ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን

Description
ሰኞ መርሃ ግብር / ማኅበረ ጽዮን:
✍የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን ያከበረቻቸው ቅዱሳን ታሪክ

✍ የቤተክርስትያኗን ትክክለኛ አስተምህሮዋን የያዙ መዝሙራት

✍ አጭርና ተከታታይ ትምህርቶች

✍ ለመናፍቃን ጥያቄዎች መልስ

✍ ወቅታዊ መረጃዎችና ሌሎችንም የሚያገኙበት ቻናል
➾ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ @Hailegebereal19አድርሱን
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 1 month, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 3 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 day, 11 hours ago

3 months, 2 weeks ago

#ወንድሞቼ!
ከእናንተ መካከል አንድ አይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው? ታድያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘለዓለም ሲወድቁ እንደ ምን እጃችንን የበለጠ አይዘረጋም?ወገኖቼ!በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰውን ስታዩ "ይህ የእኔ ሥራ አይደለም: የቀሳውስትና የመነኮሳት ሥራ እንጂ፡፡ ምክንያቱም ሚስት አለችኝ: ልጆችንም አሳድጋለሁ" አትበሉ፡፡

እስኪ ምሳሌ መስዬ ልጠይቃችሁ እናንተም መልሱልኝ፡፡ አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ "ይህ እኔን አይመለከተኝም፡ ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ" ትላላችሁን? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሡት አይደለምን?

ይህ ወደ ዘለዓለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ  እንዲወድቅ አትግፋት፡፡ እግዚአብሔር ይህን በተመለከተ በአፈ ያዕቆብ እንዲህ ብሏልና፡- "ወንድሞቻችን ሆይ! ከእናንተ ወገን ከጽድቅ ወጥቶ የበደለ ቢኖር መክሮ አስተምሮ ከበደሉ የመለሰው ቢኖር ራሱን አንድም ወንድሙን ከሞት እንዳዳነ ይወቅ፡፡ የራሱን አንድም የወንድሙን ብዙ ኃጢአቱን እንዳስተሠረየ ይወቅ፡፡ አንድም የወንድሙን ነፍስ እንዳዳነ ይወቅ"(ያዕ.5:19-20)፡፡

✞ ✞
✞ ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ✞
✞ ✞

✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✞   @mahberetsion        ✞
✞   @segnomerhagbir    ✞
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

3 months, 2 weeks ago

"ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡

የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡

የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ። ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡

እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡"

(ምክር ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም)

✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✞   @mahberetsion        ✞
✞   @segnomerhagbir    ✞
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

3 months, 2 weeks ago

እኔና ጓደኛዬ

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ጓደኛው ባስልዮስ)

አንድ ዓይነት ፍላጎት ነበረን:: በተወለድንበት ሀገር ታላቅነት አንዳችን በሌላችን ላይ አንመካም:: ወደ ምንኩስናና ወደ እውነተኛው የሕይወት ፍልስፍና ጉዳይ ስንመጣ ግን ተለያየን:: እሱ ወደላይ ከፍ ሲል እኔ ደግሞ በዓለማዊ ምኞት መውረድ ጀመርሁ:: በወጣትነት ከንቱ ምኞት ክብደት ወደ ታች እስበው ጀመር:: ጓደኝነታችን ቢኖርም ቅርርባችን ግን ተሰበረ:: ምክንያቱም ፍላጎቶቻችን ተለያይተዋልና ውሎአችንን ማውራት አልቻልንም::

ቀስ ብዬ ወደ መንፈሳዊነት ስመጣ ግን ታግሦ በተዘረጋ እጅ ተቀበለኝ:: ከሌሎች ጋር ያለውን ጓደኝነት ትቶ ከእኔ ጋር ለማሳለፍ ፈቀደ:: ሆኖም ልዩነቶቻችንን ማጥበብ አልተቻለም:: በሕግ ችሎት ውስጥ ሁልጊዜ የሚውልና የዚያን መድረክ ደስታ የለመደ ሰው ሁሌም መጻሕፍትን ብቻ ከሚያይና ገበያ እንኳን ወጥቶ ከማያውቅ ሰው ጋር እንዴት አንድ መሆን ይችላሉ?

[ክህነት ሊሠጠን እንደሆነ] ዜናውን ያልሰማሁ መስሎት ሊነግረኝ መጣ:: 'ክህነት እንቀበል ወይስ አንቀበል?' በሚለው ላይ እሱ የእኔን ውሳኔ ሊከተል ወስኖአል:: እኔ ደግሞ [ለክህነት ብቁ ባልሆንም] የእርሱን ዓይነት ብቁ ሰው ወደ ኋላ ልጎትት አልችልም:: ስለዚህ እሺ አልሁ:: ክህነት የሚሠጥ ቀን ግን ተደብቄ አመለጥኩ:: እርሱ ግን ያለሁ መስሎት ተቀበለ:: ሳገኘው እጁን ስቤ በግድ ተባረክሁ:: አውቄ እንዳደረግሁት ሲያውቅ ተጎዳ:: ክህነትን ብቀበል አልጠላም ነበር:: በግ መሆን ያልቻለ ሰው ግን እንዴት እረኛ ሊሆን ይቻለዋል?

[St. John Chrysostom: On Priesthood] (Photo ትርጉም ባለው ቀን የተነሣ)

ጴጥሮሳዊ ቅጽበት

አርብ ዕለት ጌታ ከሰማቸው ስድቦች ሁሉ በፊት ጌታን የሚያቆስል አንድ ቃል ነበረ::
የሚወደው ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስ "አላውቀውም" እያለ ሲምል ሲገዘት ጌታ ሲሰማው ምንኛ ይሰማው ይሆን? እየሰማህ ስትታማ እንኩዋን ይከብዳል:: እየሰማህ አላውቀውም መባል ደግሞ የባሰ ነው::

ጴጥሮስ ያደረገው ታውቆት መራራ ለቅሶ አለቀሰ:: የእኔና የአንተ የአንቺ ጴጥሮሳዊ ቅጽበት መቼ ይሆን?

5 months, 4 weeks ago

ድነኀል ወይስ አልዳንክም?
**ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በአንድ መጽሐፋቸዉ እንዲህ ይላሉ። አንድ ወጣት ልጅ እንዲህ ብሎ ጠይቆኛል “አንድ ሰው ድነኀል ወይስ አልዳንኽም?” ብሎ ቢጠይቀኝ መልሴ ምንድ ነው?

መጀመሪያ ይሄ ሰዉ እዉነተኛ ኦርቶዶክስ እንዳልሆነ ማወቅ አለብህ። በእርግጠኝነት ይሄ ሰዉ ፕሮቴስታንት ነዉ ወይንም ቢያንስ በፕሮቴስታንታዊ ባህል ውስጥ ነዉ የሚኖረዉ፣ ባህሉም የፕሮቴስታንት ነው። ከዚህ በፊት የተቀበልካቸዉን ምስጢራትንና ጥምቀትን እንደ ምንም ቆጥሮ፣ በሃይማኖትህ ላይ ጥርጥር ለመሙላት በመሞከር፣ ባለፈዉ የሕይወት ዘመንህ ሁሉ አሕዛብ እንደነበርክ አድርጎ እንደ ገና እመንና ዳን ሊልህ ነው። ይሄ ሰዉ በፍጹም ኦርቶዶክስ ሊሆን አይችልም አነጋገሩም ይገልጠዋል።

ለማንኛዉም እንዲህ ብለህ ልትመልስለት ትችላለህ “በጥምቀት ከአዳም የውርስ ኀጢአት ድኜያለሁ፤ ይሄ ድኅነት የሚገኛዉ በደመ ክርስቶስ የቤዛነትንና የድኅነት ኀይል ነው። ነገር ግን የመጨረሻዉ ድኅነት በስጋ ስንለይ የሚገኝ ነው። አሁንም በውጊያ ላይ ነን “መጋዳላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፣ ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር እንጂ።” (ኤፌ. 6፥12)። ይሄንን ውጊያ ድል ስናደርግና ስናሸንፍ ድኅነትን እናገኛለን…”

በስጋ እስካለን ድረስ “ድል ነስተናል፤ ድኅነትን አግኝተናል” ልንል አንችልም። ስለዚህ ቅድስት ቤተክርስቲያን የቅዱሳንን ልደት አታከብርም ወይም የተጠመቁበትን ዕለት፤ ይልቁንም ከዚህ ዓለም የተለዩበትን ወይንም መስዋዕት የሆኑበትን ቀን ታከብራለች እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና “ዋነኞቻችሁን አስቡ፣ የኑሮአቸዉንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸዉ ምሰሉአቸዉ።” (ዕብ. 13፥7)። ስለዚህ በቅዳሴ ላይ የቅዱሳንን መታሰቢያ እናደርጋለን፤ በእምነት ፍጹማን የሆኑትንና ሕይወታቸውን በእምነት የፈጸሙትን፣ በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ እናስባለን።

ይሄም የታላቁ አባ መቃርስን ከዚህ ዓለም መለየት እንዳስታውስ ያደርገኛል። ነፍሱ ከስጋው ተለይታ ስትሄድ “መቃርስ አንተ ድነኸል” እያሉ አጋንንት ነፍሱን አሳደዷት፤ ነገር ግን ገነት እስከሚገባ ድረስ “በጌታ ጸጋ ድኜያለኹ” አላላቸዉም ነበር…!

አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት ነገረ ድኅነትን አስመልክቶ ለፕሮቴስታንቶች መልስ ከሰጡበት “Salvation in the Orthodox Concept” ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ ነዉ።**

6 months ago

በሕማም፣ በመከራና መሥዋዕት በመሆን ፍቅራችን ይፈተናል
**ፍቅርን የሚያውቅ ሰው ለእግዚአብሔር እና ለሌሎች ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፡፡ ሰው በመጀመሪያ መሥዋዕት ለማድረግ መልመድ ያለበት ከእርሱ ውጪ በሆኑ ነገሮች ማለትም ገንዘቡን፣ ጊዜውን እና ሀብቱን በመለገስ ነው፤ መስጠት ከማግኘት አንድ ነውና፡፡ ለሰዎች ደስታ እንደራሱ የሚጨነቅ እርሱ ፍቅርን ያውቃል፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ይኖራል፡፡ መሥዋዕትነት መክፈል ካልቻልን ግን ፍቅር አልገባንም ማለት ነው፤ አምላካችን እግዚአብሔርን ማፍቀር ካልቻልን ደግሞ ድኅነተ ሥጋንም ሆነ ድኅነተ ነፍስን ማግኘት አንችልም፡፡

ፍቅር የሚፈተነው በሕማም በመከራና መሥዋዕት በመሆን ነው፤ መሥዋዕት መሆን የማይችል ሰው የማይወድ ወይም የማያፈቅር ሰው ነው፡፡ የሚወድ ሰው ከሆነ ግን ለመውደድ ማንኛውም ነገር መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፡፡

የአባቶች ሁሉ አባት የተባለው አብርሃም ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር የተነሣ ወገኖቹንና የአባቱን ቤት ትቶ በመውጣት በአንድነት በድንኳን ውስጥ ኖሯል፤ ይሁን እንጂ አብርሃም ለእግዚአብሔር ያለውን ፍቅር ያሳየው አንድ ልጁን በመሠዊያው ላይ ባስተኛው ጊዜ ነበር፡፡ እርሱ በልጁ ዙሪያ እንጨቶች ሰብስቦ ካቀጣጠለ በኋላ መሥዋዕት አድርጎ ሊያቀርበው ቢላዋ የያዘ እጁን ቃጥቶ ነበር፡፡

ነቢዩ ዳንኤል እግዚአብሔርን በወደደ ጊዜ ወደ ተራቡ አናብስት ይወረወር ዘንድ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ አቅርቧል፡፡ ሦስቱ ወጣቶች እንዲሁ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር ያረጋገጡት በእቶኔ እሳት ውስጥ በመወርወር የከፈሉት መሥዋዕትነት ነው፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ፍቅር የገለጠው እንዲህ በማለት ነው፤ ‹‹አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ፤….›› (ፊል. ፫፥፰-፱)

አባታችን ያዕቆብ ከራሔል ጋር በፍቅር በወደቀ ጊዜ ስለ እርሷ ብዙ መሥዋዕትነት ከፍሏል፡፡ እርሱ ራሔልን ለማግኘት ለሃያ ዓመታት ያህል በቀን ሀሩንና በሌሊት ቁር መድከም ነበረበት፡፡ ይሁን እንጂ ለእርሷ ከፍተኛ ፍቅር ስለ ነበረው እነዚህ ዓመታት ለእርሱ እንደ ጥቂት ቀናት ነበር ያለፈለት፡፡ እኛም ለሰው ዘር በሙሉ ሲል በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኖ ለቀረበው ለኢየሱስ ክርስቶስ የምናቀርበው መሥዋዕት በዚህ ምድር የሚገጥመን ችግር በወጣት፤ የሚደርስብንን መከራ እና ሥቃይ በትዕግስት በማለፍ ነው፡፡

‹‹ነገር ግን በዚያ መሥዋዕት በየዓመቱ የኃጢአት መታሰቢያ አለ፤ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና›› እንደተባለውም ጌታችን ኢየሱስ መሥዋዕት ሆኖ ካዳነን በኋላ እኛም የምናቀርበው ለእርሱ መባ እና ምጽዋዕት ኃጢአታችንን ያስተሰርይልናል፡፡ ይህም በቤተክርስቲያን ለመዘከርም ሆነ ወርኃዊ እና ዓመታዊ በዓል ለማክበር ስንሄድ እግዚአብሔር የምናቀርበው ስጦታ ነው፤ ሆኖም ግን በእምነት እና በበጎ ምግባር ያልተደገፈ ማንኛውም ስጦታ በእርሱ ዘንድ ዋጋ አይኖረውም፡፡ ሁሉን የሚያይ አምላካችን ልባችንን እና ኵላሊታችንን ይመረምራልና የውስጣችንን ክፋት ስለሚያውቅ የምናቀርበውን መሥዋዕት አይቀበለውም፤ ቅድስት ቤተክርስቲያንን በድፍረት በመርገጣችንም በኋላኛው ዓለም ይቀጣናል፡፡ (ዕብ. ፲፥፫-፬)

አባቶቻችን ሰማዕታትን ካህናት ለእግዚአብሔር ካላቸው ፍቅር የተነሣ ደማቸውን፣ ሕይወታቸውን እና መደላደላቸውን መሥዋዕት አድርገው አቅርበዋል፡፡ እነርሱ ለእግዚአብሔር የተለየ ፍቅር ስለነበራቸውና ሥቃይን ስለተለማመዱት ፈጽሞ ፈርተው አያውቅም ነበር፡፡

እኛም እንደ አባቶቻችን ለእምነታችንም ሆነ ለሃይማኖታችን ሰማዕት መሆን ባንችል እንኳን በዚህ በምድራዊ ሕይወታችን ማንኛውም ዓይነት ችግር እና መከራ ሲገጥመን ባለመማረር ሥቃዩንም ተቋቁመን ፈተናችንን ማለፍ ይጠበቅብናል፤ ከራሳችን አልፎ ለሌሎች መዳን ምክንያትም ልንሆን እንችላለን፡፡ ያን ጊዜም በሰላም፣ በፍቀር እና በአንድነት እንኖራለን፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር በሰላም እና በፍቅር አንድንኖር ፍቃዱ ይሁንልን፤ አሜን፡፡

ምንጭ፤ ‹‹መንፈሳዊ ቃላትና ጥቅማቸው- ክፍል አንድ፤›› በግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ፤ ትርጉም አያሌው ዘኢየሱስ**@kallefiretube

6 months ago
  • ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +

ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል::  ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ  ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"

ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ:: 

ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)

ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::

ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::
ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::

"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)

እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::
ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?
ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል::
እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል  የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::

የዐቢይ ጾም የወንጌል ምንባብ ስለ ዲያቢሎስ ፈተና ሦስቱ ወንጌላት የተናገሩትን ስናስተውል ሦስት ዓይነት ጥቅሶች እናገኛለን::

አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። (ሉቃ 4:2)

በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ (ማር 1:13)
የሚሉት ቃላት ጌታችን ዐርባውንም ቀን መፈተኑን ያሳያሉ::

አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ እንዲህ አለው (ማቴ 4:2)

የሚለው ደግሞ ከጾሙ በኁዋላ የቀረቡለትን ሦስት ፈተናዎች የሚያሳይ ነው::
ሦስተኛው ጥቅስ ደግሞ ከተፈተነ በኁዋላ ያለው ሲሆን

ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ። (ሉቃ 4:13) ይላል:: ዲያቢሎስ ፈተናውን ቢጨርስም የሚተወው ለጊዜው እንጂ መፈተኑን አያቆምም::  የዲያቢሎስ ፈተና ስልቱ ይቀያየራል እንጂ ይቀጥላል::

ዐቢይ ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በዐቢይ ጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: ከነስሙ ሁዳዴ (ሰፊ እርሻዬ) የምንለው ይህ ጾም ለነፍሳችን ብዙ ዘር የምንዘራበት አጋንንት መድረሻ የሚያጡበት ጾም ነው:: በዐቢይ ጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በዐቢይ ጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::

ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::

ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 15 2012 ዓ ም
ዝዋይ ኢትዮጵያ

6 months ago

እመቤታችን በአበው ቀደምት የተመሰለላት ምሳሌ እና እመቤታችን በቅዱሳን ነቢያት የተነገረላት ትንቢትና እመቤታችን በሊቃውንት ትርጓሜ

ወላዲተ አምላክ በዘመነ አበው/በሕገ ልቦና

ሀ)  የያዕቆብ መሰላል:: (ዘፍ ፳፰÷፲-፳)

"ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ ።ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አረፈ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሳ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚሀ ስፋራ ተኛ፡፡ ሕልምም አለመ እንሆ መሠላል በምድር ላይ ተተክሎ ራሱም ወደ ሰማይ ደረሶ እነሆም እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር " " ዘፍ ፳፰፥፫-፳

?ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በራዕይ ያያት ወሠላል :-  የእመቤታችን

?የተንተራሰዉ ድንጋይ ትንቢተ ነቢያት:- እመቤታችን በትንቢተ ነቢያት ፀንታ ለመግኘቷ ምሳሌ ነዉ፡፡

? ያዕቆብ መሠላል ከምድር እስከ ሰማይ ደርሶ ማየቱ :-በሰዉና በእግዚአብሔር መካከል የነበረዉ ጥላቻ ተወግዶ
ምድራዊያን ሠዎችና ሰማያዊያን መላዕክት እግዚአብሔር ወልድ ስጋዋን ለመዋሐድ የወረደና ያደረባት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ነዉ፡፡

የያዕቆብ❤️ ምሰጢር፡ ዘፍ ፳፱÷፩-፲፩

ያዕቆብ ከወንድሙ ከኤሳዉ ጋር ተጣልቶ ወደ አጎቱ ወደ ላባ በሚሄድበት ወቅት መንገድ ላይ መንጋቸዉን እየጠበቁ ከዉኃዉ አፍ ላይ የተገጠመዉን ድንጋይ የሚያነሳላቸው አጥተዉ በችግር ላይ የነበሩት እረኞችን እንደ አገኘና ራሔል ከመጣች በኋላ ያን ታላቅ ድንጋይ ከጉድጓድ ዉኃ አፍ ላይ አንስቶ በጎቻቸውን እንደ አስጠላቸዉ ቅዱስ መፅሐፍ ይናገራል። ዘፍ ፳፱÷፩-፲፩

ምስጢራዊ ምሳሌዉ።

ውኃ - የማየ ሕይወት
ድንጋይ- መርገም
አባግዕ በጎች -የምዕመናን
ኖሎት(እረኞች)- የነቢያት
ራሔል - የእመቤታችን
ያዕቆብ- የክርስቶስ

?እረኞች በላቻቸውን ለማስካት ድንጋርን ማንሳት አለመቻላቸዉ ነቢያትም በትምህርታቸው በተጋድሏቸዉ መርገምን አርቀው ማየ ህይወት ለማጠጣት አልቻሉም።

?እረኞች ራሔል እስክትመጣ ድረስ እንደጠበቁ ሁሉ ነቢያትም በትንቢታቸዉ የእመቤታችንን መምጣት ይጠባበቁ ነበር።

?ራሔል በመጣች ጊዜ ብዙ እረኞች ማንሳት ያልቻሉትን ድንጋይ ያዕቆብ ብቻዉን አንስቶ በጎቹ እንዲከጡ አደረገ።

? እመቤታችን ከተወለደች በኋላም ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ነቢያት በተጋድሎአቸዉ ሊያርቁት ያልቻሉትን መርገም በፍቃዱ በተቀበለዉ ፀዋትወ መከራ አራቀዉ:: አባግዕ ምእመናንም ከማየ ህይውት አጠጣ  (ዮሐ ፬÷፯)

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 1 month, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 3 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 day, 11 hours ago