ግጥም

Description
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

ADMIN 👉 @Big_jor
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

1 day, 6 hours ago

#የማንችለው_በዛ

በሳቅ መጋረጃ ሀዘን ተደብቆ
ጥርስ ከላይ ከላይ በማስመሰል ስቆ
ልብ እህ እህ ይላል በስቃይ ዋይታ
ለማለፍ ሲያጣጥር ሁሉን በዝምታ።
የደረሰበትን በጥርስ ሳቅ ከልሎ
ውስጥ እረመጥ ፈጀው የማይቻል ችሎ።
ላያስችል አይሰጥም ይባል ነበር ድሮ
የማንችለው በዛ እንጃልኝ ዘንድሮ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ

2 days, 6 hours ago

#ኑ_እውሸት_እንስራ !

ዘጠኝ ቁና ውሸት
ከአንድ ቁና እውነት
አሙቀን አቅልጠን
ቀይጠን አላቁጠን
በተዋበ ተንኮል በረቀቀ ሴራ
ኑ! እውሸት እንስራ!
ቅጥፈት ነው እንዳይሉ፤
የእውነት መአዛ ያውዳል በሩቁ
ሀቅም ነው እንዳይሉ፤
መጠርጠር አይቀርም እያደር ሲነቁ!
እስከ ጊዜው ድረስ ...
እስኪተላለቁ እርስ በ'ርስ ተጋጭተው
ወይ እስኪያስተውሉ ከሰመመን ነቅተው ...
ከጓዳቸው ገብተን
የቻልነውን በልተን
ቀሪውን ሸክፈን አርገን በስልቻ
እንጓዝ በስውር እንሂድ ለብቻ
በጊዜ እናምልጥ እንምጠቅ እንብረር፤
አሻራ ሳንተው ...
ክንፋቸውን ሰርቀን ፥ ከአይን እንሰወር!
ዘጠኝ ቁና ውሸት
ከአንድ ቁና እውነት
አሙቀን አቅልጠን
ቀይጠን አላቁጠን
በተዋበ ተንኮል በረቀቀ ሴራ
ኑ! እውሸት እንስራ!!
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በርናባስ ከበደ

3 days, 6 hours ago

#ጥሬ_ጨው

መስለውኝ ነበረ ፣
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች ፣
ለካ እነሱ ናቸው ፣
ጥሬ ጨው..ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች ፣
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ
መታሸት-መቀየጥ
ገና እሚቀራቸው ፣
“እኔ የለሁበትም !”
ዘወትር ቋንቋቸው ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ

6 days, 6 hours ago

#መሄድሽን_ሳስብ

ያለፉትን ቀኖች
ዳግም አልፌያቸው
.......ከኋላቸው ሄጄ
አንቺን የምትመስል
........አንቺኑ ወድጄ
መኖርን እያሰብኩ
በጣም እስቃለሁ
ለካ...
ወደኋላ መኖር
የህልም እንጀራ ነው፤
ለነገሩ...
ለነገሩ ያው ነው
ካላንቺ መኖሩም
ያው አለመኖር ነው።
ብቻ...
ጩህ... ጩህ... ይለኝና
ዝም ባለ ልቤ
ዝም'ብዬ ጮሀለው
በጠራራ ፀሀይ
ቀኔን አጨልማለሁ፤
ጉድ እኮ ነው ጎበዝ!!
ዝም ብሎ መጮህ
ዝም ብሎ ማውራት
ሰሚ በሌለበት
ሳይጠሩ መጣራት።
ብቻ...
መሄድሽን ሳስብ...
እኔ የማላውቀው
ደርሶ ያላማከረኝ
ቅልስልስ እንባዬ
ባይኔ ስር ይፈሳል
ችሎ ላይመልስሽ
አመለኛው እግሬ
ቁጭ ብሎ ይነሳል፤
ጉድ እኮ ነው ጎበዝ!!
ያላዘዙት እንባ
ካይን አልፎ ሲያነባ
ያላነሱት እግር
ቁጭ ብሎ ሲዳክር፤
ብቻ...
ትንግርት ነው ሁሉ
አንቺ ከሄድሽ ወዲያ
የሚሆነው ሁሉ፤
ግና ምን ዋጋ አለው...
ከኛ ፍቅር በላይ
ከኛ ምኞት በላይ
የሱ ትክክል ነው¡¡
በዝች ግዑዝ አለም...
አንቺ አንቺን ሆነሽ
እኔ እኔን ሆኜ
ጊዜን ብንተውንም
ደራሲና አዘጋጅ
እግዚአብሔር ነውና
ከሱ ውጪ አኖንም።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
አዱኛ አስራት

1 week ago

#ፍቅር_ጥላ_ሲጥል

በገና ቢቀኙ
ሸክላ ቢያዘፍኑ
ክራር ቢጫወቱ…..
ለሚወዱት ምነው
ሙዚቃ ቢያዜሙ
ቃል ቢደረድሩ
ጌጥ ውበት ቢፈጥሩ
ቤት ንብረት ቢሠሩ
አበባ ቢልኩ
ምነው ቢናፍቁ
አገር ቢያቋርጡ
ቢሄዱ ቢርቁ
አመት ቢጠብቁ
ለሚወዱት ምነው?
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገብረ ክርስቶስ ደስታ

1 week, 1 day ago

#መቼ_ይፈውሳል

በህይወት ውጥንቅጥ ያኮረፈ ስሜት፣
በሀሰት ጭብጨባ የተደበቀ እውነት፣
በግዜ ወለምታ ጉዳት ያጋጠመው፣
ወጌሻው ማን ይሆን አሽቶ የሚያድነው?
በማስመሰል ዜማ በግፍ ቅኝት ክራር፣
በውብ ቃል አስውበው ቢባል ፍቅር ፍቅር
መቼ ይፈውሳል ቃል ብቻ ቢንጋጋ
በደልን የሚሽር የእውነት ቀን ካልነጋ
የመከፋት ምንጩን ልብ ሆኖ መነሻው
ይቅርታ ብቻ ነው ለመርዙ ማርከሻው
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ

2 months, 3 weeks ago

#ተራርቆ_ከእውነት

ነፃነትን ሸጦ ገንዘብን ፍለጋ
በረከሰ ስደት በረከሰ ዋጋ
ህሊናን ለውጦ በሆድ አቆማዳ
እውነትን አስይዞ መግባት ትልቅ እዳ
ጎተራው ላይሞላ መሶቡ ላይፋፋ
ለኩርማን እንጀራ በውሸት ሲለፋ
አወይ ሰው ምስኪኑ ከትላንት አይማር
ውዱን እየሸጠ ለርካሽ የሚኖር
እርካታ ሳይኖረው ባለው ሳይደሰት
ሆዱ ይመራዋል ተራርቆ ከእውነት
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

2 months, 3 weeks ago

#ትዝታ

ወደሽኝ ወድጄሽ ትዳር መሥርተን
ከእኛ አብራክ የወጡ ልጆች አፍርተን
ሰላምና ፍቅር እየተጎናጸፍን
በደራው ቤታችን በምቾት ኑረን
      የእኛን ኑሮ ማማር የምቾት ሁኔታ
      እያዩ የቀኑ ነዝተው አሉባልታ
      በትዳራችን ውስጥ በነዙት ሐሜታ
      አጉል ተበጣብጠን ደረስን ልንፋታ
ደስ ብሎን የኖርነው በሳቅ በጨዋታ
አይዋሽ አይነቅዝ ያለፈው ትዝታ
የሰው ወሬ ንቀን የሰውን ሐሜታ
በሰላም እንኑር በፈጠረሽ ጌታ
        ዕጣችን ከሆነ ተለያይተን መኖር
        ላንቺም ለኔ ደስታ ለልጆቹ ክብር
        ትዝ ይበለንና የኖርነው በፍቅር
        እንድንጠያየቅ መኮራረፍ ይቅር
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደራሲ ታደለ ብጡል

2 months, 3 weeks ago

#መንፈሴን_አመመኝ!!

ሰምቶ ለሚያሰማ ችግሬን ነግሬ
ስሜ አደባባይ ነው የሚውለው ዛሬ
ይረዳኛል ያልኩት ያመንኩት ቢከዳኝ
አልቅስ አልቅስ አለኝ በድንገት ሆድ ባሰኝ
ለካስ እህ እያለ ችግሬን መስማቱ
ሊረዳኝ አይደለም አቤት ሰው ከፋቱ
ደግፈኝ ያልኩት ሰው ገፍትሮ ቢጥለኝ
ከስጋዬ በላይ መንፈሴን አመመኝ።
ከአረገልኝ በላይ ያደረገኝ ብሶ
ሆዴን እየባሰው ይቀናኛል ለቅሶ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

3 months ago

#እድሜ_ለሷ

አየሁ ራቁቷን
ውበቷን
እሳቷን
ልቤ በጣም ፈራ ድፍረቴ መከነ
ከጭኖቼ መሐል ድንኳን ተደኮነ
ና ትላለች ባይኗ
ሚሳኤል ጡቶቿን ተፊቴ ደግና
ፈራሁ ጠፋኝ አቅም
ከራዲዮኔ ውጭ ጡት ጠምዝዤ አላውቅም።
ከምኔው አቀፍኳት ከንፈሬስ እራሰ
ቋሚው ብቻ ቀርቶ ድንኳኔ ፈረሰ
ከምኔው እሳቷን አቀፍኩት እስክነድ
እንዴት በዚህ ፍጥነት ተሰራሁ እንደወንድ
በውበቷ ገዳም ገባሁኝ ምናኔ
አጎንባሹ ቀናሁ ለቀሪ ዘመኔ
ፍቅሯን በገሞራ ለውሳ ቀይጣ
ወንድ አርጋ ሸኘችኝ ሰራችኝ አቅልጣ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago