Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

Description
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡

ለማንኛውም አስተያየት @mzbot_bot
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago

10 months ago
10 months ago

መሠንቆ ዳዊት
ክራር ሮቤል
ዘማሪ በርሱ ፍቃድ

10 months ago
10 months, 3 weeks ago

በሶስቱም መንፈሳዊ አገልግሎት እያደረስን ነው ከምትወጡ አያምልጣችሁ ሼር አርጉላቸው።

ሰው ነንና በፀሎት እንተጋገዝ።
አገልጋይ ወንድሞች እሕቶች ካላችሁ በውስጥ መስመር አግዙን በአገልግሎት።

የዝግጅት ክፍሉ ዋና አዘጋጅ።
@መዝሙረ ማኅሌት

10 months, 3 weeks ago

ሼር አርጉላቸው ለወንድሞቻችን ለእሕቶቻችን።
3ቱንም መንፈሳዊ ቻናሎቻችንን።

@zemarian መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩
@zemariann መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
@zemariian መዝሙረ ማኅሌት

10 months, 3 weeks ago

በቅርቡ በመዝሙረ ማኅሌት

ምዕራፍ ዜማ ምቅናይ
የዘወትር እስከ ዕለተ ሠንበት።
ይጠብቁን።
@zemarian

10 months, 3 weeks ago

መርዓዊ ደብረ ኀይል ቅዱስ ሚካኤል
ባሕር ዳር ድባንቄ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
አዘዞ አይራ ቅዱስ ሚካኤል
40. ዛራ ቅዱስ ሚካኤል (ባሕር ዳር አጠገብ ሐሙሲት)
ጉመር ደብረ ኅሩያን ቅዱስ ሚካኤል
ካምባ ቅዱስ ሚካኤል
ሳንቃ ወይራ ቅዱስ ሚካኤል
ዳስ ዓምባ ቅዱስ ሚካኤል
45. ላሐ ቅዱስ ሚካኤል
46. ጊራራ ቅዱስ ሚካኤል
47. መለኮዛ ቅዱስ ሚካኤል
48. ዋይሎ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
@zemarian

#share #share #share

10 months, 3 weeks ago

አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ኮተቤ፥ ካራ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ኮተቤ (ካራ)
፴፰. ረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔ ዓለም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ካራ ቆሬ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ → አለም ባንክ → ካራቆሬ (ረጲ)፡፡
፴፱. ፉሪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ጋራ ኦዳ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ጋራ ኦዳ፡፡
፵. ሐመረ ወርቅ ማርያምና አርሴማ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ወርቁ ሰፈር፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቃሊቲ → ወርቁ ሰፈር፡፡
፵፩. ቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ሰፈረ ገነት፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መርካቶ) → ሰፈረ ገነት፡፡
፵፪. ቦሌ ቡልቡላ ምስካበ ቅዱሳን አባ ሳሙኤል ዘዋልድባና ቅዱስ አማኑኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ቡልቡላ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ሳሪስ አቦ → ቡልቡላ መድኀኔ ዓለም (ኮንዶሚኒየም)→ ወደ ላይ በአስፓልቱ የ5 ደቂቃ የእግር መንግድ፡፡
ወይም፤ ከቦሌ መድኃኔ ዓለም → ቡልቡላ (በአዲሱ መንገድ)
፵፫. አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔ ዓለም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ አቃቂ፥ ጋራው መድኃኔዓለም፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቃሊቲ → አቃቂ፡፡
፵፬. ሣሎ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሣሎ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቃሊቲ → ሣሎ፡፡
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ጥንታውያን #፲፱ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #እየላ_ቅዱስ_ሚካኤል፤ (#የ3 #ሺህ_ዓመታት_ባለታሪክ፤ ከታቦተ ጽዮን ጋራ በ980 ከክ.ል.በ. ታቦቱ የመጣ፤ መሥዋዕተ ኦሪት ይቀርብበት የነበረ፤ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መጥቶ የባረከው)
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ → ግዳን (እየላ)፡፡
፪. ሰሜን ትግራይ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል፤ (መሥዋዕተ ኦሪት ይቀርብበት የነበረ)
አድራሻው፤ ሰሜን ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ሰሜን ትግራይ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎሃ ጽዮን ወይም ደብረ ማርቆስ በሚለው መኪና ዐባይ በረሃ ላይ መውረድ፤
፫. ጎሐ ጽዮን ቅዱስ ሚካኤል፤ (በ4ኛው ክፍለ ዘመን በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን የተሠራ)
አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ፍቼ ሀገረ ስብከት፥ ጎሐ ጽዮን፥ ዐባይ በረሃ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎሃ ጽዮን ወይም ደብረ ማርቆስ በሚለው መኪና ዐባይ በረሃ ላይ መውረድ፤
፬. ሸኖ ጎልባ ደብረ ሣሕል ቅዱስ ሚካኤል ደብር፤ (በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን የተመሠረተ)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ሰኖ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ሸኖ፡፡
፭. መላሃይዘንጊ ቅዱስ ሚካኤል፤ (በ8ኛው ክፍለ ዘመን የታነጸ)
አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ፍቼ ሀገረ ስብከት፥ ጎሐ ጽዮን፥ ዐባይ በረሃ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎሃ ጽዮን ወይም ደብረ ማርቆስ በሚለው መኪና ዐባይ በረሃ ላይ መውረድ፤
፮. ላስታ ላሊበላ ቤተ ሚካኤል፤ (በ11ኛው ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ የታነፀ፥ ከ11ዱ የላስታ ላሊበላ ፍልፍል ሕንጻዎች አንዱ)
አድራሻው፤ ላስታ ሀገረ ስብከት፥ ላሊበላ ከተማ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ፡፡
፯. ገርዓልታ ዋሻ ቅዱስ ሚካኤል፤
አድራሻው፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ገርዓልታ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → ገርዓልታ፡፡
፰. ሚካኤል ዓምባ፤ (በ11ኛው ክፍለ ዘመን የታነጸ)
አድራሻው፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ውቅሮ፥ (በመቀለና በአዲግራት መሃል)፥ አጽቢ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ውቅሮ → አጽቢ፤
፱. ባሕር ዳር ሽምብጥ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ (በ13ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተ)
አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት፥ ባሕር ዳር ከተማ፥ ቀበሌ 13
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር ከተማ → ሆስፒታል በሚል ታክሲ (ዲፖ ጋር)፡፡
፲. እስቴ አበርጉት ቅዱስ ሚካኤል ፤ (በአፄ ዓምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት በልጃቸው በአቡነ ፊልሞና የተሠራ ታሪካዊ ጠበል ያለበት)
አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ እስቴ ወረዳ፥ ደስኳ አጋማች ቀበሌ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → እስቴ፡፡
፲፩. በሮ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል፤ በ16ኛው መ/ክ/ዘመን መጨረሻ የተመሠረተ
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ሳይንት ወረዳ
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → አማራ ሳይንት፡፡
ወይም፤ ከጎጃም በመርጠሉ ማርያም → አማራ ሳይንት
፲፪. ጎንደር ፊት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ በአፄ ፋሲለደስ ዘመነ መንግሥት ተመሠረተ፤
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡
፲፫. ጎንደር አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡
፲፬. ተንታ ደብረ ብርሃን ቅዱስ ሚካኤል፤ (ንጉሥ ሚካኤል በሚያስደንቅ ሁኔታ ያሠሩት)
አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ አምባሰል፥ ተንታ ወረዳ፥ ጠዓት ቀበሌ፥ እሜገኝ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ጻድቃኔ፡፡
፲፭. አጃና ቅዱስ ሚካኤል፤ (በቀስተ ደመና ጠበል አጥማቂው)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ተጉለት፥ አጃና፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ጻድቃኔ → አጃና፡፡
፲፮. ቦንብ አርግፍ ቅዱስ ሚካኤል (ሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት፤ የጁ ወልዲያ)
፲፯. ቦረዳ ቅዱስ ሚካኤል
፲፰. ዋሻ ቅዱስ ሚካኤል (ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ ኢቲሳ)
፲፱. አንኮበር ቅዱስ ሚካኤል (ሰሜን ሸዋ ሀ/ስብከት)
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፵፰ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
1.. ግሸን ደብረ ከርቤ ቅዱስ ሚካኤል
ጎሚስታው ሚካኤል (ትግራይ)
እንዳ ቅዱስ ሚካኤል (ትግራይ)
መቀለ ቅዱስ ሚካኤል
5. ጾረና ቅዱስ ሚካኤል (ኤርትራ)
ዓለም ገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
ደብረ ዘይት /ቢሾፍቱ/ ደብረ አሚን ቅዱስ ሚካኤል
ዱከም ቅዱስ ሚካኤል
ናዝሬት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
10. ድሬዳዋ ቅዱስ ሚካኤል
ጭሮ አሰበ ተፈሪ ቅዱስ ሚካኤል (ድሬዳዋ፥ አሰበ ተፈሪ)
ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል
አርባ ምንጭ ላከ ኢየሱስና ሚካኤል
ዲላ ቅዱስ ሚካኤል
15. አሰላ ደብረ ሰላም ቅድስ ሚካኤል
ጂጂጋ ቅዱስ ሚካኤል
ሚዛን ቴፒ ደብረ ኀይል ቅዱስ ሚካኤል
ቦንጋ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል
ኢሉባቦር ሌንቃ ቅዱስ ሚካኤል
20. እነሞርና ኤነር ወረዳ ቅዱስ ሚካኤል (ጉራጌ ሀ/ስብከት)
አሰቦት ደብረ ወገግ ቅዱስ ሚካኤል (ምሥ. ሀረርጌ ሀ/ስብከት)
ሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል
ኩክ የለሽ ዛሪያ ቅዱስ ሚካኤል
ጅሩ ሞቶሎኒ ቅዱስ ሚካኤል (ጅሩ አርሴማ ውስጥ)
25. መንዝ ይገም ቅዱስ ሚካኤል
መሐል ሜዳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
የሲጠር ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል (መንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ)
ወንጪት ቅዱስ ሚካኤል (በነብር የሚጠበቅ)
ሸዋሮቢት ጫሬ ቅዱስ ሚካኤል
30. ወልዲያ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
ኮምቦልቻ ቅዱስ ሚካኤል
ደሴ ጢጣ ደብረ ሲና ቅዱስ ሚካኤል
ራያ ቆቦ ቅዱስ ሚካኤል
ደብረ ማርቆስ ዋሻው ቅዱስ ሚካኤል
35. ደብረ ማርቆስ አጠገብ ብዕርና ቅዱስ ሚካኤል
ደምበጫ ቅዱስ ሚካኤል

10 months, 3 weeks ago

#ሰኔ_፲፪   በዓለ ተዝካሩ #ለቅዱስ_ሚካኤል ሊቀ መላእክት   (#፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን፤ ወደፊት ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚያንጽ ጌታችን የነገረውና የሕንጻዎቹን አሠራር ዝርዝር የነገረው በዚሁ እለት ነው፡፡)

ꔰ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ꔰ

#ሰኔ_፲፪ #መከበሩ_ስለምንድን_ነው_ቢሉ_
ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር፤ ንሥረ አርያም የሚባል፥ ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ፥ ንዑድ ክቡር የሆነ ፥ የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ነው  እንዲሁም  የሌሎችም ቅዱሳን መታሰቢያ ቀናቸው  (ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት) ፡፡ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ነው  እነርሱም፤
#share
፠፩. በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል፤
፠፪. ባሕራንን ያዳነበት፤
፠፫. የአስተራኒቆስ ሚስት ቅድስት አፎምያን ያዳነበት፤ በዓለ እረፍቷም በዚሁ እለት ነው፤
፠፬. በግብፅ ሃገር ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ ቅዳሴ ቤቱን ያከበረበት፤
፠፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት፤
፠ ሐናፄ መቅደስና በሰማያት ያለ ምሥጢርን የተመለከተ ቅዱስ ላሊበላ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በዓለ ዕረፍቱ ነው፤
፠67ኛ ሊቀ ጳጳስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት ዘእስክንድርያ እረፍቱ ነው፤
፠የእስክንድርያ 6ኛ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ዮስጦስ (ወንጌላዊና ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የክርስትና ጥምቀትን ያጠመቀው፥ ዲቁናና ቅስናን የሾመው) እረፍቱ ነው፡፡
/ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት/

ማብራሪያ፤
#፩. ቅዱስ ሚካኤል በፈቃደ እግዚአብሔር ከዲያብሎስ ጋር ተዋግቶ ያሸነፈበት፤ አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በዲያብሎስ ምትክ ሊቀ መላእክት ሆኖ የተሾመበት እለት በመሆኑ ነው፡፡ ቀድሞ ከ100 ነገደ መላእክት ኃይላት የሚባሉ የ10 ነገደ መላእክት አለቃ ነበር፤ በዚህች ቀን ግን የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ አጋእዝት የተባሉትንና ሳጥናኤል(ሰማልያል) ይመራቸው ለነበሩት 10 ነገዶች በተጨማሪ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በአጠቃላይ ለሌሎችም 100 (99ኝ) ነገደ መላአክት አለቃ ሁኗል፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡

#፪. ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት፤ ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /312 - 326/ በግብፅ ሃገር ንግሥት ክሌዎፓትራ ‹‹ሳተርን›› ለሚባለው ያሠራችውንና ጣዖት ይመለክበት የነበረውን ቤተ ጣዖትን አፍርሶ በቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን አግብቶ በዓሉን በታላቅ ክብር ያከበረበት እለት ነው፡፡

#፫. ባሕራንን ያዳነበት
ሊቀ ጳጳሳት እለ እስክንድሮስ የተሠራውን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ከሚያከብሩ ምእመናንን አንዱ የባሕራን አባት ነበር፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር፤ በዚህ ሰው ላይ ላይ ጥላቻ ያደረበትና ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጸጋ ጐረቤት ነበረው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር፡፡

ይህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውም በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ። ሚስቱንም ጠርቶ ‹‹በጐ ስራ ከመሥራት ለድኃ ከመመጽወት ቸል አትበይ! የቅዱስ ሚካኤልንም በዓል በየወሩ ከማክበር አትቦዝኝ፤ ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት  ቀን ከፍ ባለ ሥነ ሥርዓት እንድታከብሪ አደራ እልሻለው›› አላት፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ ሚስቱ ፀንሳ ነበር። ይህም ደገኛ ሰው በሰላም ዐረፈና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ። ሚስቱም የመውለጃዋ ሰዓት በደረሰ ጊዜ ታላቅ ጭንቅ ላይ ኾነች እርሷም መልአኩን ቅዱስ ሚካኤል እንዲደርስላት ተማጸነችው በሰላምም ተገላገለች፡፡ መልኩ በጣም ያማረ ልጅ ወለደች። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ያን ሕፃን ባረከውና ‹‹ቸርነት ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት እርሻውንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዟል›› አለ። ያን ጊዜ ያ ባለጸጋ በሴትዮዋ ቤት መስኮት አጠገብ ሆኖ ሁኔታውን ሁሉ ይመለከት ነበርና ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ልቡ በታላቅ ሐዘን ተነካ፤ ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ብላቴናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ነበር።

ብላቴናውም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ እናቱ በጣም ችግር ፀናባት፡፡ ባለጸጋው እኔ ጋር ተንከባክቤ ላሳድገው ብሎ ከእናቱ ከተቀበለ በኋላ፤ በልጅ ቁመት ልክ ሳጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አግብቶ በላዩ ላይ ቆለፈበትና ሣጥኑን ወስዶ ከባሕር ጨመረው፤ እንዲሁም የሣጥኑን ቁልፍ መክፈቻ አብሮ ወረወረው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሰጥም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈ ከዚያች አገር ርቃ ወደምትገኝ የባሕር ወደብ ደረሰ።

በባሕሩ አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ያንን ሣጥን ባየው ጊዜ ከባሕሩ አወጣውና ወደ ቤቱ ወስዶ ሣጥኑን ቢከፍተው ያ ባለ ፀጋ ሊገድለው ያሰበውን ሕፃን በሣጥኑ ውስጥ አገኘው።  ባየውም ጊዜ እጅግ ተደስቶ በባሕር ውስጥ ስላገኘው ስሙን "ባሕራን" ብሎ ሰየመውና እንደ ልጁ አድርጐ ይንከባከበው ዘንድ ወሰነ፡፡

ከባሕራን ሀገር የበግ ጠባቂው አገር የዐሥር ቀን ጐዳና የሚያስኬድ ርቀት ነበረው። ከብዙ ዓመታት በኋላ ያ ባለ ጸጋ ሰው ለንግድ ከሀገሩ ወጣ፡፡ በጉዞውም ላይ ሳለ ፀሐይ ስትገባ ከዚያ የበግ ጠባቂው ዘንድ ደረሰ። በግ ጠባቂውንም ‹‹ወንድሜ ሆይ ባንተ ዘንድ የማድርበት ቢኖር ታሳድረኝ ዘንድ እለምንሃለው፣ ኪራዩንም እከፍልሃለው›› ብሎ ጠየቀውና ያ በግ ጠባቂ ወደ ቤቱ አስገባው። ባለጸጋውም ገብቶ ጥቂት ካረፈ በኋላ በግ ጠባቂው ያን ብላቴና ባሕራን ብሎ ሲጠራው በሰማ ጊዜ ‹‹ልጅህ ነውን?›› ብሎ ጠየቀው። በግ ጠባቂውም ‹‹አዎን ይህ አሁን ጐልማሳ ሆኖ የምታየው ወጣት ገና ሕፃን ሆኖ ሳለ በሣጥን ተከቶ ከባሕር ውስጥ ተጥሎ አግኝቼው ወስጄ አሳድጌዋለሁና ልጄ ነው›› አለው። ባለጸጋውም በባሕር ውስጥ የጣለው ሕፃን መሆኑንም ስላወቀ ይህንን ነገር በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ፤ ይገድለውም ዘንድ ፈለገ፡፡ በበነጋውም መንገዱን ለመሄድ ሲዘጋጅ ልዩ ልዩ ምክንያት (ሰይጣናዊ ሐሳብ) በመፍጠር በግ ጠባቂውን ‹‹ወንድሜ ሆይ አንድ የማስቸግርህ ጉዳይ አለኝ ይኸውም በቤቴ የረሳሁት ነገር ስላለ ሄዶ መልእክት ያደርስልኝ ዘንድ ይህን ብላቴና እንድትሰጠኝ ነው የድካሙንም ዋጋ ሃያ ወቄት ወርቅ እከፍላለሁ›› አለው።

11 months, 1 week ago
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago