የአርቲስቱ ጊዜ?

Description
የተለያዩ ትዝብቶች፡ ዜናዎች፡ ቃለመጠይቆችና ወቅታዊ ሀተታዎች በራሱ በአርቲስቱ የሚቀርቡበት
Advertising
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 month ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 4 months, 2 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 6 months, 2 weeks ago

3 years, 10 months ago

ጆ ባይደን በሹመት ቀናቸው የትራምፕን ፖሊሲዎች ለመሻር መዘጋጀታቸው ተገለጸ

ሙስሊም በሚበዛባቸው 7 ሀገሮች ላይ የተጣለውን የጉዞ እገዳ ማንሳት በሹመታቸው ቀን ከሚወስኗቸው ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፈቃድ የሌላቸው ሰዎች ዜግነት የሚያገኙበት ዕድልም ይፈጠራል ተብሏል፡፡

ጆ ባይደን ከ 3 ቀናት በኋላ 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ይሾማሉ! የፓሪሱን የአየር ንብረት ስምምነት እንደገና መቀላቀል እና ሙስሊም በሚበዛባቸው ሀገሮች ላይ የተጣለውን የጉዞ እገዳ ማንሳት በቅጽበት ከሚቀየሩ የትራምፕ ፖሊሲዎች መካከል መሆናቸውን የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

በትራምፕ ፖሊሲ በሜክሲኮ ድንበር እየተያዙ ከወላጆቻቸው የተለዩ ህጻናትን ዳግም ከወላጆቻቸው ጋር እንዲገናኙ ማድረግም ፣ ባይደን በፍጥነት የሚተገብሩት ተለዋጭ ፖሊሲ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ፣ ማስክ ማድረግን ጨምሮ ሌሎች አስገዳጅ ህጎችን ሊያጸድቁ እንደሚችሉም የኋይት ሀውስ ኃላፊው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመጀመሪያ የስልጣን ቀናቸው ከሚያሳልፏቸው ውሳኔዎች በተጨማሪ ፣ በ100 ቀናት የስልጣን ጊዜያቸው ፣ በርካታ ስደተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አዲስ የስደተኞች ህግ ለኮንግረሱ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡ በዚህም አሁን ላይ በአሜሪካ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቀድ የሌላቸው ስደተኞች የሀገሪቱን ዜግነት የሚያገኙበት መንገድ እንደሚከፈትላቸው ነው የሲኤንኤን ዘገባ የሚያሳየው፡፡
(አልዐይን)

3 years, 10 months ago

ከካፒቶል ጥቃት በኃላ የትራምፕ ተቀባይነት መቀነሱን ከህዝብ በተሰበሰበ ድምፅ ማረጋገጥ ተቻለ

በዋይት ሀውስ ለአራት ዓመታት ያህል ቆይታ ያደረጉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን ሊለቁ ቀናቶች ብቻ በቀሩበት በዚህ ጊዜ ተቀባይነታቸው በሀገረ አሜሪካ ቀንሷል።በካፒቶል የደረሰው ጥቃት ደግሞ ዋንኛ ምክንያት ሆኗል።

ሶስት ተቋማት የትራምፕን ተቀባይነት በተመለከተ ከህዝብ ድምፅ ሰብስበዋል።በሁለቱ ድምፅ የሰበሰቡ ተቋማት ባገኙት የህዝብ ድምፅ ግኝት መሰረት በድጋሚ በምርጫ እንዳይወዳደሩ ሊታገዱ እንደሚገባም አመላክተዋል።

የህዝብ ድምፅ የሰበሰቡት ፒው ሪሰርች፣ዋሽንግተን ፖስት ከኤቢሲ ኒውስ ጋር በመጣመርና ሮይተርስ ናቸው።በፒው ሪሰርች ግኝት መሰረት የትራምፕ ተቀባይነት 29 በመቶ ቀንሷል።

