Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

የኦርቶዶክሰ ተዋህዶ መዝሙሮች

Description
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ;ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሳጽን ይንቃሉ " ምሳሌ 1:7
👉 የቻናሉ አላማ
✔️💠 የአባቶች ምክር
✔️💠መንፈሳዊ መዝሙሮች
✔️💠ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን መረጃ ያገኙበታል

ለማንኛውም ሀሳብ @merii19✣✣

Advertising
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 2 weeks, 1 day ago

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ


📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako

2 months, 2 weeks ago

✝️የጌታችንን ስም ኢየሱስ ብሎ የጠራው ማነው?
_________________________

2 months, 2 weeks ago
በቅርቡ ተከፍቶ የስንቱን ቀልብ ***😱***የሳበው የምንጊዜም …

በቅርቡ ተከፍቶ የስንቱን ቀልብ 😱የሳበው የምንጊዜም ምርጡ  የመንፈሳዊ ጥቅስ ቻናል ❤️

እኔ ተቀላቅዬ ወድጄዋለው እናንተም ተቀላቀሉ ትወዱታላቹ
https://t.me/+QK6y4ys5dWI1ZWI0

2 months, 2 weeks ago

#መዝሙር#ነነዌን_ሊያቃጥል

ነነዌን ሊያቃጥል የወረደው እሳት (፪)
ተመልሶ ዐረገ(፪) በሀዘን በጸሎት (፪)
ስለሆነ ከልብ የሀዘናቸው ምንጩ (፪)
ነበር እንደ ራሔል (፪)እንባን እየረጩ (፪)
ለነነዌ ሰዎች ደስታን ያበሰረ (፪)
ጋሻ እና ጦራቸው(፪)ጾም ጸሎት ነበረ (፪)
እንኳን የሰው ልጆች እንስሳት ሳይቀሩ(፪)
በዮናስ ስብከት (፪)ፆም ጸሎት ተማሩ(፪)
@yleybgal19

2 months, 2 weeks ago

አይሸሸግ እውነቱ

አይሸሸግ እውነቱ
ማርያም ብጽይት ናት
ማርያም ቅድስት ናት
ከእግዚአብሔር ያልተላከ አይችልም ሊያወድሳት/2/
አይሸሸግ እውነቱ ማርያም ብጽይት ናት
ማርያም ውድስት ናት
ከእግዚአብሔር ያልተላከ አይችልም ሊያወድሳት/2/
አዝ...
ገብርኤል ከከፍታ ከራማ ታላቅ ቤቱ
ገሊላ የተገኘው ወደ ማርያም እህቱ
ከእግዚአብሔር መላኩን ተረዳን በምስጢር
ለስሟ ክብርን ሰቶ ሰምተነዋል ሲያበስር
አዝ...
በዘካርያስ ቤት አቀረብሽ ምስጋና
የባርያዉን ውርደት ተመልክቷልና
ፍጥረት ብፅይት ካለሽ ሆኖ በአንድ ቃል
ላንቺ ያልዘመረ እንዴት ትውልድ ይባል
አዝ...
ቢያከብርሽ ገብርኤል በታላቅ ትህትና
ልእልናሽ በልጦበት ካንቺ ቅድስና
ከልቡ አመንጭቶ መች ሆነ ማክበሩ
እግዚአብሔር ልኮት ነው ላንቺ መዘመሩ
አዝ...
አንዳች አይጎልብኝ አንቺን አወድሼ
ዝማሬን ባበዛ ያለኝን ጨርሼ
እንኳን ለማርያም ለአዶናይ እናት
ምስጋናን ሰጥቷታል ለአቢጊያ ዳዊት
አዝ...
ቢያከብርሽ ገብርኤል በታላቅ ትህትና
ልእልናሽ በልጦበት ካንቺ ቅድስና
ከልቡ አመንጭቶ መች ሆነ ማክበሩ
እግዚአብሔር ልኮት ነው ላንቺ መዘመሩ *💚@yleybgal19 💚
💛@yleybgal19 💛
❤️@yleybgal19 ❤️
🌿*🌿🌿🌿🌿🌿**

2 months, 2 weeks ago
2 months, 2 weeks ago

​​​​
በጾም ወራት "ዓሳ" መብላት ይቻላልን???

ክፍል አንድ

ብዙ ጊዜ ይህ ከላይ ያነሳነው ርዕሰ ጉዳይ ሰዎችን ሲያከራክር እንሰማለን በተለይ በዚህ በያዝነው በዐብይ ፆም ደግሞ ሁኔታው ከፍ ብሎ ምዕመኑ ውዥንብር ውስጥ ሲገባ ይሰተዋላል ዓሳ ፆም አለው የለውም በሚል ንትርክም ጊዜውን ያጠፋል።

ዓሳ ፆም የለውም ብለው የሚከራከሩ ሰወች እንደ መነሻ ምክንያት አድርገው የሚያነሷቸውና የሚከራከሩባቸው ከእውቀት ማነስ የመጡ ሁለት ነጥቦች አሉ።

እነሱም ፦
1ኛ፨ በፍትህ መንፈሳዊ (በፍትሃ ነገስት ) ስለ ፆምና ሥርዓቱ በሚዘረዝረው አንቀፅ 15 ላይ ያለውን "ኢትብልዑ ስጋ ዘእንበለ አሳ" የሚለውና
2ኛ፨ በአብይ ፆም ጊዜ ጌታ ለሐዋርያቱ አሳ አበርክቶ መግቧቸዋል የሚለው ናቸው።

እነዚህን ሁለት ነጥቦች በዝርዝር ስንመለከት
1ኛ. በፍትህ መንፈሳዊ (በፍትሃ ነገስት )ላይ እውነት ነው " ኢትብልዑ ... ስጋ ዘእንበለ አሳ " የሚል ትዕዛዝ አለ። እዚህ ትዕዛዝ ውስጥ ለክርክሩ መነሻ የሆነው <ዘእንበለ> የሚለው የግእዝ ቃል ነው! ይህ ቃል በግእዙ ሁለት ትርጉም አለው እነሱም፦
ዘእንበለ = በስተቀር
ዘእንበለ = ሳይቀር (ጭምር) የሚል ነው።

በነዚህ ትርጉሞች መሰረት የትዕዛዙ ትክክለኛ የአማርኛ ፍቺ "ኢትብልዑ ስጋ ዘእንበለ ዓሳ " ለሚለው "ስጋን ሁሉ አትብሉ ዓሳንም ሳይቀር (ዓሳንም ጭምር) ማለት ሆኖ ሳለ አንዳንድ
ሰዎች ይህንኑ ትዕዛዝ "ስጋን አትብሉ ከዓሳ በቀር" ብለው አጣመው በሁለተኛው ፍቺ በመተርጎም ዓሳን በፆም ወቅት ሲበሉና መብላትም እንደሚቻል
ሲናገሩ እንሰማለን።

ይህ ነገር የቤተ ክርስቲያን አስተምሮ እንዳልሆነ ቅዱስ ሲኖዶስም እንደከለከለ ምዕመኑ ተረድቶ ነገርየውን ከመፈፀም መቆጠብ ያልተፃፈውን የሚያነቡትንም ተው ማለት ይገባዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ደግሞ ዓሳ ደም ስለሌለው በፆም መመገብ ይቻላል የሚሉ አሉ። ይህ ከየዋህነት የሚመጣ አስተሳሰብ ነው ምክንያቱም ሲጀመር ዓሳ ደም አለው ሲቀጥል እነ እንቁላል እነ ወተት እነ አይብና ቅቤ ደም ሳይኖራቸው ነው የፍስክ ሆነው በፆም የማይበሉት።

ይህ ነገር የሚደረገው መፆም ማለት ስጋን ጎድቶ ለነፍስ ማስገዛት እስከሆነ ድረስ አበልፃጊ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ ስላለብን ነው ዓሳ ደግሞ ከበግና ከበሬ ስጋ የተሻለ ጥቅም እንዳለው ይታወቃልና ከበግና ከበሬ ተከልክሎ አሳን መብላት እራስን ማታለል ነው የሚሆነው ስለዚህ አንድ ክርስቲያን በጾም ሰአት ዓሳን መብላት አይችልም ማለት ነው።

ክፍል 2 ይቀጥላል....

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yleybgal19
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

2 months, 2 weeks ago
2 months, 3 weeks ago

❤️... እንደ ትላንትና ..... ❤️

እንደ ትላንትና 2X
ከአፊ ላይ አይጠፋም የስምሽ ምስጋና
እንደ ልጅነቴ 2X
በፍቅር ያነሳሻል ዛሬም አንደበቴ

ገና ልጅ እያለው ነበር ሳወድስሽ
አፌን የፈታውት ዘምሬ ለክብርሽ
ሁልጊዜ ባነሳሽ መቼቀን ጠግቤ
ይኸው ለዚህ ደረስኩ አትሜሽ በልቤ
የአፌ ዜማ ነሽ ጥበብ ለከንፈሬ
ኪዳነምህረት ነው አሁንም መዝሙሬ
።።።።። አዝማች ።።።።።።
የእናት ውለታ ያውቃል የቀመሰ
በእቅፏ ያደገ ለክብር የደረሰ እኔም አውቀዋለሁ ያንቺን ደግነት
ከቃላት በላይ ነው ያጥራል ለአንደበት
የተደረገልኝአለ ብዙ ነገር
ለዚህ ነው እናቴ ማነሳሽ በፍቅር
።።።።። አዝማች ።።።።።
አይኖቼ በናፍቆት በስስት ያመሻል
ልሳኔ በፍቅር ደጋግሞ ያነሳሻል
ከመቅደስሽ ቆሜ የውስጤን ነገርኩሽ
ህልሜን ስትፈቺ እናቴ አየሁሽ
እውነትም አዛኝ ነሽ ለተማፀነሽ
ግራ ስለገባው ሰው ቅርብ ነው ምልጃሽ

🙏 ዘማሪ ሙሉቀን ከበደ 🙏

@yleybgal19

2 months, 3 weeks ago

#ያላንቺ_ማንአለኝ

ያላቺ ማን አላኝ እመቤቴ
ለተጎሳቆለው ለህይወቴ
እጠራሽ አለሁኝ ነይልኝ እናቴ

#አዝ====

በኃጢአት ትይዤ =እመቤቴ
ጨላማ ሲከበኝ = ነይልኝ
የማደርገው ሳጣ = እመቤቴ
ሲጨንቀኝ ሲጠበኝ= ነይልኝ
ባማላጅነትሽ= እመቤቴ
ዘወትር አትለይኝ = ነይልኝ(2)

#አዝ==

እናት እንደ ሌለው =እመቤቴ
አንገቴን አልደፋም = ነይልኝ
ተስፋዬ ነሽና =እመቤቴ
እኔስ አልተክዝም = ነይልኝ
ምርኩዜ ነሽ አንቺ =እመቤቴ
ከመንገድ አልቀርም =ነይልኝ
ምርኩዜ ነሽ አንቺ ከመንገድ አልቀርም

#አዝ==

ኪዳነ ምህረት ነሽ = እመቤቴ
ርኅርኅተ ኅሊና = ነይልኝ
ለሚማፀኑሽ = እመቤቴ
አትጨክኝና =ነይልኝ
ከልጅሽ ጋር ሆነሽ =እመቤቴ
ነይ በደመና = ነይልኝ
ከልጅሽ ጋር ሆነሽ ነይ በደመና

#አዝ==

እናት እንደ ሌለው = እመቤቴ
አንገቴን አልደፋም = ነይልኝ
ተስፋዬ ነሽና = እመቤቴ
እኔስ አልተክዝም = ነይልኝ
ምርኩዜ ነሽ አንቺ = እመቤቴ
ከመንገድ አልቀርም = ነይልኝ
ምርኩዜ ነሽ አንቺ ከመንገድ አልቀርም
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

@marakye22

We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 2 weeks, 1 day ago

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ


📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako