በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

Description
አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month, 1 week ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 1 week ago

1 month ago
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፫፻፲፫

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፫፻፲፫
"ርሱም በሥጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋራ ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት" (ዕብ. ፭፣፯)።

ሰው በሆነበት ወራት ጸሎቱን እንደ ላም፣ ስኢልን እንደ በግ አድርጎ ምእመናንን ከሞት ወደሚያድንለት ወደ አባቱ አቀረበ። እግዚአብሔርም እውነተኛ ልመናውን ሰማው። ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛ አዳም ሆኖ በሥጋው ወራት ከእንባ ጋራ ጸሎትንና ምልጃን አቅርቧል። ምልጃውም እንደተሰማለት ተገልጿል። ቀድሞ ነቢያት ምልጃን ቢያቀርቡም እነርሱም በጥንተ አብሶ ተይዘው ይኖሩ ስለነበረ ምልጃቸው ነፍሳዊ ድኅነትን ማሰጠት አልቻለም ነበር። ክርስቶስ ግን ንጹሐ ባሕርይ ስለሆነና ጥንተ አብሶ ስለሌበት ምልጃው ተሰማለት ተብሏል። ምልጃውን የሰማለት ሰሚው ማን ነው? ከተባለ ግን ራሱ ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መሆኑን ልብ ማድረግ ይገባል። ጌታን የማዳን ሥራውን በመልእልተ መስቀል ከፈጸመ በኋላ የምልጃ ሥራ አለበት አንለውም።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፫፻፲፬ ይቀጥላል

1 month ago
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፫፻፲፪

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፫፻፲፪
"አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘለዓለም ካህን ነህ ይላል" (ዕብ. ፭፣፮)።

እንደ መልከ ጼዴቅ ባለ ሹመት ተሹመህ የምእመናን አገልጋይ ነህ አለው። መልከ ጼዴቅ መሥዋዕት ሲያቀርብ በስንዴና በወይን ነበር። አብርሃም ነገሥተ ኮሎዶጎሞርን አሸንፎ ሲመለስ ከዐሥር አንድ ዐሥራት አውጥቶለታል። መልከ ጼዴቅ በብሉይ ኪዳን በዚህ ጊዜ ሞተ ተብሎ አልተጻፈም። ጌታ ሞትን ድል አድርጎ የተነሣ ዘለዓለማዊ አምላክ ነው። ለጌታ ክህነት የመልከጼዴቅ ክህነት ምሳሌው ነው። መልከ ጼዴቅ ከካም ተወልዶ ካህን ሆኗል። የሐዲስ ኪዳን ካህናትም ያለ ዘር ምርጫ ብቁ ሆነው ሲገኙ ይሾማሉ።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፫፻፲፫ ይቀጥላል

1 month ago
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፫፻፲፩

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፫፻፲፩
"ከኀጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው" (ዕብ. ፬፣፲፭)።

ኃጢአት በሦስት መንገድ ይሠራል። ይኽውም በነቢብ (በመናገር)፣ በኀልዮ (በማሰብ)፣ በገቢር (በተግባር) ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ምንም ኃጢአትን አልሠራም ማለታችን ንጹሐ ባሕርይ ስለሆነ በኀልዮም፣ በነቢብም፣ በገቢርም ጻድቅ ንጹሕ ነው ማለታችን ነው። ከኃጢአት በቀር ግን እንደ እኛ የተፈተነ ነው ማለቱ መራቡን፣ መጠማቱን፣ በሥጋ መድከሙን (ወደክመ በሐዊረ ፍኖት እንዲል)፣ በጠቅላላው መከራ መቀበሉን ያስረዳል።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፫፻፲፪ ይቀጥላል

1 month, 1 week ago
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፮

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፮
"ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብር ይሁን አሜን" (ሮሜ ፲፮፣፳፯)።

እግዚአብሔር ብቻውን ጥበብ ያለው ነው። ፍጡራን ጥበብ ቢኖራቸው ፈጣሪ በጸጋ የሰጣቸው ነው። አምላክ ግን ብቻውን ጥበበኛ ነው። "ብቻውን" የሚለው አገላለጽ ከፍጡራን ሲለየው ነው እንጂ አብን ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ፣ ወልድን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ፣ መንፈስቅዱስን ከአብና ከወልድ ሲለያቸው አይደለም። አብ ብቻውን ጥበብ ያለው ይባላል። ይህን ጊዜ "ብቻውን" የሚለው ቃል ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ ለማለት ሳይሆን ከፍጡራን ተለይቶ ለማለት ነው። ሦስቱ አካላት በጥበብ፣ በዕውቀት፣ በፈቃድ በጠቅላላው በአምላካዊ ሥራ አንድ ናቸውና።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፵፯ ይቀጥላል

1 month, 1 week ago
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፭

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፭
"የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል" (ሮሜ ፲፮፣፲፮)።

ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ትርጉም አለው። አንደኛው አምልኮ የምንፈጽምበት፣ የምንጠመቅበት፣ የምንቆርብበት ቤት ሕንፃው ቤተ ክርስቲያን ይባላል። ሁለተኛው እያንዳንዱ ምእመን ቤተ ክርስቲያን ይባላል። ይኽውም ቤተ ክርስቶስ (የክርስቶስ ወገን) ማለት ነው። ሰው በክርስቶስ ሲጠመቅ የክርስቶስ ወገን ይሆናል። ሦስተኛው የምእመናን አንድነት ቤተ ክርስቲያን ይባላል። የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል የሚለው አገላለጽ በክርስቶስ አምነው፣ በክርስቶስ ስም ተጠምቀው የሚኖሩ ምእመናን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል ማለቱ ነው እንጂ ሕንፃው ሰላምታ ያቀርብላችኋል ማለቱ አይደለም።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፵፮ ይቀጥላል

1 month, 1 week ago
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፬

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፬
"በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን" (ሮሜ ፲፬፣፰)።

ጻድቃን በዚህች ምድር ሲኖሩም ለእግዚአብሔር ኖሩ። ለእግዚአብሔር መኖር ማለትም ሕግጋቱን በመጠበቅ ኖሩ ማለት ነው። ሲሞቱም ለእግዚአብሔር ሞቱ። ለእግዚአብሔር መሞት ማለትም ሕጉን ትእዛዙን እየፈጸሙና ለዓለም ሁሉ እየተናገሩ ሰማዕት ሆኑ ማለት ነው። የቅዱሳን የኑሮ መመሪያቸው ሕገ እግዚአብሔር ነው። ለማንኛውም ሰው ባለቤት አለው። ሰው የራሱ አይደለም። ከአባት ዘር ከእናት ደም ከፍሎ ወደዚህ ምድር እንዲመጣ ያደረገው እግዚአብሔር ነው። ሁላችንም የፈጣሪ ገንዘቦች በመሆናችን ቅዱስ ጳውሎስ "የጌታ ነን" ብሎ ተናገረ።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፵፭ ይቀጥላል

1 month, 2 weeks ago
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፪

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፪
"አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ባንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስኽ ዘንድ አክብረኝ" (ዮሐ. ፲፯፣፭)።

የኢየሱስ ክርስቶስን ቀዳማዊነት ከሚያሳውቁን ኃይለ ቃሎች አንዱ ይህ ነው። ብዙዎች ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ብቻ (ዕሩቅ ብእሲ) ስለሚመስላቸው ህልውናው የሚጀምረው ድንግል ማርያም ከጸነሰችው በኋላ ይመስላቸዋል። ድንግል ማርያም ጸንሳ የወለደችው ቅድመ ዓለም የነበረ እርሷንም አባቶቿንም የፈጠረውን ወልደ እግዚአብሔርን ነው። ለዚያ ነው ሊቁ አፈ በረከት ማር ኤፍሬም ሶርያዊ "ድንግል ወለደቶ ለገባሪሃ ወውእቱኒ ፈጠረ ወላዲቶ" ያለው። ትርጉሙ ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ ማለት ነው።

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፻፺፱ ላይና ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻ ላይ እንደተገለጸው ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ አብን አከበረው ተብሎ ነበር። በዚህኛው ክፍል ደግሞ ወልድ አብን አክብረኝ እያለው ነው። ይኽውም ዓለም ያምንብኝ ዘንድ ግለጠኝ ማለቱ ነው። ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ምስጉን ሆኖ የነበረና የኖረ ፍጹም አምላክ ነው። ከድንግል ማርያም በመወለዱም ፍጹም ሰው እንለዋለን። ስለዚህም አንዱን ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ እንለዋለን።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፫ ይቀጥላል

1 month, 2 weeks ago
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፩

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፩
"እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርኹኽ" (ዮሐ. ፲፯፣፬)።

እሠራው እፈጽመው ዘንድ የሰጠኽኝን ሥራ ፈጽሜ በአግብዖተ ግብር (ዳግማይ ትንሣኤ) ገለጽኩህ ማለቱ ነው። የሰጠኸኝን ሥራ ሲል ሥራውን የሰጠው አብ ብቻ ይመስላል። ነገር ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአምላካዊ ሥራ አንድ ስለሆኑ አብ ተለይቶ ቢጠቀስ እንኳ የወልድም የመንፈስ ቅዱስም እንደሆነ ልብ ማድረግ ይገባል።

ለመሆኑ ወልድ ያደርገው ዘንድ የተሰጠው ሥራ ምንድን ነው? ብለን ብንጠይቅ አካላዊ ግብሩ መወለድ የሆነ ወልድ ጥንተ ግብሩን በሚገልጽ ሁኔታ ከድንግል ማርያም ተወለደ። ሰው ሆኖ የተወለደውም ለአዳም ቤዛ ሆኖ ተሰቅሎ ያድነው ዘንድ ነው። የተሰጠው ሥራ የተባለው ይህ ነው። ሥራውን ማን ሰጠው ከተባለ ግን ይህን ሥራ ለመፈጸም በአብ ፈቃድ በራሱም ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ መጥቷል። ይህ የሦስቱም የአንድነት ሥራ ነው። ለአዳም ቤዛ መሆንና በተዋሐደው ሥጋ መከራ መቀበል ግን በተለየ አካሉ የወልድ ነው።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፪ ይቀጥላል

1 month, 2 weeks ago
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻
"እውነተኛ አምላክ ብቻ የኾንኽ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት" (ዮሐ. ፲፯፣፫)።

አብ እውነተኛ አምላክ ነው። ወልድም እውነተኛ አምላክ ነው። መንፈስ ቅዱስም እውነተኛ አምላክ ነው። ሦስቱም አካላት አምላክ አምላክ አምላክ ተብለው ቢጠሩም ሦስት አማልክት ናቸው ግን አንልም። እርስ በእርስ በከዊን ይገናዘባሉና አንድ አምላክ ይባላሉ። ወልድ አምላክ እንደሆነ ሮሜ ፱፣፭ ላይ ተገልጿል። ይህ ከሆነ አብ "እውነተኛ አምላክ ብቻ" ተብሎ "ብቻ" የተባለ ለምንድን ነው? የሚለውን መረዳት ተገቢ ነው። "ብቻ" ያለው ከፍጡራን ሲለየው ነው እንጂ ከአካላዊ ቃሉ ከወልድና ከአካላዊ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው አይደለም። እንዳልለያቸው ምስክሩ ራሱ ዮሐንስ ሦስቱንም አካላት እግዚአብሔር ብሎ በመግለጹ ይታወቃል (ዮሐ. ፩፣፩-፫)።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፩ ይቀጥላል

1 month, 3 weeks ago
[#እንኳን](?q=%23%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8A%B3%E1%8A%95) [#አደረሳችሁ](?q=%23%E1%8A%A0%E1%8B%B0%E1%88%A8%E1%88%B3%E1%89%BD%E1%88%81)

#እንኳን #አደረሳችሁ

ወልድኪ መድኃኔዓለም ሥጋ ዚኣኪ ዘለብሰ።
በዐውደ ጲላጦስ ተወቅሰ (፪) መድኃኔዓላም።

እኛን ለማዳን ስለእኛ በዕለተ ዓርብ መጋቢት ፳፯ ቀን የተሰቀለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስሙ ዛሬም ዘወትርም የተመሰገነ ይሁን።

እንኳን አደረሳችሁ

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month, 1 week ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 1 week ago