Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

➪የሰለፍያ እንስቶች ቻናል🌺

Description
👑👑👑👑👑👑
🎀ሰለፍያ እንስቶች፣
🎀የሀያዕ ንግስቶች፣
🎀እጅግ በጣም ውዶች
🎀በሂጃብ ጥብቆች።
ውዷ እህቴ ሆይ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ ።🎁
እርምት ካሎት
@talibetul3ilm
@umu_reslan_aselefiya
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

4 months, 4 weeks ago

🟢ተጀምሯል

አሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሃዲይ አል_መድኸሊይ
አላህ ይጠብቃቸው።

🟢በቁርዓን እና በሱነህ(በሀዲስ) አንድ  ስለ መሇን
👇
https://t.me/almadkhalinet?livestream

ወይም
👇
https://t.me/almadkhaliweb?livestream

Telegram

موقع الشيخ محمد بن هادي المدخلي

القناة الرسمية التابعة لموقع فضيلة الشيخ محمد بن هادي المدخلي، والمعتمد من فضيلته بإشراف بعض طلبته www.al-madkhali.net

***🟢***ተጀምሯል
5 months ago
**እስከ 4 ማግባትን የሚከለክሉ ምዕራባዊያን ራሳቹዉ …

እስከ 4 ማግባትን የሚከለክሉ ምዕራባዊያን ራሳቹዉ ግን በአማካኝ (በራሳቸው ምስክርነት) ከ4 እስከ 8 ከሚሆኑ ጋር ያማግጣሉ።

- «አንድ ሙስሊም የሆነ ሰዉ ከሁለት ሚስቶቹ ጋር እየሄደ የሆነ ቦታ ፖሊሶች ከአንድ ሚስት በላይ ይዞ መግባት አይፈቀድም ሲሉት፣ ሰዉዬዉም “ኣይ ሚስቶቼ ሳይሆኑ ሴት ፍቅረኞቼ ናቸዉ” ሲላቸዉ አሳለፉት» ተብሎና ፈረንጅ ሀገር የተከሰተ ነው ተብሎ የሚወራ ወሬ እንሰማለን። ታሪኩ በእውን የተከሰተ ባይሆን ራሱ ትርጉሙ ትክክለኛ ለመሆኑ ከላይ ያሰፈርኩት እዉነታ ያረጋግጣል።

- ሸይጧን አምላኪዎች የሰዉ ልጅ እንዲራባ አይፈልጉም። ከሃድያን ሙስሊሙ እንዲበዛ አይወዱም። ብዙዎቻችን በነሱ ወጥመድ ወድቀን ከአንድ በላይ ማግባት በዚህ ዘመን ጭራሽ የማይቻል ነዉ እያልን ነዉ። ሸሪዓዉ እኮ ከአንድ በላይ ማግባትን ሲፈቅድ ለእኛዉ ነዉ እንጂ መላእኮችን አይደለም።

- ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከአንድ በላይ ማግባትን መላመድ አለበት። በተለይ የሱናው ማህበረሰብ እርስ በርሳችን መጋባት ነዉ እንጂ ለሌሎች አሳልፈን አንሰጣጥ!!!

https://t.me/Khedir_M_Abomsa/3102

5 months, 1 week ago

የአላህ ባሮች ሙስሊም ሰለፍዮች ሆይ ሚዲያ ላይ ዑለሞቻችሁን በጋጠ-ወጦች አታሳድቡ!!

እንደሚታወቀው ከአሁን በፊት የተምይዕ በሽታ የወረራቸው ሚዲያ ያገነናቸው ሰዎች ዘደ እያፈላለጉ የቢድዓ ባለቤቶችን እያጠናከሩ በእድሜ የበሰሉ ናቸው እያሉና ቀን ከሌት በስውር ዘደ ለነሱ እየደከሙ .  .  .
.  .  .
ለዲን ለሱና በመልፋት እድሜያቸውን የጨረሱ የሱና ዑለሞችን ደግሞ የእንጨት ሸበት በእድሜያቸው ልክ የማያስቡ እብድ ውሻ እያሉ ሲሳደቡ የታዘብነው ነው። በመሆኑም ሰሞኑን ፌስቡክ ላይ እስከ አሁንም ድረስ በዚያ መጥፎ ስምሪት የተመረዙ አላዋቂ ጭፍን ተከታይ ከንቱዎች የሱና መሻይኾችን በእድሜያቸውና በሽበታቸው ሲጽዳዱ እየተመለከትን ነው።

ሰለሆነም እናንተ እነዚህ ባሉበት ሰፈር እየሄዳችሁ ራሳችሁን ዝቅ አድርጋቸው ትልልቅ የሱና መሻይኾችንም ከማሰደብ የሙመይዓ አካሄድ ምን እንደሆነ በእነዚሁ በሱና ዑለሞች የተብራራውን ሼር ማድረግ ነው የሚጠበቅባችሁ!!

ኢስላምን እየገደሉ ስለ ኢስላም ቢያወሩ፤ የነብያችንን ሱና እያደበዘዙ የሳቸውን ሀዲስ እናስተላልፋል ቢሉ፤ የደጋግ ቀደምቶችን የነ ኢብኑ ተይምያህን ያን ሁሉ የደከሙለትን በእጅ አዙር እያስመቱ ስለነ ሸይኽ ኢስላም ኢብኑ ተይምያህን የሚደግፉና ለነሱ የሚቆረቆሩ መስለው ቢጽፉ፤ አላዋቂ ሞኛ ሞኝን ብቻ ነው የሚሸውዱት።
ሥለዚህ አሁንም የምንላቸው የሚያዋጣው ነገር ከሁሉም በፊት ሰው የሚሰበሰብበትን ዘደ እያጠኑ ያን ማድረግ ሳይሆን፤ አላህ በሚወደው ያቀዘቀዙትን ያበላሹትን ያደበዘዙትን ማስተካከል ያሳሳቱትን ያጃጃሉትን ህዝብ መጀመሪያ ራሳቸው ተፀጽተው መመለስ ነው።

እኔ በበኩሌ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ እያየሁ የግድ እየቻልኩ የማልፋቸው አሳዛኝ ነገሮች በርካቶች ናቸው። ሆኖም ግን እንደ አስፈላጊነቱ ሀቅ ፈላጊ የሆነን ሙስሊም ማህበረሰብ መታደግ ስለሚያስፈልግ ዝቅ ከፍ እያደረግን ሀቅ ለህዝብ ማድረሰ ይጠበቅብናል ብለን ስለምናስብ በተሻለ መልኩ እንቀጥላል።

በመሆኑም ከስር መሰረቱ ሱናን እንዲንገነዘብና የፈለገ በንግግራቸው ቢንቀለቀሉ እንዲሁም አበጃጅተው ቢፆፉምኳ የዲን የሱና ገዳዮች እነማን እንደሆኑ በእውቀት በመረጃ ላይ ሆነን እንዲናውቀውና እንዲንረጋገጥ በአላህ ፈቃድ እንደሚከተለው የሀገራችን ትልልቅ መሻይኾችን በቂና ጠቃሚ ትምህሮቶች የማያያይዝላችሁ ይሆናል ቻናሉን ተቀላቀሉ
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/6298
.

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

[የአላህ ባሮች ሙስሊም ሰለፍዮች ሆይ ሚዲያ ላይ ዑለሞቻችሁን በጋጠ-ወጦች አታሳድቡ!!](https://t.me/Abdurhman_oumer/6297)
5 months, 1 week ago

°°

صلاة الفجر كانت يومًا
على المنافقين دليلاً

إنها عبادة الصادقين ،
وسبيل المؤمنين ،

وطريق المخلِصين .

🌿 #صلاة_الفجر

°°

5 months, 1 week ago

🚫   የሺዓዎች ሐሰንን ትተው ሑሰይንን የመውደድ ሚስጢር

ሺዓዎች ( ኢራኖች )  ለምንድነው ከዐልይ ኢብኑ አቢጧሊብ ልጆች ውስጥ ሑሴንን ብቻ ለይተው በመውደድ ስም የሚያመልኩት ?
ይህ ብቻ አይደለም 12 የሺዓ መሪዎች የሑሰይን ዘሮች መሆናቸውንስ ያውቃሉን ?
    የዐልይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ልጆችስ 11 መሆናቸውንስ ያውቃሉን ? እንግዲያውስ መጀመሪያ የሑሰይን የእናትና የአባት ወንድሞቹን እንወቅ ።
➡️   እነርሱም የሚከተሉት ናቸው : –

1– ሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ኢብኑ አቢጧሊብ
2 – ሐሰን         "  "            "  "
3 – ሙሕሲን    "   "            "  "
4 – አል ዐባስ    "   "            "  "
5 – ሂላል           "   "            "  "
6 – ዐብዱላህ     "   "            "   "
7 – ጀዕፈር          "   "           "    "
8 – ዑስማን         "   "           "    "
9 – ዑበይዱላህ    "   "           "     "
10 – አቡ በከር      "   "          "     "
11 –ዑመር            "   "          "     "
    እነዚህ ሁሉ የዐልይና የፋጢማ ልጆች ናቸው ። የነብዩ ቤተሰብ ( አህሉል በይት) ናቸው ። እሺ በሺዓዎች ባንዲራ ላይ ያ ሐሰን ፣ ያ ሙሕሲን ፣ ያ ዐባስ የሚል ተፅፎ አይታችሇልን ?
መልሱ አላየንም ነው ። ታዲያ ለምንድነው ያ ሑሰይን የሚል የተፃፈበት ? 
🔹 አስገራሚው መልስ : –
  በዑመር ዘመነመንግስት ከፋርስ ጋር በተደረገው ጦርነት ሙስሊሞች አሸንፈው የኪስራን ንጉስ ገለው የተሸነፉትን ይማርካሉ ። ከሙርከኞቹ ውስጥ የዝደጅረድ የተባለው ንጉሳቸው ሴት ልጅ ሸህርባኑ የተባለች ልጅ ነበረች ።
    እቺን ልጅ ዑመር ለሑሰይን ይሰጡትና ያገባታል ። ከሷም ልጆች ይወልዳል ። እንግዲህ ሺዓዎች ( ኢራኖች) ሑሰይን አማቻቸው ነው ። የንጉሳቸውን ልጅ ያገባ በመሆኑ ነው በመውደድ ስም የሚያመልኩት ።
   እንግዲህ ሺዓዎች የነብዩን ቤተሰብ ሳይሆን የሚወዱት የንጉሳቸውን ቤተሰብ ፋርሳዊያንን ነው ። ነገር ግን ሙስሊሞችን ለመሸንገል የነብዩ ቤተሰቦችን እንወዳለን ይላሉ ።
በጣም የሚገርመው የሑሰይን ከርበላእ ላይ መገደል ዋናው ተጠያቂ ሺዐዎች ናቸው ። ራሳቸው ገለው ራሳቸው ያለቅሳሉ አላህ ይግደላቸውና ። ታዲያ ሺዓዎች ስለሚወዱት ነው እንዴ ጠርተው ያስገደሉት አይደለም ነገር ግን የፋርሳዊያን ዘር ካስገኘላቸው በኋላ የነብዩ ዘር ስለማይፈልጉ ነው ያስገደሉት ። ይህ ነው የሺዓዎች እውነታ ልብ ያለው ልብ ይበል ።

ፅንሰ ሐሳቡ ከሸይኽ ሙሐመድ ባዝሞል የዐረቢኛ ፅሑፍ የተወሰደ ነው ።

https://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka

***🚫*** የሺዓዎች ሐሰንን ትተው ሑሰይንን የመውደድ ሚስጢር
5 months, 1 week ago

   የሙኻሊፎችን ትምህርት አትስሙ የሚባለው ለምንድነው ?

እንደሚታወቀው የቀደምት የኢስላም ሊቃውንቶች ( ሰለፎች ) በሙኻሊፎች ላይ የነበራቸው አቋም ጤነኛ ልብ ላላቸው የሱና ሰዎች ግልፅ ነው ።
   የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጥቅሉ ከቢዳዓ በየሳምንቱ ጁሙዓ ፊታቸው ተቀያይሮ ፣ አይናቸው ቀልቶ ፣ ድምፃቸው ጠላት ሊወረው የመጣን ሰራዊት እንደሚያስጠነቅቅ መሪ ከፍ ብሎ ያስጠነቅቁ ነበር ። ከአንጃ ከኸዋሪጆች አስጠንቅቀዋል ። እንዲሁም ከዙል ኹወይስራ በነጠላ ደረጃ አስጠንቅቀዋል ።
ሶሓቦች የሳቸውን ፈለግ ተከትለው ከአንጃ ከቀደሪዮች ፣ ከራፊዳዎች ፣ ከሐሩርዮችና ከሌሎችም እንዲሁም በነጠላ ከዐብዱላሂ ኢብኑ ሰበእ አስጠንቅቀዋል ።
    የነብዩንና የባልደረቦቻቸውን ፈለግ የተከተሉት የሰለፍ ዑለሞች በአንጃ ደረጃ ከሙዕተዚላዎች ፣ ከሱፍዮች ፣ ከጀህምዮች ፣ ከሙርጂኣዎች ፣ ከአሻዒራዎችና ከመሳሰሉት ሲያስጠነቅቁ በነጠላ ደግሞ ቁጥር ስፍር ከሌላቸው ግለሰቦች አስጠንቅቀዋል ።
    የሰለፎችን ፋና የተከተሉት የሱና ዑለሞችም ከቀደምትና በኋላ ከመጡት እንደ ተብሊጝ ፣ ኢኽዋንና ሙመዪዓዎች አስጠንቅቀዋል ።
    ከዚህ መሰረት በመነሳት የሱና ሰዎች የሰለፎችን መንገድ የተቃረኑ አንጃዎች ውስጥ የተካተቱ ግለሰቦችን ኪታብ ( መፅሐፍ )ን ማንበብም ይሁን ትምህርታቸውን መከታተል ይከለክላሉ ።
🔹 ለምንድነው የሚከለከለው ሰው ሰምቶ ወይንም አንብቦ መጥፎዉን ትቶ ጥሩዉን አይዝም እንዴ ለምን እንደፈረስ ጋሪ ግራና ቀኝ አትይ አንድ አቅጣጫ ብቻ እይ ይባላል የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ  ። ይህ ጥያቄ በተለይ ከኢኽዋኖች በኩል በሰፊው የሚሰራጭ ሲሆን አላማው በአመክንዮ ሰዎችን ለማሳመን እንዲመቻቸው ነው ። 

➡️  የዚህ ጥያቄ መልስ ብዙ ቢሆንም ዋነኛው ግን እነዚህ አካላት ሙስሊሞችን ከትክክለኛው የእስልምና አስተምሮ አስወጥተው ወደ ፍልስፍና በማስገባት ከነብዩና ከሶሓቦች መንገድ እንዲያፈነግጡ ስለሚያደርጉ ነው ።
    ይህን የሚያደርጉት የሙስሊሙን ልብ በሲራና በፈዳኢለል አዕማል በመያዝ ነው ። የዚህን ጊዜ ሰሚው ልብ ውስጥ ስለሚገቡና ከዛ በኋላ ያ ሰው ተው አትስማ ሲባል ስለወደደው አልቀበልህም ስለሚል ነው ።
ለዚህ ምሳሌ : –

ሀገራችን ውስጥ የኢኽዋን መሪዎች በተለያየ ረቃኢቅ ህዝቡን ከያዙት በኋላና እንደወደዳቸው ሲያውቁ ዒሳ ፍቅር ያስተማረ ጌታ ነው አሉ ተከታዩ ምንም አልመሰለውም ።
ኢትዮዽያ ውስጥ ሁሉም አህሉሱና ነው አሉ
ቀጠለ : – እኛ ሱፍዮች ነን አሉ
አሁንም በዚህ አላቆመም የኢስላም ዋናው ክፍል ፖለቲካ ነው አሉ
አልሰማሁም አላየሁም ሆነ ። አሁንም ቀጠለ አሽዓሪያን አህሉሱና እንበል !!! ሱፍያን ነፍስን ማጥራት ነው እንበል ወጣቱ የሚቀበለው እንዲ ስንል ነው አሉ
   በዚህ ጊዜ ሁሉ ምላሽ እየተሰጠ ወጣቱ  ከእነዚህ የጥፋት አንጃዎች አልላቀቅም ያለው የሰዎቹን የመጀመሪያ የማጥመቂያ ትምህርት በመስማቱና እነርሱን በመውደዱ ነው ።
    የድሮዎቹ ሙመዪዓዎችና የአሁኖቹ ኢኽዋን የመርከዙ ሰዎችንም ሆነ የእነርሱ እንባ ጠባቂ አዲሶቹ ሙመዪዓዎችም ወጣቱ አለቅም ያለበት ምክንያትም ተመሳሳይ ነው ።
     ይህ ከመሆኑ ጋር ብዙ ሰለፍዮች አሁንም የኢኽዋንና ሙመዪዓዎች ቻናሎችን ለቀው መውጣት ከብዷቸው እያነበቡና እየሰሙ ይገኛሉ አብዛኛዎች ከመረባቸው መግባታቸው አይቀርም ። የሰለፎችን መርህ ያልተከተለ መፈተኑ አይቀርምና ።

https://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka

***✅*** **የሙኻሊፎችን ትምህርት አትስሙ የሚባለው ለምንድነው ?**
5 months, 2 weeks ago

👉 የጡት ካንሰር ወረርሽኝ

➪ ውድ እህቶች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በገጠርም በከተማም በአሁኑ ጊዜ የጡት ካንሰር በሚገርም መልኩ እየበዛ ነው። አንዳንድ እህቶች ዝም ብሎ ማሳከክ ነበር ይላሉ። ሌሎች አልፎ አልፎ ይወጋኝ ነበር ብዙም ትኩረት አልሰጠሁትም ይላሉ። በጣም የሚያሳዝነው አብዛኞች እያመመኝም ሐኪም ቤት መሄጃ ስላልነበረኝ ዝም ብዬው ነው ይላሉ። በዚህ መልኩ ቀላል ነው እያሉ ይቆዩና መጨረሻ ላይ ወደ ሐኪም ቤት ሲሄዱ ካንሰር ሆኗል ይባላሉ።

♻️ የዚህን ጊዜ ቀኑ ይጨልምባቸዋል። አብዛኞቹ ተስፋ በቆረጠ ስሜት ሞታቸውን መጣባበቅ ይጀምራሉ። በጣም ጥቂቶቹ በሕክምና ሰበብ ይድናሉ። ይህ በሽታ ካንሰር በሚሆን ጊዜ የብዙ ቤተሰብ ሰቀቀን ሆኖ ህፃናት እንዲበተኑ የሚያደርግ ስለሆነ እህቶች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ለእናቶች ግንዛቤ በመስጠት የጡት ህመም በሚኖር ጊዜ ወዲያው እንዲታዩና በጊዜው በሕክምና መፍትሄ እንዲያገኝ እንዲያረጉ ማድረግ ያስፈልጋል። በተለያየ የኑሮ ደረጃ ላይ ያላችሁ እህቶች በሽታው መፍትሄ የሌለው ደረጃ ላይ ደርሶ የትኛውም ዘመድ ምንም ቢያደርግ ሰበብ መሆን አቅቶት ሰቀቀን ውስጥ ከመግባቱ በፊት በጊዜ ሐኪም ቤት መታየት እንዳለባችሁ ለጓደኛም ለዘመድም ነግራችሁ መታየት ይኖርባችኋል።

➧ ይህ በሽታ ካንሰር ሆኖባችሁ በጭንቅ ውስጥያላችሁ እህትና እናቶች የአላህን ውሳኔ በሶብር በመቀበል በሶላት፣ በዚክርና ኢስቲጝፋር መታገዝ አለባችሁ። ይህን ጭንቅ በሞት ትገላገሉታላችሁ በጣም አሳሳቢው የአኼራው ጭንቅ ነውና ከዛ ጭንቅ ለመውጣት ዛሬ ወደ አላህ ተመልሶ ራስን ማዘጋጀት ነው የሚያስፈልገው።

አላህ ከዱንያውም ከአኼራውም ጭንቅ ይጠብቀን።

https://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka

***👉*** **የጡት ካንሰር ወረርሽኝ**
5 months, 2 weeks ago

የሀላባ ሰለፍዮች እንኳን ደስ አላችሁ!!!
➴➘➷➴➘➷
https://t.me/AbuImranAselefy/7600

ይህ የድሉ መጀመሪያ ነው። ፅኑ ታገሉ ወደ ተውሒድ መጣራት መብታችሁ ነው። ላሰሩዋችሁም ለተባበሩም ዱዓእ አድርጉላቸው አላህ ሂዳያ ሰጥቷቸው በተውሒን እንድንገናኝ ያድርገን። መስጂድ ቢወሰድ ሜዳ ላይ፣ መንገድ ላይ ፣ ዛፍ ስር ወደ ተውሒድ ተጣሩ። ወንድሞቻችን የሰለፎቻቸውን ፈለግ በተግባር አሳይተዋል። ወደኋላ ማለት የለም ወደፊት ነው። መቶ ጊዜ መታሰር ለተውሒድ ያንሰዋል።

🎞 እነዚያ ብርቅዬ የኢስላም የበኩር ልጆች አንገታቸውን ለሰይፍ፣ ደረታቸውን ለቀስትና ለጦር ሰጥተዋል። ይህ ለተውሒድ የተከፈለ ዋጋ ነው። በደማቸው ተውሒድ እንዲለመልም እንዲፈካ እንዲያብብ አድርገዋል። የኛ ከእነርሱ አንፃር ኢምንት ነው።

🍭↪️ ሞዴሎቻችን
🌴አቡበከር ሲዲቅ፣
🌴ዑመር ኢብኑል ኸጧብ፣
🌴ኢማሙ ማሊክ፣
🌴ኢማሙ አሕመድ፣
🌴ኢብኑ ተይሚያ፣
🌴ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሀብ ናቸው። አሁንም ወደፊት እንጂ ወደኋላ የለም። አብሽሩ ለተውሒድ መነሰር ሰበብ አላህ ያድርጋችሁ አላህ ሁላችንንም ሰባት ይስጠን።

📝 ኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ

https://t.me/bahruteka

🏝 ሀላባ ሰለፊዮች 🔰
🔎🔎🔎🔍🔍🔍

🔦 የሀላባ ሰለፊ ወንድሞችን በተለያዩ አጋጣሚዎች ኣግኝቻቸኃለሁ። ከሀዋሳ በቅርብ በመገኘቷ፣ ለፕራክቲስ ወደከምባታ ዱራሜ በሄድን ጊዜ ሀላባን ስለምንቋርጣት፣ እንዲሁም ለሀዋሳ ሪፈራል መስጂድ ለማስተባበር ወደሀላባ መመላለስና በዚሁ ምክንያቶችም የሀላባ ሰለፊ ወንድሞች ጋር መተዋወቅና መቀራረብ እድሉ ነበረኝ።

💻 ከዚህ ሁሉ በላጩ ደግሞ
📷 በሼይኽ አብዱልሀሚድ ለተሚ (ሀፊዘሁሏህ) መሪነት ከኢኽዋን ጋር የተካሄደዉ የሙናዘራ (የክርክር) መድረክ ልዩ ትውስታዬ ነች።

🌄 በዛ መድረክ በሀላባ የሀሰን አል በና ፍልፋዮች ምን ያህል መርዝን እንደቋጠሩና የሰለፊያን ደዕዋ ለመንቀፍ ያለባቸዉን አካሄድ፣ በዛ በበለጠ ልክ ደግሞ ሰለፊ ወንድሞች ያላቸዉ ፅኑ አቋምና ጀግንነት አይቼባቸዋለሁ። ልክ እንደጠበኩትም ከዛህን ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ኢኽዋንም ሱናን እየነቀፈ፣ ሰለፊዉም እየታገለ ነዉ።

🔭 ሰሞኑን የእስርና የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲደረግባችሁ የነበራችሁ ሰለፍይ ወንድሞች እንኳን ከእስር ተፋታችሁልን፣ አልሀምዱልሏህ!!!

🖼 ሸይጧናዊ ሴራ ነቢያዊ ተልዕኮን ያሸነፈበት ታሪክ የለምና፣ ታሸንፉ ዘንድ ተዉሂድና ሱናን ይዛችሁ ወደፊት!!!

© ወንድማችሁ ዶ/ር ኸድር ሙሀመድ (አቦምሳ) ነኝ!

https://t.me/Khedir_M_Abomsa/3071

Telegram

Abu Imran Muhammed Mekonn

ወንድሞቻችን ከእስር ተፈተዋል። ወንድሞቻችን ከእስር ተፈተዋል። ➴➘➷ ያንብቡ https://t.me/AbuImranAselefy/7601

**የሀላባ ሰለፍዮች እንኳን ደስ አላችሁ!!!**
5 months, 3 weeks ago

በ2016 ምድባችሁ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለሆናችሁ አዲስ ገቢ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን:-

በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ በውጤት ለእዚህ ስኬት እንድትበቁ ላስቻለው ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ ሰውነት ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን ::

በመቀጠል የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ በታላቅ ደስታ ልነግራችሁ እወዳለሁ ::

ስለሆነም እናንተ እህት ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያጋምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እንጠይቃለን ::

👌ፈድሉ ከድር ........0937240724(main campus )

👌መካሪም ሁሴን.........0936503106(main campus )

👌ነስረዲን ሙሐመድ ....ዐ961203437(main campus )

👌ሚስባህ  ናስር              .....ዐ931838227(main campus )

👌ቃሲም ሸሪፍ......0961860535(main campus )

የዋቸሞ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት (ጀምዓ)

https://t.me/WCUMSJ1

Telegram

WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

ይህ የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመአ ኦፊሲየል የቴሌግራም ቻናል ነው!! This is the official channel of Wachemo University Muslim Students jamea. በዚህ channel ላይ:- ① የሚቀሩ ቂርዓቶችን ② የሚደረጉ ሙሀደራዎችን ማዳረስ ፡፡ ③ እንድሁም ሌሎች ዲናዊ ምክሮች ይላኩበታል ሀሳብ ካለዎት መልዕክትዎን በዚህ ይላኩልን! @Wcumsj1\_bot

**በ2016** **ምድባችሁ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለሆናችሁ አዲስ ገቢ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን**:-
5 months, 3 weeks ago

حال السلف مع الطعام والشراب :

عن أبي جعفر رحمه الله قال:

إذا امتلأ البطن،

طغى الجسد.

📚موسوعة ابن أبي الدنيا 4/83

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago