ስሜትን በግጥም💖🙄🤔😥😏😊🤐💖

Description
"ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል።"
"ስሜትን በውብ ቃላት መግለጽ ምንኛ ያስደስታል💖💖💖"
We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads:

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ ስራ 👉 @Abusheymc

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

1 year, 7 months ago

የእግር ኳስ ችሎታዬን ለማዳበር ይሁን የውስጤን ብሶት ለማብረድ በማላውቅበት ሁኔታ ከመንገዴ ፊት ለፊት የተሰየሙትን ጠጠሮች እየለጋሁ እናዘወትርበት ከነበረው መንገድ በመሄድ ሳለሁ ከትንሽዬ ልጅሽና ከአቶሽ ጋር እየተሳሳቅሽ ጥሩ ጊዜን ስታሳልፊ ተመለከትኩ። ህልማችን ቢከሽፍም ህልሞሽ ሰምሯል ባንስቅም ስቀሻል ብናልምም ኖረሻል። አልከፋኝም አፍቃሪሽ አይደለሁ ደስታሽ ደስታዬ ነው፤ እንባሽ እንባዬ፤ እንባዬ ሳቅሽ ነው። ባታውቂውም ለሳቅሽ አልቅሻለው። ያመመኝ ግን ትዝታችንን መበረዝሽ ነው። የኔና አንቺ የሆነን ነገር አሳልፈሽ በመስጠትሽ። ትዝታሽን ለኔ ትዝታዬን ለኔ ብለን ቃል ተገባብተን አንድ ያለኝን የመኖሬ ምክንያት የምለውን ትዝታዬን ለሶስተኛ ወገን አሳልፈሽ ሰጠሽ።... ከእንግዲህ ለመኖር ምን ምከንያት አለኝ? ቻው አበባዬ የህይወቴ መዳረሻ ላይ የተገኘሁ ይመስለኛል። ባልሞትም አልኖርም። ደሞ ሳልነግርሽ ልጅሽ ማለቴ ልጃቹ በጣም ታምራለች። ካላስቸገርኩሽ አንቺን በምጠራበት ስም ሰይሚያት ሀኑኔ ትያት ዘንድ ኑዛዜዬን አኖርኩኝ። ግን ከዛ በፊት አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ።.....አፍቅረሽኝ ታውቂያለሽ?

ትዝታሽም ጠፋ ትዝታዬን ሸጥሽው
መኖሬን ነጠቅሽኝ
ለካ ለዚህ ነበር እያቀፍሽ የሳምሽኝ።

ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 year, 8 months ago

ዛሬም እዚህ ቀሚስ ላይ ነሽ? አላት አንድ ዘወትር ይሄን ቀሚስ ስታጥብ የተመለከታት ጎረቤቷ።
ንፁህ እኮ ነው ለምን ታጥቢዋለሽ?....ቀሚሱ አልነበረም የቆሸሸው የቀሚሱ ታሪክ እንጂ። ቀሚሱ ነው ማስታወሻ ከሷ ውጪ ለማንም ለማይታየው ቆሻሻ።ምን ያክል ልቧን የሰበረ ታሪክ ቢይዝ ነው ታሪክ በውሃና ሳሙና ታጥቦ ሚለቅ እስኪመስላት ለማጥፋት የጓጓችው። ዳሩ ግን ታሪክ ጭንቅላት ላይ ነው ታትሞ ሚቀረው፤ ልብን ነው የሚቆጣጠረው። እንጂማ እንዲ ታጥቦ የሚለቅ ቢሆን ስንቶቻችን መሰረዝ የምንፈልገውን ትውስታ ታቅፈን እየኖርን ነው። ቢሳካልን ለአንድ አፍታ የሰላም እንቅልፍ መተኛት ምኞታችን ነበር ምኞት ሆኖ ባይቀር። ታሪካችን አልፈቀደም እንጂ።

  ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 year, 8 months ago

የት ነሽ? ከማን ጋር? በምን ሁኔታ ላይ? አላውቅም። ግን አንቺን መርሳት በስለት ላይ ተመቻችቶ የማንቀላፋት ያህል ከብዶኛል። ታመሽ ህመምሽን እያስታመምሽ ነው? ደስታን ከሙሉ ጤና ጋር ተላብሰሽ እየኖርሽ ነው? አላውቅም። ግን ነገሮች ከትካዜ ባህር ውስጥ ሲዘፍቁኝ፤ ህይወት የመከራ አለንጋዋን ስታሳርፍብኝ አንቺን በማሰብ እረጋጋለሁ። አዲስ ህይወት ጀምረሻል? ልብሽን የምታሳርፊበት አጋር አግኝተሻል? ወይስ ህልምሽ ጉም ሆኖ አልጨበጥ ብሎሻል? ጥላ ሆኖ ስትከተይው ርቆሻል ቀን ሲጨልም ጠፍቶብሻል? አላውቅም። ግን አንቺን አለማግኘቴ፤ ጣፋጭ መንፈስን የሚያድስ ዜመኛ ድምፅሽን አለመስማቴ፤ ዕፁብ ድንቅ የሆነ ጠረንሽ ትዝታ ሆኖ መቅረቱ፤ ራሴን ካንቺ'ጋ ከማለም ከትዝታ'ጋ ተጣብቆ ከመኖር ከትላንት ወደ ዛሬ ካለመሻገር አላዳነኝም። አንቺ ግማሽ ትላንቴን፤ ሙሉ ዛሬዬን፤ የማላውቀው ነገዬን፤ የተቆጣጠርሽ እንስት ሆይ አንድ አንቺን ለመርሳት ስንት አንቺን መስበር ይኖርብኝ ይሆን?

ዝምታ አልመረጥኩኝ ጩኸቴም ላይረባን
ያለ ብድራችን ምነው እዳ ገባን
አንቺን ለማደብዘዝ ስንት አንቺን ስተካ
ለመርሳት መሞከር ማስታወስ ነው ለካ።

   ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 year, 9 months ago

ነገን ማለም ቀርቶ ዛሬን መኖር አቃተን፤አረጀን መሰል ትላንትና ላይ ቀረን አይደል? የህልም አለም ሰዎች መሆን ሆነ እጣፈንታችን። ከህልማችን ስንባንን እውነታው አሳማሚ ሆነብን።ሁላችንም በማንም ሊሞላ የማይችል ባዶ ቦታ አለችን፤ ወይም በሆነ ሰው ተከፍቶ የቀረ ሽንቁር። ለምን ማንም ህይወታችን ውስጥ ቢገባ ያለ ምክንያት መከፋታችንን ይሁን በሰው መሀል ብቸኛ መሆናችንን ሊያስወግድልን አልቻለም?

ነፍሴ ከአዳኟ እንደምታመልጥ እርግብ ይህን አለም ሸሽታ ትበራለች። መብረር ሲታክታት የምታርፈው በሸሸችው አለም ነው፤ ባያሳርፋትም። ያኔ ቀድሞ በነበረው ፍርሀቷ ላይ ተስፋ መቁረጥ ይጨመራል። እንደገና የህልም አለም በረራ ትጀምራለች፤ ስትባንን አመለጥኩት ካለችው አስቀያሚ እውነት ጋር ትላተማለች። የመሸሽ ሩጫዋ አብቅቶ እንዳልኖረች ትሞታለች። አይ ነፍሴ!

ብረሪ አምልጪ ከፍ ወደ ሰማይ
አዳኝ ነው እንጂ አዳኝ የለም ከላይ
ፈራሁልሽ ነፍሴ የህልም በራሪ
መፅደቅ የተመኘሽ በሀጥያት ዘውታሪ።

  ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 year, 9 months ago

ፈረስ ሳትፋቀር ለአህያ ታጭታለች
በቅሎም ባባቷ አፍራ እናቴ ትላለች
እርግጫ ንክሻ ትጀማምራለች
ከማን ወርሳ እንጃ አመል ታመጣለች

አለንጋና ጩኸት ሲያፈራርቅባት መግራት ይሉት ጣጣ
አመል ትጠፋለች ሰይጣኗ ተቀምጣ
ከዚህ ሁሉ ጣጣ
ፈረስ አትገደድ አህያም ለአህያ
በግርፍያና ጩኸት አይደምቅም ገበያ።

     ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 year, 10 months ago

አንቺ የማሽላን ብልሃት የተረዳሽው፤ ውስጥሽ ህመም አርግዞ ጥርስሽ ሳቅ የሚወልደው የልቤ ንግስት ሆይ! እስከመቼ ይሆን ተመልካች አይኖች የምትነፈጊው? ይኸው አድማጭ ጆሮዎች ከቀጡሽ ስንት ዘመን ተቆጠረ? አውቃለሁ ምን ያክል እንደታመምሽ። መተንፈስን እየሻትሽ የነፃነት ሳንባዋ በነቀርሳ እንደተመታ ፍጥረት ማጣጣር ላይ እንዳለሽ፤ ድካምሽ ገዝፎ ማረፊያን እንደተቀማሽ። አውቃለሁ የምትወጂውን ገላ ባትጋሪም የማትጠይውን ግዑዝ እንዳቀፍሽ። ስሜት አልባ ሆነን የምናገኘው ሰው የምንገኝበት ቦታ እሱን ተይውና ለራሳችን እንኳን ስሜት ካጣን የራሳችንን ግዑዝነትን ማጣጣም እንጀምራለን። አውቃለሁ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነሽ የተፈጠረው ይፈጠር ህይወት መምራት እንደጀመርሽ፤ እንዳሻቸው ያርጉኝ ምን ህይወት አለኝና ህይወቴንማ ቀርጥፈው ከበሉት ቆዩ። ወደድኳቸው ልቤን ከፈትኩላቸው። ለመግባት አላንገራገሩም፤ ተደስተው ነበር። ነገር ግን ሁሉም የየድርሻቸውን ተቀራመቱት። ልቤ ሲሰባበር ይታወቀኝ ነበር። መሰበሬ አልነበረም ህመሜ መሰበሬ የፈጠረብኝ ህመም ሁለት ድንጋይ ሲጋጩ ከሚፈጥሩት ብልጭታ የዘለለ አልሆነ። ያሳመመኝ ትንሽም እዝነት መራራትን ለኔ ከውስጣቸው ሳጣ ነው። አይናቸውን አነበብኩት ከይቅርታ ይልቅ ደካማነቴን ሲነግሩኝ ተመለከትኩ። አንገቴን ቀና እንዳላደርግ አድርገው ሰበሩኝ። እነማን? እነዛ ያመንኳቸው፤ የወደድኳቸው፤ የኔ ብዬ የተቀልኳቸው.....። አውቃለሁከዚህም በላይ ችለሽ እየኖርሽ እንደሆነ። ባላውቅም እንዴት መፍትሄ ልሆንልሽ እንደምችል። ባላውቅም ህመምሽን እንዴት መታመም እንዳለብኝ። አውቃለሁ....ባላውቅም።

አቤት ግፋችንስ አቤት የኛ እርኩሰት
አቻኩለን ሸኘናት ነበረች ለማለት።

   ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 year, 10 months ago

የኔ ነው ስትለኝ ምኑ አላልኳትም
ሁሉን አዋቂ ነች አስረጅ አያሻትም
ደገመች አሁንም ሰንደሏን ሰካክታ
ግን ደግሞ አጎደላት ገራባ ማጣቷ
ፈራሁኝ ለነፍሴ እንዳትሰልሰው
ንግግር አይመርጥም አቅል የተራበ ሰው
ፍርሃቴም አልቀረ ባፍዋ ነገረችኝ
ይሄም እርስት ሆኖ እብደቴን ቀማችኝ
ፈጣሪ ሲጨክን እንደዚህ ይቀጣል
ለእኔ እና እሷ ጊዜ ማበድም ያጣላል።

✍️    ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 year, 10 months ago

የት ከረምሽ አልልም በደንብ ክረሚ
እንክርዳድ ውስጥ ስንዴ በትነሽ ልቀሚ
ስንዴማ ምርጥ ዘር በሀገር የበቀለ
አባትሽ አያምኑም ከነጭ ካልዋለ።

   ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 year, 11 months ago

...አፈቅርሀለው። ለምን? አላልኩኝም እኔም ሲሉ እየሰማሁ ስላደኩ፤ እኔም አልኩኝ።....ድምጽህ ሱሴ ሆኗል። አመንኳት፤ ድምጿን ሱሴ አደረኩ።....ከእለታት በአንዱ ቀን እስክሞት አፈቅርሀለው። ያለችበት የስሜት ከፍታ እንዲህ እንደሚያስብላት አልተረዳችውም። ቢሆንም አመንኳት።

ከሁለት ሳምንት በኋላ ደወልኩኝ።

?‍?አቤት

?የኔ ፍቅር

?‍?ማን ልበል?

?አብዱሌ ነኝ

?‍?አብዱ የትኛው?....ቁልምጫውም ቀረ

?‍♂እስክትሞች የምታፈቅሪው

?‍?ይቅርታ አላወኩህም........ተቋረጠ ኔትዎርክ ነው መሰለኝ።

   ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 year, 11 months ago

ሰላም፣ሰው፣ጤና ሁሉም ሞላልኝ። ነገር ግን አንቺ ጎደልሽ። ያንቺ መጉደል እኔን አጎደለኝ። ዱኒያ ብትሞላ እኔ ከጎደልኩኝ ምን ሊረባኝ?...ታስታውሻለሽ ለመጨረሻ ጊዜ ስንገናኝ ህመማችንን በምን እንደብቀው ስልሽ የሰጠሽኝ ምላሽ "አንተ በፅሁፎችህ እኔ በጥርሶቼ" እንደዛ ስትዪኝ አምኜሽ ነበር። ሞከርኩ ሞከርኩ ግን አልሆነልኝም። ህመሜን ለመደበቅ ፅሁፎቼ በቂ አልሆኑም። አንቺስ እንዴት ነው ህመምሽን በጥርሶችሽ መደበቅ ሆኖልሻል? ከሆነልሽ እባክሽ ነይና አስተምሪኝ። ጥርሶቼ እህል ከማላመጥ የዘለለ ፋይዳ የማይሰጡ ከሆኑ ሰነባበቱ። አንድ አፍታ ከባልሽ እቅፍ ተነጠይና ሳቅን ካልሆነም ፈገግታን አስለምደሽኝ ከደረቱ ትሰየሚያለሽ። መቼስ ለኔ ስትይ ቅፅበታዊ ብርድ ቢመታሽ ቅሬታሽ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ሀኑኔ የኔ ህመም የኔ ጤና የኔ መሪር የኔ ጣፋጭ ሀኑኔ የኔ ሳቅ የኔ ሀዘን የኔ ጉድለት የኔ ሙላት እንዴት ውብ አርጎ ፈጠረሽ? እንዴትስ የምታሳሺ ነሽ? እንዴት የማትረሺ ሆንሽ? ሀኑኔ ህይወቴ ሀኑኔ ሞቴ።

    ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads:

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ ስራ 👉 @Abusheymc

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik