★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago
የእናቶች መክሊት አገልግሎት!
የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ታሪክ አካል ከሆኑት ነገሮች ውስጥ አንዱ የአገልግሎት ክፍሎች መዋቀርና መደራጀት ነው። ቤተክርስቲያኒቱ ገና ለጋ እና የምዕመናኖቿም ቁጥር ጥቂት በነበረ ወቅት ወንጌልን ለማስፋትና አብያተ ክርስቲያናትን ለማሳደግ ካላት ሰፊ ራዕይ የተነሳ ምዕመናኖቿ እንደየጸጋቸው እንደየ ዕድሜአቸውና ጾታቸው በማደራጀት ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ መሳካት ድጋፋቸውን አንዲለግሱ ስታደርግ ቆይታለች።
በመሆኑም ከባለፉት 50 ዓመታት ጀምሮ እስከ አሁን ቤተክርስቲያኒቱ እስከ ደረሰችበት ደረጃ የአባቶች፣ የእናቶችና የወጣቶች መክሊት አገልግሎት ያሉአት ሲሆን በእነዚህ የአገልግሎት ዘርፎችም ምዕመናን እየተጉ ይገኛሉ።
የእግዚአብሔር ቃል በዘካርያስ 4፥10 ላይ “የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው?” እንደሚል በእነዚያ የጥቂት ነገር ቀናት ውስጥ የነበረውን የአገልግሎቶቹን አጀማመር ትውልድ ሁሉ እንዲያውቀው እንደሚከተለው እንቃኛለን።
በአደረጃጀት ደረጃ የእናቶች አገልግሎት ከሌሎቹ የሚቀድም ሲሆን በአምስት እናቶች በአዋሳ ከተማ ተጀምሮ በድጋሚ በደንብ የተደራጀውና ሥራውን የጀመረው በ1967 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነው።
የአገልግሎቱ ዓላማም በሃገር ውስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የወንጌል ሥራ እንዲስፋፋ፣ የወንጌል መልዕክተኞች እንዲላኩ መርዳት እንዲሁም ቤተክርስቲያኒቱ ለምታካሂደው የተለያዩ የካህናትና የወንጌል አገልጋዮች ትምህርትና ሥልጠና እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤቶችንና ኮሌጆችን በገንዘብና በማቴሪያል መደገፍ ነው።
የአገልግሎቱ ጀማሪዎች የጥቂቱን ቀን ነገር እንደሚያስታውሱት እናቶች በቁጥርም ጥቂቶች በመሆናቸው አንዳንድ ያላገቡ ወጣት እህቶችን በመጨመር ጥጥ እየፈተሉ ጋቢ በማሰራት፣ የተለያዩ ጥልፎችንና ሹራቦችን እየሰሩ በመሸጥ የተገኘው ገንዘብ በወቅቱ ለነበረችው ቤተክርስቲያን ጉድለቶች ይውል ነበር።
እናቶች ቀስ በቀስ በጉልበታቸው ገንዘብን በተለያዩ ሥራዎች አማካይነት ከመሰብሰብ በተጨማሪ ለወንጌልና በቤተክርስቲያን ውስጥ ለነበሩ የተለያዩ ሸክሞችን ሰብሰብ ብለው በጸሎት በኢየሱስ ፊት ማቅረብ ጀመሩ።
ዛሬ አገልግሎቱ በሁሉም ሰበካዎች ሰፍቶ የቅዱሳንን ልብ እያሳረፈ ለሚያገለግሉት እናቶች ጭምር በረከትና ፈውስ እየሆነ ይገኛል።
Truth Media
@Truthmedia_OneGod
የወጣቶች መክሊት አገልግሎት!
የወጣቶች አገልገሎት በሚል ስያሜ ወጣቶች ለአገልግሎት መንቀሳቀስ የጀመሩት በአጠቃላይ ከቤተክርስቲያን ምሥረታ ጀምሮ ነው ማለት ይቻላል። ያኔ የነበረው አካሄድ ዛሬ መክሊት አገልግሎት ተብሎ ከሚጠራው የአገልግሎት አካሄድ ጋር አንድ አይነት አልነበረም።
በወቅቱ የወጣቶች አገልግሎት ምስክርነትን፣ የወጣቶችን መንፈሳዊ ጉባኤ ማካሄድን፣ የእርስ በርስ የሕብረትና የመጽናኛ ፕሮግራሞችን ማከናወንን እና በጥቂቱ የወርሃዊ መዋጮ መሰብሰብን፣ የግድግዳ ላይ ተንጠልጣይ ጥቅሶችን በማዘጋጀት ሽጦ ለቤተክርስቲያን ማበርከት ላይ ያተኩር ነበር።
የወጣቶች አገልግሎት ስርዓትና ደንብ ወጥቶለት ራሱን ችሎ እንዲደራጅ የተደረገው ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ነው። ዓላማውም በጸሎት ቤት ግንባታ ላይ ሊውል የሚችል ገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ያተኮረ ነው። የወጣቶች አገልገሎት እንቅስቃሴውን በተጠናከረ መልኩ ሲጀምር ወቅቱ የኮሙኒስት ዘመን ስለነበር ከአ.ኢ.ወ.ማ (አብዮታዊ ኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር) ውጭ ያለ የወጣቶች እንቅስቃሴ ሁሉ በክፉ አይን የሚታይና ክትትል የሚደረግበት ሁኔታ ስለነበር በኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶች በሚል ስያሜ ጉባኤ ማድረግም ሆነ ገንዘብ መሰብሰብ እጅግ አስቸጋሪ ነበር።
በየሰበካው ተንቀሳቅሶ የወጣቶቹን አገልግሎትና መንፈሳዊ ሕይወት ለማሳደግ ለምሳሌ በከምባታና ሃዲያ ክፍል ውስጥ በወቅቱ አገልግሎቱን ሲመራው የነበረ የእግዚአብሔር ሰው የአካባቢውን ሰው አይነት ልብስ በመልበስ ቀን ቀን በእግሩ በመጓዝ ማታ ስብሰባዎችን እየጠራ በየመንደሮች የወጣቶች ስብሰባ በማድረግ በመንፈሳዊነትም ሆነ በአገልግሎቱ እንዲተጉ ወጣቶቹን ያደራጀበት ሁኔታ ነበር።
ይህ የእግዚአብሔር ሰው በ1978 ዓ.ም. ከምባታና ሃዲያ አካባቢ አገልግሎቱን በማደራጀት ላይ ቆይቶ ማሬ በምትባል ቦታ ዛፍ ጥላ ስር ተቀምጦ መኪና ሲጠብቅ የወጣቶች አገልግሎት በሚል ስያሜ ይህን አገልገሎት ለማስኬድ እየጠበበ መሄዱን እያሰላሰለ ሳለ ድንገት ወደ አዕምሮው “የመክሊት አገልግሎት” የሚል ቃል መጣ፤ የመክሊት አገልግሎት ይባላል ብሎም ወሰነ።
አዲስ አበባ ደርሶ ይህን ለቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ ሲነግራቸው በደስታ ተቀበሉት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የመክሊት አገልግሎት የሚለውን ስያሜ ጥቅም ላይ በመዋሉ በነጻነት መንቀሳቀስ አስችሏል። ሥራው እየተቀጣጠለ ሲሄድ የተሰደዱ፣ የታሰሩ፣ ተገደው ወደ ጦርሜዳ እንዲሄዱ የተደረጉ አልፎም የመክሊቱን ሥራ እየሠሩ እያሉ በጥይት የተገደሉ ወጣቶች ነበሩ።
አገልግሎቱ ለቤተክርስቲያን የጸሎት ቤት ግንባታ መዋሉ ራሱ መዝገብህ ባለበት ልብህ በዚያ ይሆናል ተብሎ እንደተጻፈ ወጣቶች በአገልግሎታቸው ምክንያት ልባቸው በእግዚአብሔር ቤት እንዲታሰር (እንዲጠጋጋ) አድርጎታል። አገልግሎቱ ለቤተክርስቲያን ዕድገት ያበረከተውን አስተዋጽኦ ስንመለከት እጅግ ብዙ የሚሆኑ የጸሎት ቤቶች ግንባታ፣ የአዋሳ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ለአብያተክርስቲያናት የተገዙ የድምጽ ማጉያዎችና የሙዚቃ መሣሪያዎች እንዲሁም ለልዩ ልዩ ጸሎት ቤቶች የግንባታና ዕድሳት እርዳታ መለገስን ጭምር ያካተተ አስተዋጽኦ አድርጎአል።
የአገልግሎቱ ዓላማ በተለያዩ ቦታዎች ለሚሰሩ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት ቤቶች የገንዘብና የጉልበት እርዳታ ማድረግ እንደመሆኑ በአሁኑ ወቅት ለቤተክርስቲያን ጸሎት ቤት ግንባታና የተለያዩ ቁሳቁሶች መሟያ የሚሆኑ በየዓመቱ የሚጨምርና የሚያድግ የሥራ ፍሬን በማበርከት ለቤተክርስቲያን ትልቅ በረከት እየሆነ ይገኛል።
Truth Media
@Truthmedia_OneGod
እንኳን አደረሰን!
ዘመናት
ዘማሪ ኤልያስ አምዴ
አዲሱ አመት የድል፣ የስኬት፣ ቤተክርስቲያን ወደታየላት ከፍታ የምትወጣበት አመት ይሁንልን!
መልካም አዲስ አመት ?
Truth Media
@Truthmedia_OneGod
መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና...
በቢሾፕ እሸቱ ድጅቆ
የዳውሮ ኮንታ ሰበካ ኃላፊ
በማስተዋል እንስማው ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ!
Truth Media
@Truthmedia_OneGod
እግዚአብሔርን የሚፈራ ከሁሉ ይወጣል!
የመከናወን ዘመን እንዲሆንልን እግዚአብሔርን እንፍራ!
“እግዚአብሔርንም መፍራት ባስተማረ በዘካርያስ ዘመን
እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ልብ አደረገ እግዚአብሔርንም በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር ነገሩን አከናወነለት።”
2 ዜና 26፥5
“ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና
ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ
።” 3ኛ ዮሐ 1፥2
በቄስ ወንደሰን ታደሰ
የቦሌ አርሞንዔም አጥቢያ መጋቢ!
በማስተዋል እንስማው!
Truth Media
@Truthmedia_OneGod
ክፉ ቀኖቼን
ዘማሪ በረከት ደስታ
እነዚያን ክፉ ቀናት በህይወቴ ያሳለፍከኝን
አልረሳም እኔስ ፈፅሞ እየሱስ ውለታህን
በክፉ ሆነ በደጉ ከጎኔ የማትለየኝ
እዉነተኛ ወዳጅ ነህ አለዉልህ ምትለኝ
አልረሳም እኔ ፍፁም ያንን ዘመን
በህይወቴ ያለፈውን ክፉ መከራውን
ስንቱን አሻግረኸኝ ዛሬን አደረስከኝ
የናዝሬቱ የሱስ ውዴ ክበርልኝ
እንዴት እረሳለው የህይወቴን መንገድ
አንተ ያሳለፍከኝን እኔን ስትፈላልግ
ከቶ ማይረሳኝ ውለታህ አለብኝ
ፍፁም አልዘነጋው ውዴ ክበርልኝ
ስወጣ ስወድቅ ፈጥነህ ስታነሳኝ
ስደክም ስዝል ብርታት እየሆንከኝ
እኔስ አልረሳም እኚያን ክፉ ቀናት
አንተ ነህ የታደከኝ ከዘላለም ጥፋት
ክፉ ቀኖቼን ባንተ አልፌ
አሎጣ ያልኩትን ሁሉ ወጥቼ
ዛሬ በቤትህ ይኸው ኖራለው
ህይወቴን እንካ ተቆጣጠረው
የኔ የምለው አንዳች የለኝም
ውሰደው በቃ አልፈልገውም
ለኔ ደስታዬ ስትከብርልኝ ነው
ከፍ ሳደርግህ ስባርክህ ነው
ከፍ በል (2x)
ከፍ በል ጌታዬ ከፍ በል
እኔስ አልረሳውም ውለታህን
በህይወት ዘመኔ ያሳለፍከኝን
እኔስ አልረሳውም ፍቅርህን
ለኔ ያሳየኸውን መልካምነትን
Praise with understanding
Truth Media
@Truthmedia_OneGod
ባለፉት ቀናት በአውሮፓ ሲካሄድ የነበረውን ኮንፍረንስ ለመከታተል ብዙዎቻችሁ በውስጥ መስመር በጠየቃችሁ መሰረት የስሶቱንም ቀን ፕሮግራም መከታተል ለምትፈልጉ ከታች ልንኩን እናስቀምጣለን፣ መልካም የበረከት ጊዜ እንዲሆን እንመኛለን።
https://www.youtube.com/live/eX7bh_jqqbc?feature=share
Truth Media
@Truthmedia_OneGod
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago