★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago
እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ኪዳነ-ምህረት ወራዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ ።
መልካም በአል ይሁንላችሁ
@entoto16km
@entoto16km
@entoto16km
🙏ወደ ቻናላችን ሰው አንዲገባ ሼር በማድረግ ተባበሩን
"መቼም ቢሆን
በራስህ ጽድቅ አትተማመን፥
ስላለፈውም አትጨነቅ።
ግን ደግሞ ምላስህንና ሆድህን ተቆጣጠር።
''አባ እንጦስ''
መልካም ቀን
@entoto16km
@entoto16km
@entoto16km
🙏ትልልቅ ግሩፖች ላይ ሼር በማድረግ ተከታዬችን እንድናገኝ ተባበሩን
❤️ጥቅምት_5
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)
ጥቅምት አምስት በዚህች ቀን የታላቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ። ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ። አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው። የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ /ምግባቸው ምስጋና ነውና/ ልብስ ያልለበሱ /ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና/ ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል።
ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።
ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል። ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው፤ ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና።
የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።
ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት። በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።
ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ። "ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ: ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ።" እንዲል።
ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
💎ስንክሳር ዘተዋሕዶ
@entoto16km
@entoto16km
@entoto16km
🙏ሼር በማድረግ ቻናሉን ያግዙ ፤
ትመጫለሽ አይደል?
ቤተመቅደስሽን ከበን አለን - መቅደስ ገላችን ቢረክስም በሕንጻ መቅደስሽ ከትመናል
- ሕንጻ ሥላሴን ብናፈርስም በልማድና በእምነት መሀል
– በተወጠረ መንፈሳችን በጎጥ በጎሳ በታጠረ
- በተፍረከረከ አንድነታችን ስቀለው ስቀለው እንጂ
– ምን በድሎ? በማይል ልሳናችን ለክፋት ባደገደገ
- በጎ ግብር በራቀው ኃጢአት ባጠራቀመ – የጽድቅ ፍኖት በናፈቀው ነውርን መግለጥ እንጂ - ከባቴ አበሳነት በማያውቀው በረከሰ ማንነት ነው
– ንዒ ማርያም የምንልሽ ከልዑሉ ሚካኤል ጋር ከደስተኛው ገብርኤል ጋር ጽጌ ጸዐዳ ልጅሽን ይዘሽ ነይ ርግባችን የምንልሽ በሚገባን ንጽህና ሆነን አይደለም ድንግል ግን ነይ ስንልሽ አትቀሪም....
ትመጫለሽ አይደል? ልባችን ቂምን ቋጥሮ በአፍ ዜማ ብቻ - ብንጠራሽም ንዒ ብንልም ድንግል ርሕርሕተ ሕሊና እመ ትሕትና..... ትመጫለሽ አይደል?
ስለተጠራው ስምሽ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?
ስለ ኪዳንሽ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?
አልቦ ምግባር ብንሆንም
እንደ ቃና ማድጋ
ማርያም አትቅሪ እኛ ጋ
ንዒ ስንል
አዛኝቱ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?
@entoto16km
@entoto16km
@entoto16km
Ⓒገጣሚ አገሬ ኑሪ
በበሩ የሚገሥጸውን ጠሉ፤ እውነትንም የሚ ናገረውን ተጸየፉ።
ድሃውንም ደብድባችኋ ልና፤ መማለጃንም፤ ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ያማሩ ቤቶችንም መርጣችሁ፤ ሠርታችኋልና፥ ነገር ግን አትኖሩባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታ ዎችም ተክላችኋል፤ ነገር ግን ወይንን አትጠጡም።
ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የም ትቀበሉ፥ በብሩም የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኀጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ ዐውቃለሁና።
"ስለዚህ ዘመኑ ክፉ ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ ዝም ይላል።
ትንቢተ አሞጽ ፦ምዕራፍ 5
@entoto16km
@entoto16km
@entoto16km
አንተ ከሆድ አውጥተኸኛልና ፤
በእናቴ ጡት ሳለሁም በአንተ ታመንሁ፡፡
ከማኀፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልኩ
ከእናቴ ማኅፀን ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ፡፡ ልጨነቅ ቀርቤአለሁና÷ የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ ፡፡
መዝሙረ ዳዊት
@entoto16km
@entoto16km
@entoto16km
ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት ርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል።
ሉቃስ 2፡11
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰን::
@entoto16km
@entoto16km
@entoto16km
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago