ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

Description
እኛስ በትዳር ከእግዚአብሔር ጋር እንተባበራለን።
ትንሿ ቤተክርስቲያንን እናይ፣እናውቅ እና እንወድ ዘንድ እንማማራለን። @LovableFamily
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

3 weeks, 1 day ago
ኑ! እናመስግን። አምላካችን እግዚአብሔር ከሠማይ ወረደ …

ኑ! እናመስግን። አምላካችን እግዚአብሔር ከሠማይ ወረደ ከንጽሕት ድንግል ተወለደ። ደግሞም እናድንቅ ፦ ቸሩ በበረት ሆኖ እያለቀሰ ከእናቱ ጡት ወተትን ለመነ። ለነፍሳችንም ፦ ንጉሥሽና አምላክሽ ዛሬ ተወልዷልና ደስ ይበልሽ እንበላት። መልካም የልደት በዓል ይሁንላችሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

1 month, 1 week ago
ልክ እንደዚህ

ልክ እንደዚህ

1 month, 1 week ago

**ተወዳጆች።

ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤርምያስ (ዶ/ር) #በኢንቴክስ-ፉድ-ኤይድ-ፕላስ በሰላም ዘርፍ ዕጩ ሁነዋል።

ሁላችንም በመምረጥ እኛኑ ለምነው ተጨንቀው ለጉባኤ ቤት ከሚደክሙት ባሻገር በዚህም ተሳትፈን ለዓላማቸው መሳካት መንፈሳዊ ድርሻችንን መወጣት አለብን።

ካሸነፉ #10 ሚሊዮን ብር ያገኛሉ።

9355 ላይ BIW08 ን በመላክ መምረጥ ይቻላል።**

*🗓 ድምጽ መስጠቱ  እስከ ሐሙስ
ታህሳስ 17 ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!
*
@TnshuaBetechrstian

2 months, 3 weeks ago

እህት ወንድሞቻችሁን Add አድርጉ?

3 months ago
ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን
3 months, 1 week ago

የእናንተ ባል የትኛውይነት ነው?

+++

10 ዓይነት ባሎች አሉ፤ ከእነዚህ ውስጥ ወንዶች እኔ ምን ዓይነት ባል ነኝ ብላችሁ ታስባላችሁ? ሚስቶችስ የእናንተ ባል የትኛው ዓይነት ነው?

1. ላጤ ባል
ይህ አይነቱ ባል ሁሉንም ነገር የሚያደርገው ሚስቱን ሳያማክር በራሱ ወስኖ ነው። ከሚስቱ ይልቅ ከጓደኞቹ ጋር ብዙ ጊዜ ያሳልፋል። ለትዳር ሕይወት ግዴለሽ ነው።

2. መርዛማ ባል
ሁል ጊዜ እንደ አሲድ የሚፈላ፥ ሁል ጊዜም ቁጡና ጠበኛ ነው። ለሚስቱ ስሜት የማይጨነቅ፣ ሁሌም የበላይ ነኝ የሚል እና በጣም አደገኛ ሰው ነው።

3. ጨቋኝ ባል
እንደ ንጉስ መታየት ይፈልጋል ነገር ግን ሚስቱን እንደ ባሪያ ያያታል። ሚስቱ ወግ፣ ባሕልና ስርዓቱን አክብራ ተገዝታ እንድትኖር ይፈልጋል፣ እርሱ ግን በዚያው ሕግ መገዛት አይፈልግም። ከሚስቱ አንቱታን እና ሁሌም ሙገሳን ብቻ የሚፈልግ ባል ነው።

4. የሁሉም ባል
ይህ ሰው የጋራ ባል ነው። ከሚስቱ ውጭ ላሉ ሴቶች ሁሉ የሚያስብ፣ ከሚስቱ ይልቅ የሴት ጓደኞችን የሚያበዛና የሚያስብላቸው አይነት ሰው ነው። ለሴት ጓደኞቹ ገንዘብም ሆነ ጊዜ መስጠት ይወዳል እና ከወንዶች ይልቅ ብዙ የሴት ጓደኞች ያሉት ነው።

5. ደረቅ ባል
በራሱ ስሜት ብቻ የሚመራ፣ ሁሉንም ነገር እንደስራ የሚቆጥር፥ ቀልድ የማያውቅ፥ የሚስቱን ስሜት የማይጠብቅ እና ግንኙነቱን አሰልቺ የሚያደርግ ባል ነው። እንዲህ አይነቱ ባል አንዳንድ ጊዜ ምሁራዊ በሆኑ ጉዳዮች ብቻ የተጠመደና ሚስቱ ጋር ልክ እንደስራ ባልደረባዎቹ እንድትሆንለት የሚፈልግ አይነት ይሆናል።

6. ፓናዶል ባል
ሚስቱን ችግር ሲገጥመው ብቻ እንደሕመም ማስታገሻ የሚፈልጋት፥ ለእርሷ ያለው መውደድ የሚገለጠው ከእሷ የሆነ ነገር ሲፈልግ ብቻ ነው። ይህ ባል ብልጣብልጥ በመሆኑ የሚስቱን ድክመቶች አሳምሮ ያውቃል፣ ስለዚህ ከእርሷ ጋር ሰላም መሆን ሲፈልግ ብቻ ይህን ካርድ መዞ የሚጫወት ነው።

7. ጥገኛ ባል
ሰነፍ እና ለገንዘብ ሲል ብቻ ሚስቱን የሚወድ ነው። የሚስቱን ገንዘብ ግን የሚጠቀምበት መልሶ ሌሎች ሴቶችን ለማጥመድ ነው። ምንም ተነሳሽነት የሌለውና ሚስቱን ዘወር ብሎ የማያያት ነው። ቤቱ ውስጥም ቢሆን ምንም አይነት ኃላፊነት አይወስድም።

8. ጨቅላ ባል
ልጅነቱን ገና ያልጨረሰ፣ ውሳኔ ለመወሰን የእናቱን ወይም የሌሎች ዘመዶቹን እገዛ የሚፈልግ፣ በራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ነው። ሚስቱ ጋር የሀሳብ ልዩነት ከተፈጠረ ሮጦ ዘመዶቹ ጋር የሚሄድና ሚስቱን ከዘመዶች ጋር እያወዳደረ መፍትሔ ለመፈለግ የሚሞክር ነው። ይህ አይነቱ ባል ፍቅር የሚሰጥ (Romantic)፣ መዝናናት የሚወድ (Adventurous) ወይም በጣም የተጋነነ ሕልም ያለውና የማይተገብር (Ambitious) ሊሆን ይችላል። ይህ ባል ገና ባለማደጉ በምንም ነገር ላይ ኃላፊነት የጎደለው እና ችግር ከተፈጠረ ደግሞ በመሸሽ ነው የሚያምነው።

9. እንግዳ ባል
ሁልጊዜ ቤት ውስጥ ስለማይገኝም ልክ እንደ እንግዳ ነው የሚመጣው። ለቤተሰብ ሁሉንም አይነት ቁሳዊ ነገሮች የሚያቀርብ ሲሆን ለእነርሱ የሚሰጠው ግን ምንም አይነት ጊዜ የለውም። ይህ ባል በሥራ ሱስ የተጠመደ (Workholic) በመሆኑ በአካልም ሆነ በስሜት ከቤቱ ከመራቁ የተነሳ ትዳሩን በሥራ የተካ ሰው ነው።

10. ትጉህ ባል
ተንከባካቢ እና አፍቃሪ ሲሆን ቁሳዊ እና ስሜታዊ ፍላጎቶችን አመጣጥኖ ማቅረብ የሚችል ነው። ይህ ባል ለቤተሰቡ በቂ ጊዜ የሚሰጥ፣ በነገሮች ላይ ኃላፊነት የሚወስድ፣ የሚስቱን ደስታ የሚያስቀድም፣ ቤቱን በመተማመን የሚመራና ሰላም እና የደስታ የሁሉም ነገር ቁልፍ መሆኑ የገባው ባል የሚወስን ነው።
ትጉ ባል ለመሆን ጣሩ ሁኑም?
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
?????????
@TnshuaBetechrstian

