Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

ሐሽማል ቤተ-መዘክር

Description
👉Only for readers
👋መግቢያ👋

መግቢያ ለመግባቢያ
ገታ አርገነዋል የቃላትን ግልቢያ
እናም በዚህ ሀሳብ ከተስማማህበት
ያንኳኳኸዉን በር የገለፅከዉን ገፅ ፈቅደናል ግባበት

ምንጭ - ካልታወቀ ገጣሚ
Join the group
@amharicbooksforeadersgroup
አድሚኑን በ ቀጥታ ለማናገር ይህንን ቦት ተጠቀሙ @Digitallibraryofhashmal_bot
Advertising
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 2 weeks, 1 day ago

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ


📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako

1 month, 3 weeks ago

ሶስት ነው አደራ
የማላውቀው፡ መንገድ ጠራኝ
ልሄድ ነበር ... ግን አስፈራኝ...
ተነስቼ ልራመድ ስል
ጥቅም ያለው የማይመስል
አስጨነቀኝ ተራ ያልኩት
ለሶስት ነፍስ ያስለመድኩት
አሳሰበኝ ግዴታዬ።
ከኔ ሳይጎል የምቸረው
እኔ ብቀር የሚቀረው
ትዝ ቢለኝ ልቤ ፈራ
እባካችሁ እንኩ አደራ...
አደራ...ባካችሁ!
ገና ከሩቅ ሰው ሲያይ፡ ጭራ የሚቆላ
ከቤቴ ከፍ ብሎ፡ ካያችሁ ቡችላ
ባታበሉት እንኳ፡ እንዳትሉት ችላ...
ዳብሱልኝ እራሱን ፡ ኮርኩሩልኝ ሆዱን
እንደ ቁራሽ ዳቦ፡ እንዳትነሱት ልምዱን
አደራ... ባካችሁ...
የሚቀመስ ቢያጡ፡ የሚላስ ቢጠፋ
አጫዋች ካገኙ፡ ይቀጥላል ተስፋ።
ደግሞም ሁለተኛ... አደራ በሰማይ
ጥቂት ስትጓዙ ፡ ከኔ ቤት ወደላይ
በሁለት ክራንች ፡ የቆመች ተዛንፋ
ካያችሁ አንድ ህፃን፡ ምላሰ ኮልታፋ
አብሮ አደግ ጓደኞች፡ አይኖሯትምና
አደራ በሰማይ፡ ተጠግታችሁ ጎኗ
ትርጉም የሌላቸው፡ መድፊያቸው የጠፋ
ቀልዶች እያመጣች፡ ልታስቅ ስትለፋ
እያደመጣችሁ
አደራ ሁላችሁ
ባይገባችሁ እንኳ፡ ስቃችሁ እለፏት
እግር አያስራትም፡ ጆሮ ከደገፋት።
ደግሞም ለሶስተኛ...ባካችሁ... አደራ...
አደራ በምድር ፡  በጠዋት ስትነቁ
ልጆቿ በርሃብ፡ በጠኔ ያለቁ
አንዲት አረጋዊት፡ ከገጠመቻችሁ
አደራ ሁላችሁ
ቁጢጥ ብላ ፀሐይ፡ ስትሞቅ ስታገኟት
አደራ ቆማችሁ፡ እንዴት አደርሽ? በሏት
አይኖቿ ደካክመው፡ ዝለው ጆሮዎቿ
እንዴት ነሽ የሚሏት፡ መስለዋት ልጆቿ
አቅፋ ስትመርቅ ነው ፡ የኖረች እስካሁን
አደራ በምድር...ያገኛት ሰው ሁሉ፡ ላፍታ ልጇ ይሁን...
አይደለም የእጆቹን፡
አይደለም ልጆቹን
አይደለም ተስፋውን፡ ፍሬውን ያጣ እለት
ማጣቱን ሲያውቅ ነው ፡ ሰው የሚያበቃለት።
ስለዚህ... ድንገት...
ወደማላውቀው፡ መንገድ ስጠራ
ችዬ እንድራመድ፡ ልቤ እንዳይፈራ...
አርፌ እንድሄድ...ሶስቱን አደራ።
Red - 8

1 month, 3 weeks ago

የሁለት ሰዓቱ lecture ተጀምሯል መቼም ፍልስፍና መሆኑ አይሰለችም እንጂ " ... ሱስን ሱስ የሚያሰኘው ጥሩ ስሜት ማምጣት አለማምጣቱ አይደለም እንደውም ተጨማሪ ማስፈለጉ ነው" ስለ ሱስ መሆኑ ነው የዛሬው ትምህርት

"ሱስ ጥሩ ሆኖ አያውቅም የምንም ነገር ሱስ መጥፊያ እንጂ መዳኛ አይሆንም" አስተማሪው ዲስኩራቸውን ቀጥለዋል "ለምሳሌ እስኪ ጥሩ የሚመስላችሁን ሱስ ተናገሩ " ሲሉ

"working hard, being obsessed with work ችግር ያለው አይመስለኝም" አለ ሜጋው ተማሪ ከፊተኛው ረድፍ ተሰይሞ አስተማሪው በአይናቸው ቂጥ ገረመሙትና(ድሮም አይወዱትም) "ከማህበራዊ ህይወትህ፥ ከመንፈሳዊ ህይወት አስተጓጉሎህ በስራህ ውጤታማ ብትሆን ትርጉም የለውም" አሉትና "እሺ ሌላስ?" ሲሉ

ከእጇ መፅሀፍ የማይለያት ወሬዋ፣ ስራዋ ስነፅሁፍ የሆነች ልጅ "የማንበብ ሱስ እንደውም ሊኖረንና ልናዳብረው የሚገባ ነው" አለች

ፈገግ አሉና "አትሳሳቺ ልጅ ቤቲ 'ማርም ሲበዛ ይመራል' ነው ብሂሉ ለእሱ እንዳልኩት ነው በአስተሳሰብ ብትመነደጊ እና በሀሳቦች ብትራቀቂ ከተጨባጩ አለም ከራቅሽ ዋጋ የለውም ለሚያጋጥምሽ ነገር ሁሉ ከወረቀት ጀርባ መደበቁ ሁሌ መፍትሄ አይሆንም" አሉና "እሺ ሌላስ" ብለው ክፍሉን በአንድ እይታ አዳረሱት።

የሚመጣባቸውን ምላሽ ፈርተው ይመስል ሁሉም ፀጥታን መረጡ "እንዴ በቃ ይኸው ነው?" አሉ ሌላ ጊዜ ብዙሀኑ ተማሪ ከእሳቸው ጋር እኩል በእኩል ስለሚያወሩ "እሺ የሰው ሱስም መጥፎ ነው?" አለ ከወደ ጀርባ ጉርንን ያለ ድምፅ

"የሰው ሱስ? እንደውም እሱ ሳይከፋ ይቀራል ብላችሁ ነው? የሰው ሱስ እንደሌሎች የሱስ አይነቶች ቶሎ ምልክቶቹን ላያሳይ ይችላል፥ አንዳንዴ በሱስ የተያዘው ሰው ራሱ የሚያውቀው መለያየት ሲመጣ ነው።

ያው እንደሌሎቹ የሱስ አይነቶች የባህሪ ለውጥ ይኖረዋል ድብርት፥ ቁጣ ቁጣ የማለት ስሜት ይኖረዋል ከሌሎቹ ለየት የሚያደርገው 'ምነው ያንን ሰው ባልተዋወኩት' የሚል ፀፀትና ብስጭት ሊያመጣም ይችላል..."

"በፍፁም" አለ የቅድሙ ድምፅ ሁላችንም ዞረን አየነው ዳዊት ነው "እኔ እሷን ባልተዋወኳት ብዬ አልተበሳጨሁም፥ ድብርት ውስጥም አልገባሁም፤ ስለሷ ማሰብ ቀኔን ለማድመቅ በቂ ነው... ሱሴ እንደሆነች ያወኩትም ሳጣት አይደለም ካየኋት ቅፅበት ጀምሮ ነው "አለ ስሜት በተሞላበት ድምፅ

"ምናልባት አሁን የጠቀስናቸው ምልክቶች ለሁሉም ላይሰራ ይችላል፥  ግን አንድ የሚያስማማን ነገር ሁሉም ሱስ መጥፊያ መሆኑን ነው" አሉ

"መጥፊያዬ አይደለችም!!! እንደውም ብርሀን ምን እንደሆነ ያየሁት በሷ ነው። መጥፊያዬስ ብትሆን?! ትሁና ራሴው አይደል የፈቀድኩላት?! ራሴው በገዛ እጄ..." እያለ ተነስቶ በሩን አጋጭቶ ወጣ "ራስ መውቀስም ያመጣል ያልኳችሁን በተግባር ያያችሁት ይመስለኛል" አሉ አስተማሪው በሳቅ አውካካን
✍️nani

1 month, 3 weeks ago

“ጤናማ” ስህተቶች!
(የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1886 አንድን መድሃኒት ለመፈልሰፍ በሙከራ ላይ የነበረ ጆን (John Pemberton) የተሰኘ ሰው በሙከራ ምርምር ውስጥ ንጹህ ውኃ እጨምራሁ ብሎ በስህተት ጋዝ ያለው ውኃ (Carbonated water) ጨመረበት፡፡ መሳሳቱን ለማወቅ ብዙም ባይፈጅበትም በስህተቱ ምክንያት የተፈጠረውን ነገር ለማወቅ ፈልጎ ሲቀምሰው አስገራሚ ጣእም ያለውና አርኪ ስሜት ሰጪ መጠጥ ሆኖ አገኘው፡፡ ብዙም ሳይቆይ ኮካ ኮላ በመባል የታወቀ ዝነኛው መጠጥ ወደመሆን እንደመጣ ይነገራል፡፡ ስህተት ወደ ስኬት ሲለወጥ!

ከብዙ መቶ አመታት በፊት ሸን (Shen Nung) የተሰኘ የቻይና ገዢ ከቤቱ ወጣ ብሎ በግቢው ውስጥ ተቀምጦ ውኃ በማፍላት ላይ እያለ በአካባቢው ከነበሩ ዛፎች ከአንዱ ላይ የረገፈ ቅጠል በድንገት በሚያፈላው ውኃ ውስጥ ወድቆ ይገባበታል፡፡ ገጠመኙን ባይወደውም ውሃውን ሲቀምሰው ቅጠሉ ለውኃው የሰጠውን አዲስ ጣእም ወደደው፡፡ ሻይ የተሰኘው በአለማችን ተወዳጅ የሆነው መጠጥ የተጀመረው በዚያው እንደሆነ ይታመናል፡፡ አላስፈላጊ ገጠመኝ ወደ አስፈላጊ ግኝት ሲቀየር!

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1928 አሌክሳንደር (Alexander Fleming) የተሰኘ አንድ ሰው ለብዙ ቀናት ከሄደበት የእረፍት ጉዞ ወደቤቱ ሲመለስ በወጥ ቤቱ ውስጥ አንድን የሻገተ ነገር ተመለከተ፡፡ ያንን ሻጋታ ለማስወገድ ከመቸኮል ይልቅ ቀረብ ብሎ ለማጥናት ፈለገ፡፡ ጊዜን ወስዶ ሲመራመር ዛሬ ፔኒሲሊን (Penicillin) በመባል የታወቀውን የብዙ በሽታ መድሃኒት የሆነውን ግኝት ደረሰበት፡፡ አላስፈላጊ የተፈጥሮ ክስተት ወደ ጥቅም ሲያድግ!

ከላይ ያነበብናቸው ሶስት አጫጭር ታሪኮች በየእለት ኑሯችን ከሚከሰቱ ድንገተኛ ሁኔታዎችና ስህተቶች፣ እንዲሁም ደግሞ አዳዲስ ነገሮች ውስጥ ለመግባት በምንወስዳቸው እርምጃዎች የሚገጥሙንን ገጠመኞች የሚጠቁሙ ናቸው፡፡ እነዚህን መሰል ስህተቶች ወይም ገጠመኞች “ጤናማ የስህተት ገጽታዎች” ብለን ልንሰይማቸው እንችላለን፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች እንዳይከሰቱ ሕይወትን መኖርና ማጣጣም ማቆም አለብን፤ የምንወደውን ነገር ከማድረግ ራሳችንን መግታት አለብን፤ ችግር እንዳይፈጠር በሚል ፍርሃት መንቀሳቀስን መተው አለብን፡፡

ስህተት እሰራለሁ ወይም ያልተጠበቀ ነገር ይፈጠራል በሚል ፍርሃት ኑሮን ከመኖርና አዳዲስ ነገሮችን ከመጀመር አትገታ፡፡ ተፈጥሯዊ ስህተቶች የአዳዲስ ምእራፍ ደጆች ናቸውና!
ማሬ ኑሪ መሀመድ

2 months ago

ኮስታራ ናት እንኳን ገና ላልቀረበቺው ቀርቶ ለቀረቧትም ፊቷ አይፈታም።ጭምት ናት።ለሰዎች ደግ እና ቁምነገረኛ መሆኗን ግን ብዙ ሰው ይስማማበታል።እኔ ደግሞ ጥሎብኝ ኮስታራ ሰው እወዳለሁ፤ምንም እንኳን ሳቂታ ብሆንም...ለምንም ነገር ሳቅ ይቀድመኛል...ስናደድ እንኳን እስቃለሁ።
"ያለ ሳቅ ህይወት ምንድነው?" ብዬ የማስብ አይነት ሰው ነኝ።

የእሷ ህይወት?
ሳቅ ፈፅሞ የማይታወቅበት ጨለማ ነው ብዬ ደመደምኩ...የማስፈልጋት መስሎ ተሰማኝ...ለጨለመ ህይወቷ ጭላንጭል ብርሃን ልሆን...ፋኖሴን ይዤ ቀረብኳት፥ፈገግታዬን።
አልገርምም?
ማን ነኝ ብዬ ነው የማስበው?

የመጀመሪያ ሰሞን በቀልድ የተከሸኑትን ረጃጅም አረፍተ ነገሮች...በአጭር መልስ ድባቅ መትታ ጨዋታ ታስጠፋብኝ ነበር።እንኳን ለማሳቅ በወጉ ለማውራትም ቃላት እያጠረኝ መጣ...ይቺ ሴት ፋኖሴን፥ፈገግታዬን እፍ ብላ አጥፍታ እኔንም ያለሳቅ ልታስቀረኝ ነው?

እሷን ሳያት "በፌዘኞች ወንበር አትቀመጥ" የሚለውን የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አስታውሰዋለው...በተገናኘንባቸው አጋጣሚዎች ላስቃት ስውተረተር፣ቃላት ጠፍቶብኝ ስደናበር...ርቃኝ ልደርስባት ስንጠራራ...በቀልዶቼ ሳይሆን በሁኔታዬ ፈገግ ማለት ጀመረች...ኋላ ላይ ሁኔታዬ አሳዝኗት ነው መሠል እሷው ታስቀኝ ጀመር...

አልፎ አልፎ እንደ ቅመም ጣል የምታደርጋቸው ቀልዶቿ ሆዴን አስይዘው ያስቁኛል...በሳቄ እሷ ትስቃለች...ሳቋ ደስ ይለኛል...ሳቋን ለማየት አንዳንዴ እንዲሁ እገለፍጣለሁ።

አንድ ቀን ብዙ ግርግር በማይበዛበት እሷ ባሳየቺኝ ካፌ ቁጭ ብለን ስንጨዋወት..."ከሳቅ ያኳረፈሽ ምንድነው?" ብዬ ጠየኳት።መልሱን ለመስማት ከመጓጓቴ የተነሳ መላ አካላቴ ጆሮ የሆነ እየመሰለኝ።

ጥያቄን በጥያቄ መለሠች። " ሰው ስለሳቀ ደስተኛ ነው ማለት ነው? " አለቺኝ በአይኖቿ ትኩር ብላ እየተመለከተቺኝ።
"ይመስለኛል...ሳቅ የደስታ መገለጫ አይደል፤እንባ ደግሞ የሐዘን።" አልኳት።
"ሐሴት ምን እንሆነ ታውቃለህ?" አለቺኝ።
"ደስታ አይደል"አልኳት በጥርጣሬ።
"አዎ ነው ግን ምን አይነት ደስታ?" ዝም አልኳት ግራ መጋባቴን አይታ ቀጠለች።
"ውስጣዊ ደስታ!" አለችና እርካታ የተሞላበት ፈገግታ ተጎናፀፈች...ሐሴት አደረገች?
ማብራሪያዋን ቀጥላለች "...ሐሴት ማለት ከትክክለኝነት የሚመነጭ ደስታ ነው...አደርገዋለሁ ያልከውን ስታደርገው ነኝ ያልከውን ስትሆን...ብዙዎቹን የራቀው ደስታ ይሄ ነው...እኔ ደስ እንዲለኝ...በየማዕበራዊ ገፁ የሚያሥቅ ነገር ሳስስ ውዬ አላውቅም...ውጪያዊ ደስታ ውሥጥን አርክቶ አያውቅም፤ይልቅ ባዶነት እንዲሠማህ ያደርጋል አንዳንዴም...ሰዎች ደስታ ውስጣቸው እንዳለ ዘንግተውት ደስታን ፍለጋ አይሆኑ ሲሆኑ ያሳዝኑኛል።እኔ ምንም እንኳን ባልስቅም ውስጤ ባለው ሰላም ሐሴት አደርጋለሁ። "

አለች ፍፁም መረጋጋት እና ስክነት ከሁናቴዋ እያነበብኹ።

ከተለያየን ፤ ከሄደች በኋላ ራሴን ጠየቅኹ...

እውነት ደስተኛ ነኝ?
እንጃ!

እኔም ብሎ ፋኖስ ለኳሽ፤ብርሃን አብሪ

እፍፍፍፍፍ....ፋኖሴን(ፈገግታዬን) አጠፋዋት!

ደግሞ ለፀሐይ የፋኖስ ብርሃን ምኗ ነው?
ለካ ጨለማ የነበረው የእኔ ህይወት ነው።

ከተቀደደው ማስታወሻ
©ሶፊ

2 months ago
ዜና ***❗️******❗️***

ዜና ❗️❗️
ጋዜጠኞችና ደራሲያን ዕውቅና ሊሰጣቸው ነው

ቃል መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን "ክብር" የተሰኘ የደራሲያንና የጋዜጠኞች ሽልማት ዕውን ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ቃል መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን በደራሲና ጋዜጠኛ ቃል ኪዳን ኃይሉ በ2015 ዓም ተመስርቶ "ክብር ሽልማት" ለማዘጋጀት አስር የቦርድ አባላትን አዋቅሮ የተጀመረ ድርጅት ነው።

አበረ አዳሙ ( የደራስያን ማኅበር ፕሬዝዳንት)፣ አቶ አገኘሁ አዳነ ( በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የአለ ሥነ ጥበብና ሥነ ዲዛይን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር) ፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ( ሰአሊና ቀራጺ)፣ አቶ ጥበቡ በለጠ ( የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች  ማህበር ፕሬዝዳንት)፣ ዶ/ ር ተሻገር ሽፈራው (፣ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጋዜጠኝነትና ተግባቦት ት/ቤት መምህር)፣ ዮናስ ሐጎስ ( ጋዜጠኛ)፣ አዳነች ወ/ ገብርኤል ( አርቲስት)፣ ሰለሞን አለሙ ፈለቀ ( ደራሲና አዘጋጅ) እና ቶማስ በየነ ( አርቲስት) የቦርድ አባል አድርጎ በማዋቀር ለደራስያንና ለጋዜጠኞች ውድድር አድርጎ በመጪው ግንቦት ወር ውስጥ ሽልማት ሊሰጥ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

በመሆኑም ሐሙስ መጋቢት 12/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4-5 ሰዓት የሽልማቱ ዋና አዘጋጅ ቃልኪዳን ኃይሉና የቦርድ አባላት በተገኙበት መስቀል አደባባይ በሚገኘው ግሮቭጋርደን የውድድር ሁኔታውንና የሽልማት ሥነሥርአቱን የምንገልጽበት እና ውድድሩን የሚጀመርበት ዕለት መሆኑን የውድድሩ አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡

2 months ago

ጣፋጭ አታብዙ

ወግ ቢጤ✍🏾

ከኹለት ዓመት በፊት ከተለያየኋት የቀድሞ ወዳጄ [ Ex ሚለውን ቃል አልወደውም] ጋር በድጋሚ ተገናኘኹ!!

የዛሬን አያድርገውና እስትንፋሴ ነሽ፡ ሕይወቴ ነኽ፤ ያላንቺ-ያላንተ ሕይወት ወና ነው እየተባባልን እንንቆለጳጰስ ነበር። ስወዳት ለነብስ ነበር አቤ……ት🧏‍♂ ፤ ሰው ይወደኛል ባይባልም እርሷም እንደምትወደኝ ነበር የሚሰማኝ።

ግና ኹሉ እንደአማረ አይዘልቅምና አበባዮሽ ግጥም ላይ እንዳለችው 'ጥላኝ ጠፋች በሐምሌ ጨለማ'። ምን ኾንሽ ብዬ ጠይቄአት ነበር። ምን ብዬ እንደምነግርኽ አላውቅም፤ ግን በቃ We are not meant to be together ከ'ኔ የተሻለ ሰው ይገባኻል" ምናምን ብላ ነበር የቀባጠረችው።

ይኽቺን ቃል አማርኛ ፊልም ላይ ስለማውቃት በቃ ቅባት ጠብሳ ይኾናል [ ሀብታም ተዋውቃ ] ይኾናል ብዬ ገምቼ ይስፋልሽ ብዬ በልቤ መርቄአት ተለይቻት ነበር።

ዛሬ ከኹለት ዓመት በኋላ ይበልጥ አድጋ፣ አምራ በስላ ከልቧ ወይዘሪት/siñorita ኾና ቦሌ ላይ አገኘኋት።

እንዳንተላለፍ ኾነን ነበርና የተገጣጠምነው አጠገባችን ባገኘነው ካፌ ቁጭ ብለን ማውጋት ጀመርን።

ከብዙ ወሬዎቻችን መሐል ግን መቅረት የሌለበትን ነገር ጠየቅኳት። " ያኔ ግን ለምን ተቷቷውን? " አልኳት እኔም ኃላፊነት ተጋርቼ።

"እንዴት እንደምገልጽልኽ አላውቅም"ብላ አንድ ቁና ትንፋሽ ተነፈሰች።

' ዛሬማ አንላቀቅም: እውነታውን ማወቅ አለብኝ' ብዬ ማፋጠጥ ያዝኹኝ። " እኔ ላንቺ ኹለ ነገሬን ሰጥቼሽ ነበር፤ ፕሮፋይሌም፣ ምሣሌዬም መሐላዬም ኾነሽ ነበር፤ ጥዋትም ማታም ፍቅሬን እገልጽልሽ ነበር……: ታድያ የቱ ጋር ነበር ጥፋቴ🤷‍♂"

"እርሱ እኮ ነው ችግሩ…" ብላ ጀመረች ማምለጫ እንደሌላት ስታውቅ።

" ይኸውልኽ ጌት፡ አንተ ጥሩ ሰው ነኽ፤ ችግሩ ግን ከመጠን በላይ ጥሩ ነኽ!"