አንዳንድ ሪፓብሊካን የካፒቶል ጥቃት ቢያወግዙም አሁንም ያለ አንዳች ማስረጃ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን የትራምፕን ክስ የሚደግፉ ግን በርካቶች ናቸው።

3 years, 10 months ago

ፍልስጤም ከ15 ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ልታካሂድ መሆኑን አስታወቀች

የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አባስ እንዳስታወቁት በ15 አመታት ጊዜ ዉስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍልስጤም ህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላትና የፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ታከናዉናለች ብለዋል፡፡

የአባስ ቢሮ ባወጣው መግለጫ መሠረት በእስራኤል በተያዘው ዌስት ባንክ ውስጥ የራስ አገዛዝ አስተዳደር በሆነው ግዛት በግንቦት ወር የሕግ አውጪዎቹ ምርጫ እንዲሁም በወርሃ ሐምሌ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ ቀነ ቀጠሮ መያዙን ይፋ አድርጓል፡፡

በ2006 ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደዉ የፍልስጤም ምርጫ ባልተጠበቀ መልኩ ሀማስ ማሸነፉ ውስጣዊ የፖለቲካ አለመግባባት እንዲሰፋ በማስገደድ ምርጫዉ እንዲራዘም አድርጓል፡፡ሀማስ የጋዛ ሰርጥን እያስተዳደረ ይገኛል፡፡

የሐማስ እንቅስቃሴ አካባቢውን መቆጣጠር ከጀመረበት ከ2007 አንስቶ ጋዛ በእስራኤል እገዳ ውስጥ ትገኛለች ፡፡

የሙሃሙድ አባስ አስተዳደር በምስራቃዊ እየሩሳሌም ምርጫዉ እንደሚደረግ ያስታወቀ ሲሆን በኢየሩሳሌም ምርጫ ለማከናዉን የሚያስችል ምንም ፍንጫ ከእስራኤል ዘንድ አልታየም፡፡

3 years, 10 months ago

የሰረቀው ገመድ ጠልፎ የጣለው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አምቼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሰረቀው ገመድ ጠልፎ የጣለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ቡድን ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሰለሞን አሰፋ፣ ጥር 5 ቀን 2013 ዓ/ም ምሽት ላይ ወደ ግንባታው ስፍራው ሰራተኛ መስሎ የገባው ተጠርጣሪው ለሊቱን የህንፃው የምድር ወለል ውስጥ ሆኖ ያሳልፍና ከንጋቱ 12 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ገደማ ለህንፃው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ከተቀመጠ ገመድ ላይ 40 ሜትር ያህል ቆርጦ በመውሰድ በወገቡ ጠምጥሞ በላዩ ላይ ጃኬት በመደረብ ከግቢው መውጣቱን ገልጸዋል፡፡

የግንባታ ስራው የሚከናወነው 24 ሰዓት ሙሉ በመሆኑ የጥበቃ ሰራተኞችም ሰራተኛ መስሎ የገባው ተጠርጣሪ ላይ ሲወጣም ትኩረት እንዳላደረጉ የገለፁት ምክትል ኢንስፔክተር ሰለሞን ግለሰቡ ገመዱን ሰርቆ በመንገድ ላይ ሲጓዝ አረማመዱን ተመልክተው ጥርጣሬ ያደረባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለማረጋገጥ ሲያስቆሙት ለማምለጥ ሲሮጥ፤ ሰርቆ በወገቡ ላይ የጠመጠመውየኤሌክትሪክ ገመድ ጠልፎ እንደጣለውና በህብረተሰቡ ትብብር ተይዞ ወደ ፖሊስ እንደቀረበ ተናግረዋል፡፡

የጥበቃ ሰራተኞች ተገቢውን የፍተሻ ተግባር ቢያከናውኑ መሰል ወንጀሎችን መከላከል እንደሚቻል ምክትል ኢንስፔክተር ሰለሞን አሰፋ ማሳሰባቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

3 years, 10 months ago

በአዲስ አበባ የተቀረጹ ቁልፎች ሽያጭ መበራከት የመኪና ስርቆትን እንዳባባሰው ተነገረ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተሸከርካሪ ስርቆት ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በተያዘው አመት እየቀነሰ መምጣቱን አስታውቋል ፡፡

ሆኖም ግን አሁንም ድረስ ስርቆቱ እንዲቀጥል ያደረገው በየአካባቢው የሚሸጡ የተቀረጹ ቁልፎች ሽያጭ እተበራከተ በመምጣቱ ነው ሲሉ በኮሚሽኑ የሚዲያ ዲቪዥን ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ በተለይ ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡

በአዲስአበባ አንዳንድ አካባቢዎች የተቀረጸ ቁልፍ የሚሸጡ ሲሆን ህብረሰተቡ የተቀረጸ ቁልፍ ግዢ ሊያቆም እንደሚገባም ኢንስፔክተር ማርቆስ ተናግረዋል ፡፡

በተቀረጸ ቁልፍ ግዢ ወቅት ተጨማሪ ቁልፎች ሻጭ ጋር የሚኖርበት ሁኔታ ሰፊ በመሆኑ ተከታታለው ተሸከርካሪያቸውን ከካቆሙበት እንዲሰረቅ ምክንያት መሆኑን አንስተዋል ፡፡

ፖሊስ በያዝነው አመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ላይ 41 ተሸከርካሪዎች መሰረቃቸውን ሪፖርት የተደረገለት ሲሆን ከነዚህ መካካል አራቱን ተሸከርካሪዎች ከሃዋሳ መስመለስ መቻሉን አስታውቋል ፡፡

የተሸከርካሪ ጠፋብን ሪፖርት ቁጥር እንዲጨምር ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል ተሸከርካሪያቸውን ያቆሙበት አካባቢ አንዳንድ አሽከርካሪዎች ሲዘንጉ በሚመጣ ችግር እንደሆነም ጭምር ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

3 years, 10 months ago

አቶ ስብሃት “አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችንን ነው በማስፈጸም ላይ ያላችሁት” ማለታቸውን ሌ/ጄኔራል ባጫ ገለጹ

አቶ ስብሃት በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶ ሲስቁ ታይተዋል፡፡በርካቶችም አቶ ስብሃት ምን አሉ በሚል ሲነጋገሩ ነበር፡፡ሌፍተናንት ጄኔራል ባጫ ደበሌ እንደገለጹት አቶ ስብሃት ከተያዙ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡አቶ ስብሃት በተያዙበት ሰዓት ለከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች ፣ “እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል“ የሚል አስተያየት እንደሰጡ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

አቶ ስብሃት ከመያዛቸው አስቀድሞ “ቢያዙ ምን ይሉ ይሆን“ ብለው ጄነራሎቹ ይወያዩ እንደነበር የገለጹት ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ “ግለሰቡ ቢያዙ ሕገ መንግስቱ ጥሩ ነው ፤ ሕገ መንግስቱ እንደዚህ ነው… ብለው ነው የሚያወሩት“ የሚል ግምት በጄኔራሎቹ ሀሳብ እንደነበር ተናግረዋል፡፡አቶ ስብሃት ከተያዙ በኋላም እንደተገመተው፣ አንደኛው ጄኔራል ሲያናግሯቸው “ሕገ መንግስቱ ጥሩ ነው፤ ተወያዩበት“ እያሉ ሲያወሩ እንደነበር የምዕራብ ዕዝ አዛዥ እንደገለጹላቸው ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ ገልጸዋል፡፡

ሌ/ጄኔራል ባጫ ተጫዋች ያሉት የምዕራብ ዕዝ ሌላ ጄኔራል አቶ ስብሃትን “ስለ ሕገ መንግስቱ ተወውና አንተ እስኪ ምን ይሰማሃል“ ብሎ እንደጠየቋቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ስብሃት ሲመልሱ “እኔ የሚሰማኝ እኛ ከሞትን እኮ ቆይተናል“ የሚል ነው፡፡

“መቸ ነው የሞታችሁት“ የሚል ጥያቄ እንደተነሳላቸው ያስታወቁት ሌ/ጄነራል ባጫ “እኛ የሞትነውማ ኢህአዴግ የሚባለው የጠፋ ጊዜ ነው ፤ አሁን የምታደርጉት ምን እንደሆነ ልንገርህ? አሁን እያደረጋችሁ ያላችሁት የቀብር ሥነ ስነስርዓታችን እየፈጸማችሁ ነው“ ሲሉ መመለሳቸውን አንስተዋል፡፡

3 years, 10 months ago

አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ የሕወሓት ቀንደኛ አመራሮች ተገደሉ
በትግራይ ክልል በነበረው ውጊያ ከጥበቃዎቻቸው ጋር አብረው ተገደሉ የተባሉት የሕወሓት አመራሮች፣
1. አቶ ስዩም መስፍን: የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም ውጊያውን የመሩና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዙ፣ በመጨረሻም በሰራዊቱ ላይ ውጊያ እንዲከፈት ትዕዛዝ የሰጡ፣
2. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ" የሕወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ
3. አቶ አባይ ፀሃዬ" የሕወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ
4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ ከመከላከያ የከዳ - ከነጥበቃዎቻቸው ናቸው

3 years, 10 months ago

"ይቅርታ አንዴ ችሎቱን አቋርጠን በዚህ ጉዳይ ማውራት አለብን...." የማሃል ዳኛው ተናገረ

ዛሬም ችሎት በርካታ ሰው ተገኝቷል። የአዲስ አበባ ወጣት አሁን አሁን የኦህዴድ ብልፅግና ተረኝነት ያቃረው ይመስላል። የእነ እስክንድር ዕስር የእናት ሞት የድንጋይ መቀመጫ ሆኖበታል። አሁን ተረኝነት አይደለም ወጣቱን የእሳት ላንቃ እንኳን የሚያቆመው አይመስልም።

ወደ ችሎት ለመግባት ከዋናው በር ጀምሮ ረጅም ሰልፍ ስለነበረ ችሎት ከጀመረ በኋላ ገባሁ። ብዙም አላመለጠኝም።

"በቅድሚያ ከአራት ወራት ቀጥሮ አሻሽላችሁ ለጥር 5 በማድረጋችሁ አመሰግናለሁ። ግን አሁንም ከጥር 26 ጀምሮ አስከ የካቲት 28 ድረስ ምስክር ለማሰማት በሚል ፍ/ቤቱ ያስቀመጠው ትክክል አይደለም ። የተፋጠነ ፍትህ እንፈልጋለን በምርጫ ተወዳድረን ህዝብ እንዲዳኘን እንሻለን። በመሆኑም ቀጠሮው ይስተካከልልን።" እሰክንደር ነበር ችሎት ገብቼ ከመቀመጤ የተናገረው።

ሁለተኛ ተከሳሽ ..ስንታየሁ ቸኮል ቀጠለ..." እኔ አሁንም እደግመዋለሁ እኛ ሰው ገለን አይደለም። ጄኖሳይድም ፈፅመን አይደለም። ህዝብ እንዲራብ እንዲጠማ እናቶች እንዲያለቅሱ አድርገን አይደለም እዚህ የታሰርነው። ይልቁንስ ህዝብን ስለመገብን ጄኖሳይድ እንዳይከሰት ስለተከላከልን ...ለግፉሃን እና ለጭቁኖች የተሻለ ሃሳብ ይዘን ድምፅ ስለሆንን ብቻ ነው። በመሆኑም አሁንም ህዝብ በየቦታው እየታረደ ነው ጄኖሳይድ እየተፈፀመ ነው። ነገ የተሻለ ሃሳብ ለህዝቡ በማቅረብ እና በምርጫ ተወዳድረን አገሪቱ አሁን ከገባችበት አረንቋ ማውጣት እንፈልጋለን። ስለዚህ አሁንም የቀጠሮ ቀን ይሻሻል።"

ሶስተኛ ተከሳሽ አስቴርም የስንታየሁን ንግግር ተከትላ ቀጠለች...እኔም ከአራት ወራት ቀጠሮ ወደዚህ ዝቅ ስላደረጋችሁት አመሰግናለሁ። ክቡር ፍ/ቤት እኛ ከዚህ መንግስት የተሻለ ሃሳብ ...ፖሊሲ...እና አገር የማስተዳደር አቅም አለን በመሆኑም በዚህ ስለምንፈራ እንጅ አቃቤ ህግ ባቀረበው የፈጠራ ክስ አይደለም እዚህ የቆምነው። በመሆኑም ቀጠሮው ዝቅ ይበል።

አስካለ...አዎ በዙ ህዝብ ይጠብቀናል። አሁንም በዚህ መልኩ የተራብነውን ፍትህ በተፋጠነ ሁኔታ እናገኛለን ብለን ተስፋ አናደርግም። በመሆኑም ምስክር የሚሰማበት ቀን ዝቅ ይበልልን!

"በተጨማሪም በየቀኑ 20 ይሆናሉ የተባሉት ምስክሮች እንድ አንድ አየተደረጉ ይደመጥ የተባለው ትክክል አይደለም ሆን ተብሎ ጊዜውን ለማጓተት ታስቦ ነው።" በመሆኑም በበዛት እንዲሰሙ ሊደረግ ይገባል!" (እስክንድር)

የማሃል ዳኛው አድምጦ ጨረሰ... እንዲህም አለ "ይህ ጉዳይ ጊዜ ስለሚያስፈልገው እባካችሁ አረፍ በሉ ! እኛ አንድ አንድፍታ ቢሮ ተነጋግረን እንመጣ ።" ብሎ ከተሰየሙበት ችሎት ሶስቱም ዳኞች ለቀው ወጡ። (እረፍት ሆነ) የታፈኑ ድምጿች ተለቀቁ።

ከደቂቃዎች ቆይታ በኋላ ፀጥታ ሆነ ። ከተቀመጥንበት ተነስተን ዳግም እንድንቀመጥ ታዘዝን። ዳኞች ገቡ።

እሽ የማሃል ዳኛ ቀጠለ...."ቀጠሮው ጥር 26 ምስክር ለማሰማት የሚለው እደፀና ሆኖ ነገር ግን እስከ የካቲት 26 የሚለው ቀርቶ እስከ አራት ድረስ ማለትም ከጥር 26 ,28, 1 2 3 4 በየቀኑ አራት አራት ምስክሮች እየተደመጡ እንዲካሄድ ይሁን።

የምስክሮች ስም ዝርዝር ይቅረብለን የሚለው ግን ምስክሮቹ ማንነታቸው ከታወቀ እውነቱን አፍረጥርጠው ለመመስከር ስለሚቸገሩ ይሄ አይሆንም ።ማንነታቸው በችሎት እለት እንዲቀርብ ይሁን!....

የችሎት ፍፃሜ ሆነ።

የእገታ ዜና...

ችሎት የታደመውን የአዲስ አበባ ወጣት እንዲሁም የባልደራስ አባሎች ደጋፊዎች ጋዜጠኞችንና ሴቶችን ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ሞክራችኋላ በሚል በቁጥር ከ30 በላይ የሚሆኑ ከጠኋቱ አራት ሰዕት ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ደረስ ማለትም አስከ ዘጠኝ ሰዕት በልደታ ባልቻ ፖሊስ ጣቢያ ያላንዳች መፍትሄ ታገተው ይገኛሉ።

በወግደረስ ጤናው
ፍትህ ለጭቁኑ አዲስ አበቤ
ድል ለእውነተኛ ዴሞክራሲ!!
ጥር 2013
ወግደረስ ጤናው

3 years, 10 months ago

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ በቀጠለዉ ጥቃት ሰዎች እየሞቱ ነዉ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ፣ ወምበራ፣ ድባጢና ቡሌን ወረዳዎች ከባለፈው ሃሙስ ጀምሮ እስከ ዛሬው ማክሰኞ በደረሰ ጥቃት የሰው ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎቸ ገለፁ። በዞኑ ጉባ ወረዳ ትናንት ሰኞ በደረሰው ጥቃት ከ 11 ሰዎች ህይወት አልፎአል። በወምበራ ወረዳ በጎንዲ በተባለ ስፋራ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ሃሙስ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩ 16 ሰዎች በዚሁ ጥቃት ሕይወታቸዉን አጥተዋል፤በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች የአካባቢዉ አመልክቷል፡፡ አካባቢዉ ላይ ይኖሩ የነበሩና ጥቃቱ ሲከሰት የደረሱበት ያልታወቀ ሰዎች መኖራቸዉን ተጠቁመዋል፡፡ ከአካባቢው ኮማንድ ፖስት ይህንን ጉዳይ ለማጣራት ያደረግነዉ ጥረት የስልክ ጥሪን ባለመቀበላቸዉ አልተሳካም፡፡
በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሽመሽ በተባለ ስፋራ ትናንት ከሰዓት ታጠቂዎቹ በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ጉዳት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የግለሰቦችን መኖሪያ ቤቶችንም ማቃጠላቸው የተነገረ ሲሆን የተለያዩ የቁም እንስሳትን መዝረፋቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃት አድራሾቹ ዛሬ በማንዱራ ወረዳ ጉዳት ማድረሳቸው ታዉቋል።
ከመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ከተማ በ40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኘዋ በጎንዲ በተበለ ስፋራ ከባለፈው ሃሙስ ጀምሮ የታጡቁ ሸማቂዎች ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ጉዳት ደረሰባቸው የአካቢው ነዋሪዎች በስልክ ለዶቼቬሌ ገልጸዋል። በዕለቱ ታጠቂዎቹ አድፍጠው በመጠበቅ በጸጥታ ኃይሎች ላይም ጥቃት መፈጸማቸውን ጠቁመዋል። በወምበራ ወረዳ ሰንኮራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ለሚ ሰንበታ በበጎንዲ የግብርና ስራ ተሰማርተው የነበሩ ሲሆን በስፋራ የደረሰውን ጥቃት ሸሽተው አሁን ከወረዳው ከተማ እነደሚገኙ አመልክቷል።
"ታጠቂዎቹ በጎንዲ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኃላ ሁለት መኪኖችን አቃጥለዋል። የሞቱት ሰዎች 3ቱ የመነስቡ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ ሌሎቹ የሰንኮራ፣ ደብረዘይት፣ ጎጆር የተባለ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ናቸው። ሁለቱ ደግሞ የአንድ በተሰብ አባላት ሲሆኑ የጸጥታ ሀይሎችም ይገኙበታል። ወደ አስራ ስድስት ሰዎች ህወታቸው አልፈዋልም" ብለዋል።
ከክልሉ ሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ፣ከዞኑ አስቸካይ ጊዜ አስተዳደደር( ኮማንድ ፖስት) ኃላፊዎች ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ ለማግኘት በስልክ ያረኩት ጥረት ስልክ ባለማሳታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡ በቅርቡ በዞኑ የተቋቋመው ግብረ ኃይልም በዞኑ ሰላምን ለማስፈን ያስችላሉ የተባሉ ምክክሮችን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ማድረጉን ከኢዜአ ያኘነው መረጃ ያመልክታል፡፡

ዘገባ፤ ነጋሳ ደሳለኝ «DW» ከአሶሳ

We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 month ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 4 months, 2 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 6 months, 2 weeks ago