6 months, 2 weeks ago

# ይድረስ_ለሴቶች_እህቶቼ_አንብቡት
ወንዶችም አንብባችሁ ለእህቶቻችን ሼር ሼር ሼር በማድረግ አጋሩ
አዲስ ተች ስልክ የገዛችውን ልጅ አባቷ ሲያያት . . . . . . . ››
አባት ፡ “”ስልኩን ስትገዢ በመጀመሪያ ያደረግሽው ምንድነው ? “” ብሎ
ጠየቃት፡፡
ልጅ ፡ “”በመጀመሪያ ያደረኩት . . . ስክሪኑ እንዳይጫጫር መከላከያ ስቲከር
ለጠፍኩበት . . . “”
አባት ፡ “” እንደዚ እንድታደርጊው የገፋፋሽ ሰው እለ ?””
ልጅ ፡ “” የለም ! ! ! “”
አባት ፡ “”ያመረቱትን እንደ ማንቋሸሽ አይሆንም ግን . . .””
ልጅ ፡ “”ኧረ አባዬ ! እንደውም የሚመክሩን እንድንለጥፍበት ነው ! ””
አባት ፡ “” የሸፈንሽው ግን ርካሽ ስለሆነ ወይም ስለሚያስጠላ ነው ??? “”
ልጅ ፡ “”” በነገራችን ላይ የሸፈንኩት . . . እንዳይበላሽብኝ እና ብዙ ግዜ
እንዲያገለግለኝ ስለምፈልግ ነው ! “”
አባት ፡ “”” ስትሸፍኝው . . . ውበቱን አልቀነሰውም “”
ልጅ ፡ “”” እንደውም በጣም አምሮበታል በዛ ላይ እንዳይበላሽ
ይከላከልልኛል “”
አባት ፡ በአባትነት ዓይን እያያት “”” አንድ ጥያቄ ብጠይቅሽስ. . .
ከስልክሽ የሚበልጠውን ገላሽን እንድትሸፍኝው . . . እሺ ትይኛለሽ ወይ ??? ``
ሁሌም አባታችን እግዚአብሔር ይጠይቀናል በሰው ላይ አድሮ . . . . ብቻ በብዙ
ነገር ራሳችንን እንድንሸፍን ይጠይቀናል !
☞የምናስተውል ካለን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል"፤
፨ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን
ይሸፍኑ (1 ኛ ጢሞ 2፥9)
፠ በሚሞት ስጋችሁ ሐጢያት አይንገስ
ብልቶቻችሁን የፅድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ (ሮሜ
6፥12-14)
፠ ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው ካልተቻለ ዝሙትን ለመከላከል በአንድ
ይፅና ከዚህ ውጭ ጉዞ ወደ እሳት ነው (1ኛ ቆሮ 7፥1)
፠ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱ
ያፈርሰዋል ቤተ መቅደሱም እናንተው ናችሁ (1ኛ ቆሮ 3፥17)
፠ የወንድ ልብስ የለበሰች ሴት በአምላክ ዘንድ የተጠላች ናት (ዘዳ 22፥5; ዘፀ
39፥28)
፠ ፀጉሯን ሳትሸፍን የምትፀልይ ሴት እራሷን ያዋረደች ናት(1ኛ ቆሮ 11፥5)
እንድናስተውል እና እንደ እግዚአብሔር ቃል እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን
አሜን (ለምታውቁት ሰው እና መንፈሳዊ ግሩፕ ትልኩ ዘንድ በእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም አበክሬ እጠይቃችኋለሁ አደራ)
@TnshuaBetechrstian

7 months, 2 weeks ago

የፍቅር የበላይነት!

ላላገባችሁ . . .

ለእናንተ እውነተኛ ፍቅር ሳይኖረው ሁሉን ነገር ከሚያሟላችሁ ሰው ጋር ከመሆን ይልቅ፣ ለእናንተ እውነተኛ ፍቅር ኖሮት ሁሉን ነገር ማሟላት የማይችል ሰው አይሻልም ብላችሁ ነው!!!???
@TnshuaBetecrstian

8 months, 2 weeks ago

የእናት አስፈላጊነት

በልጆች አስተዳደግ ውስጥ እናት ያላት ድርሻ ጡት ከማጥባት ያለፈ ነው፡፡ እናት በልጆች ሕይወት ውስጥ በማትገኝበት ወይም እያለች ያላት ተሳትፎ ግን አናሳ በሚሆንበት ጊዜ በልጆቹ የስነ-ልቦናና ማሕበራዊ እድገት ላይ ትልቅ ቀውስ ይፈጥራል፡፡

ከእናት ውጪ ያደገች አንዲት ሴት ከሁኔታው ተገቢውን ፈውስ ካላገኘች ለበርካታ ቀውሶች ልትጋለጥ ትችላለች፡፡ ከእነዚህ ቀውሶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

ድፍረትን ማጣት፣ ሰዎችን ማመን አለመቻል፣ የቀይ መስመርን (personal boundary) ለማስመር ያለመቻልና የሁሉ አስደሳች የመሆን ዝንባሌ፣ በራስ ላይ ያለ የተዛባ እይታ፣ ራስን ከሰዎች ማግለል፣ የስሜት ስስነትና በማይሆን ፍቅረኛ ላይ መውደቅ፡፡

ከእናት ውጪ ያደገ ወንድም ጉዳዩ ይለከተዋል፡፡ የእናት መገኘትና አለመገኘት በወንድ ልጅም ላይ እስከ መጨረሻው የሚዘልቅ አሉታዊ ተጽእኖ አለው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ወንድ ልጅ የመጀመሪያውን አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ተጽእኖ የሚቀበለው ከእናቱ ነው፡፡ 

አንድ ወንድ ወደዚህች አለም ከተቀላቀለ በኋላ በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያውቃት ሴት እናቱን ነው፡፡ ስለሆነም ከእናቱ ጋር ያለው የልጅነት ትውስታና ግንኙነት ወደፊት በሴቶች ላይ በሚኖረው አመለካከት ላይ ዘርን ጥሎ ማለፉ አይቀርም፡፡

በእናቱ አማካኝነት የደረሰበትን የመጣል፣ ችላ የመባልና የመሳሰሉት ባህሪዎችን ወደፊት በሚኖረው ግንኙነት ውስጥ የመፍራትን ዝንባሌ ሊያዳብር ይችላል፡፡ በእናቱ “በርታ” ተብሎ ያደገ ልጅና ያንን ሳያገኝ ወይም ተቃራኒን ሰምቶ ያደገ ወንድ ይህ ልምምዱ ወደፊት ከሴቶች ጋር በሚኖረው ግንኙነት ላይ የሚጫወተው ሚና ቀላል አይሆንም፡፡

አንዳንድ የእናትን ጣእም ሳያገኙ ያደጉ ወንዶች ፍቅረኛ ወደመያዝ ደረጃ ሲደርሱና በዚያ መስክ ሲሰማሩ ሳያውቁት ያንን በልጅነት ያጡትን የእናትነት ምስልና እንክብካቤ ፍለጋ ከእድሜያቸው በብዙ ወደሚበልጡ ሴቶች የመሳብ ዝንባሌ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ሆኖም፣ የዚህን ዝንባሌና ተጽእኖ የሚያዩት በትዳር ውስጥ ከቆዩና የእድሜ ልዩነቱን በግላጭ ማየት ሲጀምሩ ነው፡፡

ከላይ በጥቂቱ ለመጠቃቀስ የሞከርናቸው ሃሳቦች የአባትንና የእናትን ተገቢ የሆነ ግንኙነት፣ ፍቅር፣ እንክብካቤና ሚና ሳያገኙ ያደጉ ልጆች ሊጋፈጧቸው የሚችሉትን ሞጋች ሁኔታዎች አመልካች ናቸው፡፡ እነዚህ ልጆች አድገው ወደ ወጣትነት፣ አልፎም ወደ አዋቂነት ሲሻገሩ ከተቃራኒ ጾታ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በምን አይነት ቅድመ-ምልከታ እንደሚቀርቡት የሚወስንላቸው ይህ በልጅነታቸው አመታት ቀምሰው ወይም ሳይቀምሱ ያደጉት የቤተሰብ ጣእም ነው፡፡
@TnshuaBetechrstian

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago