Prophet Jossy Elijah JN

Description
We preach the kingdom of Christ to take over the seven mountain!!!
Advertising
We recommend to visit

Community chat: https://t.me/hamster_kombat_chat_2

Twitter: x.com/hamster_kombat

YouTube: https://www.youtube.com/@HamsterKombat_Official

Bot: https://t.me/hamster_kombat_bot
Game: https://t.me/hamster_kombat_bot/

Last updated 2 месяца, 1 неделя назад

Your easy, fun crypto trading app for buying and trading any crypto on the market

Last updated 2 месяца назад

Turn your endless taps into a financial tool.
Join @tapswap_bot


Collaboration - @taping_Guru

Last updated 2 недели, 2 дня назад

3 weeks, 6 days ago
I see angels announcing your miracles

I see angels announcing your miracles

መላእክቶች ተአምራታችሁን ሲያውጁ አያለሁ

4 weeks ago
ልዩ ትንቢታዊ እሁድ

ልዩ ትንቢታዊ እሁድ

🔥🔥🔥Prophetic Sunday🔥🔥🔥

⛔️የማይቀርበት ልዩ ቀን⛔️
📍 እሁድ ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ

የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ሀይል የምንቀበልበት ልዩ ትንቢታዊ ቀን!!!

በተለያዩ ጥያቄዎች ውስጥ ያላችሁ እና የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ምሪት እና በረከት የምትፈልጉ ሁሉ ተጋብዛችኋል!!!
እግዚአብሔር ዛሬም ይሰራል!!!

1 month ago
Prophet Jossy Elijah JN
1 month ago

የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት እንወቅ?
ሮሜ 12:2

የእግዚአብሔር ፈቃድ እግዚአብሔር በሕይወታችን ሊያደርግ/ሊፈጽም የፈለገው ዓላማ ማለት ነው።

የዚህ ዓለም አስተሳሰብ፣ የመጣንበት ማኅበረሰብ ወይም ቤተሰብ፣ አስተዳደጋችን እና በርካታ ነገሮች ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ፈቃድ ለይተን እንዳናውቅ እንከን ይሆኑብናል።

የሁላችንም የሕይወት ጎዳና የተለያየ ቢሆንም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ/ዓላማ ግን በድንገት የተከሰተ አንድም ሰው የለም።

አንዳንድ ጊዜ ከምንከተላቸው ሰዎች፣ ተቋማት፣ ቴክኖሎጂዎችና መሰል ጉዳዮች አኳያ ከእግዚአብሔር ፈቃድ በመውጣት መንገድ ስተን እንደሄድን የምናውቀው ብዙ ርቀት ከተጓዝ በኋላ ነው።

ጳውሎስ «በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ» የሚለው የእንግሊዝኛ አቻ ትርጉሙ Renewal of your mind ማለት ሲሆን ይህም Practical Knowledge ወይም ጥበብን/ በተግባር የተገለጠ ዕውቀትን የሚያመለክት ነው።

እግዚአብሔርን ማወቅ እንዲሁ ባገኘነው መረጃ ሳይሆን ፍቅሩን በመቅመስና እርሱንና የእርሱን ነገር በመለማመድ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እርሱን በማወቅ ውስጥ በልጁ የተሰጠን የዘላለም ሕይወት አለ። ይህ የዘላለም ሕይወት በእግዚአብሔር ሐሳብ/ፈቃድ/ዓላማ ውስጥ መኖርን ይገልጻል።

ብዙ ጊዜ በስብሰባዎች ላይ ሐሳቦች ተነስተው ካበቁ በኋላ «በቀረው የእግዚአብሔር ሐሳብ ይጨመርበት» የሚል ተለምዷዊ ስሕተት ይነገራል። ሆኖም ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ እኛ የምንጨመርበት እንጂ በቀረው ነገር ላይ የሚጨመር አይደለምና ከሁሉ በፊት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል።

ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ደግሞ የእግዚአብሔርን እርምጃ እና አሠራር ስለሚያሳውቀን ምንም ዓይነት መወዛገብ በእኛ ዘንድ እንዳይኖር ያደርጋል።

የሐሳብ ፈተናዎች ጥፋትን ያመጣሉ፤ ምክንያቱም ምኞት ፀንሳ የምትወልደው ኃጢአትን ነውና። ከእግዚአብሔር ፈቃድ ፈቀቅ ማለት በራሱ በኃጢአት ውስጥ መገኘት ነው።

በአብዛኛው ሰዎች በትክክለኛ መንገድ እየሄዱ ለመሆናቸው ማረጋገጫ የሚያደርጉት ዓለማዊ መስፈርቶችን እንደሆነ እንመለከታለን። አንድ ሰው ሊወስን ላለው ነገር ከእግዚአብሔር ፈቃድ ይልቅ ከእሱ በፊት ነገሩን ቀድሞ ካከናወነ ሰው መስማትና መረዳትን ያስቀድማል።

ስኬትንም ሆነ ውድቀትን ከሰዎች ውጤት ጋር ማያያዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከሁሉ አስቀድሞ ስለ የትኛውም ጉዳይ እግዚአብሔር ምን ይላል የሚለውን መጠየቅና ማወቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።

ሰው የእግዚአብሔር ፈቃድ በሕይወቱ ምን እንደሆነ ለይቶ ካወቀ 95% ተሳክቶለታል፤ ቀሪው 5% የአካሄድ ጉዳይ ብቻ ነው የሚሆነው። ሕንፃ ግንባታ ከመደረጉ በፊት ስለ መሬቱ ጥናት ተደርጎ፣ ዲዛይን ተሠርቶና መሠረት ተጥሎ ካበቃ በኋላ ግንባታው ግን ጥቂት ጊዜ ብቻ እንደሚፈጅ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመተግበር ሂደት ላይም ቀዳሚው ነገር ዓላማውን ለይቶ ማወቅና ራስን ከእርሱ ፈቃድ ሥር የማስገዛት ጉዳይ ነው።

እያንዳንዱ ሰው ወደ ምድር የመጣበት ዓላማ እግዚአብሔር ጋር ተሰውሯል። መጽሐፍ ቅዱስ «ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው፤ ባደገ ጊዜም ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።» የሚለው ልጅ በልጅነቱ የተሰጠው ነገር የዕድሜ ልክ ስንቅ ስለሚሆነው ነው። አብርሃምም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ለልጅ ልጆች አስተምሯል።

በአብዛኛው ሰዎች የእግዚአብሔርን ሥራ ለመተቸት መነሻቸው የሥርዓት ልምምዶች እንጂ የተገለጡ ዕውቀቶች ወይም የቀመሷቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመንፈስ ዓለም ልምምዶች አይደሉም። በነቢያት አገልግሎት ወይም በሌሎች መሰል ጉዳዮች፣ ሰዎች ብዙ ጊዜ ጥያቄ ይኖርባቸዋል። ነገር ግን ከመፍረድ በፊት እግዚአብሔርን መጠየቅና ከእርሱ መስማትን ቢያስቀድሙ ሰዎች ሁሉ ዕውነትን ወደማወቅ እና ወደ መረዳት እንዲመጡ የሚፈልግ አምላክ ስለሆነ ነገሩን ይገልጥላቸዋል።

የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምናውቅባቸው ሦስት ደረጃዎች (ሰዎች እንደደረሱበት መረዳት ልክ የሚመላለሱባቸው እንደሆኑ በምሳሌ እንመልከት)

  1. በጎ / The good will
    አንድ ሰው ቢታመም ሐኪም ቤት ሄዶ ሕክምና ማግኘቱ ስሕተት አይደለም። ምክንያቱም የሕክምናን ጥበብ ለባለሙያዎቹ የሰጠው እግዚአብሔር ነውና። ከወንጌላት መጽሐፍት መካከል ስለ ፈውስ በብዛት የጻፈው ሉቃስም ሐኪም ነበር። ስለዚህ አንድ ሰው ሕክምናን ፍለጋ ወደ ሐኪም ቤት ቢሄድ ይህ በጎ ፈቃድ ነው።

  2. ደስ የሚያሰኝ / Acceptable
    ይኸው ሰው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል በታመመ ጊዜ ፈውስ እንዳለ አምኖ ወደ ቤተክርስቲያን ቢሄድና ቢያጸልይ በበጎነት ባለፈ ደስ የሚያሰኘውን ፈቃድ አግኝቷል ማለት ነው።

  3. ፍጹም / Perfect will of God
    ይሄኛው ደረጃ ኢየሱስ ራሱ ያደርገው የነበረ ነው። በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ኢየሱስ ተአምራት ያደረገባቸውን ቦታዎች ሁሉ ብንመለከት ሙታንን ሲያስነሳ፣ በሽተኞችን ሲፈውስ፣ ለምጻሙን ሲያነጻ፣ ሽባን ሲተረትር፣ ዕውርን ሲያበራ እና በርካታ ምልክቶችን ሲያደርግ የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ በኢየሱስ ውስጥ ስለነበር የትኛውንም ነገር የማዘዝም ሆነ የመቀየር ሙሉ ሥልጣን ነበረው።

በምሳሌ አስረጂነት የቀረቡት እነዚህ ሦስት ደረጃዎች ሰዎች እንደደረሱበት መረዳት ልክ የሚመላለሱባቸው ሲሆኑ በአጠቃላይ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰላም፣ ደስታ እና ዕረፍት ያለበት ነው።

ስለሆነም...

ኤፌሶን 5
¹⁵ እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤
¹⁶ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።
¹⁷ ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።

1 month ago
Prophet Jossy Elijah JN
1 month, 1 week ago
Prophet Jossy Elijah JN
1 month, 1 week ago

የዘር መርገምን መስበር
ኢሳ 54:17

የዘር እርግማን ከቤተሰብ መካከል አንድ ሰው ከአጋንንት ጋር በገባው ኪዳን ምክንያት የሚመጣ ነው። ይህም የአንድ ቤተሰብ አካላት ባላቸው blood line አማካይነት በተመሳሳይም ሆነ በተለያየ መንገድ ነገራቸውን ያበላሻል።

በቤተሰባቸው ውስጥ ያለውን የዘር መርገም ለመስበር ተግተው የሚጸልዩ በርካቶች ናቸው። ትግላቸው የሠራላቸው ነገር ቢኖርም በብዙዎች ዘንድ መርገሙ ሙሉ ለሙሉ ያልተሰበረው ግን ከሥር መሠረቱ ስላልተነቀለ ነው።

መርገሙ የተመሠረተበትን root cause ማወቅ እጅግ አስፈላጊና የመፍትሔ መንገድ ነው። አንድ ሕንፃ ከመሠረቱ እንደሚጀመር ሁሉ ሰዎችም በረከታቸው እንዲለቀቅ መሠረታቸው መስተካከል/መፈወስ አለበት።

የዘር እርግማን ሰው የራሱ ያልሆነውን ሕይወት ከሌሎች በተቀበለው ሸክም እንዲኖር ያደርጋል። በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ እንደምንመለከተው ያዕቆብ ይዞ የሄደው ኤሳው የተሸከመውን ሁሉ ነበር። እስራኤል የሚለውን ስም ይዞ ሲመለስ ግን የዘር እርግማኑ ተሰብሮ ሊገድለው ይፈልግ የነበረ ወንድሙ ኤሳውም አቅፎ ተቀብሎታል።

በቤተሰብ መካከል መርገም ብቻ ሳይሆን በረከትም ትስስራዊ ውጤት አለው።

አንድ ሰው ከአጋንንት ጋር የገባው ኪዳን ትውልድን ይከተላል። የዕብራይስጥ ቃል የሆነው ካላል (ሲነበብ ካል) መሣሪያ የሚል ትርጉም ሲኖረው ያነጣጠረባቸውን ዘሮች እስካላጠፋ ድረስ የማያርፍ ነው።

አጋንንት በብዙ ቤተሰቦች ውስጥ ጥቂት ሰጥቶ ብዙ መሥዋዕት ይወስዳል። አንዳንዶች ጋር ሀብት ይኖራል ግን ትዳር ይፈርሳል፤ በልጅ መባረክ አይኖርም ... በእነዚህና መሰል ጉዳዮች ነገራቸውን ሁሉ ያበላሻል።

ይህ የትውልድ ከርስ በአጋንንት ኪዳን ምክንያት የመጣ ነው ካልን ታዲያ መፍትሔው ምንድን ነው? እዚህ ጋር አንድ ልንረዳው የሚገባ ምሥጢር አለ።

ኪዳን የሚቀየረው በጸሎት ሳይሆን በሌላ ኪዳን ነው።

በአንዱ (አዳም) አለመታዘዝ ምክንያት ሞት ወደ ዓለም እንደገባ ነገር ግን በአንዱ (ኢየሱስ) መታዘዝ ምክንያት ለሰው ልጆች ሁሉ መዳን እንደሆነ ሁሉ በቤተሰብ ውስጥ በአንድ ሰው የአጋንንት ኪዳን ምክንያት የገባ መርገም ከዚያው ቤተሰብ የሆነ አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር በሚገባው ኪዳን ይሰበራል ማለት ነው።

የትኛውም ቤተሰብ ውስጥ መሠዊያ አለ። ይህ መሠዊያ ደግሞ በብዙዎች አእምሮ ውስጥ ሥፍራ የያዘ ነው። ምክንያቱም በአጋንንት ኪዳን ምክንያት የገባው የዘር መርገም ምን እንደሚያደርግ (ሲያደርግ እንደኖረ) የቤተሰቡ አካላት አንደኛቸውን ዕውቅና ሰጥተውታል።

አእምሯችንን የመሠዊያው ሥፍራ እንዲሆን ላለመፍቀድ በክርስቶስ ያገኘነውን ሥልጣን መረዳት እና የአዲስ ኪዳን ካህናት መሆናችንን ማወጅ ይኖርብናል። ያለፈውን ኪዳን የሚሽር እና የሚቀይር አዲስ ኪዳን ከእግዚአብሔር ጋር ስንገባ እኛ ውስጥ የሚታደስ የአጋንንት መሠዊያ አይኖርም።

ጌዴዎንም ለተገለጠለት እና ለላከው እግዚአብሔር መሠዊያን ከሠራ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ጌዴዎንን የአባቱን የበአል መሠዊያ እንዲያፈርስ አድርጎታል።

ስለሆነም የእግዚአብሔርን አሠራር ማወቅ እጅጉን አስፈላጊ ነው።
እግዚአብሔር ኪዳን ሊያደርግ ሲመጣ የሚፈልገው የተዘጋጀን ነው።

እግዚአብሔር የሚልከውን ሰው በፈለገ ጊዜ ተዘጋጅቶ የነበረው ነቢዩ ኤርሚያስ እኔን ላከኝ አለ፤ እግዚአብሔርም ላከው።

እስኪ በዚህ መረዳት ላይ ሁኑና ራሳችሁን ጠይቁ፤ ከእግዚአብሔር ጋር ኪዳን ለማድረግ ዝግጁ ናችሁ?

1 month, 1 week ago

Joy in the Holy Spirit

We recommend to visit

Community chat: https://t.me/hamster_kombat_chat_2

Twitter: x.com/hamster_kombat

YouTube: https://www.youtube.com/@HamsterKombat_Official

Bot: https://t.me/hamster_kombat_bot
Game: https://t.me/hamster_kombat_bot/

Last updated 2 месяца, 1 неделя назад

Your easy, fun crypto trading app for buying and trading any crypto on the market

Last updated 2 месяца назад

Turn your endless taps into a financial tool.
Join @tapswap_bot


Collaboration - @taping_Guru

Last updated 2 недели, 2 дня назад