ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን እና ሌሎች ገጣሚያን ⚖️⚖️????????

Description
#ገጣሚ_ኤልያስ_ሽታሁን ከሁሉም በላይ በዚህ ቻናል ይነግሳል ! ሌሎችም ድንቅ እና እውቅ ገጣምያን ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ፣ ኤፍሬም ስዩም ፣ ገብረክርስቶስ ደስታ ፣
መስፍን ወንድወሰን አስታወሰኝ ረጋሳ እና ሌሎች ገጣሚያን ስራቸው በዚህ ቻናል ይለቀቃል ! እናንተ ቻናሉን ተቀላቀሉ #Share በማድረግ ቤተሰባዊ ሀላፊነታችሁን ተወጡ? እኔ @Henilogy ነኝ ????? ኢትዮጵያዊ
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago

3 months ago

ስንት ነው

ክርስቶስን ልትሸጥ ስትደራደረው
ሴጣን አይመስለኝም አብሯት ያደረው
ክፍት መስኮት ስታይ አይችል ቢላት ልቧ
30 ዲናር ነው ለሷ የእለት ምግቧ
ጥርሷ ሳቀ ዛሬ ጥርሷ ሳቀ ዛሬ ዘለለ እንደ እምቦሳ
ምን ተሰማት ይሆን ልትሸጥ ስትነሳ
ስንት ነው ያወጣህ ስንት ነው ያዋጣት
ስህተትን ትታ ማንሳት አመልካች ጣት
እሱ ነው እሷ ነች መግደፏን ስትሸሸው
መፍታት አይቀልም ወይ ይዛ ከምታሸው
ስንት ነው
30 ዲናር ነው
እሷ ከካደቺህ ማንን ነው የማምነው

Ezku Buzz
AlazarB

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

3 months ago

#`የፈረሱ_መልኮች

ኤፍሬም ስዩም

ከዘመናት ኋላ
ድንገት ባጋጣሚ አንድ ቀን ያየኋት
እሷን እያሰብኩኝ
በበራቸው በኩል ትላንትና አለፍኩኝ።
ገረመኝ
ደነቀ…
ለካ...
ስፍራቸውን ለቀው
ቤተሰቡ ሁሉ ከዚያ ቦታ ጠፍቷል
ኮረብታው ላይ ያለው መኖሪያቸው ግና…
ግድግዳና ጣሪያ አጥሩ ፈራርሶ ወለሉ ይታያል
እኔ በበኩሌ… ከዚህ የበለጠ ላወራ ምችለው
አንድም ቃል የለኝም
ፈርሶ ለማየው ቤት አራት ኪሎ ላለው
ሁኔታው…

ክፍት የእንጨት አጥር
ትንሽ ገደድ ያለ… ልሙጥ ቆርቆሮ በር
መላ ቅጥ የሌለው
ለቅሶና ሙዚቃው የማይለይ ሰፈር
ነበር …
ግን…
ፈገግታ የሞላው
በቤቱ ጥበት ልክ ደስታ የማያጣው
ግድግዳውን የሚያልፍ ሃዘን የወረረው
ላ'መት በዓልና ላ'መት በዓል ዋዜማ ብቸኛ ቀናቸው
እፎይ የሚሉበት ህፃናት ተጫውተው
ጠግበው የሚያድሩበት አዋቂዎች በልተው
ሰፈር…
እዚያ ነበር።
አሁን ግን የለችም
ውበቷ ተረስቶ የገባችበትን አንድም የሚያውቅ የለም
የትገባ - ያ - ውበት
የትገባ- ያ - ቁመት
ሲያስጨንቅ የኖረው ወንዱን ሁሉ ባምሮት
ተስፋ የነበረው ለመንደሯ ጭንቀት።
እልፍ መአት ወንዶች በበሯ አልፈዋል
ባይተኟትም እንኳ አይኗን አይተው ብቻ እድሜ ቀጥለዋል
ግና…
ያሳዝናል…
እድሜ የጠገቡ ጉልበተኛ ወንዶች ቤቷን አፍርሰዋል
እንኳን ቤቷ ፈርሶ
አንድ ቀን ስታኮርፍ እድሜ እንደምትቀንስ መች ይገባቸዋል።

ድንገት ባጋጣሚ
አንድ ቀኑን ያየኋት እሷን እያሰብኩኝ
ከዛማ ኋላ
በበራቸው በኩል ትላንትና አለፍኩኝ
ገረመኝ
ደነቀኝ
ለካ…
ስፍራቸውን ለቀው
ቤተሰቡ ሁሉ ከዚያ ቦታ ሄዷል
ኮረብታው ላይ ያለው መኖሪያቸው ግና
ግድግዳና ጣሪያው አጥሩ ፈራርሶ ወለሉ ይታያል
እኔ … በበኩሌ…
ከዚህ የበለጠ ልናገር የምሻው
አንድም ቃል የለኝም ፈርሶ ለማየው ቤት
አራት ኪሎ ላለው
ልደታ ላይ ላለው
ሰንጋ ተራ ላለው
የትም ሰፈር ላለው።
ስለሷ ግን ላውራ
ውበት ጠፍቶ እዳይቀር ከግድግዳው ጋራ
በእርግጥም መንደሯ
ተስፋው የሞላበት
ጦር የወደቀበት
በተራ ወታደር የተረታ ንጉሥ የሚመስል አይነት።
ሞቱን የሚጠብቅ
ታስሮ የሚማቅቅ
መሞት አለመሞት የኑሮ ትንቅንቅ
እሷ መንደር መሃል ይታያል ይሄ ሃቅ።

የፈረሱ መልኮች
የገጠጡ ገፆች … የወየቡ እጆች … ያፈጠጡ አይኖች
የጠቆሩ ቀዮች
ወዝ አልባ ጥቁሮች
ቆዳውን የበላ እረዣዥም አጥንት
ብዙዎች የሞሉበት
ሞልተው ሚሞቱበት
ከሕይወት ተፋተው በተስፋ እጦት ምክንያት።
ሕዝቡ ሚደርበው
ነጠላና ጋቢው
ሀዘን የሸመነው ጨለማ ብርድልብስ
ግራ ጎረቤቷ ህፃን የሚያለቅስ
እናቱን የሞተች በዐዋላጅ እጦት።
የቀኝ ጎረቤቷ እናት ምታቃስት
ሴት ልጇ ያበደች የምታስታምማት።
እወዲያ ጥግ ላይ…
ቤት አልባ- ጎልማሳ
በረሃቡ ምክንያት አካሉ የከሳ
ከዘመናት በፊት…
በሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሁለት ዓመት
ሁለት ዓይኑን ያጣ …በወንድሞቹ ቀስት…
ወዲህ ከትቦው ጎን
ያገሩ ቆሻሻ በሚያልፍበት በኩል
መምጫው ያልታወቀ አንድ ትንሽ ህፃን…
እድሜው የሚመጥን አስር ዓመት ያህል
የሰውና የከብት ቆሻሻ ካለበት
ትቦ- ጎንሚተኛ
በልጅነት እድሜ የሌሉት ወላጆች
በልጅነት ዕድሜው የሽማግሌ አይኖች
ችግር የሰራበት…
ትንሽ ግንባሩ ላይ አንድ ሺህ መስመሮች
መንተራሻው ድንጋይ ፍራሹ ኮረኮንች
በጀርባዋ በኩል...
ሰባት የወለደ አባት የሚያነክስ
ሰባቱን ልጆቹን ድንጋይ ፈልጦ ሚያጎርስ
ሰባቱን ልጆቹን ለምኖ የሚያለብስ።
ከፊቷ ትንሽ ሱቅ ሃሊማና ከድር
ሁለት ባለትዳር
የሰፈሩ ህይወት የሰፈሩ አለኝታ
በጭልፋ የሚሸጡ የሃምሳ ሳንቲም ፓስታ
ይህን የሚመስሉ ብዙዎች የሞሉበት
በቁም የሚያለቅሱ ብዙዎች የሞቱበት
የፈረሱ መልኮች የሕይወት ግምጃ ቤት።
ነበረ…
ዛሬ ፈርሶ ማየው
መንደሯን የሞላው
የሚገርመው ግና?…
መሶብ ሙሉ ስቃይ እንስራ ሙሉ እምባ
የሆነው ይህ ቦታ
የመንገድኛውን ዓይን
የመንገደኛውን ልብ ባዘን እያጓጓ
እሷ ግን ነበረች ቀይ ፅጌረዳ የእሾህ ማ'ል አበባ
እናም በዚያ ሰፈር
እናም በዚያ መንደር
የርሷ መኖር ብቻ ለሰፈሩ ሰዎች ሳቅ ይፈጥር ነበር
ተስፋ ይሰጥ ነበር
ጥጋብ ይሆን ነበር
ባለማወቅ እንጅ...
ጤዛውን ለማበስ
ፅጌውን መቀንጠስ… ማስተዋል ቢመስለን
ባለማወቅ እንጂ…
ላንድ ዝግባ ሲባል
እልፍ አበባ መቁረጥ እልፍ አበባ መጣል
ማስተዋል ቢመስለን
ባለማወቅ ነው እንጅ
ያለማወቅ እውቀት ስልጣኔ መስሎን
ልማት ነው እያልን የሙጥኝ ስላልን
እንጂ…
ብናውቀው ኖሮማ
ውበት ቅርስ እንዲሆን…
ብናውቀው ኖሮማ!
በህይወት ግምጃ ቤት ተጥሎ የሚኖር ተምሳሌት እንደሆን
ብናውቀው ኑሮማ!
በውበት ብናምርን ቅርስን ብናከብር
ያን ያህል ጨክኖ ይህን የርሷን መንደር
ይህን የእርሷን ሰፈር
ማን ያፈርሰው ነበር!

....ዛሬ...

በዚያ መንደር
ከልጅት መኖሪያ ፍርስራሽ ጣውላ ስር
ከቤተ-መንግስቱ አረንጓዴ ሰፈር
ክፉ ጠረንይዞ ነፋስ ይጓዝ ነበር።` @eliyasshitahun
@eliyasshitahun

3 months ago

ጸሎት እንደስካር
ኤልያስ ሽታኹን
~    ~     ~     ~    ~

ሀና  በእግዚአብሔር ፊት አለቀሰች።
በደጁም ተንበረከከች።

ካህኑ ኤሊ
የአፏን እንቅስቃሴ አይቶ  "ሰክራለች" አለ።

ያውም ካህን ነው።
ሲሆን ተጠግቶ ነው  "ምነው" ሊላት ሲገባ ፈረደባት።
እንዲያውም ተናገራት "ወይን መጠጣት አቁሚ" አላት

ልክ ከዚህ በፊት  ሰክራ የሚያውቃት ይመስል
"ስካርሽ እስከመቼ  ነው" አላት

ይሄ በኛ ቢደርስ  ይሄን ብንባል 
አኩርፎ ለመውጣት ሀይማኖት ለመቀየር ሁለቴ ባላሰብን ነበር።

ሀና ግን አስረዳችው።

ታጋሽ ናትና እግዚአብሔር ባርያውን እንዲያየኝ ነው የምለምን አለችው።

አንዳንዴ እኮ
የናንተ ሀዘን የናንተ ለቅሶ ለአንዳንዶች ስካር ነው። ጤና ማጣትም ነው። ምን አልባትም ለብዙዎችም "ፋራነት" ነው።
ግን እንዲህ በሉት

"እኔስ ልቧ ያዘነበኝ ሴት ነኝ።  ጠጅና የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት  ነፍሴን አፈፈስሁ"

መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
1:15

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

#ሼር #ሼር

5 months, 3 weeks ago
5 months, 3 weeks ago
5 months, 3 weeks ago
6 months ago

✍️   

ባለፈው ለት'
ፈራሻለው ስልሽ፣ እንዲያ አኩርፈሻል
                ትላንትና ደሞ'
ውብ ቆንጆ ነሽ ስልሽ እንደዚያ ስቀሻል
            ዛሬም ልድገምልሽ
እፈራሻለው ከሩቅ፣ አፍርሻለው በደምብ
እንደዚያ ባይሆንም፣ የወንድ ወግና ደምብ
             አኮረፍሽኝ እንዴ?
            ምነው እንዲህ ባንዴ?
   የፈሩትን ሁሉ ፣ ይጠሉታል እንዴ?
   (ያከበሩትን ሰው አይወዱትም እንዴ?)
     በማስፈራትማ  እዝጌሩም  ያስፈራል
   ውበቱ ግን ረቂቅ መውደድን ይጭራል
                 (  አንቺዬ...)
ርቀቷን ሳጠብቅ ፣ ብርሃንሽ ተገልጣ
ፀሐይን ደፍሬ ፣ ለምን አይኔን ልጣ?
        ደሞ አስቢበት ብርሃንን ስትለቂው
ፀሐይ ከሰው ልጆች እንደምን ይርቃል? እዝጌሩን ጠይቂው!
       "ሰይጣንምኮ ያስፈራል" ብለሽ ለጠየቅሽው
ፍቅር እያወጉ ሰይጣን አይነሳም፣ ወደዚያ መልሽው
እንዲያ ባፈቅርሽም
       ታስፈሪኛለሽ ይቅር አላይሽም
       ግን ደግሞ አልጠላሽም።

እንግዳዬሁ ዘሪቱ✍️

6 months ago

#ከ___እስከ_ያንቺ_ፍቅር

የገፋሺኝ ሰሞን ስትይ -አይንህን አልየዉ
ልብሽ ላይ መሽቶብኝ -ንጋትን ከቶም አላስበዉ
ቀን ጥሎት ይሆን ፍቅሬን...

ልብሽ ከልቤ እንዲርቅ -ምክኒያት ሰበብ ሆኖ
ከአይንሽ ያራቅሺኝ -ልብሽ በኔ ላይ ጨክኖ
ማረፊያ ከሆነኝ ከተጠለልኩበት
የማላዉቀዉን አለም ከተመለከትኩበት
ከልብሽ ዳስ አርቀሽ ገፍተሺኝ
ያላንቺ ህይወትን እንዳይ ካረግሺኝ
ከአፍሽ ቃል ወጥቶ
ከእንትን አንፃር ተብሎ ፍቅሬ ተለክቶ
ካሻሽ እንዲጓዝ ልባችን ለየቅል
ዝም እላለዉ እንጂ ሌላ ምንም አልል
ብቻ ግን! ብቻ ግን
በዚች ባዶ አለም
ያላንቺ መኖር ማለት
እናት ልጇ ጠፍቶ ስታነባ ማየት
መኪና እየነዱ ነፍሰጡር እንደመግጨት
በጦር ወዳጅ ሙቶ ሳይቀብሩ እንደመቅረት
ከሞት ፍርድ ለመትረፍ አንድ ምስክር ማጣት
በእንቅልፍ ልብ ሰዉ አንቆ እንደ መግደል
አንድ ምስኪን እናት ፍርድ ላይ መበደል
አንቺን ማጣት ማለት
በመብረቅ መመታት
ሲኦል እንደመግባት
አንቺን ትቶ መኖር
የሞት በር እያንኳኩ እንደመጠበቅ
ከቤተከርስቲያን ገንዘብ እንደመስረቅ
ልጅ ወልዶ እንደ መጣል
ለጠንቋይ ስለት እንደ መ'ሳል
የሚወለድ ጠፍቶ ሟች -ስፍር ቁጥር ሲያጣ
ህዝቡ ፈጣሪን ዘንገቶ -ፈጣሪ ሲቆጣ
በድቅድቅ ጨለማ እየሄዱ የተኛ ጅብ መርገጥ
የነፍሰ ጡር ምጥ እየሰሙ እንደመገልፈጥ
ምድር በድርቅ ተመቶ ዝናብ ብርቅ ሲሆን
ዘፋኝ ከመድረክ ወርዶ ቄስ እንደመሆን
በጥም እሳት ሲ'ፈጅ ምድሩ ሬሳ ሲገፋፋ
ሬሳ ተደራራቦ መቅበሪያ መሬት ሲጠፋ
ይሆናል...
እጥፍ ሁኖ ግለቱ የሚፈጅ የፍቅርሽን ሀሩር
ረ'ጥቦ እንድታይዉ ከስሜት ዳርቻ ላይ ባህር
በሆሳስ በጆሮዋ ጣቶቼን ጸጉሯ ላይ ልኬዉ
አይኖቼን በስስት አይኖቿ ላይ ጥዬዉ
ቅንጥብ ቃል ፈልጌ ልነግራት ስል ቀና
እንቅልፍ ወስዷቷል ከአንገቴ ስር ሁና።

