በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

Description
አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion ? @Share_Home

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 6 months, 3 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 8 months, 3 weeks ago

1 month ago

▶️፲፪. ኩፋ.፯÷፴፭ "የተቀደሱትን ቀናት የረከሱ የረከሱትንም ቀናት ለቅድስና ያደርጋሉ" ሲል የቀን መርከስና መቀደስ ሲል እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ማለት መከበር ያለባትን ዕለት ሳያከብሯት ይቀራሉ። የማትከበረዋን ዕለት ደግሞ ያከብሯታል ማለት ነው። እግዚአብሔር እንዲያከብሩት ያዘዛቸውን ዕለት በሥራ ያሳልፉና እንዲያከብሩ ያላዘዛቸውን ደግሞ ያከብሩ ስለነበረ የተነገረ ቃል ነው።

▶️፲፫. ኩፋ.፰÷፩ ኖኅ በሉባር ተራራ ወይንን እደተከለ ተጽፏል። ከየት የተገኘ ወይን ነው? በንፍር ውሃ ያልጠፋ ፍጥረት (ዕፅ) ነበረ ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ወይን አልጠፋም ነበረ። በማየ አይኅ ጠፉ የተባሉት ደማውያን ፍጥረታት ናቸው እንጂ ዕፀዋት አልጠፉም ነበረ። ኖኅ በመርከቡ እንዳተረፋቸው የተጻፉም ደማውያን ፍጥረታት እንጂ ዕፀዋት አይደሉም።

▶️፲፬. ኩፋ.፰÷፲፱ "አርበኛውም ናፊልን ገደለው። ናፊልም ኢዮልዮንን ገደለው። ኢዮልዮንም የሰውን ልጅ ገደለው÷ ሰውም ባልንጀራውን ገደለው" ይላል። ከዚህ ላይ ሰው የተባለው ማነው? ሌሎችስ ሰው አይደሉም?

✔️መልስ፦ ሰው የሚለው መጠነኛውን ነው። ቁመታቸው ሦስት ሺ፣ ሁለት ሺ የሚደርሱትን ምንም እንኳ ሰዎች ቢሆኑ ናፌል፣ ኤልዮ እያለ ጠርቷቸዋል። ቁመቱ የተመጠነውና ከቀድሞ ጀምሮ እንደነበሩት ሰዎች የነበረው ሰው ተብሏል። ይኸውም ከረጃጅሞቹ ለመለየት ነው።

▶️፲፭. ኩፋ.፰÷፳፮-፳፯ "ማንኛውንም አውሬና እንስሳ በምድር ላይ የሚበረውንም ባረዳችሁ ጊዜ በዘመናችሁ ሁሉ ከማንኛውም ደም ሁሉ በእናንተ ላይ አይታይ። በምድር ላይ የሚፈሰውን ደም በመቅበር ስለ ሰውነታችሁ ምጽዋት
መጽውቱ" ይላል። በእርድ ጊዜ ደም መንካትም ያረክስ ነበረ? በአዲስ ኪዳንስ የግድ የታረደው እንስሳ ደም መቀበር አለበት?

✔️መልስ፦ በእርድ ጊዜ ደም መንካት ያረክስ እንደነበረ የሚናገር ጽሑፍ አላገኘሁም። ነገር ግን እንስሳትን አርደን ስንበላ ደማቸውን መቅበር እንደሚገባ ከዚሁ ተገልጧል። ምክንያቱ ርኅራኄ ነው። ደሙ ፈሶ እንዳልነበረ ሆኖ ሲያዩት ያሳዝናልና። በሐዲስም ደሙ እንዳያስጸይፍ ቢቀበር መልካም ነው።

▶️፲፮. ኩፋ.፱÷፲፩ ሁለተኛውም ዕጣ ወደ ግዮን ማዶ በገነት ቀኝ በሰሜን በኩል ለካም ወጣ ወደ ሰሜንም ይደርሳል። ከዚህ ላይ ገነት በአቅጣጫ አንጻር የቀረበችው እንዴት ነው? ከዚች ምድር ጋር ትገናኛለች እንዴ? እንዲያውም በእግር ይደረስ ነበረ የሚሉም እሰማለሁ። ቢያብራሩልኝ። ገነት ኢትዮጵያ ውስጥ ጣና ውስጥ ወዘተ እያሉም የሚጽፉ አሉ። እውነት ነው?

✔️መልስ፦ አወ ገነት የዚህች መሬት አንድ አካል ናት። እግዚአብሔር ሠውሯት ማየት አልችል ብለን እንጂ የምንኖርባት ምድር አካል ናት። ገነት ጣና ውስጥ ናት፣ ኢትዮጵያ ናት ወዘተ የሚለው አባባል ግን መሠረት የለውም። ከላይ እንደገለጥኩት እግዚአብሔር ሠውሯት ስለሚኖር ከዚህ ናት ከዚህ አይደለችም ማለት አንችልም።

▶️፲፯. ኩፋ.፱÷፲፮ "ሴምም በልጆቹ መካከል አካፈለ። መጀመሪያውም እጣ ለኤላምና ለልጆቹ እስከ ሕንደኬ ምድር ሁሉ ምሥራቅ እስኪቀርብ ድረስ ወደ ጤግርስ ወንዝ ምሥራቅ ወጣ ኤርትራም በእጁ ነበረ" ይላል። ኢትዮጵያ የካም እጣ አይደለችም እንዴ?

✔️መልስ፦ ኢትዮጵያ የካም እጣ እንደሆነች ይነገራል። ከዚህ ላይ ለይቶ ኤርትራን የሴም እጣ ብሏታል። ስለዚህ የካም እጣ የተባለችው ኢትዮጵያ ኤርትራን ሳትጨምር ነው ማለት ነው።

▶️፲፰. በኩፋ.፲÷፬ "አንተም በሕይወት ያሉ የእነዚህ ረቂቃን አጋንንት አባቶቻቸው ትጉሃን ያደረጉትን ታውቃለህ" ሲል አጋንንት አባት አላቸውን? ማለቴ ይዋለዳሉ እንዴ? በዚህ አገባብ አባቶቻቸው ትጉሃን የተባሉት እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ አጋንንት ያላቸው በኋላ ሥራቸው ምክንያት ደቂቀ ሴትን ነው። እንጂ የረቂቃኑ አጋንንትስ እናት አባት ልጅ የላቸውም። ትጉሃን የተባሉም ራሳቸው ደቂቀ ሴት ናቸው። በቀድሞ ሥራቸው እንደመላእክት ተግተው ያመሰግኑ ነበርና።

▶️፲፱. ኩፋ.፲÷፭-፮ የአጋንንትም አለቃ መስቴማ መጥቶ አቤቱ ፈጣሪዬ ከእነርሱ በፊት ጥቂት አስቀርልኝ ቃሌንም ይስሙ። እኔ የማዝዛቸውንም ያድርጉ። ከእነርሱ ካልቀሩልኝ በሰው ልጆች ላይ የፍቃዴን ሥልጣን ማድረግ አልችልምና። የሰው ልጆች ክፋታቸው ብዙ ስለሆነ ከፍርዴ አስቀድሞ እነርሱ ለማጥፋትና ለማሳት ናቸውና በፊቱ ዐሥረኛው ነገድ ይቅሩ። ዘጠኙን ነገድ ግን ወደ ፍርድ ቦታው ያውርዷቸው" ይላል። ከዚህ ላይ የማን ፍቃድ ነው የተሳካለት? ለማለት የተፈለገው ጭብጥ ነገር አልገባኝም? መቸም አወ አስታቸው ሰዎች ያምልኩህ እኔን ትተው አይልም እግዚአብሔር።

✔️መልስ፦ ይህን የተናገረው ረቂቁ ሰይጣን ነው። ከአሥሩ ነገድ አንዱ ነገድ በዚህ ምድር ይኑርልኝ ብሏል። አንዱ ነገድ የተባለው ከደቂቀ ሴትና ከደቂቀ ቃየል ተደቅለው ክፉ ከሠሩት ሰዎች ከአሥሩ አንዱ እጅ ማለት ናቸው። እነዚህን ሰይጣን ተዋርሷቸዋልና ይትረፉልኝ ብሏል። አሁን ሰይጣን በእግዚአብሔር ፊት ባለሟልነትን አግኝቶ ለምኖ አይደለም። እግዚአብሔር የሰይጣንን ሐሳብ አውቆ እና እርሱ ራሱ ባወቀ አንዱን ነገድ አስተርፎታል እንጂ።

▶️፳. ኩፋ.፲÷፴፱-፵ "አብራምም በአምስተኛው ሱባዔ በአንደኛው ዓመት የበሬ እቃ ለሚሠሩት ሰዎች እንጨት መጥረብን አስተማረ። በምድርም ላይ የበሬ ዕቃ ሠሩ" ይላል። መጀመሪያ በሬ ጠምዶ ማረስ በአብርሃም ነው የተጀመረው ማለት ይቻላል?

✔️መልስ፦ አወ

▶️፳፩. "ገነትም ከከበሩ የከበረች የእግዚአብሔርም ማደሪያ እንደሆነች አውቋልና ይመስገን አለ። ደብረ ሲና በምድረ በዳ መካከል ናት ደብረ ጽዮንም በምድር መካከል ናት። እነዚህ ሦስቱ ሁሉ አንዱ በአንዱ አንጻር ለምስጋና ተፈጠሩ" ይላል። እዚህ ላይ ደብረ ሲናና ደብረ ጽዮን ያላቸው አሁን እኛ የምኖርባት መሬት ላይ ያሉ ናቸው?

መልስ፦ አወ። ደብረ ሲናም እግዚአብሔር ለሙሴ የተለጠለት ቦታ ነው። ደብረ ጽዮን ያለውም ጌታ የተሰቀለበት ቀራንዮ ነው።

▶️፳፪. "እነዚህ እንዲህ የተዘጋጁ ናቸው ወደ ሰማይ ጽላትም ያወጧቸዋል" ይላል። በተደጋጋሚ  በሰማይ ጽላት ተጻፈ ሲል የሰማይ ጽላት ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በሰማይ ጽላት ተጻፈ ማለት በእግዚአብሔር ዘንድ ታወቀ/ታውቋል ማለት ነው። ጉዳዩ ቀድሞ በእግዚአብሔር የባሕርይ ዕውቀት የታወቀ ነው ለማለት ነው።

▶️፳፫. "ከሰው እጅ የአውሬዎችን ደም እመረምራለሁ። የሰውንም ደም ከሰዎች እጅ እመረምራለሁ" ያለው ምን ለማለት ይሆን?

✔️መልስ፦ ደማቸውን ቅበሩት ባትቀብሩት ግን እፈርድባችኋለሁ ማለቱ ነው።

▶️፳፬. "እኛም እንደ ቃሉ አደረግን ፈጽመው የከፉ አጋንንትን መቻያ ባለበት በገሃነም አሥረን አጋዝን። አሥረኛውን ነገድ ግን በሰይጣን ትእዛዝ በምድር መቻያ ይሆኑ ዘንድ አስቀረን። በምድር እንጨቶችም ያድን ዘንድ አጋንንት ከሚያመጡት ደዌ የሚድንበትን ሁሉ ከሚያስቱበት ጋር ለኖኅ ነገርነው" ይላል። እነዚህ የነገሩት እንጨቶች እንዴት አሁንስ እንድንጠቀምባቸው ይፈቀዳል ብዙ ጊዜ እነዚህ መርጌቶች ማስረጃቸው እንጨት አትጠቀሙ ሲባሉ እግዚአብሔር ለአባታችን ኖኅ የሰጠው አይደለምን ይላሉና እንዴት ነው? ቢያስረዱን።

1 month ago

✔️መልስ፦ የሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዓላማ አንድ ነው። ለሰው የድኅነት ዕውቀትን ሊሰጡ፣ ለሰው ሥነ ምግባርን ሃይማኖትን ሊያሳውቁ ነው።

▶️፲፱. ኩፋ.2፥12-13 ዕፀዋት በ3ኛው ቀን ፀሐይ በ4ኛው ቀን ከተፈጠሩ ዕፀዋት እንዴት ያለ photosynthesis ቆዩ?

✔️መልስ፦ photosynthesis የሚባለው ዕፀዋት ከፀሐይ የሚያገኙትን Light energy ወደ chemical energy ቀይረው በኋላ የሚጠቀሙት ነው። ይህንን የተፈጥሮ ሕግን ራሱ የሠራው እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ በከሃሊነቱ ለአንድ ቀን አቆይቷቸዋል። ያለፀሐይ ቀድመው እንዲኖሩ አድርጓቸዋል። ይህ ደግሞ ከሃሊነቱን ያስረዳናል።

▶️፳. ኩፋ.4፥7 ባል እና ሚስት አንድ ልብ እንጂ እንዴት ሆኖ አንድ አካል ይሆናሉ?

✔️መልስ፦ አንድ አካል ይሆናሉ ማለት ሁለቱ በሚያደርጉት ግንኙነት አንድ አካል የሆነ ልጅን ያስገኛሉ ማለት ነው። ሴት ብትወለድ የእርሷ፣ ወንድ ቢወለድ የእርሱ ብለን አንለያያቸውምና። አንድ አካል ይሆናሉ ማለት ሌላው ትርጉሙ በመኝታ አንድ ይሆናሉ ማለት ነው። በሥጋው በደሙ አማካኝነትም ፍጹም የተሳሰሩ አንድ ልብ ይሆናሉ።

▶️፳፩. ኩፋ.4፥9 ላይ አዳም ገነት ሳይገባ ሔዋን ተፈጠረች ይላል። ቀለሜንጦስ 2፥1 ግን አዳም በገነት ተኝቶ ሔዋን ተፈጠረች ይላል አይጋጭም ወይ?

✔️መልስ፦ አዎ አዳም ገነት ሳይገባ ገና በሳምንቱ ሔዋን ከጎኑ ተገኝታለች። በገነት ተኝቶ ሔዋን ተፈጠረች የሚለው ግን ገነት ያለው የአትክልት ቦታን ለመግለጽ ካልሆነ በስተቀር በአርባኛው ቀን የገባባትን ገነት አያመለክትም።

▶️፳፪. ኩፋ.5፥3-4 እንስሳትም ተባረው ከሆነ አሁን ገነት ውስጥ እንስሳ የለም ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ አሁን በገነት ደማዊ ፍጥረት ስለሌለ እንስሳት፣ አራዊትና የመሳሰሉት የለም።

▶️፳፫. ኩፋ.5፥22 ከዘፍጥረት በፊት ምን መጽሐፍ ኖሮ ነው ሄኖክ መጻሕፍትን የተማረ ነበረ የሚል?

✔️መልስ፦ ፊደላት ለሰው ልጅ የተገለጹት በአዳም ሦስተኛ ትውልድ በሄኖስ ጊዜ ነው። ስለዚህ ከዚያ ጀምሮ አሁን ለእኛ ባይደርሱንም መጻሕፍተ አበው ነበሩ እነዚያን ሄኖክ ተማረ ማለት ነው።

▶️፳፬. ኩፋ.5፥28 ላይ ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ 6*49=294 ዓመት ከመላእክት ጋር ኖረ ይላል። ዘፍ.5፥22 ግን ማቱሳላን ከወለደ በኋላ 200 ዓመት ኖረ ይላል አይጋጭም ወይ?

✔️መልስ፦ ዘፍጥረት ላይ ያለው ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ የሚል ሲሆን ኩፋሌ ላይ ያለው ግን ከመላእክት ጋር የኖረውን እድሜ የሚገልጽ ነው። የተለያዩ ጉዳዮች ስለሆኑ አይጋጭም።

▶️፳፭. ኩፋ.5፥34-35 ላይ ከአዳም እስከ ላሜህ 14 ኢዮቤልዩ ሲል ዘፍ.5፥3-25 ስናነብ ከአዳም እስከ ላሜህ 1374 ዓመት (28 ኢዮቤልዩ) ይሆናል አይጋጭም ወይ?

✔️መልስ፦ ኩፋሌ ማለት ዘተከፍለ እምኦሪት (ከኦሪት የተከፈለ) ማለት ነው። ከኦሪት ዘፍጥረት ከፍሎ የሚናገር ከኦሪት የተከፈለ ማለት ነው። እና በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ አምስት ከተገለጹ አባቶች ከእያንዳንዳቸው መቶ መቶ ዓመት ከፍሎ ቀሪውን በኢዮቤልዩ ስለቆጠረው 14 ኢዮቤልዩ አለ እንጂ መደበኛው ኦሪት ዘፍጥረት ላይ ያለው ነው። የኦሪት ዘፍጥረቱ ተከታዩን ልጅ የወለዱበትን እድሜ በቅደም ተከተል 230, 205, 190, 165, 162, 165, 187 ሲል ኩፋሌ ደግሞ ከእያንዳንዱ መቶ መቶ እየቀነሰ በቅደም ተከተል 130, 105, 90, 65, 62, 65, 87 ያደርገዋል።

▶️፳፮. ኩፋ.3፥11 "በመጀመሪያው ሱባዔ ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ" ይላል። ቴዎፍሎስ ዘአንጾኪያ ደግሞ ከምድር በፊት ሰማይ ተፈጠረ ይላል (to autolicus) የትኛው ነው መጀመሪያ የተፈጠረው?

✔️መልስ፦ ቴዎፍሎስ ዘአንጾኪያን አላውቀውም። ነገር ግን ሐሳቡ ከዚህ እንዳቀረባችሁት ከሆነ ያየበትን አንጻር ብናስተውል መልካም ነው። በመጀመሪያው ቀን ሰማይና ምድርን ፈጠረ ማለት ሰባቱን ሰማያትና ምድር የተፈጠረችበት መሬት፣ እሳት፣ ነፋስ፣ ውሃ ተፈጠሩ ማለት ነው። አሁን ያለንባት ምድር አሁን እንደምትታየው ሆና የተገለጠችው በዕለተ ሰኑይ ነው። መገለጫዋን ካየን አዎ ምድር ትዘገያለች። ውሃው በአራት አቅጣጫ ሲወሰን ነው መሬት የታየችው። መገለጫዋን ካላየን ግን እድሜያቸው እኩል መሆኑን እንረዳለን።

▶️፳፯. መጽሐፈ ኩፋሌ መግቢያው ላይ "በዚህ ዓለም በሚመላለሱት ዘመኖች ሁሉ ሰባት ሰባት ተብለው የሚቆጠሩ የዘመኖችን ሥራ ለማወቅ አምልኮቱና ሕጉ የሚነገርባቸውን የዘመኖችን አከፋፈል የሚናገር መጽሐፍ ይህ ነው" ይላል። ሰባት ሰባት ተብለው የሚቆጠሩ የዘመኖችን ሥራ ለማወቅ ያለው ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ዘመን የሚቆጠረው በሱባዔ መሆኑን የሚያመለክት ቃል ነው። ሌላ የተለየ ምሥጢር የለውም።

▶️፳፰. ኩፋ.5÷30 ሄኖክን ወደ ኤዶም ገነት መወሰዱን ይናገርና ቀጥሎ የአዳምንም ልጆች ኃጢአት ሁሉ ይጽፋል ሲል ቢብራራ። ኩፋ.5÷32 ለእግዚአብሔር በምድር አራት በታዎች አሉትና÷ እነዚህም የኤዶም ገነትና ደብረ ዘይት÷ ደብረሲናና ደብረ ጽዮንን ናቸው ብሎ ይጠቅሳል። ከአምስቱ ዓለማት መሬት እነዚህ ብቻ እንዴት እንደተለዩ ቢብራራ። የኤልዳና የኤዶም ገነት ልዩነት?

✔️መልስ፦ ሄኖክ የሰውን ኃጢአት የሚጽፍ ሆኖ አይደለም። ለሰው ኃጢአት የሚሆኑ ሥራዎችንና ጽድቅ የሚሆኑ ሥራዎችን ለይቶ እነዚህ እነዚህ እያለ ስለሚያሳውቅ ይጽፋል ተብሏል። ኤዶም ገነት የምትባለዋ አዳም በአርባኛው ቀን የገባባትና ሲበድል ግን ከእርሷ የወጣባት ቦታ ናት። ኤልዳ ቀራንዮ (የመሬት እንብርት) ናት። ደብረ ጽዮን ኤልዳ ወይም ቀራንዮ ናት። እነዚህ ደግሞ ከአምስቱ ዓለማተ መሬት በአንዷ በምንኖርባት ምድር የሚገኙ ናቸው እንጂ እንደብሔረ ሕያዋን፣ ብሔረ ብፁዓን፣ ገነትና፣ ሲዖል ለብቻቸው የሚቆጠሩ አይደሉም።

▶️፳፱. ኩፋ.5፥30 ላይ "ከሰው ልጆች መካከል ተወሰደ። ለጌትነትና ለክብር ወደ ኤዶም ገነት ወሰድነው እነሆ በዚያ የዘላለም ቅጣትንና ቁርጥ ፍርድን የአዳምን ልጆች ኃጢአት ሁሉ እርሱ በዚያ ይጽፋል" ይላል። ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ የተወሠደው ወደ ገነት ወይስ ወደ ብሔረ ሕያዋን?

✔️መልስ፦ ሄኖክ የሄደው ወደብሔረ ሕያዋን ነው። ነገር ግን ምቹ ቦታዎችን ሁሉ ገነት ስለሚላቸው ከዚህ ገነት ያለው ብሔረ ሕያዋንን ነው።

▶️፴. "በሦስተኛይቱም ቀን ውኃዎች ከምድር ላይ ወደ አንዱ ቦታ ሄደው ይወሰኑ ምድርም ትገለጥ ብሎ እንደ ተናገረው አደረገ" ይላል (ኩፋ.2፥3)። እግዚአብሔር በመናገር ፈጠረ ሲባል እኛ (ሰው) በምንናገረው ዓይነት አነጋገር (ቃል) ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በመናገር ፈጠረ ሲባል ድምፁ ከእኛ ድምፅ የተለየ ነው። ተለይቶ ነቢያት ከእግዚአብሔር የሰሙት ድምፅ ቦርፎሪኮን ሲባል የእኛ ግን አተርጋዎን ተብሎ ተገልጿልና።

▶️፴፩. "አዳምም በየስማቸው ጠራቸው ስማቸውም አዳም እንዳወጣላቸው እንደዚያው ሆነ" ይላል (ኩፋ.4፥1)። አሁን በዓለም ላይ ብዙ ቋንቋ አለና ሁሉም በየቋንቋው እንስሳትን፣ አራዊትን ወይም አዕዋፋትን የሚጠራበት ስም ይለያያል። አዳም ስም ሲሰጣቸው በምንኛ ነበር የጠራቸው?

✔️መልስ፦ አዳም በምን ቋንቋ ይናገር እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት በዚህ ቋንቋ ብለን መናገር አንችልም።

1 month ago

? የጥያቄዎች መልስ ክፍል 81 ?

▶️፩. ኩፋ.3፥1 "ከዚህም ሁሉ በኋላ ሰውን ፈጠረ። ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው" ይላል። ኩፋ.4፥3 እንደ እርሱ ያለ ረዳትንም ለራሱ አላገኘም ነበር ይላል። ምዕራፍ ሦስት ላይ ወንድ እና ሴት ከተፈጠረ እንዴት አዳም ብቻውን ነበረ ይላል? ቢብራራ?

✔️መልስ፦ ፍጥረት ተፈጥሮ ያለቀው በዕለተ ዓርብ ነው። ሔዋን በአዳም ጎን ስለነበረች የሔዋን መፈጠርና የአዳም መፈጠር በአንድ ጊዜ የሆነ ነው። አዳም በተፈጠረ በሳምንቱ ዓርብ ሔዋን ከአዳም ጎን ተገኝታለች። ስለዚህ ከአዳም ጎን እንደነበረች ሲያይ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ብሏል። ከአዳም አካል ተለይታ አልወጣችም ነበርና ረዳት አልነበረውም ተብሏል። ስለዚህ የሚቃረን ነገር እንደሌለው አስተውል።

▶️፪. "የዘመኑ አከፋፈል ከዓለም ፍጥረትና አዲስ ፍጥረት ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ" ይላል (ኩፋ.2፥2)። ከዓለም ፍጥረትና አዲስ ከተፈጠረበት ጊዜ የሚለው ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው? ቀጥሎም የሰማይ ሠራዊት እንደመሆናቸው እስኪታደሱ ድረስ ያለውን ጻፍ ይላል። እስኪታደሱ ድረስ የሚለው ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሰማያት እስኪታደሱ ድረስ ማለቱ ዝናም እስኪያዘንሙ ለማለት ነው። ከዓለም ፍጥረት ከተፈጠረበት ጀምሮ የሚለው ከጥንተ ዕለት ከእሑድ ጀምሮ ማለት ነው። አዲስ ፍጥረት ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ የሚለው አዳም ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ ማለት ነው።

▶️፫. "ለሥጋዊ ሁሉ ሳይታወቅ እኛ በሰማያት ዕረፍት አደረግንባት" ይላል (ኩፋ.3፥17)። ቅድስት ሥላሴ መድከም ማረፍ አለባቸውን?

✔️መልስ፦ በሥላሴ ዘንድ መድከም ማረፍ የለም። በሥነ ፍጥረት እግዚአብሔር አረፈ ማለት መፍጠሩን ተወ ማለት ነው። ስለዚህ ዕረፍት አደረግንባት ማለት በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ፍጥረትን አልፈጠርንም ማለታቸው ነው።

▶️፬. አንድ ሱባዔ ስንት ቀን ነው?

✔️መልስ፦ አንድ ሱባዔ በቀን ሰባት ቀን፣ በዓመት ሰባት ዓመት ነው።

▶️፭. "በኤዶም ገነት እንደተማረ ምድርን ያርሳት ነበር" ይላል (ኩፋ.5፥7)። አዳም በገነት ያርስ ይቆፍር ነበር ወይ?

✔️መልስ፦ ይቆፍርና ይኮተኩት ስለነበረ አረሰ ተባለ እንጂ በሬ ጠምዶ ማረስስ የተጀመረው በአብርሃም ነው።

▶️፮. "የቁርበት ልብስንም አደረገላቸው" ይላል (ኩፋ.4፥24)። ያለበሳቸው ቁርበት ከየት ተገኘ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋን ልብስ እንዳለበሳቸው ተጽፏል እንጂ ልብሱ ከምን እንደተገኘ መጽሐፍ ቅዱሱ ተጨማሪ ነገር አልጻፈልንም።

▶️፯. "እግዚአብሔር ለእኛ እንዲህ አለን" ይላል (ኩፋ.4፥4)። ሰሚዎቹ እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ መጽሐፈ ኩፋሌን ለሙሴ የገለጹለት መላእክት ናቸው።

▶️፰. "በባሕርይ ዕውቀቱ ባዘጋጃቸው ላይ የተሾሙ መላእክትን ፈጥሯልና" ይላል (ኩፋ.2፥7)። በባሕርይ ዕውቀቱ የተሾሙ መላእክት የሚለው ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ ዓረፍተ ነገር በባሕርይ ዕውቀቱ የተባለ እግዚአብሔር ነው። በባሕርይ ዕውቀቱ መላእክትን ፈጠረ ማለት እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ እንደመሆኑ ፍጥረታትን መፍጠሩን የሚያመለክት ነው።

▶️፱. "መልአከ ገጹንም እንዲህ አለው" ይላል (ኩፋ.1፥25)። መልአከ ገጽ ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ መልአከ ገጽ ማለት በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት ያለው መልአክ ማለት ነው።

▶️፲. አንዳንድ መምህራን ሔዋንን ከግራ ጎኑ እንደ ተገኝች ያስተምራሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ሔዋንን ከአዳም አጥንት መገኘቷን እንጂ ቀኝ ግራ አይሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ አለው?

✔️መልስ፦ የመጽሐፍ ቅዱሱ ማስረጃ ሔዋን ከአዳም ጎን እንደተገኘች ይናገራል እንጂ ቀኝ ግራ ብሎ አላስቀመጠም። በቀኝ ወይም በግራ የሚሉ ሰዎች ካሉ ግን ከምን አንጻር እንዳሉና ምንጫቸው ምን እንደሆነ ማጣራት መልካም ነው።

▶️፲፩. "ቃይናን እና ቃየን" የተለያዩ ሰዎች ናቸው? በመጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ ምዕራፍ 1 ላይ በአዳም ዘር የቃየን ስም አልተጠቀሰም። ለምን ስንል ዘሩ ስላልቀጠለ እንደሆነ አይተናል። በዚህ ምዕራፍ ግን ቃየን ልጅ እንደወለደ ይናገራልና ይህ እንዴት ሆነ?

✔️መልስ፦ የተለያዩ ሰዎች ናቸው። ቃይናን የሄኖስ ልጅ ሲሆን ቃየን ደግሞ የአዳም ልጅ ነው። የቃየን ዘር የተቋረጠ በማየ አይኅ ነው። በማየ አይኅ የቃየን ዘር ጠፍቷል። ከዚያ በኋላ የቀጠሉ የሴት ዘሮች ናቸው።

▶️፲፪. "የእግዚአብሔር መላእክት በምድር የሰው ልጆችን ያስተምሩ ዘንድ ወደ ምድር ወርደዋልና" ይላል (ኩፋ.5፥21)። አስተምረዋል ወይ? እነዚህ መላእክት እንዴት ከሰው ልጆች ጋር ረከሱ? ፍጥረታቸው እንዲህ ዓይነት ሥጋዊ ባሕርይ አላቸው?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር መላእክት የተባሉ ከዚህ በደብር ቅዱስ ይኖሩ የነበሩ የሴት ዘሮች ናቸው እንጂ በዕለተ እሑድ የተፈጠሩት ረቂቃን መላእክት አይደሉም። ቅዱሳን ስለነበሩ መላእክት እስከመባል ደርሰዋል። በኋላ ግን ከደቂቀ ቃየል ጋር ዝሙትን ስለሠሩ ጠፍተዋል።

▶️፲፫. ኩፋ.1፥15 "እገለጥላቸዉ ዘንድ ይፈልጉኛል። በፍጹም ልባቸዉና በፍጹም ነፍሳቸዉ በፈለጉኝ ጊዜ እኔ በእውነት ብዙ ሰላምን እገልጥላቸዋለሁ በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ ወደ ቀና ሕግ እመልሳቸዋለሁ" ይላል። እግዚአብሔር ፍጹም ነፍሴ ሲል ምን ማለቱ ነዉ እዚህ ላይ ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ በፍጹም ነፍሴ፣ በፍጹም ልቤ እያለ የተናገረው ረድኤቱን ነው። እንጂ ለእግዚአብሔር ሌላ ነፍስ አለችው ማለት አይደለም።

▶️፲፬. ኩፋ.4÷8 በመጀመሪያይቱ ሱባዔ አዳም ተፈጠረ ሚስቱም የተገኘችበት ጎኑ ተፈጠረ። በሁለተኛይቱም ሱባዔ እርሷን አሳየዉ ስለዚህም በሕርስ ጊዜ ለወንድ ልጅ አንድ ሱባዔ ለሴት ልጅ ሁለት ሱባዔ የመጠበቅ ትእዛዝ ተሰጠ" ይላል። በመጀመሪያይቱ ሱባዔ አዳም ተፈጠረ ሚስቱም የተገኘችበት ጎኑ ተፈጠረ ይላልና ተፈጠረች ለማለት ነዉ? በሕርስ ማለት ምን ማለት ነዉ?

✔️መልስ፦ አዎ ሔዋን ተፈጠረች የሚባለው አዳም በተፈጠረበት ጊዜ ነው። ይህ ብቻ አይደለም እኛ እንኳ በቅርብ ከእናቶቻችን ከአባቶቻችን ብንወለድ እንኳ ተፈጠርን የሚባለው ግን አዳም የተፈጠረ ጊዜ ነው። ሕርስ ማለት የአራስነት ጊዜ ማለት ነው።

▶️፲፭. ኩፋ.1፥25 እግዚአብሔርም ለሁሉ ተገልጦ እስኪታይ ድረስ የሚለዉ በሥጋ መገለጡን የሚያሳይ ነዉ?

✔️መልስ፦ በሥጋ እስኪታይ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በዘፈቀደ እስኪታይ ድረስ፣ በረድኤት እስኪገለጥ ድረስ ተብሎም ይተረጎማል።

▶️፲፮. ኩፋ.፬÷፩ "ከሁለተኛው ሱባዔ በስድስተኛው ቀን በእግዚአብሔር ቃል ታዝዘን እንስሳትን ሁሉና አራዊትን ሁሉ በዚህ ዓለም የሚመላለሰውን ፍጥረት ሁሉና አዕዋፍን ሁሉ በውኃውም ውስጥ የሚመላለሰውን ፍጥረት ሁሉ በየወገናቸው በየመልካቸው ወደ አዳም አመጣን" ይላል። እነማን ናቸው ወደ አዳም ያመጡለት?

✔️መልስ፦ ቅዱሳን መላእክት

▶️፲፯. ኩፋ.3፥1 “በስድስተኛይቱም ቀን ሰውን ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጠረ” ይላል። ገድለ አዳም ደግሞ ሔዋን በሳምንቱ ወይም አዳም በተፈጠረ በስምንተኛው ቀን እንደተፈጠረች ይናገራል እና አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ከዚህ በስድስተኛው ቀን ያለ አራዊት ስም ከተሰጡበት ከእሑድ ጀምሮ እስከ ዓርብ ቆጥሮ ነው። ገድለ አዳም ስምንት ማለቱ አዳም ከተፈጠረበት ከዓርብ ጀምሮ ቆጥሮ ነው። ስለዚህ በሁለቱ መካከል ምንም ልዩነት የለም።

▶️፲፰. የመጽሐፈ ኩፋሌ ዓላማው ምንድን ነው?ለምን ተጻፈ?

1 month, 1 week ago
***?***፪ኛ ዜና መዋዕል ክፍል 4***?***

?፪ኛ ዜና መዋዕል ክፍል 4?

?ምዕራፍ 16፡-
ይሁዳና ሰማርያ ጦርነት እንደገጠሙ

?ምዕራፍ 17፡-
ኢዮሳፍጥ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር እንዳደረገ

?ምዕራፍ 18፡-
ነቢዩ ሚክያስ በአክዓብ ላይ ትንቢት እንደተናገረ

?ምዕራፍ 19፡-
ነቢዩ ኢዩ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሳፍጥን እንደገሠፀው

?ምዕራፍ 20፡- ኢዮሳፍጥ እንደጸለየ

✝️የዕለቱ ጥያቄዎች✝️
፩. የይሁዳ ንጉሥ አሳን “በሶርያ ንጉሥ (በወልደ አዴር) ታምነሀልና…ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሀል” ያለው ነቢይ ማን ነው?
ሀ. ነቢዩ ሰማያ
ለ. ነቢዩ አዳድ
ሐ. ነቢዩ ኢዩ
መ. ነቢዩ አናኒ
፪. ሐሰተኛ ነቢያት የሚባሉት እነማን ናቸው?
ሀ. የራሳቸውን መሰለኝ ትንቢት ነው የሚሉ
ለ. ከእግዚአብሔር ሳይሰሙ እግዚአብሔ አለ የሚሉ
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም
፫. የሞዓብና የአሞን ልጆች ከእነርሱም ጋር ምዑናውያን ኢዮሣፍጥን ሊወጉ በመጡ ጊዜ “ሰልፉ የእግዚአብሔር ነውና አትፍሩ” ብሎ ኢዮሣፍጥንና የይሁዳን ሰዎች ያበረታታቸው ነቢይ ማን ነው?
ሀ. ምታንያስ
ለ. ኢያሔል
ሐ. ኡዝሔል
መ. ብልአንያ

https://youtu.be/ly4Ajd-p5kY?si=6S7R3OKQkfa0tMaV

1 month, 1 week ago
***✔️***መልስ፦ ብዙ ሚስት ማግባትን ብሉይ ኪዳን …

✔️መልስ፦ ብዙ ሚስት ማግባትን ብሉይ ኪዳን አይከለክልም ነበረ። በሐዲስ ኪዳን ግን አንድ ወንድ በአንዲት ሴት ተወስኖ መኖር ይገባዋል። ያን ጊዜ ለምን እንዳልተከለከለ ምክንያቱን አላገኘሁትም። ብዙ ተባዙ ብሏቸው ስለነበረ መብዛታቸውን ይሻ ስለነበረ ነው የሚሉ አሉ። አታመንዝር የሚለው ቃል ሚስትህ ካልሆነች ሴት አትድረስ ተብሎ ይተረጎማል። አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ሲያገባ አንዲት ሴት ግን ብዙ ወንድን አታገባም ነበረ። ባል ሚስቱ ካልሆነች ሴት፣ ሚስትም ባሏ ካልሆነ ወንድ ግንኙነት አለማድረግ ነው አለማመንዘር ማለት።

▶️፲፫. "ኢትዮጵያዊውም ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሰዎችና ሦስት መቶ ሠረገሎች ይዞ ወጣባቸው፤ ወደ መሪሳም መጣ" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.14፥9)። ከዚህ የተጠቀሰችው ኢትዮጵያ አሁን የምንኖርባት ኢትዮጵያ ናት? ግዛቷስ በወቅቱ እዚያ ይደርስ ነበር ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ያን ጊዜ የተጠቀሰችው ኢትዮጵያ ወሰኗ ከየት እስከ የት እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ አይገልጽም።

▶️፲፬. "ንጉሡም አሣ እናቱን መዓካን በማምለኪያ ዐጸድ ጣዖት ስላደረገች ከእቴጌነቷ አዋረዳት። አሣም ምስሏን ቈርጦ ቀጠቀጠው በቄድሮንም ወንዝ አጠገብ አቃጠለው" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.15፥16)። ምስሏን ያለው ሥዕል ነው ወይስ ጣዖቱን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ምስል የሚለው ቅርጹን ነው። መዓካ ታመልከው የነበረውን ጣዖት ልጇ አሣ ቀጥቅጦ እንዳጠፋው ይገልጽልናል። ሥዕል ግን የማይዳሰስ ነገር ነው። ከዚህ ግን አሣ ቆርጦ ቀጠቀጠው ስለተባለ ቅርጽ መሆኑን ያሳውቀናል።

▶️፲፭. በ2ኛ ዜና መዋ.15፥12 መሠረት ሰውን በፍጹም ነፍስ በፍጹም ልብ መውደድ ይቻላል ወይ? origen of Alexandria አይቻልም የሚል ጽፎ አነበብሁ።

✔️መልስ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ማድረግ የማንችለውን ነገር አያዝዘንም። ስለዚህ ምናልባት Origen of Alexandria ከምን አንጻር እንደተናገረ ባላውቅም መጽሐፍ ቅዱስ ግን በፍጹም ልባችሁ በፍጹም ነፍሳችሁ እግዚአብሔርን ውደዱ እያለ ነግሮናል። የነገረን ደግሞ መደረግ ስለሚችል ነው። በአንድ ጊዜ መደረግ ባይችል እንኳ ቀስ በቀስ እስከ አሥረኛ የቅድስና ደረጃ ደርሰን ማድረግ እንችላለንና።

▶️፲፮. ፪ኛ ዜና መዋ.፲፬ ÷፲፪ "እግዚአብሔርም በአሣና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን መታ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ። አሣም ከእርሱም ጋራ ያለው ሕዝብ እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዷቸው ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና እጅግም ብዙ ምርኮ ወሰዱ" ይላል። ኢትዮጵያውያን በሕገ ልቡና በሕገ ኦሪት ይመሩ የነበሩ ሕዝቦች እንደሆኑ እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ ትውፊት ይነግረናል። እና ታዲያ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን አሳልፎ የሰጣቸው ለምን ይሆን? አሞ.፱ ÷፯ ላይም ኢትዮጵያውያንን ከእስራኤላውያን አብልጦ እንደሚወዳቸው ይናገራልልና።

✔️መልስ፦ ኢትዮጵያውያን በሕገ ልቡና በሕገ ኦሪት ጸንተው የሚኖሩ ሕዝቦች እንደነበሩ ተገልጿል። ነገር ግን በአምልኮ ቢኖሩም ሁሉም ቅዱሳን ነበሩ ማለት አይቻልም። እስራኤላውያን እንኳ እግዚአብሔርን በማምለክ የኖሩ ቢሆኑም አንዳንድ ጊዜ ኃጢአትን እየሠሩ በተለያዩ መከራዎች እንደተቀጡ ይታወቃል። ስለዚህ ምንም እንኳ ከዚህ ያን ጊዜ የኢትዮጵያውያን በደል ምን እንደነበረ ባይገለጽም ነገር ግን በእስራኤላውያን እጅ አሳልፎ እንደሰጣቸው ተገልጿል።

© በትረ ማርያም አበባው

?የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

?የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

1 month, 1 week ago

? የጥያቄዎች መልስ ክፍል 75 ?

▶️፩. 2ኛ ዜና መዋ.9፥8 "በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት" ይላል። ንግሥቲቱ ለምን በአምላካችን አላለችም? የሳባ ሀገር ሰዎች (ኢትዮጵያውያን) በምን ነበር የሚያምኑት?

✔️መልስ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሕገ ልቡና እግዚአብሔርን ሲያመልክ የኖረ ሕዝብ ነው። ንግሥተ ሳባም እግዚአብሔርን ታመልክ የነበረች ሴት ናት። አምላክህ ማለቷ እየተናገረች ያለችው ስለእርሱ ስለሆነ አቅርባ ለመናገር ነው። እግዚአብሔር እንኳ ሕዝቤ ይላቸው የነበሩ እስራኤላውያንን ለሙሴ ሕዝቦችህ ማለቱ ለሙሴ አቅርቦ ለመናገር ነበር። ስለዚህ ንግሥተ ሳባም ሰሎሞንን አምላክህ ማለቷ እርሷ ሌላ አምላክ ያላት ሆና አይደለም። ለሰሎሞን አቅርባ ለመናገር ነው እንጂ።

▶️፪. "እግዚአብሔር በጨለማ ውስጥ እኖራለሁ ብሏል። እኔም ለዘላለም የምኖርበትን ዝግጁና ቅዱስ ቤት ለስሙ ሠራሁ" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.6፥1)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ አልገባኝም። በጨለማ የሚኖር ነው ብሎ ለምን ማደሪያ ሠራሁ አለ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ የሚኖር ስለሆነ በተለየ ማደሪያ የሚወሰን አይደለም። ማደሪያ ተሠራለት መባሉም ከሌላው ቦታ በተለየ ጸጋን ለሰው የሚያድልበት ቤት ተሠራ ማለቱ ነው።

▶️፫. "ሰሎሞን በመንግሥቱ ከእስራኤል ልጆች ማንንም አገልጋይ አላደረገም" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.8፥9)። አገልጋዮች ለምን አላደረገም አያምናቸውም ነበርን?

✔️መልስ፦ ማንንም አገልጋይ አላደረገም ማለት ሁሉም ነጻ ሕዝቦች ሆነው በኃላፊነት ሀገራቸውን ያስተዳድሩ ነበር ማለት ነው። ይህም ማለት በሰሎሞን ዘመን አንዱ ሰው ለአንዱ ሰው አገልጋይ ሆኖ ሳይሆን ሁሉም በባለቤትነት ስሜት ሆነው ይኖሩ ነበር ማለት ነው። እንጂ አያምናቸውም ነበር ለማለት የመጣ ሐሳብ አይደለም።

▶️፬. "የእግዚአብሔር ታቦት የገባችበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥ" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.8፥11)። ሰሎሞን አሕዛብ እደሆነች እያወቀ ለምን አገባ? በቤቱስ መኖሯ ቤቱን ታረክሳለችን?

✔️መልስ፦ ሰሎሞን ከአሕዛብ ወገን ማግባቱ ሕግ አፍራሽ ያሰኘዋል እንጂ አያስመሰግነውም። ስለዚህ ኢይባዕ ሞዓባዊ ወአሞናዊ እስከ ሣልስ ወራብዕ ትውልድ ስለሚል በሕጉ መሠረት እንዳትገባ አድርጓታል። የእግዚአብሔር ታቦት የነበረችበት ቅዱስ ቦታ ስለነበረ ከዚያ ተከልክላለች።

▶️፭. "አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር። አንተም ጽኑውን የአባትህን አገዛዝ ቀንበር አቅልልን እኛም እንገዛልሃለን" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.10፥3)። እና ንጉሥ ሰሎሞን የጫነባቸው ቀንበር ምን ነበር? በእስራኤል ላይ ሁሉ መልካም ፍርድ አልነበረውምን?

✔️መልስ፦ አገዛዙን ማጽናቱን ለመግለጽ ቀንበር ጫነብን አሉ እንጂ በሬዎች በሚጠመዱበት ቀንበር ጠመደን ማለቱ አይደለም። ሰሎሞን መልካም ፍርድን ቢፈርድም በሕዝቡ ዘንድ ግን እንዳከበደባቸው ተሰምቷቸዋል። ስለዚህ ያ በሮብዓም እንዲቀልላቸው ጠይቀዋል።

▶️፮. 2ኛ ዜና መዋ.7፥2 ላይ የእግዚአብሔር ክብር ቤቱን ሞልቶት ስለነበር ካህናት መግባት እንዳልቻሉ ይነግረናል። ታዲያ ክብሩ ይህን ያህል ለመግባት እንኳን የሚከለክል ከሆነ አሁን ባለችው ቤተ መቅደስስ ይህ ነገር እንዴት አልሆነም?

✔️መልስ፦ ያ የእግዚአብሔር ክብር የተባለው ለጥቂት ጊዜ እግዚአብሔር በቤተ መቅደስ አድሮ ረድኤቱን እንደሚሰጥ እንዲረዱና በደል ከበደሉ ግን እንደሚያጠፋቸው እንዲያውቁ የተደረገ ነው። እንጂ እስከመጨረሻው እንደዚያ አልሆነም። አሁን ላይ ለምን አይደረግም የሚለው ግን ከዓላማው አንጻር ነው። ያን ጊዜ እስራኤላውያን አንዳንዴ ጣዖት እያመለኩ ያሳዝኑት ነበረ። ስለዚህ ጣዖት ማምለክ እንደማይገባና እርሱን ብቻ እንዲያመልኩ ማስረጃ ነው። አሁን ግን ክርስትና በዓለም ተሰብኳል። ክርስቶስ በአደባባይ ተሰቅሎ ምሕረትን ሰጥቶናል። ያንን አስበን ጽድቅ እየሠራን መኖር እንጂ አዲስ ተአምር ፈላጊ መሆን አይገባንም።

▶️፯. 2ኛ ዜና መዋ.7፥5 ላይ "ቅዳሴ" ሲል ያኔም ቅዳሴ ነበር ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ቅዳሴ ማለት በመሠረቱ ምስጋና ማለት ነው። ስለዚህ ምስጋና ያን ጊዜም ነበረ። ቅዳሴ ቤት የሚለው ግን የምረቃውን ሥነ ሥርዓት ነው። አንድ የእግዚአብሔር ቤት ተሠርቶ ሲመረቅ ቅዳሴ ቤቱ ሆነ ተደረገ ይባላል።

▶️፰. 2ኛ ዜና መዋ.10፥15 "ለውጡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበርና" ሲል እግዚአብሔር ግድ ብሎት ነው ማለት ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር የሰዎችን ነጻነት አይጋፋም። ነገር ግን በበደላቸው ምክንያት እስራኤላውያን እንደሚከፋፈሉ ያውቅ ስለነበረ ማወቁን ለመግለጽ ለውጡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ተብሏል።

▶️፱. ዐሥሩን ነገደ እስራኤል ብቻ ነጥሎ "እስራኤል" በሚለው ስም መጥራት ያስፈለገበት ምክንያት ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ምክንያቱ ሁለቱ ነገድ ከተማ ለይተው ከተማቸውን ኢየሩሳሌም ሀገራቸውን ይሁዳ ብለው በመለየታቸው ቀሪዎቹ የቀድሞውን ስም ይዘው ከተማቸውን ሰማርያ ብለው ቀጥለዋል።

▶️፲. ፪ኛ ዜና መዋ ፮፥፩ ሰሎሞንም እግዚአብሔር በጨለማ ውስጥ እኖራለኹ ብሏል። እኔ ግን ለዘለዓለም ትኖርበት ዘንድ ማደሪያ ቤትን ሠራኹልኽ አለ። በውኑ እግዚአብሔር በጨለማ ነው የሚኖረው ማለት እንችላለን?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር አለመመርመሩን ለመግለጽ በጨለማ ይኖራል ተብሎ ይገለጻል። በጨለማ ያለን ነገር አጥርተን እንደማናውቀውና እንደማናየው ሁሉ እግዚአብሔርንም በባሕርይው ማየት አንችልምና በጨለማ ይኖራል ይባላል። እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ማለቱ በብርሃን ሁሉን ማየት እንደሚቻል በእግዚአብሔር ቸርነትም ሁሉን ማየት እንችላለንና ነው። አንድም በባሕርይው ብርሃን ነው ማለት ነው።

▶️፲፩. ፪ኛ ዜና መዋ.፯÷፫ የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ "የእግዚአብሔርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር" ሲል የእግዚአብሔር ክብር በሰው ዐይን ይታይ ነበር?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር ባሕርያዊ ክብር አይታይም። እግዚአብሔር ከመታየት በላይ ነውና። ነገር ግን መኖሩን በብዙ መንገድ ለሰው ልጆች ይገልጻል። ስለዚህ በወቅቱ ለሕዝቡ የታየ ነገር ነበረ። ያም የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ስለሆነ የእግዚአብሔር ክብር ብለውታል።

▶️፲፪. ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሳባ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን መሄዷን አይተናል። የእሷ ስሟ ሳባ? ማክዳ? አዜብ? አዜብ የሚለው በአዜብ አቅጣጫ ስለመጣች ነው እንጂ ስሟ አይደለም ሲሉ ስለሰማሁ ነው። ሳባ የሚለውም ንግሥተ ሳባ እንደ ማለት ነው የሚል ያየሁ ይመስለኛል። ከእግሯ እንደ አህያ ሸኮና ያለ ነገር ነበራት ይባላል እውነት ነውን? በምን ምክንያት ይዟት ነው ስትወለድ ነውን ወይስ በሆነ ምክንያት ነው ሸኮና የወጣባት? ከንግሥት ሳባ በፊት ኢትዮጵያ ሥርዓተ ኦሪት ትፈጽም ነበርን? ከነበረች በማን ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ?

✔️መልስ፦ ሳባ የሀገሩ ስም ነው። ንግሥተ ሳባ ማለት የሳባ ንግሥት ማለት ነው። ንግሥተ አዜብ መባሏም ሀገሯ ሳባ ከእስራኤል በአዜብ አቅጣጫ ስለነበረ ነው። ስለዚህ ሳባ የሀገር ስም፣ አዜብ የአቅጣጫ ስም መሆኑን ልብ ያድርጉ። የእርሷ ስሟ ማክዳ ይባል እንደነበረ በትውፊት ይነገራል። ከእግሯ እንደ አህያ ሸኮና ነበረባት የሚባለው እውነት ነው። እንደዚያ የሆነችው በኢትዮጵያ ዘንዶ ይገዛ ስለነበረ አባቷ ያንን ሲገድለው ደሙ ተፈንጥቆባት ነው እየተባለ ይነገራል። ያ ሸኮና ወደሰሎሞን ስትሄድ ገባሬ ተአምር እንጨት ነበረ እርሱን ስትሻገር ሸኮናው ወድቆላት ድናለች። በዚያ እንጨት አንድ ብር እርሷ ሰሎሞን አንድ ብር

We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion ? @Share_Home

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 6 months, 3 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia ? ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 8 months, 3 weeks ago