለን!
#ስለጤናዎ ማማከር ሲፈልጉ በውስጥ መስመር ይፃፉልን
?????
@Drabufewzan1
#ሸር በማድረግ ቻናላችን ያስተዋውቁ
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks, 1 day ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago