Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ከመጽሐፍት መንደር💠💫

Description
አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። ማንብብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና
🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩
🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨
🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥

ለማንኛውም አስተያየት
@manbabemuluyadergal_bot
We recommend to visit

ማራኪ ცЯムŋの የጫማ መሸጫ ቻናል

✔ማራኪ ብራንድ የፈለጉትን ጫማ በፈለጉት ሳይዝ እና ጥራት እናቀርባለን!
With free delivery
🔰Contact me
👉 @Maraki2211 or Call 0913321831
Admin
@maraki2211

💯Spammed users⚠
@Marakibrand2bot

Last updated 4 days, 12 hours ago

ማንኛውም መሸጥ የምትፈልጉትን ስልክ እንገዛለን
በ +251909255008 ወይም
+251912739699 ላይ ያናግሩኝ
@Abd_phone

Last updated 1 week, 1 day ago

🔑Quotes

“Life is generally meaningless beyond the choice we have to assign how meaningful it can be. I don’t fear death because I know this and therefore am able to live with peace of mind.”
@Quote_U
...

Last updated 2 years, 9 months ago

3 Tage, 1 Stunde her

🔪🔪🔪ግድያው 🔪*🔪*🔪

ክፍል 3**

መቼም ዝምተኛ ሰው ምንም እንደማይሰማው የሚያስበው **ሁሉም ነው ከባለቤቱ ውጪ። አሁንም እውነት እውነት እየመሰለው አይደለም። እትዬ አበሩ መጥተው "አቤልዬ እኔ አፈር ልብላ ና እስኪ ግባ አፍህ ላይ እህል ቢጤ አድርግ" አሉት

ቀና ብሎ አያቸው 'ከመቼው እንደዚህ ገረጡ' አለና እናቱን አያቸው ሰው ከአጠገባቸው ዞር ባለ ቁጥር ፊታቸውን እየቧጠጡ አሰቸግረው ሁለት ሰዎች ናቸው ይዘዋቸው የተቀመጡት ብሩክን ሲያየው ጭንቅላቱን ይዞ ይጮሀል ሊያረጋጉት የሚሞክሩትን ሰዎች "እኔ እኮ ሌላ ወንድም የለኝም" ይላቸዋል**።

ሰዎች መቼም እሱን ሳይታዘቡት አይቀሩም 'ወንድሙ ቁጭ ብሎ ብሩክ እንደዚ ሲሆን' ብለው አባቱን ግን የገረማቸው አይመስሉም ምናልባት እሳቸውም እንደሱ መሞቱን አልተቀበሉት ይሆናል ድንኳን ምናምን እያሉ ተለቅ ካሉ ሰውዬ ጋር እየተነጋገሩ ነው። ወይም ደግሞ ውስጣቸው በሀዘን እየደቀቀ ማሳየት አይችሉ ይሆናል።

"እ አቤልዬ?" አሉት ለካ እስካሁን አጠገቡ ቆመዋል። እስካሁን ያዘኑት ይበቃል ደግሞ በእኔም ይዘኑ እንዴ ብሎ እሺ ብለሏቸው ተከትሏቸው ወደ ሳሎን ገባ። ዛሬ እንደዚ የእድርተኛ እና የሰፈር ሰው ሊተራመስበት ትላንትና እነሱ ብቻ ነበሩ የነበሩት

ማታ ቡና ተፈልቶ ሲንጫጩ አርሰናል አሸነፈ ብሎ አየሮጠ ሄዶ ወንድሙን ሲያበሽቀው ወዲያው ማኪ መኖሯን ሲያይ አፍሮ መመለሱን አስታውሶ ፈገግ አለ።  "አቤል?" አለችው ማክዳ በለቅሶ ብዛት ያ ቀይ ፊቷ ቲማቲም መስሎ "ማኪዬ" ብሎ ሄዶ አቀፋት "ለምንድነው? እሱን ለምን? ላገባው ነበረ እኮ" ደረቱ ላይ እዬዬዋን አስነካችው።

እውነት ነው ማለት ነው? ሞቷል በቃ እሺ ማኪን ለማን ጥሎ ብሩክ ብቻ እኮ ነው የማይወዳት እንጂ በፍቅራቸው የማይቀና አልነበረም። በቃ ጥሏት ሄደ? ቆይ ግን እውነትም ለምን ገደሉት? መጀመሪያ ማን ነው የገደለው?

nani

3 Tage, 9 Stunden her

[🔪🔪🔪ግድያው 🔪🔪🔪

ክፍል 2

ቅዳሜ ጠዋት ረፋድ ላይ የትልቅ ሴት ጩኸት ተሰማ። አብዛኛው ሰው ገና ከመኝታውም ሳይነቃ ስለነበረ ጩኸታቸው ሲቀሰቀሳቸው 'ለመርዶ ራሱ ረፍዷል እኮ" እያሉ እየተሯሯጡ ሲሄዱ

እትዬ አስካለ ራሳቸውን ይዘው ላንቃቸው እስኪላቀቅ ያቀልጡታል "ልጄን... ልጄን... ምነው ምን አደረጋችሁ?...ጧሪዬን... ጧሪዬን ቀባሪዬን... ታሞ በተኛ ባስታመምኩ?... አሁን ከአሁን ዳነልኝ ብዬ አይን አይኑን ሳይ..." አለቃቀሳቸው የሁሉንም ሆድ አባባው

የሞተው ልጃቸው በጩቤ ተወጋግቶ አልጋው ላይ በደም ተጨማልቆ አልጋው ላይ ተንጋሏል። ሰፈርተኛው ለቅሷቸውን ተቀላቅሎ ሰፈሩ ተናጋ። እትዬ አስካለ የያዛቸውን ሁሉ እጃቸውን እየመነጨቁ ሙሾ ሲያወርዱ ቆይተው አበሩ ስትመጣ

"አበሩዬ ልጄን ነጠቁኝ እኮ?!...  ልጄን!!..." ብለው ተቃቅፈው ማልቀስ ጀመሩ አበሩም ተቀብላ "አስካልዬ ለኔም እኮ ልጄ ነበረ ከብሩኬ ለይቼ አላየውም ነበረ" ጓደኛሞቹ እናቶች ሌላውንም ሰው አልቅሰው አስለቀሱት

በዚህ ሁሉ ወከባ ውስጥ የተረሳው አቤል ለራሱ ጥግ ላይ ድንዝዝ ብሎ ተቀምጧል "በቃ ወንድሜን ገደሉት በቃ ወንድም የለኝም ማለት ነው" እያለ ጭንቅላቱ ያቃጭልበታል

የሰፈሩ ወጣቶች ፖሊስ ጠርተው የሰፈሩን ሰዎች እያረጋጉ እያለ የአበሩ ልጅ ብሩክ ደግሞ አይኑ በርበሬ መስሎ "እንደዚህ ያደረገውን ውሻ ላግኘው ብቻ" እያለ የሲሚንቶ ግርፍ የሆነውን ግንብ ሲደበድብ ሳይታወቀው እጁ በደም ተለውሶ እሱን ማረጋጋት ራሱ ሌላ ስራ ሆነ

nani](https://t.me/manbabemulusewyaderegal)

3 Tage, 14 Stunden her

🔪🔪ግድያው 🔪🔪

ክፍል 1
መርማሪ ፖሊስ ሆኖ መቆየቱ ይሆናል መሰል እንደ ወታደር ሰዓት ላይ ያለው አቋም ጠንካራ ነው። አብረውት የሚሰሩትም ሰዎች ወይ ለምደውት ወይም ደግሞ ጭቅጭቁ መሯቸው ከመውጫ ሰዓታቸው በፊት ውልፍት አይሉም።
አሁን ግን ሚኪያስ ከሚባለው አዲስ የሰራ ባልደረባው ጋር መስማማት አልቻሉም። ከስራ ለመውጣት ያለው ጥድፊያ ነው መሰል ሲያየው አይጥመውም "ጋሽ ብስራት ደህና እደር" ብሎ ሰዓቱን እያስተካከለ ወጣ። " 'ጋሼ' ይለኛል አያፍርም? ምን ያህል ብንበላለጥ ነው" አለ በሆዱ

ገና ወጥቶ ብዙ ሳይቆይ ፅዳቷ  ስንታየሁ እየተጣደፈች መጣችና "አዬ ሚኪ ወጣ እንዴ? መውጣቱን አይቼ ላፀዳ ስገባ ቢሮው ውስጥ ወድቆ አግኝቼ ነው የአይን ጠብታ ናት መሰለኝ" ብላ ትንሽ ብልቃጥ አቀበለችው

"እኔ ነገ እሰጠዋለሁ ይሄ ልበ ቢስ" ተቀበላት።ተቀብሏት ኪሱ ጨምሮት ወደ ቢሮ ተመለሰ።

ሁሉንም ነገር መጨራረሱን አይቶ ቆልፎ ወጥቶ ቁልፉን ኪሱ ሲያስገባ ብልቃጡን ነካው። አውጥቶ ከኪሱ አገላብጦ ሲያየው ጠብታ አልመስል አለው። ላዩ ላይም ምንም አልተፃፈበትም። በዛውም ይሄ ተንኮለኛ ምን በኪሱ ይዞ እንደሚዞር ጉዱን ልይ ብሎ ብልቃጧን ሳምሶን (የላብራቶሪ ቴክኒሻኑ) ጋር ይዞለት ሄደ።

"ሳሚዬ የኔ ምርጥ ጓደኛ" አለው ሲሸነግለው እሱም ሊወጣ በሩን ሲቆላልፍ ስለነበረ "ቸኩያለሁ ምንም እንዳትለኝ" አለ ተኮሳትሮ "ሳሚሻ ነገ ራት በእኔ ነው" ሲለው "በአንድ አፍ" ብሎ ከፍቶ አብረው ገቡ

"ይቺ ነገር እይልኝ እስኪ" አልኩት "እሺ" ብሎ ተቀብሎ ማይክሮስኮፑ ላይ ጠብ አድርጎ ሲያይ ቆየና

"እንዴ እንዴ ከየት አመጣሀት ባክህ" አለኝ ፈገግ ብሎ ከአጉሊ መነፅሩ ቀና ሳይል "ምነው ምንድነው?" አልኩት ሰፍ ብዬ

"<truth serum> እኮ ነው" አለኝ "ምንድነው እሱ" አልኩት ሰምቼው ስለማላውቅ "ድሮ አጋቾች ለማናዘዝ የሚጠቀሙበት አሁን ተከልክሎ ቀርቷል" አለኝ

ይሄ መናጢ መች አጣሁት ጭራሽ

nani

2 Monate, 1 Woche her

የ18 አመቷ ታዳጊ አሳዛኝ ወግ
በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
  ደራሲ ናቲ
የ18 አመቷ ታዳጊ አሳዛኝ ወግ
ክፍል 30
ህሊናየ ከሀሳብ በማረፉ ሳልሳቀቅ በሙሉ የራስ መተማመን ያይኔ አበባን አንገቷ ስር ሳም አደረኳትና እጄን ደረቷ ላይ ጣል አድርጌ ከአጠገቧ ሞት የሆነ እንቅልፍ ወስዶኝ ዝርር ብየ ተኛሁ።
ስነቃ ከጠዋቱ 2፡30 ሆኖ ነበር። እሱንም ያይኔ አበባ ባትቀሰቅሰኝ ኑሮ በጭራሽ አልነቃም ነበር። "ናቲ ቁርስ ሰርቼልሀለሁ። እናትህ የሆድህን ነገር አደራ እንዳለችህ ነግረኸኝ የለ!" አለችኝ ብርድ ልብሴን እስከ ደረቴ ድረስ ወደታች እየገፈፈችብኝ። እውነት! ሰው ትክክለኛ ውበት ለማግኝት ከፈለገ እንደጠዋት የተመቸ ግሩም ጊዜ ያለ አይመስለኝም። ምንም አይነት ልዩ ሜካፕ የማትጠቀም ቢሆንም ትላንት ሳገኛት አይኗ ላይ በስሱ ተቀብታው የነበረው ኩል ሳይቀር ለቆ ረጃጅም የአይኗን ሽፋሽፍት አጋልጧቸዋል። ለቀልዷ ፈገግ ብየላት በልቤ ለቁንጅናዋ መቀኝት ጀመርኩ።
< አይንሽ እዳ አለበት ለስነ ከዋክብት የሚገብረው
ጥርስሽ እዳ አለበት ለጨረቃ መድመቅ የሚገብረው
እግዜር ስራ አለበት ገና ካንቺ ወስዶ የሚያካፍለው
ጨረቃም ብቅ አለች አይንሽን አይታው ከዋክብት እረገፋ አንቺን ፈልገው
በብርሀን ሊደምቁ ካንቺ ተውሰው!>
አቦ እንዴት ያናድዳል!? ምንም የልቤ አልደስ አለ። ለዛሬ ብቻ ምናለበት ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህንን በሆንኩኝ ብየ ተመኝሁ፤ የፋርሱ ኡመር ሀያምም የፐርሺያው ሩሚም በኛ ሀገር ደረጃ ለያውም ለኢትዮጵያዊት ቆንጆ የሀገራቸው ቃል ስለማይበቃቸው ናቅኳቸውና የሀገራችንን ሀያላን ባለቅኔዎች መሆን ተመኝሁ። እነደበበ ሰይፉ፣ እነ ከበደ ሚካኤል፤ እነጋሽ መንግስቱ ለማ፣ እነጌትነት እንየው፣እነ በውቀቱ ስዩምና አንዳንድ በስም የማላስታውሳቸው ባለቅኔዎች ለአፍታ ያህል በአይነ ህሊናየ ገዝፈው ተመላለሱብኝ። ምነው አንዳቸውን በሆንኩ ስል ናፈኩኝ። የኔን ግጥም ብትሰማ ምን ያህል ትስቅብኝ ይሆን? ደግነቱ ውበቷን በአይኔ እያጣጣምኩኝ ቅኔየን በልቤ የዘረፍኩት በመሆኑ ማንም ስላልሰማኝ ከመሳቂያነት ተርፌአለሁ። እንደ መላፋት አይነት በሁለቱም እጆቿ እየጎተተችኝ ከአልጋየ ላይ ቀሰቀሰችኝ። ለዘለዓለም ጠዋት ጠዋት በእሷ ለመቀስቀስ ተመኝሁ። ፊቷ ላይ የፈካው የደስታ ፀዳል እኔም ላይ ተጋብቶብኝ ደስታ በደስታ አደረገችኝ። ሁሌም ከጎኔ እንዳትለየኝና እንዴት የተሰበረ ልቧን መጠገን እንደምችል በማሰላሰል ተጠመድኩ። ልቤ ለመጀመሪያ ጊዜ እጅ ሰጠ። ቢያንስ ሰላሳ አመት ሳይሞላኝ በፍፁም ትዳር አልይዝም ስል የነበርኩት ልጅ ህሊናየ ከሷ ጋር ካልተጣመርክ ብሎ ፋታ ነሳኝ። እያየኀት ናፈቀችኝ። ፈገግታዋ ልቤን ማሞቅ ብቻ ሳይሆን ቤቴን ማድመቅ የሚችል ምትሃታዊ ሀይል ነበረው። ፊቴን ታጥቤ አብረን ቁርስ ለመብላት ጠረጴዛው ጋር ተሰናዳን። ህይወቴ እንደዚህ ሆኖ እንዲቀር ተመኝሁ። ካሁን በውኃላ ከዚ ቤት መቼም አልወጣም እንድትለኝ ፀለይኩ። እሷ ሁሉንም ነገር ፍቃደኛ እስክትሆን ድረስ መቼም በምንም ነገር ሳላስቀይማትና ላላስቸግራት ሁሌም ከቤቴ ብቻ እንዳያት ጓጓሁ። የምበላው እህል በቅጡ አልዋጥልህ አለኝ። የሷ መኖር ይሆን ያጠገበኝ? ድንገት አንድ ሀሳብ መጣልኝና ከተቀመጥኩበት አፈፍ ብየ ተነሳሁ። "እንዴ ምን ሆነህ ነው አትበላም እንዴ?" አለችኝ። <ይቅርታ ያይኔ በናትሽ አንድ ቦታ ደርሼ መምጣት አለብኝ አሁኑኑ እመለሳለሁ!> አልኳት እየተጣደፍኩ። ሁኔታየ ያስደነግጥ ነበር። "ምነው ችግር አለ?አብሬህ ልምጣ?"
<አይ አሁኑኑ እመለሳለሁ በሰላም ነው አታስቢ> አልኳት ድንገት ከፊቷ ላይ ባየሁባትና እኔ በፈጠርኩባት ጭንቀት በራሴ እያፈርኩኝ።
" እሺ በሰላም ከሆነ እኔም ወደቤቴ መሄድ አለብኝ ከጠበከኝ አብረን እንውጣ፤ ካልጠበከኝም ሒድ እኔ ቀስ ብየ እወጣለሁ።" አለችኝ እሷም ቁርሷን ትታ አብራኝ ለመውጣት ከወንበሩ ላይ እየተነሳች። <ኧረ በፍፁም በጭራሽ መሔድ የለብሽም> አልኳት ሳላስበው ትከሻዋን ቁልቁል ተጭኜ ወደ ወንበሯ እየመለስኳት። ካፏ 'መሔድ አለብኝ' የሚለው ቃል ሲወጣ ልቤ ተሸበረ ካሁን በፊት አብራኝ ትኖር የነበረ ይመስል ቤቴ ሲቀዘቅዝ ተሰማኝ እንባ አይኔን ጋረደኝ። <እባክሽን አሁንነው የምመጣው ከሰላሳ ደቂቃ የበለጠ ከዘገየሁ ከፈለግሽ ጥለሺኝ ሒጂ ይሄው ቁልፉ" አልኳት እግሯ ላይ መውደቅ በቀረው ልመና እየተለማመጥኳት። <ቶሎ ካልመጣሁ ቆልፊና ቁልፉን በሩ ምንጣፍ ስር አስቀምጪልኝ> አልኳት እንድታምነኝ ብየ። ልብሴን በፍጥነት ቀያየርኩኝ። ዛሬ በጭራሽ አላፈርኳትም እንዳውም ብዙ አመት የማውቃት ያህል ዘና ብየ ነበር። ......ይቀጥላል

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@zeeddr አድርሱኝ

2 Monate, 1 Woche her

የ18 አመቷ ታዳጊ አሳዛኝ ወግ
በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
  ደራሲ ናቲ
የ 18 አመቷ ታዳጊ አሳዛኝ ወግ
ክፍል 29
ትንሽ ሳያት ከቆየሁ በኃላ እያመነታሁና ራሴን እየተጠራጠርኩ እኔም ከጎኗ ሄጄ ጋደም አልኩ፡፡ ምንም አላለችኝም። ትንሽ እንደ መገላበጥ ብላ በደንብ ወደ ግርግዳው በመጠጋት በመካከላችን ሌላ ሰው የሚያስተኛ ያህል ባዶ ቦታ በመልቀቅ ተጠጋችልኝ። አይኗን ጨፍና ቢሆንም አለመተኛቷን በማወቄ <ግን የህይወት ፍልስፍናሽ ምንድነው?>ስል ጠየኳት። እንቅልፍ ባሰለለው ድምፅ " ሰው ከሆንክ ሰው ሆነህ ትኖራለህ የሚል ነው" ብላ ምላሽ ሰጠችኝ። ላብራራው ፈልጌ ነበር ግን ምንም ግልፅ ስላልሆነልኝ በፀጥታ ማሰላሰል ጀመርኩ። ከትንሽ ቆይታ በዉሃላ ሳናግራት አትመልስልኝም። ሀሳቧን ጥላ መተኛቷን አረጋገጥኩ። አሁንም በጎኔ ጋደም ብየ ክንዴን ትራሴ ላይ አስደግፌ አተኩሬ ተመለከትኳት። በእንቅልፍ ልቧ ፊቷን ወደኔ መለሰች። እይታየ ከደረቷና ከከንፈራ አላልፍ ሲለኝ ትዕዛዟን ሽሬ መብራቱን አጠፋሁት። ባስተዋልኳት ቁጥር እቀፋት እቀፋት የሚል ከባድ ስሜት ስለተፈታተነኝ ጭለማ መሆኑን መረጥኩኝ።ግና እንቅልፍ የሚባል ባይኔ አልዞር አለ። በጭለማ ውስጥ ከብርሀኑ በበለጠ በሀሳቤ እየመጣ አላስተኛ የሚል የሰውነቷ ቅርፅ ፊቴ እየተደቀነ ተሰቃየሁ። ቤቴ እንደምታድር ሳውቅ ቤቴ ገነት የሆነ ያህል ተሰምቶኝ ነበር፤ አሁን ግን ቅልጥ ያለ ገሀነም ውስጥ መግባቴ ተገለጠልኝ። በመካከላችን የነበረው ርቀት ጠፍቶ እጇን ደረቴ ላይ በእንቅልፍ ልቧ ጣል ስታደርግብኝ ደስ የሚል መአዛዋ ከልቤና ከአይምሮየ ተቀርፆ በልቤና በህሊናየ መሀል ሀይለኛ ሙግት ተፈጠረ፡፡ ልቤ በቻለው ፍጥነት እየመታ " ናቲ እኔ መረጋጋት የምችለው ፍላጎትህን ስታሳካ ብቻ ነው" ሲለኝ ህሊናየም በተራው <ናቲ ለስጋህ ብለህ ነፍስህን እንዳታቆሽሻት እሷም እርሟን ሰው ብታምን እንዴት አደራዋን ትበላለህ?> ይላል "ናቲ እኔ ምልህን ስማ! አንተን አምናህ አይደለም፤ አንተ ምን የተለየ ነገር አለህ? ካንተጋ መዝናናት ስለፈለገች ነው። በደንብ አስደስታት" ይለኛል ልቤ። <ወንድ ባገሩ ሞልቷል ካንተ የምትፈልገው ሰላም ነው። እያት እስኪ እንዴት ሀሳቧን ጥላ እንደተኛች!። አየህ አንተን በሆነ ምክንያት አምናሀለች፡፡ ተው!> ይላል ህሊናየ < በቃ! ህሊናህ የሚልህን ከሰማህ ይህቺን ቆንጆ ልጅ ለዘለዓለም ታጣታለህ። ምክንያቱም ወንድ አይደለም ብላ ትንቅሀለች። ታያለህ ዞር ብላ አታይህም" ልቤ ይመክረኛል። <ኧረ ልብህን አትስማ! ዛሬ ሳትፈልግ አስገድድደህ አንድ ነገር ብታደርግ ካለፉት ደፋሪዎቿ በምን ትለያለህ? ነገ የገዛ ልብህ ፊቷን ታዞርብሀለች። እኔንም ለዘለዓለም በፀፀት ትቀጣኛለህ ይቅርብህ!> ህሊናየ ያስጠነቅቅቀኛል። ልቤ ደግሞ ሙጉቱን ያጧጡፋል። "አንተ ኮ ደፋሪ አትባልም ቤትህ ድረስ መታልህ ለያውም የገዛ አልጋህ ላይ ተኝታልህ ነው። እምቢ ብላ ብትታገልህ እንኳን እንዳትተዋት ሴቶች እየፈለጉም እስከመጨረሻው ህቅታ ትግል ይወዳሉ በርታ!" መጮህ አሰኘኝ። ሀሳቤ ቅዠት መሠለኝ። በቀስታ ፀጉሯን እየነካካሁ ከንፈሯን በመሳም ይበልጥ በጣም ተጠግቻት ጡቶቿን እየነካካሁ ያዝ ለቀቅ ሳደርጋቸው በልብሷ ላይ ውብ ጡቶቿን መንካት የልቤን አላደርስ ሲለኝ ከታች ከቢጃማዋ ስር ገብቼ በቀስታ ዳሌዋን በጣቶቼ እየዳሰስኩ በወገቧ በኩል አልፌ ጡቶቿን ያለከልካይ በግላጭ እንደብርቱካን አሸት! አሸት! እያደረኩ እሷም ከእንቅልፏ ሙሉ በሙሉ ነቅታ እየተንሰፈሰፈች ከንፈሮቼን እንደ ከረሜላ እየመጠጠች ቀስ ብየ ጭኖቿን እየዳበስኩ የውስጥ ሱሪዋን አውልቄ ጣቶቼን መሀል ለመሀል ሳንሸራሽራቸው ቆይቼ ጭኖቿን ወደ ላይ ሳነሳቸው እሷም በሲቃ እያቃሰተች በሀይል ወደ ጭኖቼ ስትጠጋ ከቅዠቴ እወጣለሁ፤ ጭኖቼ መሀል ያለውን እንደብረት የጋለ አካሌን በምን እንደማቀዘቅዘው ግራ ይገባኛል። ማከኪያ የሌለው እከክ ይሆንብኛል። እሷ ግን እኔ እንቅልፌን አጥቼ ስሰቃይ ያለ ሀሳብ የእንቅልፏን አለም ትቀጫለች። እንደኔ ብዙ ነገር ስለማታብሰለስልና በንፁህ ህሊናዋ ስላመነችኝ ለጥ ብላ የሚያስቀና እንቅልፍ ተኝታለች። እኔ በገዛ የፍትወት ሀሳቤ እየተሰቃየሁ ከዚ በፊት የደፈሯትን ሰዎች ሳይቀር አሞካሻለሁ፤ <እና ይህቺን የመሰለች ልጅ ማሳለፍ ሀፂያት አይሆንም?> እላለሁ፡፡ በመጨረሻ ግን ህሊናየ አሸነፈ። መጥፎና ነገ የምፀፀትበት ስራየን ልቤና አዕምሮየ በህብረት ሆነው አወገዙት። ሁሉም ሰዎች ለአምስት ደቂቃ እርካታ በሰዐትና በገንዘብ የማይለካ እምነታቸውን መናድ እንደሌለባቸው ለራሴ ነገርኩት። ለያይኔ አበባ ሰው ስሜቱን በመግዛት ከእንስሳ የተሻለ ፍጡር መሆኑን ላሳያት ቆረጥኩኝ። እምነቷን ታምኜላት ትልቅ እምነት ልቀበላት ወሰንኩኝ። የሚያልፈውን ነገር ማሳለፍ ወደድኩኝ። ተነስቼ በሩን ከፍቼ የደብረ ማርቆስን ቅዝቃዜ ሳልፈራ ገላየን ታጠብኩ። ስመለስ ከግማሽ ያላነሰ የተረፈንን ወይን ከነጠርሙሱ አንስቼ በአንድ ትንፋሽ ጨለጥኩት። ሰአቱ ሊነጋጋ ተቃርቦ ነበር። መልካም ማሰብ ለራስ ነው የሚባለው እውነት ነው። ህሊናየ ከሀሳብ በማረፉ ሳልሳቀቅ በሙሉ የራስ መተማመን ያይኔ አበባን አንገቷ ስር ሳም አደረኳትና እጄን ደረቷ ላይ ጣል አድርጌ ከአጠገቧ ሞት የሆነ እንቅልፍ ወስዶኝ ዝርር ብየ ተኛሁ።......ይቀጥላል
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@zeeddr አድርሱኝ

2 Monate, 1 Woche her

የ18 አመቷ ታዳጊ አሳዛኝ ወግ
በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
  ደራሲ ናቲ
የ 18 አመቷ ታዳጊ አሳዛኝ ወግ
ክፍል 28
ከተቀመጠችበት ስትነሳ አንገዳገዳትና ደገፍ አለችኝ። ግን የምታወራውን ታስተዉላለች። ምንም ሳታፍርና ሳትፈራ "ፊትህ አዙር እሺ" ብላ ፊት ለፊቴ ልብሷን ማወላለቅ ስትጀምር እኔ 'መጣሁ' ብየ ልብሷን እስክትቀይር ድረስ ከቤት ወጥቼ ደጅ ላይ መንጎራደድ ጀመርኩ፡፡ ትንሽ ቆይቼ ወደቤት ስገባ ቢጃማዋን ቀይራ ስትጨርስ ደረስኩ፡፡ ሲያጠፋ እንደተቆጡት ህጻን ድንግጥ ብየ ፈዝዤ ቆምኩ። እንዴ! ይሄ ቢጃማ እንደዚህ ስስ ነበረ እንዴ? እህቴ ስትለብሰው ልክ እንደ ብርድ ልብስ ድርጁ የሆነ ያህል ሰውነቷን ልብ ብየው አላውቅም። ያይኔ አበባ ግን ራቁቷን የቆመች ነው እንጂ ገላዋ ላይ ጨርቅ ያለ አልመስልህ አለኝ፡፡ ዳሌዋ ከዳር ዳር ወጥሮ አስጨንቆታል፡፡ከነ ገዋኗ ለመብረር የተዘጋጀች መልአክ መስላ ታየችኝ። በቀይነትና በጠይምነት መሀል ያለው የሰውነቷ ከለር እንደቸኮሌት ግመጠኝ ግመጠኝ እያለ የሚጠራኝ መሠለኝ። ከናፍርቶቿን አንጀሊና ጂሊ ብታያቸው በቅናት እየተንጨረጨረች የምትሳሳላቸው ስለመሆኑ አልተጠራጠርኩም። ያለምንም መቀባባት የተፈጥሮ ሮዝ ቀለም ብቻ ተቀብተው እየተርበተበቱ 'ና እንጂ!' ብለው ወተት በመሰለው ጥርሶቿ ታጅበው ወለላ እያመረቱ ውብና ጎላጎላ ያሉት አይኖቿም ጭምር እየተስለመለሙ የጠሩኝ መስሎኝ ሳልጠግብ በስስት ልመጠምጣቸው ከጀለኝ። እንዴት ጡት ማስያዢያ አላደረገችም? ጡቶቿ እንዴትስ እንደ ሰሜን ኮርያ ሚሳኤል ለመወንጨፍ ዝግጁ እንደሆኑ ሁሉ በምን ተአምር እንዲህ ወደ ጎን ቀጥ ብለው ሊወደሩ ቻሉ? እኔ ሴት አውቃለሁ። ምንም ፍቅር ይዞኝ ባላውቅም ከሴት ግን አድሬ አውቃለሁ። እንደዚህ አይነት አማላይ ጡት ግን በፊልም ላይ እንኳን ተመልክቼ አላውቅም። እንደ ብርቱካን ሰፋ ብለው ጫፎቻቸው እንደ ንጉስ ሚኒሊክ ጦር ሾል ሾል ብለው 'መጣሁልህ መጣሁልህ' የሚሉኝ መሠለኝ። ወገቧ እህል ቀምሳ የማታውቅ ይመስል ከዳሌዋ ሸሽቶ ወደውስጥ ገብቶ ዘፋኙ እሷን እያየ የሴት ምሳሌ ትሆን ዘንድ 'ችቦ አይሞላም ወገቧ' ብሎ የዘፈነላት መሰለኝ። የተላገ የሚመስለው የሆዷ ቅርፅ በምን እንደተስተካከለላት ፈጣሪም ይገረምበት ። ጭኖቿ ሆን ብለው ዳሌዋን የገፉት ይመስል በኩራት እርስ በእርስ ተጠባብቀዉ መግባት ክልክል ነው እንደሚሉ ሁሉ ያለምንም ክፍተት ዝግት ብለዋል። የሰውነቷን ልስላሴ በአይኖቼ ዳሰስኩት። የባቷ ውበቱ በትዕዛዝ ለጌጥ ብቻ ተብሎ የተሰራ እንጂ ሁሉም ሰዎች ላይ የተተከለ አይነት ተራ እግር አይደለም። ተረከዟ እንደ ፖም ፍሬ ሳይላጡ የሚበሉ እንጂ አካሏን ለመሸከም የተፈጠሩ አልመሰሉኝም። ሰው እንዴት የእግሮቹ ጣቶችና ጥፍሮች ቀለበት ይደረግባቸው ይመስል አለንጋ ይመስልለታል? ፈዝዤ በእግዜር ስራ ስደመም "ምነው ምን እያየህ ነው?" የሚለው ንግግሯ ከተመሰጥኩበት እይታየ አስደንብሮ አናጠበኝ <ፀጉርሽን አይቼ እየገረመኝ ነው> አልኳት አፌ ላይ የመጣለኝን ቃል እየተናገርኩና ወገቧ ላይ የተዘናፈለ ፀጉራን ለመንካት እየዳዳኝ። "ታውቃለህ እናቴ በህይወት በነበረችበት ጊዜ አብዝታ የምትንከባከበው ፀጉሬን ነበረ። ስለ ሶምሶን ታሪክ እየነገረችኝ ከተወለድኩ ጀምሮ ምላጭ አርፎብኝ እንደማያውቅና ፀጉሬንም በፍፁም በምንም ምክንያት እንዳልላጨው አያስጠነቀቀች ስላሳደገችኝ ስትሞት እንኳን እንደ ባህላችን ሳልላጨው ነው የቀረሁት። እሷ ሁሌም ከፀጉሬ ጋር በመንፈስ አብራ ያለች ይመስለኛል። ሰዎች ፀጉሬን ባደነቁልኝ ቁጥር እናቴን በናፍቆት አስታውሳታለሁ። እናም ፀጉሬን ሲወዱልኝ እናቴን የሚወዱልኝ ነው የሚመስለኝ ደስ ይለኛል" አለችኝ ከንፈሮቿ ገለጥ አድርጋልኝ እየተፍለቀለቀች። እኔ ግን በውበቷ ተነድፌ የምትለውን በደመ ነፍስ ነበር የሰማኃት። ፒካሶ ቢሉ ዳቬንቺ ፣ ሚካኤል አንጀሎ ነሽ ሎሬት አፉወርቅ ተክሌ እያንዳንዳቸው ቢተጋገዙና አንድ የአይኔ አበባን እንዲስሉ ቢታዘዙ ሁሉም በልባቸው ከመሳል በስተቀር በእጃቸው ለመሳል ብሩሽ እንደማያነሱ ያያት ሁሉ በመሰከረልኝ ነበር። ምላሽ ስላልሰጠኃት "አልሰማኸኝም ወይስ አንተም እንደኔ ደክሞሀል?" አለችኝና ምላሼን ሳትጠብቅ አልጋዉ ላይ በቁሟ ወደቀችበት። ካለዛዉም ስስ ቢጃማ ተሸብሽቦ ጭኖቿ በስሱ ተጋለጡ። ወንድነቴ ተፈታተነኝ፤ እላዯ ላይ ሄጄ ልከመርባት ፈለኩኝ። እሷ ግን የልቤን ያወቀች ይመስል "እባክህ ናቲ ልተኛ ነው ደና እደር ምን ያህል እንዳመንኩህ ታውቃለህ። ግን ለምን እንደሆነ ለኔም ገና በደንብ አልተረዳሁትም።" አለችኝ። ምን አይነት ፈተና ነው!? ሰውነቴ መልሶ ሲኮማተር ታወቀኝ። ስራዋ ሰውን ካስራቡ በኃላ እህል እያሳዩ አፋ ላይ አድርሶ እንደመከልከል አይነት ሆነብኝ። "በነገራችን ላይ ከይቅርታ ጋር መብራት እንዳታጠፋ ጭለማ በጣም ነው የምፈራው እስከሚነጋ ድረስ ይብራ እሺ ዋ! የእንግዳህ ትዕዛዝ ነው።" አለችኝ። መብራቱ ቢጠፋ ሳይሻለኝ አልቀርም ቢያንስ ውበቷን እንዲህ አልመለከተውም ነበር፡፡ ትንሽ ሳያት ከቆየሁ በኃላ እያመነታሁና ራሴን እየተጠራጠርኩ እኔም ከጎኗ ሄጄ ጋደም አልኩ፡፡......ይቀጥላል

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@zeeddr አድርሱኝ

2 Monate, 1 Woche her

ፀር የእቅዱ ጠንቅ
ነበረች።
እኼን ግዜ መሳይ ካቀረቀረበት ቀና እለና ሚኪ ላይ አፈጠጠበት ።
አይኖቹ ደም ለብሰዋል።
ፅናት መሳይን ስትመለከተው ጥርሶቹ እርስ በርሳቸው እየተፋጩ
ነው።
ፈራች መሳይ እብደቱ የጀመረው መሰላት "ሚኪ አብደኻል ምንድን
ነው የምታእወራው ተነስ በቃ እንኺድ !" አለች ብድግ ብላ ቀና
ብሎ እየተመለከታት"የትም አልኼድምም! አላበድኩምም!
ያበድኩት እኼን እውነት እያወቅኹ ሳልቃወም እውነቱን ደብቄ
ለመሳይ እብደት ተባባሪ የኾንኩ እለት ነበር ፅናቴ ። እባክሽ
አታቋርጭኝ! "ቀጠለ•••
" እናም ይኽቺን የእቅዱ ጠንቅ የኾነችውን ናርዶስን በዘበኝነት
ተቀጥረው እየሰሩ እንደ እናትም እንደ አባትም ኾነው ባሳደጓት
ባባቷ መጣባት።
ላቧታ ያላትን ፍቅር ለመግለፅ ቃላት ለሚያጥሯት ናርዶስ ! አባቷን
በሸረበው ተንኮል ወንጀል ውስጥ መግባታቸውን መስማት ከባድ
ነበር። አባቷ እስር ቤት ገብተው እንዲማቅቁ የማትፈልግ ከኾነ
አንተን እስከመጨረሻው ትቷ እሱ ወደ ሚላት ቦታ ጨርቄን ማቄን
ሳትል መኼድ እንዳለባት ሲጠይቃት ምርጫ አልነበራትምና
ተስማማች። "
መሳይ በዛን ግዜ የነበረው ያባቱ ኹኔታ በሙሉ ፊቱ ተደቀነበት
ከናቱ ሞት ቡሀላ የኺወቱን መራር ለቅሶ እያለቀሰ " እባክህ
ወዴት እንደወሰዳት የት እንዳስቀመጣት ንገረኝ ሚኪ!"
ፅናትም ሚኪም አብረውት አነቡ። ሚኪ ብድግ ብሎ ወደ መሳይ
በመኼድ "እራስኽን አረጋጋ መሳይ ወንድሜ ከዚህ ሰአት ቡኳላ
በፈለግከው ሰአት ያንተ ናርዶስ ወዳለችበት ልወስድህ ዝግጁ
ነኝ!! አንድ ቀን እንዲህ በአጋጣሚ እኔንም የኔ ምኛት ወዳለችበት
ቦታ የሚወስደኝ ሰው ይልክልኝ ይሆናል ፈጣሪ !!" አለው።
መሳይ ውስጡ ያለውን የተደበላለቀ ስሜት መረዳት ከበደው
ተነስቶ ሚኪን አቅፎት ለሰከንዶች ቆየና ለቆት ወደ ሆቴሉ
መታጠቢያ ቤት አመራ ። መታጠቢያ ቤት ገብቶ እራሱን
በመስታወት እየተመለከተ ሚኪ ይቅር በለኝ ምን ማለት
እንዳለብኝ እና እንደሌለብኝ መለየት አልቻልኩም ። ለምን ይኾን
ስለምኞት ላንተ ለመንገር አቅም ያጣኹት። ይቅር በለኝ ሚኪ!"
አለ የራሱ ፊት ላይ አፍጥጦ ።ወደ ሚኪ በመመለስ ከማኪ ጋር
ስልክ ተለዋውጦ ከተረጋጋ በኋላ እንደሚደውልለት ነግሮት
ከሆቴሉ በመውጣት ወደ መኪናው ገብቶ ወደ ምኞት በረረ።
ከምኞት ጋር አዲስ የተከራዩት ግቢ በር ላይ ሲደርስ ምኞትን
ሲያያት ምን ሊሰማው እንደሚችል ያውቀዋልና ወደ ውስጥ
መግባት ፈራ። ለደቂቃዎች አዛው በሀሳብ ሲታመስ ከቆየ በኋላ
ከመኪናው ወርዶ ወደ ውስጥ ዘለቀ የተዘጋውን በር በያዘው ቁልፍ
ከፍቶ ወደ ቤት ሲገባ ፊልም እያየች የነበረችው ምኞት ብድግ
ከማለቷ መሳይ ተንደርድሮ ተጠመጠመባት።
ከእቅፉ እንዳትወጣ አጥብቆ እንደያዛት ቆየ ምኞት በሁኔታው ግራ
ተጋባች ። በውስጧ ለበፍቅር አብረን እንሁን ጥያቄው ምላሹ
ይቆይ ስላለችው የተረበሸ መስሎ ተሰማት ።
እቅፉ ውስጥ እንዳለች እራሱን አዳመጠ ።ናርዶስን አሰባት።
ማድረግ ያለበትን ወሰነ። ውሳኔውን ለመፈፀም ለራሱም ቃል ገባ
ለሷ ግን ምንም አላላትም።
በንጋታው በጠዋት ከሚኪ ጋር ተገናኝተው ናርዶስ ወዳለችበት
ከአዳስ አበባ 280 ኪሜ በላይ ወደሚርቀው ክፍለ ሀገር
በሚቀጥለው ቀን ጥዋት ለመሄድ ቀጠሮ ያዙ።ወደ አንድ የቅርብ
ጓደኛው በማምራት ከሚኪ ጋር በተቀጣጠሩበት በተመሳሳይ ሰዓት
ቀጠሮ ያዘ
ያን ቀን ቀኑን ሙሉ ምኞትን ሲያጫውታት እና ሲንከባከባት ዋለ።
ማታ ላይ ነገ ጥዋት ከአባቱ ጋር ወደ ክፍለ ሀገረ ለአስፈላጊ
ጉዳይ እንደሚሄዱ ነገራትና ተሰነባብተው ወደየ ክፍላቸው ገብተው
ተኙ።
በጠዋት ሊኼድ ሲነሳ ከሌላኛው ክፍል ድምፅ ሰማ ። ወደ
ማብሰያው ክፍል ሲኼድ ምኞት ቀድማው ተነስታ ቁርስ
እያዘጋጀችለት ነበር። እስካሁን የተቆጣጠረውን እንባ ከዚ በላይ
ሊገድበው አልቻለም። አነባ ። ምኛት እጅግ በጣም ተረበሸች ።
መሳይ ላይ የምታየው ድንገት ስሜታዊ የመሆን ባህሪ ግራ
ቢያጋባትም ምን ሆነሀል ብላ አልጠየቀችውም።ቀጣዩን ጥያቄ
ፍራቻ።
ከቤት ወጥቶ በኼደ 20 ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ አባቴ ቶሎ
ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለስና እኔ ግን እዛ ለጉዳይ እንደሚቆይ
ስለነገረኝ ብቻሽን ከምትሆኚ ብዬ እንዲያመጣሽ ጓደኛዬ ጋር
ደውዬለታለው ከደቂቃዎች ቡሀላ አንቺ ጋር ይመጣል ተዘጋጂና
ጠብቂው ብሎ በስጦታ መልክ ወደ ሰጣት ሞባይል መልዕክት
ላከ።
ምኛት መልክቱን እንዳነበበች ለምን እንደሆነ ባይገባትም ሆዷ
ኣካባቢ የፍርሀት ስሜት ተሰማት።
ቢሆንም መዘጋጀት ጀመረች ስትጨርስ የክላክስ ድምፅ ሰምታ
ስትወጣ የመሳይ ጓደኛ ነበር
እነ መሳይ ከሄዱ ከደቂቃዎች በኋላ ናርዶስ ካባቷ ጋር ተደብቃ
እምትኖርበት ቤት ደረሱ በሩን ሲያንኳኩ የከፈተችው. እራሳ ነበረች
ስታየው ወደ ጀርባዋ ወደቀች መሳይ እሷ ላይ ተደፍቶ ሲያነባ
ሁሉም በሁኔታቸው ማለቀስ ጀመሩ።
ከቆይታ ቡሀላ መሳይ እየነዳ ናርዶስ አጠገቡ ጋቢና ውስጥ
ተቀምጣለች ከኋላ ሚኪ እና ፅናት ተቀምጠው ይዟቸው
በመውጣት ካንድ ጭር ካለ ሰፈር ውስጥ ሲደርስ ካንድ ግቢ በር
ላይ አቆማት ለምን እዛ አምጥቶ እንዳቆማት ከሱ ውጪ
የሚያውቅ የለም።
ከነሱ ፊት ለፊት ከሩቅ አንዲት መኪና ወደነሱ እየመጣች ነው።
የመሳይ መኪና ጋ ከመድረሷ በፊት ራቅ ብላ ቆመች ።
የመሲ ጓደኛ የሚነዳት መኪና ነች ውስጥ ደግሞ ምኞት ብቻዋን
ከውኻላ ተቀምጣለች።
የመሳይ ጓደኛ ምኞትን " ያውልሽ የመሳይ መኪና እየሄድሽ
ጠብቂኝ መኪናዋን አስተካክዬ ላቁማት።" አላት ለምን መጠጋት
እንዳልፈለገ ግራ እየገባት ለመውረድ ተዘጋጀች።
መሳይ ሚኪን " ውረድ !" አለው ሚኪ "ለምን? አለ ። "እሺ በለኝና
በሩን ከፍተህ ውረድ"
አለው።
"ወርጄ ምን ልስራ?
"ነው ሚኪ ተወው በቃ አትውረድ ከሰከንዶች በኋላ በሩን ከፍተህ
ሳይሆን ገንጥለህ ካልወረድክ መሳይ ምን አለ በለኝ !"
አለው።
ሚኪም " ይሄ ሰው ምንድንነው ሚለው ናርዶሴ ገላግይኝ እንጂ!"
ብሏት ቀና ሲል•••
ምኞትን ፊት ለፊት ከቆመው መኪና ውስጥ ወርዳ ስትመጣ
ተመለከታት።
ያቺ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ጥሏት የሄደው ምኞት ሳትሆን
መጀመሪያ ፌስ ቡክ ላይ ያያት ውበቷ ልብ የሚንደው ምኞት
ከላይ እስከታች መሳይ በገዛላት የሚያምር ልብስ ተሽቀርቅራ
እነሱ ወዳሉበት መኪና ስትመጣ ተመለከተ።
" ፅናቴ እኔ የማየው ላንቺም እየታየሽ ነው ያቺ የምትመጣው
እውነት የኔ ምኞት ነች አለ ፍቅር በገደለው ድምፅ መሳይ አንባው
ግጥም አለ።
መሪው ላይ ተደፋ።
ሚኪ የመኪናው በር እንዴት እንደሚከፈት ጠፋበት ለመክፈት
ይሞክራል ሳይከፍተው መልሶ ይተወውና ምኛትን ይመለከታል ።
የሚኪን ሁኔታ መግለፅ ፍቅርን በአካል ምን እንደሚመስል
የማሳየት ያኽል ይከብድ ነበር። መኪና ውስጥ ፈንጅ ጠምደው
በሩን ከቆለፉበት ሰውም በላይ የቱን እንደሚይዝ የቱን እንደሚነካ
ቤት በኩል እንደሚወጣ ግራ ገብቶት ሲርበተበት ለተመለከተው
ሰው ከምንም በላይ የሚንበረከከው ለፍቅር ብቻ መሆኑን
ያረጋግጣል።
ምኛት እየቀረበች ነው። በደመነፍስ በሩን ከፍቶ ከመኪናው ወረደ።
ቆሞ ሲመለከታት አየችው። አይኖቹ እንባ እንዳዘሉ በፍቅር ፀሀይ
በርተው ተመለከተች። በድንጋጤ ባለችበት ቀጥ ብላ ቆመች።
ሮጦ በማቀፍ ሽቅብ አንስቷት እንደ እብድ መጮህ ጀመረ።

ከሶስት ወር ቡሀላ••

ለሁለቱ ጥንዶች ባንድ ላይ ድል ያለ ሰርግ ተደገሰ። በዛ ሰርግ ላይ
ፅናት እራሷን ስታ ወደቀች ። ለሙሹሮቹ የፅናትን መውደቅ
የነገራቸው አልነበረም። ፅናት ከተሻላት ቡሀላ እትዬጲያን ለቃ ወደ
ሀገረ እንግሊዝ አቀናች። ፅናት በሄደች በሁለተኛው ወር
በመጀመሪያው እሁድ ። ሚኪ ፣ መሳይ፣ ምኛት እና ናርዶስ ወደ
አማንኤል የኧእምሮ ህሙሟን

2 Monate, 1 Woche her

ቤተሰብ ጋር ለመደወል ስለፈለገች የብሩክን ስልክ ከፍታ
እንድትሰጣት ጠየቀቻት። ሰጠቻት። ወድያው የቤታቸውን ሰራተኛ
ስልክ ላይ የተላኩትን መልክቶች አገኘቻቸው። ደወለችላት። "
እቅድ ሁለትን ለሚኪ ደውዬ ነግሬዋለሁ ጌታው!" አለች ሰራተኛዋ።
ስልኩን ጠርቅማባት። እንደ እብድ እያደረጋት ወደ ክፍሉ
በመግባት " ፈጣሪ
ምላሽ ስለሰጠህ እኔ ምንም አልልህም!" ብላ
ስልኩን ብሩኬ ላይ ወርውራ ሚኪን እየጎተተች ከክፍሉ ይዛው
ወጣች።
መሳይና ምኛት አዲስ አበባ ደርሰው የተገኘላቸውን ቤት
ሲመለከቱት የተሰማቸው ደስታ ወሰን አልነበረውም ቤቱ እጅግ
በጣም ያምራል። ምኛት እንደገባች ነበር የምትወደውን እና
የናፈቃትን ቡና ለማፍላት ማቀራረብ የጀመረችው።
ከደስታዋ ብዛት የባጥ የቆጡን ጫወታ እያነሳች መሳይን እንባው
ጠብ እስኪል ስታስቀው ቆየች። ጫወታዋ እንዳይላወስ ይዞት
እንጂ ሚኪ ጋር ለመኼድ ልቡ ቆሟል መሳይ።
እንዳይከፋት ጥሏት መውጣት ፈርቶ አብሯት ዋለና አመሻሹ ላይ
አባቱ ቤት ደርሶ ቶሎ እንደሚመለስ ነግሯት ወደ ሚኪ ቤት ሄደ።
ሚኪ ቤት አከባቢ እንደደረሰ መኪናዋን ጥግ አስይዞ ትንሽ
እንደቆመ ሚኪ እና ፅናት በፅናት መኪና ከግቢ አብረው ሲወጡ
ተመለከተ። አይኑን ማመን ተሳነው" ከዚች ልጅ ጋር ጀመረ ማለት
ነው።" ልቡ በደስታ ጮቤ ረገጠች። እንደህፃን ልጅ እየቦረቀ
"ምኛትዬ ፈጣሪ ያለ ምክንያት ምንም ነገር አያደርግም። ባንቺ
ሊክሰኝ እንደሆነ እርግጠኛ ሆንኩ!" እያለ የሆነ ቦታ ሲቀመጡ ፎቶ
ሊያነሳቸው ስላሰበ ፅኑና ሚኪን መከተል ጀመረ።
ትንሽ እንደሄዱ ሳይታወቀው ተጠግቷቸው ነበርና ሚኪ ድንገት
መሳይ የያዘውን መኪና ታርጋውን በስፖክዬ አየው።የመሳይ አባት
መኪናዋን ይይዛት ስለነበር ወድያው ነበር የለያት።
እየነዳ ያለው መሳይ ይሆናል ብሎ ግን በጭራሽ አላሰበም።
ምክንያቱም ለሚኪ መሳይ አሁንም እቤት ውስጥ የሚውል
ሚስኪን እብድ ነውና ።
ወደ ፅናት ዘወር አለና "ፅኑዬ ምኛትን ካላገኘዃት መጨረሻዬ እንደዛ
እንደጓደኛዬ ልጅ እንደመሳይ ማበድ ነው አላት ስለመሳይ ታሪክ
እያሰበ....

ይቀጥላል

ከወደዱ ለወዳጅዎ ያጋሩት!

2 Monate, 1 Woche her

ከሞተች ቆይቷል
[ ገብረክርስቶስ ደስታ ]

ከሞተች ቀይቷል
ብዙ ዘመን ሆኗል
ብዙ ነበር ጊዜው
ግን ፎቶግራፏ አለ
ደብዳቤዋም አለ
በጠጉሯ ጉንጉን የጠቀለለችው
ምን ቀን ቀጠሮ ነው
ቀን የቀን ጎደሎ
የቀን ጥቁር መጥፎ
አበባ ሄድኩ ይዤ
እዛ አበባ አልጠፋም
በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡
ስሜቴ ፈነዳ ገላዬን በተነው
ነፍሴን ነቀነቃት ገላዬን በተነው፡፡
ነፍሴን ነቀነቃት
እንባዬ ወረደ ጉንጬን አረጠበው
ለተረሳ ነገር እንዴት ያለቅሳል ሰው!
ለተረሳ ነገር
ምን ጊዜው ቢረዝም
የዚህ ዓለም ጣጣ እያንከራተተኝ
የዚህ ዓለም ስቃይ እየቦረቦረኝ
ሲጨንቀኝ ሰውነት
ፍቅሬ ይሁን ያንቺ የኔ መቃብር ቤት
ህይወት ነዶ ጠፍቶ
ሞት ፍሙን ሲያዳፍን
ያን ጨለማ ጓዳ ሄጄ ልተኛበት።

ይመስላል ዘላለም
ሰው ሰውን ሲወዱት
አይኑን አይኑን ሲያዩት
ይመስላል ዘላለም
አድማስ አልፎ አድማስ
ምጥቀት አልፎ ምጥቀት
ጠፈር አልፎ ጠፈር
ይመስላል ዘላለም
ሰው ባካል የሚኖር
ድሮ አውቀዋለው
ተረድቼዋለው
ፀሀይ ጥቁር ስትሆን
ቀን ቀንን ሲያጠላው
ሌት ሌትን ሲሸፍን
እረስቸው እንደሁ፡፡
እንዴት አንቺን ልርሳ
ነፍሴ አብሯት የሚኖር
የፍቅርሽ ጠባሳ፡፡
˝ፍቅርሽና ፍቅሬ የተወሳሰበው
አልበጠስ አለኝ ብስበው ባስበው˝
ማን ነበር ማ ነበር
ማ ነበር እንደዚህ ብሎ የገጠመው?

ይመስላል ዘላለም
አንቺ የኔ እመቤት ብያት የነበረ
አንተ የኔ ጌታ
አንተ የኔ ጌታ ብላኝ የነበረ
አንቺ የኔ እመቤት

ይመስላል ዘላለም፡፡
እንባዬ ወረደ ልቤን አቃጠለው
ልቤ ተነደለ
የሰቀቀን እሳት አካሌን ሲያነደው
ደሜ ገነፈለ
የደም ጥቁር እንባ
ቆዳ የሚያሳስር መንፈስ የሚያባባ
አለቀሰቅሳትም
ቡዳ እሷን አይበላም
ቢስ አሷን አያይም
አልቀሰቅሳትም በነብሴ ተጉዤ እጠይቃታለው
አውቃለው አውቃለው
በመቃብሯ ውስጥ
ጢስ እንጨት ይጨሳል
ከርቤ ብርጉድ እጣን
መቃብሯ ሽቱ
ጣፋጭ መኣዛ አለው አጥንቷ ታቦቱ
መቅደስ ቤተልሄም ቅኔ ማህሌቷ
እጣኑ ይጨሳል ይታጠናል ቤቷ
ፍቅሬ ሙሽራዬ
እመቤቴ ፍቅሬ ያለም አለኝታዬ
አቴቴዋ ይታጠናል
ልዩ መዓዛ አላት
በመቃብሯ ውስጥ ጢስ እንጨት ይጨሳል
በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡
ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ፤
ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ
እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ፤
እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ
ፍቅሬ አለኝታዬ ፍቅሬ አለኝታዬ፤
ፍቅሬ አለኝታዬፍቅሬ አለኝታዬ
እንባዬ ወረደ…………………..
እንግዲህ ይበቃል ይቅር ይቅር ይብቃ
በድካም መድከም ባሳብ ሀሳብ አለ
ባዘን………….. ሃዘን……….ሃዘን

2 Monate, 3 Wochen her

#ምኞት

#ክፍል_36

ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ
.
.
.ሚኪ የምኛት እህት ባል ደርጉን ራቅ ብሎ ከውሃላ እየተከተለው
ነው። ደርጉ ጫንቃውን ከበደው መሰል በተደጋጋሚ ወደ ጀርባው
እየዞረ ሚኪን እየገላመጠ ይጓዛል። ምን ትገላመጣለህ ድሮም ክፉ
ሰዎች ጥላቸውንም አያምኑም የሚሰሩት ክፋት እና ተንኮል ፈሪ
ስለሚያደርጋቸው ከውኻላቸው የሚከተላቸው ሰው ሁሉ
የሚያጠቃቸው ይመስላቸዋል። በራስ መተማመናቸው በራስቸው
እኩይ ምግባር ተሸርሽሮ በማለቁ ባጋጣሚ እንኳን ከማያውቁትና
ከማያውቃቸው ሰው ጋር አይን ለአይን ቢገጣጠሙና የሚያያቸው
ሰው እይታ ትንሽ ግዜ ከወሰደ ...."እሄ ሰውዬ ለምን ያፈጥብኛል?
የት ያውቀኛል? ምን ፈልጎ ነው? የሚሉ ጥያቄዋች በአእምሮአቸው
ቶሎ ቶሎ እየተመላለሱ ሰላም ይነሷቸዋል ። "የሰው ትልቁ ጠላቱ
የራሱ ባህሪ ነው " የሚባለው ለዚህ አይደል ።እንደዚህ አይነት
ሰዎች በተለይ በዛ ካለ ሰው ጋር በታደሙባቸው አጋጣሚዋች
ከሆነ አቅጣጫ ወደ እነሱ እያዩ የሚያወሩ እና የሚስቁ ሰዎች
ካጋጠሙአቸው መላቅጣቸው ይጠፋና መግቢያ ቀዳዳ
ይጠፋቸዋል።
ሰው ሁሉ ስለነሱ የሚያወራና በጥቅሉ ስንት እሚወራ ነገር ያላት
አለም በነሱ ዙርያ ብቻ የምትሽከረከር ስለሚመስላቸው በራሳቸው
ክፋት የተረጋጋና ሰላም የሰፈነበት ህይወት መምራት ይቸገራሉ።
አታውቀኝ አላውቅህ ከጀርባህ መጋዜ ብቻ የሚረብሽህ የስራህ
ውጤት ነው ዘመዴ ዝም ብለህ መንገድህን ቀጥል አለ ሚኪ
በሆዱ አስሬ እየዞረ የሚመለከተውን ደርጉን እየተመለከተ።
ደርጉ አንድ መንደር ውስጥ ያለች ጨለምለም ያለች ግሮሰሪ
ውስጥ ሲገባ....ሚኪ ጥርጣሬውን ለመቀነስ አስቦ ግሮሰሪዋን
አለፋትና ራቅ ብሎ ካለ አንድ ስልክ እንጨት ላይ ተደግፎ
ለደቀቃዋች ስልኩን እየነካካ ከቆየ ቡሀላ ደርጉ ወደ ገባባት
ግሮሰሪ ዘው ብሎ ገባ ። ከደርጉ በስተጀርባ ጨለም ያለ ቦታ
መርጦ ተቀመጠና ቢራ አዘዘ።
ደርጉ ካንድ ሴት እና ካንድ ስካር አፉን ያዝ ካረገው ጎልማሳ ወንድ
ጋር ሞቅ ያለ ጫወታ ይዞ ስለነበር የሚኪን መግባት ልብ
አላለም።
ደርጉ ሞቅ እስኪለው ሌላ ጫወታ ሲጫወት ከቆየ ቡሀላ ሞቅ
እንዳለው የየእለት ርእሱ የሆነውንና የለመደውን የምኛትን ስም
የማጥፋት ዘመቻ ለመጀመር መንደርደሪያ ሀሳብ እንኳን
አላስፈለገውም ነበር።
"ዛሬ ደሞ ያቺ ጋጠ ወጥ እህታ ኬት ትዝ እንዳለቻት እንጃ ሚስቴ
እህቷን አንስታ ስትነፋረቅብኝ እኮ ነው ዛሬ መጠጣት ሳልፈልግ
ተበሳጭቼ የመጣሁት " ብሎ ርእሱን አስተዋወቀና ወደ ዝርዝር
ቡጨቃው ገባ። ደርጉ ወሬውን ከሚያወራላቸው መሀል ወንዱ እሄ
ወሬ የሰለቸው ይመስላል ሴታ ግን ስለምኛት መጥፎ መወራቱ
አስደስቷት ይሁን ገበያዋን ለማሞቅ ደርጉ በተነፈሰ ቁጥር
ታስካካለች።
ደርጉ የወሬውን ዙር እያከረረ : የሴቷ ሳቅ እየናረ : ሚኪ
የሚያዘው የቢራ ቁጥር እየጨመረ በደርጉ ወሬ የጀመረው
ብስጭት እየመረረ መጣ።
ደርጉ ቀጠለ " የማንም ዲያስቦራ ነኝ ተብዬ አጭበርባሪ በፌስ
ቡክ ላግባሽ ሲላት አምና ከምትሄድ እዚሁ የኔ ገረድ ሆና ብትኖር
ይሻላት ነበር እቺ ገልቱ ዘረ ገልቱ ።
ደሞ ሰሞኖን አንድ አዲስ አበባ የሄደ ዘመዴ "ቺቺንያ"የሚሉት
ሰፈር ውስጥ በአንድ ጭፈራ ቤት ሴተኛ አዳሪ ሆና አይቻታለሁ
አለኝ "
ሲል ሚኪ ብስጭቱ ከአቅሙ በላይ ሆነ እራሱን መቆጣጠር
ተስኖት ብድግ አለና ... ስማ ውሽተም ቀዳዳ ነህ ይችን ልጅ
አውቃታለሁ ከሚወዳት ሰው ጋር ተጋብታ በደስታ እየኖረች ነው።
"ግን አንተ የሚስትህ እህት አይደለች የሷን ክፉ ስታወራ
አታፍርም ? ነው ወይስ ያሰብከው ስላልተከልህ ነው?!"
ሲለው ደርጉ ድንገት በወረደበት ዱብዳ በመደናገጥ መጠጥ
በሰጠው ድፍረት ለፀብ ብድግ ከማለቱ ሚኪ ያልተከፈተውን ቢራ
አናቱ ላይ አፈነዳው ደርጉ ወደቀ ጥግ ላይ የነበሩ ሁለት የደርጉ
ወዳጆች ወደ ሚኪ ተንደረደሩ..

ይቀጥላል

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!   

We recommend to visit

ማራኪ ცЯムŋの የጫማ መሸጫ ቻናል

✔ማራኪ ብራንድ የፈለጉትን ጫማ በፈለጉት ሳይዝ እና ጥራት እናቀርባለን!
With free delivery
🔰Contact me
👉 @Maraki2211 or Call 0913321831
Admin
@maraki2211

💯Spammed users⚠
@Marakibrand2bot

Last updated 4 days, 12 hours ago

ማንኛውም መሸጥ የምትፈልጉትን ስልክ እንገዛለን
በ +251909255008 ወይም
+251912739699 ላይ ያናግሩኝ
@Abd_phone

Last updated 1 week, 1 day ago

🔑Quotes

“Life is generally meaningless beyond the choice we have to assign how meaningful it can be. I don’t fear death because I know this and therefore am able to live with peace of mind.”
@Quote_U
...

Last updated 2 years, 9 months ago