አፌን በአድናቆት ከፈትኹ፡ " Sorry ምን ማለት ነው?? " አልኳት።

" ጠዋት እንዴት አደርሽ ትለኛለኽ፡ ቁርስ በላሽ ወይ ትለኛለኽ፤ ሥራ ቦታ ስላሉት ነገሮች ኹሉ እንድነግርኽ ታደርጋለኽ፣ አመመኝ ካልኹኽ የመድኃኒት ዓይነት ሸክፈኽ ደጄ ላይ ትገኛለኽ፤ ስልክ ስናወራ መጀመርያ አንቺ ዝጊው እያልክ ታዝገኛለኽ፤ ላናድድኽ እንኳ አውቄ አንዳች ነገር ሳጠፋ ያለምንም ቅድመ ኹኔታ ይቅር ትለኛለኽ። መጀመሪያ ላይ መልአክ ከሰማይ ወረደልኝ ብዬ እየተደሰትኩ ነበር። ኋላ ላይ ግን ፍጽምናኽ ሲጋነንና እንክብካቤኽ ሲበዛብኝ ጨነቀኝ፡ ነጻነት ያሳጠኸኝ መሠለኝ፤ ደስ እያላለኝ መጣ……"

ዐይኖቼ እንባ እያቀረሩ መጡ። ከዚያ በኋላ ያወራችውን በሰመመን ውስጥ ነበር የምሰማው። 2 ዓመት ወደኋላ ተመልሼ የዋኹ እኔ እርሷን ለማስደሰት አደርግ የነበረውን ጭንቀትና ጥበት እያሰብኹ ሆድ ባሰኝ።

……እና ምን ልላችኹ ነው፦ ሰውን ስትወዱ በልኩ ይኹን። አንዳንዴ ኹሉም ነገር ሲበዛ ከልክ ያልፍና አዕምሮ መቀበል ስለሚያቅተው ያልተጠበቀ ተቃራኒ ምላሽ ይሠጣችዃል። ከሕይወት ያገኘኹትን ተሞክሮ ደግማችኹ እንዳትሳሳቱ አካፈልዃችኹ።

ደኅና ዋሉ🙏
የካቲት 16_16

2 months ago
የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም ወዳጆች አዲስ የሕዝብ …

የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም ወዳጆች አዲስ የሕዝብ ቤተ-መጻሕፍት በማደራጀት ላይ ይገኛሉ። ለዚህም ቤተ-መጻሕፍት የመጽሐፍ ማሰባሰብ ሥራ እየሠራን እንገኛለን። ተያያዥ ዝርዝሮችን ከታች የምናስቀምጥላችሁ ሲሆን የመጻሕፍት እና ሌሎችም ድጋፎች ማድረግ የምትችሉ  @TheDawit እና @Ahmedteyib98 ላይ አግኙን።
በጊዜያዊነት ለመጻሕፍት መሰብሰቢያ ያሰብናቸው ቦታዎች:

  1. ሜክሲኮ - ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን ሕንጻ ምድር ቤት የሚገኘው ፊሊ ኮፊ

  2. መስቀል አደባባይ - እስጢፋኖስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ከቤት እስከ ከተማ፤ የከተማ ማዕከል

ቤተ-መጻሕፍቱ ምን ሊመስል እንደሚችል ለመረዳት ትችሉ ዘንድ:

ቦታ:

ሜክሲኮ አደባባይ፣ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ሕንጻ ምድር ቤት የሚገኘው ፊሊ ቡና

አባላት ለመመዝገብ ሁለት መጻሕፍት ማበርከት ይኖርባቸዋል። እነዚህ መጻሕፍት ያሉንን የመጻሕፍት ስብስብ ለማብዛት እንዲሁም ለአባላትም በዋስትናነት ያገለግላሉ። (ያው ከሁለት መጻሕፍት በላይ እንሰጣለን ካላችሁም እምቢ አንልም።)

የቤተ-መጻሕፍቱ አሠራር

- የአባልነት መታወቂያ የምናዘጋጅ ሲሆን፤ አባላት መጽሐፍ በሚዋሱበት ጊዜ ከመጽሐፉ ጋር ባለው ኪስ ውስጥ መታወቂያቸውን ያስቀምጣሉ። ሌላ አዲስ መጽሐፍ ለመዋስ የሚፈልጉ አባላት በቅድሚያ የተዋሱትን መጽሐፍ መመለስ ይኖርባቸዋል።

የአባልነት መመዝገቢያ ሊንክ:

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSf4U_-0Nma9ZetY_tRDYC_-RdnU84bzHm6OE4Wfsixa86nvXw/viewform?usp=sharing

2 months ago

ታውቃለህ ??

የተደገፍከው ያ እንዳንተ ስጋ ለባሽ ሰው የህይወትህን መንገድ ያካሂድህ (አብሮህ ይጏዝ) ይሆን ይሆናል እንጂ ... ያንተን ጉዞ አይጏዝልህም!!

ልበ-ቀና ከሆነ መንገድህ ያዛለህ ጊዜ ያበረታሃል!! ... የወደቅህ ሰዓት ደግፎ ያነሳሃል!! ....

የፍቅር ሰው ከሆነ በመንገድህ ስታነክስ ትከሻውን አስደግፎህ በምትጎትተው እግርህ ልክ የራሱን መንገድ ፍጥነት ገትቶ አብሮህ ይጏዛል::

በጣም ለፅድቅ የቀረበ ከሆነ እስከሚችለው ድረስ ያዝልህ ይሆናል:: .... (አንተ ጀርባው ላይ ሀሳብህንም ክብደትህንም ጥለህ ለሽ ብለህ እያንቀላፋህ ... ፈሱ እስኪያመልጠው አይሸከምህም!! ... 🤷🏽‍♀️🤷🏽‍♀️)

በተረፈው ሁሉም ልክ እንዳንተው የራሱ ሩጫ.. የራሱ መውደቅ እና መነሳት ... የራሱ ጉድለት አለው እና የራሱን አቁሞ እንዲያቋቁምህ መጠበቅ የዋህነት ነው!!!

ወደቅህም ተነሳህም .. ፈረጥክም ... ቀደምህም ... ዘገየህም ...ህይወቱኮ ያንተ ነው!! እገሌ እንዲህ አላደረገልኝም ... እገሊት ትታኝ አለፈች... ታምሜ ሳይጠይቁኝ ... ሞቼ ሳያለቅሱልኝ ... እያልክ የምታላዝነው ምን ሆነህ ነው??

ለራስህ ህይወት ሀላፊነቱን ራስህ ውሰድ እንጂ 🙄ምን ሆነህ ነው ቤተሰብ .. ጎደኛ .. ፍቅረኛ ... ደርበው ያንተን ስንክሳር እንዲኖሩልህ ቁጭ ብለህ የምትጠብቀው??

እንኳን ሰው አምላክ ራሱ ሲረዳህኮ የምትጏዝበትን ጉልበት እና ጥበብ እንጂ የሚሰጥህ በአስማት ነገር እንደንፋስ አያስወነጭፍህም!!

እንዳልኩህ ነው!! ማንም ቢሆን አብሮህ ይሮጥ ይሆናል እንጂ ያንተን ሩጫ አይሮጥልህም!! ...

ሰው እንዲረዳህ ከመጠበቅህ በፊት በራስህ የምትችለውን አድርግ !!! ሰው እንዲወድህ ከመጠበቅህ በፊት ራስህን ውደድ !! ሰው እንዲያከብርህ ከመጠበቅህ በፊት ራስህን አክብር!!)

(ሄዋንዬ ለአዳም ነው ብለሽ አላለፍሽማ?? 🤣🤣🤣 ለኛም ነው እህትዬ❤️❤️❤️❤️ )

ሜሪ ፈለቀ

2 months ago

አዳዲስ 🗒ግጥሞችን
📚መፃህፍቶችን
🔖የመፃህፍት ጥቆማዎችን
እና ሌሎች አዳዲስ ኪነታዊ ድርጊቶችን ለማግኘት በፍጥነት ጆይን ይበሉ

2 months ago
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 2 weeks, 1 day ago

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ


📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako