ተግሳጽ

Description
በዚህ channel ለህይወት አስፈላጊ የሚባሉ ተግሳጾች ይለቀቃሉ ከኛ የሚጠበቀው መማር ብቻ ነዉ ። ጥር ፪፯ ፪1፫
ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇
@uraman4u13
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 7 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month, 1 week ago

1 month ago

ተወዳጆች

ለጸሎት ጊዜ የለኝም ማለት እጅግ አስጸያፊና ዘግናኝ ኃጢዓት ነው። አንድ ሰራተኛ(ባሪያ) አሰሪዬን(ጌታዬን) የማነጋገሪያ ጊዜ የለኝም ቢል እንዴት ያለ ድፍረት ይሆን..??

ፍጡሩስ ከፈጣሪው ጋር ለመነጋገር ጊዜ የለኝም ቢል ምን ይደንቅ! ዋጋ ቢስ ለሆኑ ምንም ረብ ለሌላቸው ንትርኮች ከበቂ በላይጊዜ አለህ። ምነው ታድያ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን እንደ ጊዜ ማባከን ቆጠርከው..?

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

1 month ago

ጥበብ ማን ነው ?

ጥበብ ሀይሉ እግዚአብሔር ነው ።

1 month ago

'ወዳጄ...!

ከፍ ከፍ ትል ዘንድ ትሑት ሁን፤ ባለጸጋ ትሆን ዘንድ ድኻ ሁን፤ ትጠግብ ዘንድ ረኃብን ውደዳት።

ጤነኛ ትሆን ዘንድ የመብል ሸክምን አቅልል፤ ትከብር ዘንድ ተዋረድ፤ ደስ ይልህ ዘንድ አልቅስ፤ ትኖር ዘንድ ሙት፤ ትበራ ዘንድ ትጋ።

ትድን ዘንድ በማስተዋል ጸልይ፤ ኃጢአትህን ይቅር ይልህ ዘንድ አብዝተህ ጹም፤ ታገኝ ዘንድ ፈልግ፤ ታተርፍ ዘንድ ለመነገድ ተፋጠን።

ባለጸጋ ትሆን ዘንድ በብርሃናውያን መንገድ ትመላለስ ዘንድ መስቀልህን ተሸከም፤ ሥጋህን ጥላት ነፍስህን አንጻት።

ሰናይ ቀን🙏

3 months ago

*ተወዳጆች

ከመጠጥ በላይ አዕምሮን የሚያዞር ነገር አለ ?

በዚህ ዓለም እኮ

አለምን የሚያሸንፉ መጠጥ, ሴት እና ንጉስ ናቸው ።
ምንም ጀግና ሊቅ ቢሆን ሲጠጣ በገዛ እጁ ይወድቃል።
ብዙ ጠላቶች ተኩሰው ያልጣሉትን
መጠጥ በ3ት ኩባያ ይጥለዋል።
ይህ እኮ ነው የሰው ልጅ አዕምሮ
ለምንድን ነው ግን የምትሰክሩት ?

መጽሐፍ የሚለው

እባብ ከነደፈው ሰው መጠጥ የነደፈው ሰው ይበልጣል ነው የሚለው ።

ለምሳሌ ፦

ተረከዙ ላይ ቢነድፈው
ወደ ላይ እንዳይወጣ ባቱ ላይ እናስረዋለን

የሰከረን ሰው ምን ላይ እናስረዋለን ጠቅላላ ተመርዟላ
ምን ላይ ሊያዝ ይችላል።

በእውነቱ በጣም አስቸጋሪ ነው

የመስቀሉ ልጅ ከሆናችሁ ስካር አቁሙ**?***

3 months, 1 week ago

ተወዳጆች

ስለ መተላለፋችን ምንም ዓይነት ቅጣት የማንቀበል ቢሆን ኖሮ \ እግዚአብሔር ሕሊናን የሚያህል ፈራጅ ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር አሳይቷል::

*እግዚአብሔር ስለ መተላለፋችን ከዚህ በኋላ በሚኖረው ሕይወት የሚጠይቀን ቢሆንም የማያዳላውን ዳኛ ሕሊናን ግን በውስጣችን ፈጠረ።

ይህ ዳኛ በዚህ ዓለም ሳለ ስለ ኃጢአቶቻችን እየወቀሰ በማረም ከሚመጣው ፍርድ እንድናመልጥ ይረዳናል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ያለው ይህንኑ ነው:- «ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር» (1ኛ ቆሮ 11:31)።

ራሳችንን ብንመረምር በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አይፈረድብንም ነበር ለማለት ነው፡፡ስለ መተላለፋችን ምንም ዓይነት ቅጣት የማንቀበል ቢሆን ኖሮ \ እግዚአብሔር ሕሊናን የሚያህል ፈራጅ ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር፡፡

በዚህም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር አሳይቷል:: እግዚአብሔር ስለ መተላለፋችን ከዚህ በኋላ በሚኖረው ሕይወት የሚጠይቀን ቢሆንም የማያዳላውን ዳኛ ሕሊናን ግን በውስጣችን ፈጠረ።

ይህ ዳኛ በዚህ ዓለም ሳለ ስለ ኃጢአቶቻችን እየወቀሰ በማረም ከሚመጣው ፍርድ እንድናመልጥ ይረዳናል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ያለው ይህንኑ ነው:- «ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር» (1ኛ ቆሮ 11:31)።

ራሳችንን ብንመረምር በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አይፈረድብንም ነበር ለማለት ነው፡፡*

3 months, 1 week ago

?ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ?

ተወዳጆች ኾይ

በነፍሱ መከራ የሚቀበል የትኛው ነዉ።
የተሳደበ ሰዉ ወይስ የተሰደበ ሰዉ?
አወ የተሰደበ ሰዉ መሆኑ ግልጽ ነዉ።

ምክንያቱም

አንድን ሰዉ ሐጢአተኛ የሚያሰኙት ከዉስጥ ከሰዉየዉ የሚመነጩ ክፋቶች እንጂ ከአፍአ የሚመጡ አይደሉምና

?ከድርጊቱ ራሱ የታወቀ ነዉ

ስሜት መባሉም ለዚህ ነዉና።

?ዳግመኛም በተሳዳቢው ላይ በሚፈጥሩት ነገር የታወቀ ነዉ።

ማለትም

ተሳዳቢው ሲቆጣ

?አይነ ልቦናው ይታወራልና
?አንጎሉም ይታወካልና
? የጤና መታወክ ሳይቀር ሌሎች ስፍር ቁጥር የሌለው ጉዳት ይደርስበታልና

ስለዚህ

መከራ እየተቀበለ ያለው ተሰዳቢው ሳይኾን ተሳዳቢዉ
መኾኑን በዚህ መረዳት ይቻለናል ።

?የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ? አማላጅነት አይለየን

3 months, 1 week ago

"ከምግባራት ሁሉ ታላቁ ጸሎት ነው ነገር ግን የእርሱ መሠረቱ ጾም ነው፡፡ የምንጾምበት ምክንያት ርኩስ የሆነውን የሰይጣንን መንፈስ በነፍሳችን ውስጥ እንዳያድር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥጋችንን ለጾም ባስገዛነው ጊዜ ነፍሳችን ነፃነትንጥንካሬንሰላምንንጽሕናን እንዲሁም እውቀትን ለመለየት እንድትበቃ ትሆናለች፡፡"

(ጻድቁ ዮሐንስ ዘክሮስታንድ)

3 months, 1 week ago

ተወዳጆ

*እኔ ተስፋዬ ጤና አይደለም
እኔ ተስፋዬ ሀብት አይደለም
እኔ ተስፋዬ የሰው መውደድ አይደለም
እኔ ተስፋዬ ክርስቶስ ነው ።

ክርስቶስን እስካለኝ ድረስ የፀሎቴ ምላሸ
ከጌታየ ጋር እኖራለሁ አለበት

እንጂ ልክ እንደ ኤሳው ሰይጣን ሁልጊዜ ስትተኙ
ውዳሴ ማርያም ስትደግሙ ዳዊት ስትደግሙ
ንስኃ ስትገቡ ንስኃ ገባህ አልገባህ ምን አምጥተሀል ቢላችሁ
ለሰይጣን ይሄን መልሱለት ።

እግዚአብሔር አይለወጥም
እግዚአብሔር በቃኝ አይባልም
እግዚአብሔር አይሰለችም
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ደስታ ነው።
የዚህ ዓለም ደስታ ሀዘን ተክቶ ነው የሚሄደው
እግዚአብሔር ግን ሀዘን ተክቶ የማያልፍ ዘላለማዊ ደስታ ነው።

የድንግል ማርያም እራስ ግን እግዚአብሔር ነው
ህሊናዋ ውስጥ ከእግዚአብሔር ውጭ አስባ አታውቅም
ስለዚህ ምን ትባላለች የእግዚአብሔር ከተማ ትባላለች

ርዕሰ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን❣️*

3 months, 1 week ago

?ቀጭኔ ልጇን ቆማ ስለምትወልደው ገና ከማህፀኗ አንደወጣ ቀጥታ መሬት ላይ ይፈጠፈጣል፤

?ከወለደችውም በኋላ ከመንከባከብ ይልቅ ብዙ ጊዜ እንደ ኳስ እየጠለዘች ታፈርጠዋለች፤

? እጣ ፈንታው ስለሆነ እየወደቀ ይነሳል።

? ይሄን ድብደባ ለብዙ ጊዜ ታደርግና የሚደርስበትን ጫና ተቋቁሞ ቀጥ ብሎ መቆም ሲጀምር ልጇን መምታት ታቆማለች።

?ይሄን እውነታ ዛሬ ገና የሚሰማ ሰው "ምን አይነት ጭካኔ ነው ግን?" ሊል ይችላል፤

?ግን ህፃኑ ቀጭኔ እንደዚህ ሆኖ ካልጠነከረ ነገ ተልፈስፍሶ ከጠላት ማምለጥ አቅቶት በአውሬዎች ሊበላ እንደሚችል እናት ጠንቅቃ ታውቃለች፤

?ስለዚህ በወለደ አንጀቷ ታንገላታዋለች።

?ፈጣሪም ዛሬ የሚፈትነን ነገ ለሚመጣ ከባድ ችግር ራሳችንን እንድናዘጋጅ ነው።

? አንዱን የህይወት ፈተና ባለፍክ ቁጥር አይበገሬ ማንነትህ ጎልቶ ይወጣል፤

?ስለዚህ ለምን ይሄ ችግር ገጠመኝ ብለህ እንዳትማረር ወዳጄ!

3 months, 2 weeks ago

ተወዳጆች

እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ነው

አባታችን እግዚአብሔር ነው
እናታችን እግዚአብሔር ነው

እግዚአብሔር በሁሉ ይሆናል።

*"አንተ አቡነ ወአንተ እምነ " እንዲል

አባታችን አንተ ነህ እናታችን አንተ ነህ

የፈጠረን ያስገኘን እና በእኛ ዘንድ
የሚያስፈልገንን ሁሉ ተክቶ
መሆን የሚችል አምላክ እግዚአብሔር ነው ።*

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 7 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month, 1 week ago