★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 week, 1 day ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months ago
ፍቅረኛ አሎት???♂
[??የማንን ሙዚቃ ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
? Mikaya Behailu
? Minyeshu Kifle
? Muluken Melesse
? Neway Debebe
? Nati Haile
? Nhatty Man
? Sami Dan
? Sayat Demissie
? Seleshe Demissie
? Shewandagne Hailu
? Tamrat Desta
? Teddy Afro
?Aster Awoke
?Abnet Agonafr
?Geremew Asefa
? All Ethiopian Music???????????](https://t.me/addlist/Brme6a7XIcU1MjI8)
??የአሁን ተጠባቂ ሩጫውን በቲክ ቶክ ገፃችን መመልከት ይችላሉ ??????
ድል ለ ኢትዮጵያ????
https://www.tiktok.com/@ethiopiancoffeesc?_t=8o8BrVFHlzx&_r=1
?? በቤቲንግ መበላት ሰልችቷችኋል❓
እንግዲያውስ ይሄን ቻናል ተቀላቅላችሁ ትርፋማ ሁኑ ✅ ማየት ማመን ነው ?
ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ በ2017 ዓ.ም ላለበት የኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ጨዋታዎች ጥሩ ተፎካካሪ ለመሆን ከ2016ዓ.ም የውድድር ዓመት አጋማሽ ጀምሮ ውላቸው ከሚጠናቀቅ ተጫዋቾች ጋር ድርድር አስቀድሞ ድርድር መጀመሩ ይታወቃል።
ክለባችን የቤት ስራዎቹን ቀድሞ ለመጨረስ ዝግጁ ቢሆንም በተጫዋቾቹ "የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት እንንነጋገራለን!!!" የሚል ሀሳቦችን በማቅረባቸው ድርድሮቹን ለመዘግየት ተገደናል።
ከዚህም ባሻገር ክለባችን ላለበት ኢንተርናሽናል ጨዋታ ከእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ጋር በመነጋገር የውድድር መስኮቱ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ እንዲከፈት እና ውላቸው የተጠናቀቁ ተጨዋቾችንና አዲስ ክለባችንን የሚቀላቀሉ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። እየተደረገም ይገኛል።
በዚህ መነሻነት በክለባችን የአሰልጣኞች ቡድን የታመነባቸው እና ለድርድር ፍቃደኛ ከሆኑ ተጨዋቾች ጋር ድርድር እያደረግን እንደሆነ ይታወቃል።ለዚህም እንዲያግዝ በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት በከፍተኛ ምስጢር ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
በዚህም መነሻነት ውላቸው የተጠናቀቁ እና ለድርድር ፈቃደኛ የሆኑ ተጨዋቾች በተለይም በኢትዮጵያ ቡና ውስጥ የቆዩ ተጫዋቾች ከፍተኛ የደሞዝ እና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
ለዚህ ድርድር የተመረጡ ኮሚቴዎችም ከቦርዱ እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር በተለይም ይበልጥ የምንፈልጋቸውን ተጫዋቾችን ለማቆየት ጠንካራ ሥራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ።
በዚህም መሰረት በልዩነት የምንፈልጋቸው ተጨዋቾች ያቀረቡት የደሞዝ እና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ቡና ካለው በጀት እና አዲስ ተግባራዊ የሆነው ህግ መሰረት ክለባችንን የሚፈትን ሆኗል።
ያም ሆኖ ክለባችን ብዙ ርቀቶችን በመጓዝ ተጨዋቾቹ ያቀረቡትን ጥያቄዎች እና አቅማችንን ለማመጣጠን ለመጓዝ ጥረቶችን እያደረገ እና ድርድሩ ባልተቋጨበት ሁኔታ ከእኛ ጋር ገና በድርድር ላይ የነበሩ ተጨዋቾች በሌሎች ክለባት ለመጫወት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከተለያዩ ድህረ-ገፆች ላይ መመልከት ችለናል።
ለማሳያነትም ድርድር እያደረግን ከነበሩት ቀደምት ተጨዋቾች መሐከል አማኑኤል ዮሐንስ እና አብዱልከሪም ወርቁ በማሳያነት እናነሳለን።
ኮሚቴው ከተጨዋቾቹ ጋር ባደረገው ተደጋጋሚ ንግግር መነሻነት ለእያንዳንዳቸው ጥቅማጥቅምን ሳይጨምር ያልተጣራ ክፍያ 687,069(ስድስት መቶ ሰማንያ ሰባት ሺ ስልሳ ዘጠኝ) ብር ለመፈፀም ሀሳብ አቅርቦላቸዋል።
በዚህም መነሻነት አብዱልከሪም ወርቁ 773,276 መነሻ ብር የተጣራ ክፍያ ጥያቄ አቅርቧልም
አማኑኤል ዮሐንስ በተደጋጋሚ ኮሚቴው ያቀረበለትን የደሞዝ መጠን መነሻ አድርጎ የእርሱን ጥያቄ እንዲያቀርብ ቢጠየቅም ትክክለኛ ፍላጎቱን ወይም የደሞዝ መጠን ለማስቀመጥ ፈቃደኛ አልሆነም።
ያም ሆኖ አብዱልከሪም ያቀረበውን የገንዘብ መጠን እንዲያስተካክል ክለባችንም ወደ እርሱ ፍላጎት ለመቅረብ የማሰቢያ ጊዜ ለመውሰድ ተስማምተው ተለያይተዋል። አማኑኤል ዮሐንስም የቀረበለትን የደሞዝ መጠን መነሻ በማድረግ የእርሱን ሀሳብ እንዲያቀርብ ከስምምነት ላይ ተደርሶ የነበረ ቢሆንም ከኮሚቴው ሀሳባቸውን ለማወቅ የሚደረጉላቸውን ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪዎች ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነው አልተገኙም። ይህ ጥረት እስከ ትናንት ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ቀጥሏል። ሆኖም ተጨዋቾቹ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የጀመሩትን ድርድር በውል ሳይቋጩ ወደ ሌሎች ክለቦች ማምራታቸውን ማወቅ ችለናል።
ሁለቱ ተጨዋቾች ከኢትዮጵያ ቡና ጋር እንዲቀጥሉ ከፍተኛ ፍላጎት ያለን ቢሆንም ወደ ሌላ ክለብ አምርተዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ሁለቱ ተጨዋቾች ለክለባችን የሰጡትን አገልግሎት በክብር የሚያየው መሆኑን እየገለፅን በተጓዙበት ክለብ መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማቸው እንመኛለን።
በዚህ አጋጣሚ አሁንም ክለባችንን የማጠናከር ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ለማስታወስ እንወዳለን።
ምንጭ ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ቻናል
ምን እየተፈጠረ ነው? ጭራሽ ሊገባኝ አልቻለም። እንዴት ነው የኢትዮጵያ ቡና ብቻ ይኼን ሁሉ ተጫዋች የሚለቀው?? በየአመቱ ሁሉም ተጫዋች እየለቀቁ ሁሌ እንደ አዲስ ቡድኑ እየፈረሰ እስከመቼ ነው የሚቀጥለው?? በሊጉ 3ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቀቀ። የኢትዮጵያ ዋንጫ ላይ አሳማኝ ብቃት አሳይቶ እና በውድድሩ ደምቆ ዋንጫውን አሸንፏል። በዚህም ኢትዮጵያን ወክሎ በኮንፌደሬሽን ካፕ ላይ ተሳታፊ መሆን ችሏል። ምስኪኑ ደጋፊ በዘንድሮ አቋሙ ተደስቶ በቀጣይ አመት ዋንጫ ሲጠብቅ ጭራሽ የኢትዮጵያ ቡና የልብ ምት የሆኑ ተጫዋቾች አመኑኤል እና አብዱል ከሪም ለቀቁ። የምር በጣም ያማል። እንዴት አንድ ክለብ ቋሚ የሆኑ ሁለት የመሃል ሜዳ ተጫዋቾችን ሊለቅ ይችላል?? የበለጠ መሻሻል ባለበት ሰዓት እንደዚህ ፍርስርስ ማለቱ በጣም ያሳዝናል፤ያማል። ከተመሠረተበት አንፃር እኮ 1 ዋንጫ ብቻ እኮ የሚገባው ክለብ እኮ አይደለም። ከታች የመጡ ክለቦች እኮ ከቡና በፊት ስንት ዋንጫ በሉ? እግር ኳስ ተመልካቹ ያውቀዋል። የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ፕሪሜሊግ ላይ ያለው አላማ ምንድነው ?? ከአመት አመት እኮ ክፍተት እየተፈለገ ያንን ክፍተት ለመሙላት ደፋ ቀና ይላል አላማ ያለው ክለብ። ብቻ ለምን እንደሆነ ባላውቅም የኢትዮጵያ ቡና ከአመት እስከ አመት ያለው እቅድ አይገባኝም። በወጣት ተጫዋቾች የምናምን ከሆነ እኮ ከታች ብቻ ማሳደግ በቂ ነው። አራት አምስት የማይታወቅ እና ከቲሙ ጋር ገና ለማሃዋድ ጊዜ የሚፈልግ ተጫዋች ከማምጣት ይልቅ ለምን ሁለት ውል የጨረሱ ተጫዋቾች አሳምኖ ውል ማሳደስ አቃተው??
ከላይ ያላቹ አመራሮች፤ ስለቡድኑ የሚመለከታቹ እና በክለቡ ውስጥ ድርሻ ያላቹ ሰዎች ለምን ዝምታን መረጣቹ?? እባካቹ ነቃ በሉ ክለባችንን አድኑልን። ደጋፊው እኮ ከአመት አመት ተሳቀቀ ለምን?? ኢትዮጵያ ቡና እኮ እውነቱን ለመነጋገር ከማንም እና ከየትኛውም ከኢትዮጵያ ክለብ በላይ ደጋፊ አለው። ችግሩ ደጋፊውን እንዴት መጠቀም ያላወቀው በክለቡ ውስጥ ያለው አመራር ነው። ለምን ?!
እኛ ደጋፊዎች በሰንት ፌደራል የምንደበደበው፤ ከተለያዩ አካላት ዛቻ የሚደርሰን በጣም ብዙ ብዙ መከራዎችን ያነው እያየንም ያለነው ለምንድነው?? ክለቡን ስለምንወደው ነው ሌላ ለምንም ነገር አይደለም። ደጋፊው እኮ የምር ከክለቡ በላይ ብዙ መከራዎችን እያየ ነው። እንደዚህ መስዋዕትነት የከፈለበት እና እየተከፈለለት የሚገኘው ክለብ የታለ??
የኢትዮጵያ ቡና ክለብ የ2017 ዓ.ም ዓላማ ምንድነው ?? ሩጫ በየአመቱ ይደረጋል። ሩጫው ቢያንስ 1 ወሳኝ ተጫዋች ካላቆየ የቱ ጋር ነው ጥቅሙ?? ዘንድሮ መሉ ተጫዋቾች ውላቸው እንደሚጠናቀቅ ከታወቀ ሩጫውን ቀድሞ አካሂዶ ገቢ መሰብሰብ ለምን አልተቻለም??
ጠዋት ከእንቅልፌ አንደተነሳሁ የዝውውር ዜና ስሰማ በቡና ቤት ሁሌም እየሰማሁ ያለሁት መርዶ ብቻ ነው። ይኼ ደግሞ በጣም ያማል።
አሁንም አልረፈደም ክለባችንን ታደጉልን። ለትልቅ ክብር አብቁልን።
ከቡና ጋር ጥሩም መጥፎም አመት ከክለቡ ጋር የተለያያቹ ተጫዋቾች መልካሙን ሁሉ ይግጠማቹ። በተለይ አማኑኤል ዮሃንስ ከልቤ አትጠፋም።
አመሠግናለሁ።
ታሬ ከጀርመን የኢትዮጵያ ቡና ወዳጅ። ድል ለታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና።
✅የቡናችን መወያያ ግሩፓችንን ያልተቀላቀላችሁ ተቀላቀሉ ሀሳባችንን በጋራ እናውራ!??
? ቤቲንግ ለምትመድቡ ሁሉ ይህን ምርጥ ቻናል እናስተዋውቃቹ ?
? ብዙ ዓመት ልምድ ባላቸው ቀማሪዎች የተከፈተ ብችኛ ታማኝ ቻናል ነው ከኛጋ በመሆን ከሳምንት እስከ ሳምንት አሸናፊ ለመሆን ቻናሉን JOIN ያድርጉ ?
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 week, 1 day ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months ago