✍️ዳዊት

@eliyasshitahun
@eliyasshitahun

@betagitim

6 months ago

ምናብ አለሚቱ✍️

ከህንድ ጠጉርሽን ፣ ከአሜሪካ አፍንጫ
አይኖችሽ ካውሮፓ' ፣ ቀለምሽ ሃር ቢጫ
ከንፈርሽ ከእስያ ፣ ጡቶችሽ ከአረብ
ከየሩሳሌም ስር፣ እንዲኖርሽም ረብ
ሃበሻ ተላብሰሽ፣ እንድል ገራገሬ
ልብሽ ከኢትዮጵያ፣ ከዚው ከሃገሬ
       (ቢቻል የጣይቱን)
እንትንሽን ከሰማይ ፣ ከሌለበት ማንም
              ለምን?
እስክትመጪ ድረስ፣ እኔ ሰው አላምንም።
'
'
ከሁሉም ስብጥር ፣ የሳልኩሽ እንደዛ
ምናብ አለም ሚስቴ ፣ የኔ ሞናሊዛ
እኒያ ጓደኞቼ ፣ አግባት ከተባለህ
ወደፊት ምን አይነት ሚስት ታገባለህ?
ብለው ሲጠይቁኝ
በልጅነት ልቤ
በአፍላነት ቀልቤ
እንዲያ ብትሆን ብዬ፣ እንደዛ የሳልኩሽ
ከአልጋዬ በላይ፣ እንዲያ የሰቀልኩሽ
(አንቺዬ)
በውኑ አለም ላይ ላገባ ነውና፣ ከምናቤ ውጪ
ውጪ ብዬ ስልሽ   ፣   ዳግም እንዳትመጪ
            (አግብቻለው)
የመጣሽ ለት' ግና
ከኔና አንቺ አዳር
የት አባቱ ትዳር
(ግን እንዳትመጪ)
(ከመጣሽ ግን!)
እግዚያሩም አይወደው፣ የኔና አንቺን ነገር
አስጠፍርሻለው እሪ!..ብዬ በሃገር
(እንዳትመጪ)
(ከመጣሽ ግን ነይ)

እንግዳዬሁ ዘሪቱ ✍️

6 months, 1 week ago

የሰካራሙ ፍልስፍና ✍️

እዚያ ሰማይ
ከማደሪያው ከመቅደሱ፣ ሱራፌል ተጋርዶ ፊቶቹን ይሰጋል
እዚህ ምድር
አንድ ሰካራም ሰው፣ ለእግዚያር ምክር ይዞ በድፍረት ያወጋል
እንደዚህ ይለዋል በሰካራም ድምጡ
በደልና መፅድቅ  እንዲለዋወጡ...

እንዲህ ተናገረ...
" ሰማያት ያለኸው፣ እግዚያር ሆይ ጌታዬ
  ሃሳብ  ቢጤ ላንተ፣ በፊትህ ከታዬ
  ምን መሰለህ እግዚያር...  
  በዚህኛው አለም በምንኖርባት፣
                     ሰዎች በተቃርኖ መርህ ይኖራሉ
  ተው!...ስትል ጥሰው፣
                 አድርግ ያልካቸውን መቼ ያደርጋሉ?
እኔንም ተመልከት...
አትስከር ያልከውን፣ ትዛዝህን ልጥስ
ዘውትር እየጠጣው፣ ዘውትር ለምን ላልቅስ?
ስለዚህ እግዝያር
ለዚህ ተቃርኖ ዛር
አንድ መፍትሔ አለኝ...
አታድርግን ጓግተን ከምንላወሰው
ህግጋት ቀልብሰህ ብትቃረን ከሰው
እጥር ምጥን ያለች፣ ፈጥረህ ሰማይ ድግስ
አድርግን አታድርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ?...
(ቤተ መቅደስ እንዳትመጡ
የወይን ጠጅ ሂዱ ጠጡ
ቅድስናን እንዳትኖሩ
በደል ብቻ ሂዱ ዝሩ)...
በዛች ትንሽ ድግስ
አድርግን አታድርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ?
እኔንም ተመልከት...
እዚህኛው ዓለም ላይ፣ ሰው ተቃርኖን ተግቶ ይከውናል
እንዳትመጡ ስላልክ
ፍቃድህን ልጥስ፣ ምናልባት መቅደስህ እመጣ ይሆናል።"
"
እዚያ ሰማይ
ከማደሪያው ከመቅደሱ፣ ሱራፌል ተጋርዶ ፊቶቹን ይሰጋል
እዚህ ምድር
አንድ ሰካራም ሰው፣ ለእግዚያር ምክር ይዞ በድፍረት ያወጋል።
ፈጥረህ ትንሽ ድግስ
አድርግን አታደርግ፣ እንዲያ ብታደርግስ

በደል አቅፎ እየኖረ፣ እንዲያ ያመካኛል
ሐጥያት መፅደቅ ቢሆን፣ እያለ ይመኛል።

ፈጥረህ ሰማይ ድግስ
እንዲያ ብታደርግስ።

እንግዳዬሁ ዘሪቱ✍️

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago