★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago
"ጾም ፈቃደ ሥጋን በማድከምና ፈቃደ ነፍስን በማጎልበት ምሕረተ እግዚአብሔር መሻታችንን የምናሳይበት መንፈሳዊ ማመልከቻ ነው"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የጾመ ፍልሰታ አስመልክተው ያስተላለፉት አባታዊ ቃለ በረከት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በሀገር ውስጥና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ!
በማሕፀነ ማርያም በፈጸመው እውነተኛ ተዋሕዶ የሰው ልጅን ከኃሣር ወደ ክብር የመለሰ እግዚአብሔር አምላካችን፣ እንኳን ለሁለት ሺሕ አሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት ጾመ ቅድስት ማርያም በደኅና አደረሰን አደረሳችሁ!
‹‹ተፈሥሒ ኦ ምልእተ ጸጋ፣ ተፈሥሒ እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፡- ምልእተ ጸጋ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ በእግዚአብሔ ዘንድ ሞገስን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ››
(ሉቃ. 1÷28-30")
የክብር አምላክ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ከወደቀበት ዐዘቅተ ኵነኔ የሚያድንበት ዕድል እንዳዘጋጀ በብሉይ ኪዳን በስፋት ተገልጿል፤ የማዳን ሥራውም ከሰው ወገን ከሆነች ቅድስት ድንግል በሚወለደው መሲሕ እንደሚፈጸም አስረድቶአል፤ የማዳን ቀኑ በደረሰ ጊዜም መልእክቱን በፊቱ በሚቆመው በቅዱስ ገብርኤል በኩል ልኮአል፤ ቅዱስ ገብርኤልም የተነገረውን መልእክት ለድንግል ማርያም አድርሶአል፡፡
ቅዱስ ገብርኤል ለድንግል ማርያም እንዲነግር ከታዘዘባቸው መካከል ‹‹ጸጋን የተመላሽ ደስተኛይቱ ሆይ÷በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ›› የሚል አስደናቂ መልእክት ይገኝበታል፡፡
የተወደዳችሁ ሕዝበ ክርስቲያን!
ከእግዚአብሔር መንጭቶ በቅዱስ ገብርኤል በኩል ለድንግል ማርያም የተነገረ ይህ መልእክት፣ የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር ከመግለጽ ባሻገር ለሰው ልጆች ሁሉ ያለው ፋይዳ በእጅጉ የላቀ ነው፤
‹‹ጸጋ›› የሚለው ቃል እንደ ቅዱስ መጽሐፍ አስተምህሮ ያልተወሰነ፣ ገደብና ቅድመ ሁኔታ የሌለው ስጦታን ሲያመለክት ‹‹ሞገስ›› የሚለው ቃል ደግሞ ተወዳጅነትን ተደማጭነትን ተሰሚነትን የሚያመለክት የክብርና የባለሟልነት መግለጫ ቃል ነው፡፡
እነዚህ ቃላት ከእግዚአብሔር ዘንድ በቅዱስ ገብርኤል በኩል ለቅድስት ድንግል ማርያም ተነግረዋል፤ የእግዚአብሔር ቃል የማይለወጥ ነውና ቃላቶቹ ለድንግል ማርያም ቃል ኪዳን ሆነው የተሰጡ ናቸው፤ የተሰጡበትም ምክንያት ሰውን ለማዳን ሥራ እንዲውሉ እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡
ምክንያቱም የእግዚአብሔር የማይናወጥ ፈቃድ ሰውን ማዳን ነውና፤ በመሆኑም ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር በተሰጣት በዚህ ገደብ የሌለው ቃል ኪዳኗ ሰውን ልትታደግ በቅታለች፤ይህም በቃና ዘገሊላ ባደረገችው ምልጃ በጭንቀት የተዋጡትን ሰርገኞች እንዴት እንደታደገች በቅዱስ ወንጌል ተጽፎ እናገኘዋለን፤ ቅድስት ድንግል ማርያም ቀድሞውኑም ከፍ ያለ ሞገስ ተሰጥቶአታልና የሰርጉ አሳላፊዎችን ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› በማለት ስታዝዝ እናያለን፤ ይህ ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ አስደናቂ የትድግና ስጦታ ነው፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!
የድንግል ማርያም የጸጋ ስጦታ በብሥራተ ገብርኤል ተገልጾ፣ በቃና ዘገሊላ ተተግብሮ በዕለተ ስቅለት ‹‹እነሆ ልጅሽ፣ እነኋት እናትህ›› በሚል መለኮታዊ ማኅተም የታተመ ነው፤ ይህ ቃል እሷ እናታችን መሆኗን፤ እኛም ልጆችዋ መሆናችንን ያረጋገጠ ማኅተመ ቃል ኪዳን ነው፤ የቃል ኪዳኑ ይዘት እሷ በአማላጅነቷ እንደ ልጅ ልትንከባከበን እኛም እንደ እናት ልናከብራትና ልንማፀናት የሚገባን መሆኑን ያሳያል፤ የእናትነትና የልጅነት ማረጋገጫ የሆነ ይህንን የቃል ኪዳን ማኅተም ሊሰርዝም ሆነ ሊፍቅ ሊደመስስም የሚችል ኃይል የለም፡፡
ይህ ጸጋና ሞገስ በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም የሚቀጥል እንጂ የሚገደብ አይደለም፤ ሞት፣ ቦታና ዘመንም አይወስኑትም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን በሞት በቦታና በዘመን አይገደብምና ነው፤ ‹‹ኪዳኑንም ለዘለዓለም ያስባል›› ተብሎ የተገለጸውም ለዚህ ነው፤ (መዝ. )111÷5)
መንፈስ ቅዱስም በእሷ አንደበት ‹‹እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ነሽ ይሉኛል›› በማለት የተናገረው ይህንን ለማስረዳት እንደሆነ ማስተዋል ያሻል፡፡
በእግዚአብሔር ተሰጥቶ፣ በቃል ኪዳን ታትሞ፣ በቅዱስ ገብርኤል ተብራርቶ፣ በጌታችን ተረጋግጦና በሐዋርያት በኩል የተላለፈልን፣ ሰውን ማዳን ግቡ የሆነ የድንግል ማርያም ምልጃ ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ በሁሉ ያለች፣ አንዲትና ቅድስት ኦርቶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ሺሕ ዓመታት ያህል አምና እና ተቀብላ ስትጠቀምበት ኖራለች፤ አሁንም በዚሁ ትቀጥላለች፡፡
በኦርቶዶክሱ ዓለም ዛሬ የሚጀመረው የጾመ ማርያም ሱባዔም የዚሁ ጭብጥ ማሳያ ነው፤ ዋናው መልእክቱም ድንግል ማርያም በተሰጣት ጸጋና ሞገስ በጸሎቷ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትንና ይቅርታን የምታሰጠን ስለሆነች እሷን በመማፀን ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ የሚል ሆኖ ይመሰጠራል፡፡
የተወደዳችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ልጆቻችን!
ጾም ፈቃደ ሥጋን በማድከምና ፈቃደ ነፍስን በማጎልበት ምሕረተ እግዚአብሔር መሻታችንን የምናሳይበት መንፈሳዊ ማመልከቻ ነው፤ ጾም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ነው፤ ቀደምት አበው በጾም ምክንያት ከጥፋት ድነዋል፤ የለመኑትንም አግኝተዋል፤ ምስጢርም ተገልጾላቸዋል፤ ዲያብሎስም ድል አድርገውበታል፡፡
እኛም ዛሬ ጾምን ስንጾም በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን ብሎም በዓለም ዙሪያ ሁሉ ስጋትን እየጫረ ያለው የጥፋት እንቅስቃሴ እግዚአብሔር እንዲያስቆምልን ከልብ በመጸለይ ሊሆን ይገባል፤ ይህንንም ስናደርግ በጸሎት ብቻ ሳይሆን ንስሐ በመግባትና ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል እንደዚሁም የሰላም የፍቅርና የዕርቅ ሰው ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት በመቆም ሊሆን ይገባል፡፡
ችግሮችንና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በምክክር ለመፍታት የሚደረገው ጥረትም በእጅጉ ሊደገፍ ይገባል፤ ግጭትና ጦርነት ከሚያጠፋን በቀር ሊያተርፍልን የሚችል አንዳች ጥቅም የለም፡፡
በመሆኑም በየትኛውም የሀገራችን አካባቢ ያላችሁ ልጆቻችን እባካችሁ ለሰላም ለውይይትና ለሰው ልጆች መብት መከበር ቅድሚያ ስጡ፤ ግድያ፣ ዕገታ፣ አብያተ ሃይማኖትን መዳፈር፣ ዘረፋና ቅሚያ፣ የሴት ልጅን መድፈርና ሰውን ማንገላታት አቁሙ፤ እነዚህ ድርጊቶች ሰብአዊነትን ዝቅ የሚያደርጉ፣ እግዚብሔርን የሚያስቆጡ፣ በታሪክም የሚያሳፍሩ ናቸው፤ እነዚህን ሳናርም የምንጾመው ጾም ትርጉም ስለሌለው ንስሐ ገብተን ከእንደዚህ ያለው ድርጊ ርቀን ጾሙን መጾም ይገባል፤ ይህን ስናደርግ ጾማችን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ ይኖረዋል፡፡
በመጨረሻም
የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ በተለይም በጾመ ማርያም ሱባዔ በንስሐና በጸሎት የሚያሳልፉ ሕዝበ ክርስቲያን ስለ ሃይማኖት መጠበቅ፣ ስለሀገር ሰላምና አንድነት፣ እንደዚሁም ስለሕዝቦች ደኅንነትና ጤንነት አጥብቀው እንዲጸልዩ በእግዚአብሔር ስም መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
መልካም የሱባዔ ወቅት ያድርግልን
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም
ዋሽንግተን ዲሲ - ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ
፪. በቦታ ያለመርጋት (አጽንኦ በዓት) አለመኖር፡-
ትልቁ የአንድ መናኝ ፈተና አጽንኦ በዓት ማለትም በዓትን አጽንቶ ወዲያ ወዲህ ሳይሉ ከቦታ ቦታ ከመዘዋወር ተቆጥቦ በገዳም መኖር አለመቻል ነው፡፡ የምንኩስና ጀማሪው አባ ጳውሊ ይሁን እንጅ መልክና ቁመና የሰጠው አባ እንጦንስ እንደሆነ ይነገራል፡፡ አባ አንጦንስ ከ፪፻፶፩-፫፻፶፮ ዓ.ም ለ፻፭ ዓመት የኖረ አባት ሲሆን በአባ እንጦንስ እንደ መነኮሰ የሚነገርለት ቅዱስ አትናቴዎስ ጽፎታል ተብሎ የሚታመነው የአባ እንጦንስን ታሪክ አባ እንጦንስ በ፹፭ የምናኔ ዓመታት ከበአቱ የወጣው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ይባላል፡፡ (ገድለ አባ እንጦንስ)
አንድ ጊዜ በመክስምያኖስ ስደት የደረሰባቸውን ክርስቲያኖች ለማጽናናት በ፫፻፲፩ ዓ.ም ሲሆን ሁለተኛው አርዮሳውያን በአትናቴዎስ ላይ በተነሱ ጊዜ በ፫፻፴፰ ዓ.ም ለተመሳሳይ ዓላማ ወጥቷል፡፡ በሕንጻ መነኮሳትም ‹‹በአቱን ትቶ ከቦታው ውጭ የሚያድር መነኩሴ አይኑር›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ (ክፍ. ፪ ቁጥ ፭) ሕንጻ መነኮሳት በዚህ ሳይወሰን መነኮሳትን የሚያረክሱ አምስት ነገሮች ብሎ ከሚዘረዝራቸው አንዱ ‹‹ከቦታ ቦታ ከሀገር ሀገር መዘዋወር›› ነው ይላል፡፡
‹‹በገዳም መኖር ማቅ መልበስ፣ በዝናር መታጠቅ ይገባል›› የሚል ሕግ ቢኖርም አሁን ያለው ችግር ከገዳም መውጣት ከገዳም ገዳም መዘዋወር አይደለም፤ እርሱስ ቢሆን በተሻለ ነበር፡፡(ፍት.መን. አንቀጽ ፲ ቁ ፫፻፶፯) ከገዳም ወደ ከተማ ከከተማም ወደሌላው ከተማ፣ ከሀገር ወደ ውጭ ሀገር ያለው የመነኮሳት ፍልሰትና እንቅስቃሴ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ‹‹ለመነኩሴ ከተማ መግባት፣ አደባባይ ተቀምጦ መፍረድ፣ ምስክርነት ዋስነት አይገባውም፡፡ ለምውት ይህ ሁሉ ሥራው አይደለምና›› ተብሎ ቢጻፍም አሁን ላይ ብዙ ገዳማት ባዶ ናቸው፤ ጥቂቶቹም ጥቂት መነኮሳት ብቻ ይኖሩባቸዋል፤ መናንያኑ ከተሞችን ሞልተውታል፤ ግብረ ምነኩስናን የሚፈጽሙበት፣ ለአገልግሎት ለትሩፋት የሚፋጠኑበት ጊዜ የላቸውም፤ በጣም ከዓለማዊው ሰው ባነሰና በሚያስደነግጥ በዓለማዊ ሐሳብና ግብር ላይ ተጠምደው ይታያሉ፤ ያሰቡትን የሚያሳካ ፍላጎታቸውን የሚያረካ ነገር ሳያገኙ ሲቀሩ ባልተገባ አኳኋን ባልተገባ ቦታ የሚገኙ ወንጀል የሚሰሩ በርካታ መነኮሳት የታዩበት ዘመን ነው፡፡ (መ-ምዕዳን ገጽ ፻፶፪)
፫. በዚህ ዓለም ሐሳብ መሸነፍ፡-
በገንዘብ ፍቅር መሸነፍ ሁሉን ትተው ፍጹም ይሆኑ ዘንድ የተከተሉ መነኮሳት ትተውት ከሄዱት ዓለም ተመልሰው ሀብትና ባለጸግነትን በመሻት ብዙዎች ወድቀዋል፡፡ አንድ መነኩሴ/መነኩሲት እንዲመንኑ የገፋቸው አምላካዊ ቃል ‹‹ሂደህ ገንዘብህን ሁሉ ሸጠህ ለነዳያን መጽውት፤ በሰማይም ድልብን ታከማቻለህ ና ተከተለኝ›› የሚለው ነው፡፡ (ማቴ.፲፱፥፳፩) አሁን ውሻ ወደ ትፋቱ እንዲመለስ ተፍተውት የሄዱትን ሀብት ፍለጋ ብዙዎች በገንዘብ ፍቅር ወድቀዋል፡፡ አርአያ ምንኩስናን ፈተና ላይ ጥለዋል፤ ስለሚነዱት መኪና ስለሚሰሩት ፎቅና ምድር፣ ስለሚያጌጡበት ወርቅና ብር የሚጨነቁ፣ ይህን ክፉ መሻታቸውን ለማሳካትም በየፍርድ ቤቱ በየመንግሥት ተቋማቱ ደጅ ተሰልፈው በክርክርና በንትርክ በአሕዛብ መድረክ ዳኝነት የሚፈልጉ ብዙ መነኮሳትን እንመለከታለን፡፡
በአንድ ወቅት የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ማኔጅመንትን ያጨናነቁ መነኮሳትና የደብር አለቆች መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ተሰራጭቶ ተመልክተናል፡፡ (መገናኛ ብዙኃናት) ይህ ብቻ ሳይሆን እነዚህ መነኮሳት በሕይወት ሲያልፉ የሚነሳው የወራሽነት መብት ጥያቄና ሙግት በራሱ የቤተ ክርስቲያኗን ክብር የሚያዋርድ፣ ምእመናንን አንገት የሚያስደፋ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ በተራ መነኮሳት ሳይወሰን በአንዳድ ጳጳሳትም ዘንድ ይስተዋላል፡፡
በሥልጣን ፍቅር መውደቅ፡- የአንድ መናኝ (መነኩሴ) ሥልጣንን ሹመትን መሻት አንዱ የፈተናው ምንጭ እንደሆነና እንዲጠነቀቅ መጽሐፍ ይመክራል፡፡ ፍትሐ ነገስሥት እንዲህ ይላል፤ ‹‹የሹመት ፍቅር ሰይጣናዊ በሽታ ነውና በዚህ በሽታ ላይ የወደቀ ሰው ካህናትና ሹማምንት ሊሆኑ በሚገባቸው ላይ ቀናተኛ ይሆናል፡፡ ሰው ጠቅሶ ያነሳሳባቸዋል፡፡ በእነርሱ ሹመት ይተካ ዘንድ ሞታቸውን ይወዳል፡፡ ሹመቱ ባልሆነለት ጊዜ በርሱና በነርሱ ችግር ይፈጠራል፡፡ ከዚህ መጥፎ ፈቃድ ይራቅ እንጅ፡፡›› (ፍ.መ አ.፫፣ ቁ. ፫፻፹፭) ብዙ መነኮሳት በዛሬዋ ቤተ ክርስቲያናችን ተፈትነው የወደቁበት ፈተና ነው፡፡
አለቃ ለመሆን፣ ጸሐፊ ለመሆን፣ የመምሪያ ኃላፊ ወይም ሌላ ሥልጣን በመሻት ቦታቸውን ለመንጠቅ፣ በተሾሙት ፋንታ ለመሾም፣ በተቀቡት ቦታ ለመቀመጥ አባቶቻቸውንና ወንድሞቻቸውን ለመወንጀል በዓለም ያሉ ተባባሪዎችን ለማግኘት የጠላት በር ሳይቀር ያንኳኳሉ፤ የተከበሩትን ያዋርዳሉ፤ በሐሰት ክስም ይከሷቸዋል ክፉዎችን ቀስቅሰው ያነሳሱባቸዋል፡፡ አሁን ደረጃውን ከፍ አድርጎ እስከ ጵጵስናም ደርሷል፡፡ መጽሐፍ ግን ‹‹ወኢያፍቅር ምንተኒ ዘዝንቱ ዓለም፤ የዚህን ዓለም ምንም ምን አይውደድ›› ነው የሚለው፡፡ (መጽሐፈ ምዕዳን ገጽ ፶፩)
በሥጋ ምቾት መጠመድ፡- ብዙ መነኮሳት በሥጋዊ ምቾት ውስጥ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን እንዳንበላ፣ እንዳንጠጣ፣ እንዳንለብስ፣ እንዳናጌጥና እንዳይመቸን አይደለም የፈጠረን፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ አላፊ ጠፊ መሆናቸውን ተገንዝበን ሁሉንም በመጠን በአግባቡ በሥርዓት ብናደርገው በሚያልፈው ዓለም ውስጥ የተውነው ምቾት በማያልፈው ዓለም ውስጥ ዋጋ እንደሚያሰጠን በተለይ ለመነኮሳት ሲሆን የበለጠ መሆኑን በቀኖና መጻሕፍት ተጽፎ እናነባለን፡፡ እንኳንስ መነኮሳት የዚህን ዓለም ውበቱን ድምቀቱን፣ መብሉን መጠጡን ትተው የመነኑትን፣ ራሳቸውን በፈቃዳቸው ከሙታን ዓለም የቆጠሩትን ቀርቶ ሕዝባውያንም በሚበላ በሚጠጣ በሚለበስ ነገር ሁሉ በመጠን እንዲኖሩ ታዟል፡፡ ይሁንና አሁን ላይ ብዙዎች በሥጋ ምቾት በመብል መጠጥ ተጠልፈው ፈተና ብዝቶባቸው ለምእመናንም ለቤተ ክርስቲያንም ኃፍረት ሲሆኑ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ሕንጻ መነኮሳት ‹‹መነኩሴን ከሚያረክሱ ነገሮች አንዱ ከመጠን በላይ መብላትና መጠጣት ነው››ይላል፡፡
መጽሐፈ ምዕዳን ደግሞ ‹‹መነኩሴ የእንጦንስን የመቃርስን የቅዱሳንን ገድል ይመልከት፤ እንዲጸና ምግብ ይክፈል፡፡ አይምረጥ፤ የመጠጥንም ነገር የጽም ያህል ይጠጣ፡፡ ሥጋ አይብላ፤ ወይን ጠጅ አይጠጣ፡፡ ለመነኩሴ ምሳ የለውም፡፡ ዓመት እስከ ዓመት ጾም ነው እንጅ መነኩሴ ምሳውን ከበላ ሴት ከወንድ ጋራ አድራ በማኅፀኗ ልጅ እንዲፀነስ በሰውነቱ ሦስት ነገሮች ይፀነስበታል፡፡ ትዕቢት፣ ምንዝርነት፣ ቁጣ ይመጣበታል፤ ከዚህ በኋላ ሰይጣን ይሰለጥንበታል፤ ቆቡን ከመቅደድ፣ ዲቃላ ከመውለድ ያደርሰዋል፤ የንጽሕና መሣሪያ ከመብል መከልከል ነው›› ይላል፡። (ገጽ ፻፶፩) አሁን ሁሉም ነገር እየሆነ ነው፡፡ ብዙዎች በሆዳቸው ተገምግመዋል፤ በትዕቢትም፣ በቁጣም፣ በምንዝርነትም እየተፈተኑ ያሉበት ዘመን ነው፡፡
ይቆየን!
**‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ››
ክፍል ሰባት**
ተወዳጆች! እንዴት ሰነበታችሁ? እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ!
በክፍል ስድስት “ክብረ ምንኩስና ትናንት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ክብርና ሞገስ ያስገኘውን የቅድስና ፍሬና ያሳረፈውን አሻራ” አንስተን ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡
በዚህ በክፍል ሰባት ደግሞ ምንኩስና ዛሬ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እያጋጠመው ያለውን ተግዳሮት ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡ ቀደም ብለን እንደ ተመለከትነው ምንኩስና ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊውን፣ ከሰው ይልቅ የመላእክትን ግብር መምረጥ፣ ፍጹም ሆኖ ፍጹም የሆነችውን መንግሥት ለመውረስ ሁሉን ትቶ መመነን፣ ከሰው ከዓለም መለየት፣ በገዳም በአጽንዖ በአት፣ በግብረ ምንኩስና መወሰን መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ በዘመናችን ምንኩስና በዘርፈ ብዙ ተግዳሮት ውስጥ ይገኛል፤ የተወሰኑ ችግሮችን ለማሳየት ያህል፡-
፩. የምንኩስና ሥርዓትን ተከትሎ አለመመንኮስ፡-
በገዳም ሕግ አንድ መናኝ ሁሉንም ትቶ ወደ ገዳም ሲገባና “እመነኩሳለሁ” ሲል በገዳሙ ያለውን ሥርዓተ መነኮሳት መማርና መጠበቅ፣ የተቀመጠውን የአበው ሥርዓት ማክበር፣ በጉልበቱ እንጨት ሰብሮ፣ ውኃ ቀድቶ፣ ከብት ነድቶ፣ ቡኮ አብኩቶ፣ ዳቤ ጋግሮ በእርድና መነኮሳትን መርዳት ይገባዋል፡፡ ‹‹መነኮሳትን ሳይረዱ “እመነኩሳለሁ” ማለት ሳይበጡ መታገም ነው፡። ምክንያቱም ከሁሉም እርድና ይበልጣልና ከእርድና በኋላ ቢመነኩስ ይጠቅማል›› ይላል መጽሐፈ ምዕዳን፡፡ (ገጽ ፻፶) ይሁን እንጅ በአሁኑ ሰዓት የአመክሮ ጊዜ የሌላቸው ገዳማትን አበው መነኮሳትን በጉልበታቸው በእርድና ያላገለገሉ፣ የኋላ ታሪካቸውና የወደፊት ትልማቸው ያልተገመገመ፣ አንዳዶቹም የትና በማን እንደመነኮሱ የማይታወቁ፣ ተጠየቅ የሌለበት የምንኩስና ሥርዓት ቤተ ክርስቲያንን ፈትኗታል፡፡
መሠንቆ ዳዊት
ክራር ሮቤል
ዘማሪ በርሱ ፍቃድ
በሶስቱም መንፈሳዊ አገልግሎት እያደረስን ነው ከምትወጡ አያምልጣችሁ ሼር አርጉላቸው።
ሰው ነንና በፀሎት እንተጋገዝ።
አገልጋይ ወንድሞች እሕቶች ካላችሁ በውስጥ መስመር አግዙን በአገልግሎት።
የዝግጅት ክፍሉ ዋና አዘጋጅ።
@መዝሙረ ማኅሌት
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago