ስሜትን በግጥም💖🙄🤔😥😏😊🤐💖

Description
"ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል።"
"ስሜትን በውብ ቃላት መግለጽ ምንኛ ያስደስታል💖💖💖"
Advertising
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc

1 month, 1 week ago

የኔ ነው ስትለኝ ምኑ አላልኳትም
ሁሉን አዋቂ ነች አስረጅ አያሻትም
ደገመች አሁንም ሰንደሏን ሰካክታ
ግን ደግሞ አጎደላት ገራባ ማጣቷ
ፈራሁኝ ለነፍሴ እንዳትሰልሰው
ንግግር አይመርጥም አቅል የተራበ ሰው
ፍርሃቴም አልቀረ ባፍዋ ነገረችኝ
ይሄም እርስት ሆኖ እብደቴን ቀማችኝ
ፈጣሪ ሲጨክን እንደዚህ ይቀጣል
ለእኔ እና እሷ ጊዜ ማበድም ያጣላል።

✍️    ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 month, 1 week ago

የት ከረምሽ አልልም በደንብ ክረሚ
እንክርዳድ ውስጥ ስንዴ በትነሽ ልቀሚ
ስንዴማ ምርጥ ዘር በሀገር የበቀለ
አባትሽ አያምኑም ከነጭ ካልዋለ።

   ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 month, 2 weeks ago

...አፈቅርሀለው። ለምን? አላልኩኝም እኔም ሲሉ እየሰማሁ ስላደኩ፤ እኔም አልኩኝ።....ድምጽህ ሱሴ ሆኗል። አመንኳት፤ ድምጿን ሱሴ አደረኩ።....ከእለታት በአንዱ ቀን እስክሞት አፈቅርሀለው። ያለችበት የስሜት ከፍታ እንዲህ እንደሚያስብላት አልተረዳችውም። ቢሆንም አመንኳት።

ከሁለት ሳምንት በኋላ ደወልኩኝ።

👩‍🦱አቤት

👨የኔ ፍቅር

👩‍🦱ማን ልበል?

👨አብዱሌ ነኝ

👩‍🦱አብዱ የትኛው?....ቁልምጫውም ቀረ

👱‍♂እስክትሞች የምታፈቅሪው

👩‍🦱ይቅርታ አላወኩህም........ተቋረጠ ኔትዎርክ ነው መሰለኝ።

   ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

1 month, 3 weeks ago

ሰላም፣ሰው፣ጤና ሁሉም ሞላልኝ። ነገር ግን አንቺ ጎደልሽ። ያንቺ መጉደል እኔን አጎደለኝ። ዱኒያ ብትሞላ እኔ ከጎደልኩኝ ምን ሊረባኝ?...ታስታውሻለሽ ለመጨረሻ ጊዜ ስንገናኝ ህመማችንን በምን እንደብቀው ስልሽ የሰጠሽኝ ምላሽ "አንተ በፅሁፎችህ እኔ በጥርሶቼ" እንደዛ ስትዪኝ አምኜሽ ነበር። ሞከርኩ ሞከርኩ ግን አልሆነልኝም። ህመሜን ለመደበቅ ፅሁፎቼ በቂ አልሆኑም። አንቺስ እንዴት ነው ህመምሽን በጥርሶችሽ መደበቅ ሆኖልሻል? ከሆነልሽ እባክሽ ነይና አስተምሪኝ። ጥርሶቼ እህል ከማላመጥ የዘለለ ፋይዳ የማይሰጡ ከሆኑ ሰነባበቱ። አንድ አፍታ ከባልሽ እቅፍ ተነጠይና ሳቅን ካልሆነም ፈገግታን አስለምደሽኝ ከደረቱ ትሰየሚያለሽ። መቼስ ለኔ ስትይ ቅፅበታዊ ብርድ ቢመታሽ ቅሬታሽ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ሀኑኔ የኔ ህመም የኔ ጤና የኔ መሪር የኔ ጣፋጭ ሀኑኔ የኔ ሳቅ የኔ ሀዘን የኔ ጉድለት የኔ ሙላት እንዴት ውብ አርጎ ፈጠረሽ? እንዴትስ የምታሳሺ ነሽ? እንዴት የማትረሺ ሆንሽ? ሀኑኔ ህይወቴ ሀኑኔ ሞቴ።

    ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

2 months, 1 week ago

በራፉ አልተዘጋም ገርበብ ብሎ ነበር። በደከመ ሰውነት ከፍቶት ሲገባ እናቱ ምስር ስትለቅም አገኛት። እግሯ ስር ወደቀ፤እናት አልተደናገጠችም አዘነች እንጂ ነገሩ ገብቷታል። ምስሩን ከጎኗ ካለ ወንበር ላይ አስቀመጠችም። ደገፍ አርጋው አንስታ ጭንቅላቱን ጭኗ ላይ አስቀምጣ ፀጉሩን ትደባብሰው ጀመር ልክ እንደ ልጅነቱ። ....አለቀሰ፤ አላባበለችውም። በማባበል የሚድን ህመም እንዳልሆነ ታውቃለች። ቃል አወጣ። አ...አ...አገባች እኮ። ምንም አልተናገረችውም። ውስጡ ያፈነውን አውጥቶ እንዲቀለው የፈለገች ይመስላል፤ ባይቀለውም። ....ዳርኳት እያየኋት ችቦ አይሞላም ወገቧ ብዬ ብር አምባር ሰበረልሆ ጨፍሬ። አናስገባም ሰርገኛ ሲባል እውነት የማይገባ መስሎኝ አምላክ የውስጤን አይቶ ረዳት እንደላከልኝ ተደሰትኩ፤ ሰርገኞቹ መልአክ ናቸው አልኩኝ። ትንሽ ተጋፉና መሳሳቅ ጀመሩ፤ ሙሽራው የጫጉላው ንጉስ ገባ። እንዴ አምላኬ ሆይ ምነው ተስፋ ሰጥተህ ነሳኸኝ? በወደደ ይቀለዳል? በምን ሀጥያቴ? አምላኬን አማረርኩ። መልአክ የነበሩት በቅጽበት ጋኔል ሆነው ታዩኝ፤ እየተጠቋቆሙ የሳቁብኝ መሰለኝ። ህመሜን ታማው ይሆን ብዬ ተመለከትኳት አይኖቿን ከአይኖቼ ታሸሻቸዋለች፤ ጥርሷን ማሸሽ አልቻለችም ነበር። አየኋቸው ደስተኛ ነበረች አይኖቿን ባላያቸውም። በድንገት እንባ ከአይኖቿ መፍለቅ ጀመረ። ሀዘኔን አዝናለች ይኸው አነባች አልኩኝ ለራሴ፤ በሰዎች መሀል ብቸኛ ሆነናል የሚረዳን አጣን እንጂ። አንድ የማላውቀው ሰው "ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ" ሲል ሰማሁት። እውነት ነው ሲዳሩ እንጂ ሲያገቡ የሚያለቅሱ ማን ናቸው? እንዴትስ ቢሞኙ? ከጭኖቿ ቀና ብሎ እማ...አቤት ልጄ...በቃ አገባች አትደውልልኝም ድምጿን አልሰማውም አትደውልልኝም እንደ ድሮው አባቴ ብላ አጠራኝም እኔም ሀኑኔ እያልኳት ደስታዋን ማየት አልችልም ናፍቀኸኛል አትለኝም....እማ ወሰዷት እኮ። እናቱ ስታዳምጠው ቆይታ ልጄ ልብህን አደንድነው። እነዛ በወደዱት የተወደዱ የሚወዱትን ያገኙ ምነኛ እድለኞች ናቸው።....ልብህን አደንድነው ልጄ። በረጅሙ ተነፈሰች ዝምታ ሰፈነ....።

አፈቀራት ተከልክሎ
ይኸው ዳራት እልል ብሎ
አንቺን ይንሳኝ ምሎ ነበር
ልታገባ ቆሞ ሊቀር።

   ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

2 months, 1 week ago

በጨዋታቸው መሀል...ሀኑኔ...ወዬ...ብር ባይኖረኝም ታገቢኛለሽ?...ሳቋ ደበዘዘ፤አንገቷን ደፋች። ለጥያቄው ዝምታዋ መልስ ሆነ ግና ዝምታዋ ብዙ ያወራል። ሀሳቡ ተደበላለቀበት፤ ተነስቶ መንገዱን ጀመረ። አልጠራችውም። ቆይ አንዴ ላስረዳህ አላለችውም። የምታስረዳው ነገር እንዳልሆነ ታውቃለችና። ሊወቅሳት አልፈለገም ቤተሰቧ ጋር የምታገኘውን ምቾት እሱ ሊሰጣት አይቻለውምና። ከእናንተ ውስጥ ምቾቱን ለፍቅር ሲል የሰዋ እስቲ ይውቀሳት። ፍቅር የተራበ ሆድን አይሞላም የታረዘ ገላን አያለብስም የተጠማ ጉሮሮን አያርስም። ፍቅር መንፈስ ነው። የማይታይ የማይዳሰስ የማይጨበጥ በምናብ ያለ የሀሴት ምንጭ የመኖር ሚስጥር የተግባቦት ቀመር የመፈላለግ ጥልቀት። እሷ ንግስት ንብ ፈላጊዋ ብዙ በመልክ ብትሻ በስነምግባር ቢያሰኛት ሀብትማ የግሏ እሱ እሱ ግን ተራ ሰራተኛ መኖሩ የማንም ብስራት ያልሆነ ቢሞት ሞቱ የማንም ሀዘን የማይሆን ታዲያ ስለምን እሱ የመጀመሪያ ምርጫዋ ሊሆን ይቻለዋል። በእርግጥ ማንም እንደሱ አይሆንላትም እሱም እንደ ማንም አይሆንላትም። መንገዱን ቀጠለ በጨለማው ሰፈር በጣም በሚያስፈራው። ፀሀይ ከጠለቀች ማንም ዝር ከማይልበት፤ እሱም ከዚ በፊት ያልደፈረው ነገር ግን ዛሬ ምንም ሆነበት። ለካስ የሰው ልጅ ፍረሀት ውስጡ የሚጫረው ተስፋ ሲኖረው ነው፤ የሚወደው ነገር ህይወቱ ውስጥ ሲያገኝ ግና እሱ ያንን ተነጥቋል። ጨለማው ለሱ ምንም ሆኗል። መኖሬ ትርጉም ይሰጣታል ያላት ለፍጡራን ቀሎ ለእሷ የከበደ ማንነቱ ወድሟል። ታዲያ ስለምን መኖሩን ይኑረው? ፍርሀትንስ ይፍራው? ልቡ ለጨለመ የመንገድ ብርሀን ምኑም ነው። የልቤ ብርሀን...እኔነቴን አለመለመችልኝ ያላት...እሷ...ዝም አለች.....

ከበትር የላቀ የማይቀል ከቃል
ለካ ለተረዳው ዝምታም ይሰብራል.... መንገዱን ቋጨው የጨለማውን....ወደ ሌላ ጨለማ....

ቆመሽ እንዳትቀሪ ቆሞ መቅረት ለኔ
ላንቺ ጀምበር ወጥታ ምሽት ይሁን ቀኔ
የሰርግሽ 'ለት ጥሪኝ ተረረም ተረረም
ባላገባሽ እንኳን ላጨብጭብ ግዴለም።

ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

4 months, 1 week ago

...ትሂድ ግዴለም። ሳትመጣ መሄድን ማን እንዳስተማራት እንጃ። እንደ ምክንያትነት ያቀረበችው ለኔ የሚሆን በቂ ጊዜ የለህም የሚል ነው። አጠገቤ ያለች እየመሰላት ሰማይ ምድርን የራቀቻትን ያህል እንደራቀችኝ አልተረዳችም ይሁን አልያም እውነቱን መቀበል ያልፈለገች አላውቅም። ሀቁን ለመናገር እኔም ሰማይ ምድርን ትራቃት ወይም ምድር ሰማይን ትራቃት የማውቀው ነገር የለም፤ ጉዳዬም አይደለም። ብቻ ይሄን ተረድቻለው ሳይመጡ መሄድ መቻልን ሳያገኙ ማጣት እንዳለ....ትሂድ ማጣት ለኔ ብርቄ አይደለ፤ እንኳንስ እሷን እራሴን አጥቻለው...ትሂድ ማጣት ከመኖር እኩል የተሰጠኝ ገፀ በረከቴ ነው። እየሸኙ መሳቅ እየሳቁ ማልቀስ እያነቡ እስክስታ እጣ ፈንታዬ ከሆነ እንደሰነበተ አልገባትም መሰለኝ...ወዶ ለመጠላት አምኖ ለመከዳት ደግሞ እኔን ማን ብሎኝ ።....በእርግጥ የመጣች መሰላት....ልቧ ተሰብሮ ነበር በማን እንደሆን እንጃ፤ ብቻ በሆነ ሰው....ህመሟን ያሽርላት ብዬ ከልቤ ዘግኜ ልቧን ሞላሁላት....ትንሽ ትንሽ መሳቅ ጀመረች። የኔ ነፍስ ሻማ ነች ሌላን ታበራለች ለራሷ ታልቃለች በፅልመት ትዋጣለች። ....ዛሬ መጉደሌን አይታ ሳትመጣ ልሄድ ነው ትላለች...የኔ መጉደል የሷ ሙላት እንደሆነ አልገባትማ። ትሂዳ ትሂድ እንኳን እሷ እኔም ሄጃለው የት እንደሆን ባላውቅም። ሳያገኙ ማጣት እየሳቁ ማንባት ማንባትን መሰወር ህመምንም መቅበር ደህንነት መዘከር እጣፈንታዬ ነው የህይወቴ ገፀ በረከቴ...በማግኘት መደሰትማ ከእትብቴ ጋር አብሮ ተቀብሯል።....ትሂዳ ትሂድ።

   ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

4 months, 2 weeks ago

...እየጠበኩት...እየጠበቀኝ...እያረፈደ...እየቸኮልኩኝ ብዙ ተጠባበቅን፤ ስለኔ እያዘነ...ስለሱ እያነባሁ...በጊዜዬ ከመጣ እያየሁ ካረፈደም እንዳያጣኝ በመናፈቅ የሌለሁ መስሎት ከደጅ እንዳይመለስ አንገቱን እንዳያቀረቅር ስንት ዘመን በራፌን ክፍት አድርጌ ጠበኩት።መሰነባበት የሌለው መለያየት ምንኛ ያማል? ደጄን ክፍት አድርጌ ስንት ተኩላዎች፣ ጅቦችና ውሾች ሲተናኮሉኝ ስመልሳቸው እንደኖርኩ ማን በነገረው...ብርቱ ክንዴ ሳይዝል ተስፋዬ ተስፋ በነበረው ሰአት ፤ አለመሸነፌ መሸነፍ ሳይሆን በፊት። አልቀረም በጊዜዬ ሳይሆን በጊዜው መጣ እንጂ...መቅረቱ አድኖኝ ማርፈድ ሲሆን ጎዳኝ። ለምን? ሌላ ሰው አገባኝ። ለምን? በአራተኛው ጣቴ ቀለበት ታሰረ። የሴት ልጅ እድሜ ቁማር ነው ወይ ትበላለች ወይ ትበላለች። ልክ እሱን እንዳየ እንዳቀረቀረ...ከመታሰር ላልድን መሄዴ ላልቀረ....መቅረቱ ማርፈድ እንዳይሆን እልፍ ጊዜ ፀልያለሁ፤ በሱ አያስችለኝም ባሌን ፈታዋለው። ዋጥ ፀጥ ረጭ ዝም...ግን እንደ እውነታው ጩኸት እንዲ አይጮህም...ምናለ በልጅነታችን ት/ቤት ስናረፍድ ካሁን ቡሀላ ተብለን ድጋሚ እድል እንደሚሰጠን ህይወትም ያን እድል ብትሰጠን...ምናለ ማርፈድ የስንፍና ምልክት ብቻ እንደሆነ ባይነግሩን...ራስን እንደሚያሳጣ ቢያስተምሩን...አንዳንድ ማርፈዶች ትልቅ ዋጋ ያስከፍላሉ።

ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

4 months, 3 weeks ago

ምናልባት ይሄ ማንነቴ ይሆን እሷን ያሳጣኝ? በገራባና ሰንደል ተከብቤ ስታየኝ ቀልዬባት ይሆን? የተበጫጨቀ ልብሴን ብቀይር የተሰበረ ልቤን ትጠግንልኝ ይሆን? ሳቄን ማልቀስ በቅቶኝ ሳቄን እስቀው ይሆን? ሲል አሰበ። እሷን ያሳጣው ማንነቱን ጠላው። ሊቀየርም ወሰነ። ሰንደሉን ለመጨረሻ ጊዜ በሚመስል ሁኔታ አሸተታት አይኑ በእንባ ተሞላ የረጅም ጊዜ ታማኝ ወዳጁን ያጣ ያህል ተሰማው። ለሷ ሲል ምንም ለማድረግ ቃል ገብቷልና መንገድ መሀል ወረወራት.....ለረጅም ጊዜ ተመለከታት.....ገራባውን እየተቃጠለ ካለ ቆሻሻ ውስጥ ጨመረው ሲቃጠል ማየት አልፈለገም እሱን በመመልከት ጊዜውን ማባከን እንደሌለበት ያውቃል። የተበጫጨቀ ልብሱን ቀየረ ሌላ ማንነት የያዘ መሰለው....ወዲያው ጉዞ ጀመረ የተሰበረ ልቡን ለመጠገን።...ድንገት ልቡ በፍጥነት ትመታ ጀመር ጉልበቱም ከዳው ...ምላሱ ገና እንደተወለደ ህፃን አንዳች ቋንቋ እንደማያውቅ ተሳሰረበት። ለምን? ተመለከታት። ብቻዋን አልነበረችም.....ሮጦ እግሯ ስር ተንበረከከ እጆቿን ይበልጥ አጥብቆ ያዛቸው....እባክሽ አትራቂኝ አላት። ጥላው እንዳትሄድ እጆቿን አጥብቆ ያዛቸው.....ሰው ተሰበሰበ፤ ደግሞ ተነሳበት ብለው ከሷ ነጠሉት.....ዘንግቶት ኖሯል ለካስ...ለካስ ተድራለች።...ለካስ አብዷል.....አትይዘው ተድራ አትለቀው አፍቅራ ግራ ተጋባች....መንገዷን ቀጠለች። የሱ ነፍስ የሱ ህይወት እዛው ቦታ ቀረች እንዳልተወለደች ዳግም ቀና ላትል እንዳቀረቀረች። አካሌ ንግስቴ ባክሽ አትስሚያቸው፤ ይኸው አታዪኝም ገራባዬ ርቋል ሰንደሌም ተጥሏል...ይኸው አታዪኝም የተቀዳደደው የጨረተው ልብሴ በአዲስ ተቀይሯል።...ዞራ እንኳን ሳታየው መንገዷን ቀጠለች። ለምን? ተድራለች!....የውስጧን ማን ያውቃል። በድንገት ተነስቶ እየሮጠ ሄደ ። ሰንደሉን ፍለጋ ነገር ግን ከቦታው አልነበረም። አንዴ ከእጅ የወጣ ነገር መመለሻ እንደሌለው አልተረዳም ነበር። ከእጅ የራቀ ለልብ ቅርብ እንደሆነ ለመገንዘብ ረፈደበት...ልክ እሷን እንዳጣት። ከአይኑ እንባ መፍለቅ ጀመረ። በጉንጮቹ አልፈው ደረቱ ላይ ጠብ ጠብ ጠብ...በእንብርክክ መሬት ላይ ወደቀ.....ሰንደሌን...ልክ እንደ ህይወቱ እንባው አብሮ ቆመ። ከየት እንዳመጣው የማያውቀውን ግጥም አነበነበ....

ሰዉ ለሰው መድሀኒት ሰውም ለሰው መርዙ
ከጀርባ ጠቅ ጠቅ ከላይ ነው ትዛዙ
ለምን ነፍሴ ትኑር ምን ቀረኝ ትላለች
ሰንደሌን አጨሷት
እኔም አብጃለሁ ሚስቴም ተድራለች።

ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

5 months ago

ዘወትር ከምንቀመጥበት ስፍራ ተቀምጬ ነበር። መጥታ ካጠገቤ ተቀመጠች፤ ሰላምታ የለ ንግግር የለ። ዝምምምምምምም.....ግን ተረድቻታለሁ፤ ዝምታዋን እንዳዳምጥ ፈቃዷ ነውና። በእርጋታ አይኖቿን አየኋቸው። ደክሞኛል ማረፍ እፈልጋለው የሚል መልክት አዝሏል። ፊት ለፊቷ የተበተኑትን ትናንሽ ጠጠሮች እያነሳች መልሳ ትጥላቸዋለች፤ አስተውሎ ላያት ድርጊቷ ለጠጠሮቹ እንዳልሆነ ማወቅ አይሳነውም። .....ከብዙ ዝምታ ቡሀላ ቃል አወጣች፤ ተ.ለ.ያ.የ.ን......በቃ ይኽን ብቻ ነበር ያለችው። አይዞሽ....ለበጎ ነው...ይህም ያልፋል...እያልኩ የማጽናኛ ቃል ብደረድር ለሷ ምኗም እንደሆነ አውቃለሁ። እሷ ለሱ ምን ማለት መሆኑን ተረድቻለሁና። ....ከብዙ ዝምታ በኋላ ተሰነባበትን። ከዛ በፊት ግን ይህን አልኳት፤ መለያየት እንዲህ ቀላል ቢሆን ኖሮ.....አልጨረስኩትም። በየመንገዳችን አመራን። ከሳምንት በኋላ....ናፈቀኝ አለችኝ። እኔም አልኳት። ማን...ግርታ በተቀላቀለበት ስሜት፤ ሳቅሽ። ቃል ሳታወጣ አንደበቷን አነበብኩት እኔም ነበር ምላሿ። ሳቋ እሱ እንደሆነ ከኔ በላይ ማን ሊረዳት ይችላል? ማንም?......አንዳንዶቻችን የተለያየን ቢመስለንም እውነታው ግን......። መለያየት እንዲህ ቀላል ቢሆን ኖሮ......

   ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc