#ZENBILL_STORE
በኢትዮጲያ ውስጥ ትልቁ የመገበያያ የቴሌግራም መድረክ ነው።
? ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ይግዙ!
ካሉበት ሆነው ይዘዙን
Last updated 2 years, 6 months ago
ማራኪ ცЯムŋの የጫማ መሸጫ ቻናል
✔ማራኪ ብራንድ የፈለጉትን ጫማ በፈለጉት ሳይዝ እና ጥራት እናቀርባለን!
With free delivery
🔰Contact me
👉 @Maraki2211 or Call 0913321831
Admin
@maraki2211
💯Spammed users⚠
@Marakibrand2bot
Last updated 3 months, 4 weeks ago
ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-20
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ከምስራቅ ካር ስምምነት ላይ ከደረሱ በኃላ ይገጥመናል ከሉት በላይ በጣም የተወሳሰበው ነገር ነበር የገጠማቸው፡፡በመጀመሪያ የት እንደተወሰዱ ያለማወቃቸው ነበር ከባድ ነገር፡፡ መስታወቱ ደፍን ጥቁር ሆኖ ወደውጭ በማያሳይ መኪና ውስጥ ተከተው…ለአንድ ሰዓት ለበለጠ ጊዜ ሲጓዙ ከቆ በኃላ መኪናዋ ቆመችና ሲወርዱ አምስት የሚሆኑ ባለአምስት ፎቅ ዘመናው ህንፃዎች ያሉበት የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፤ የመረብ ኳስ እና የመሳሰሉት ሜዳዎች ያሉበት ዙሪያውን በደን የተሸፈነ እና ቢያንስ 3 ሜትር ሚሆን ከኮንክሪትና ከብሎኬት የተሰራ አጥር ….በአጥሩ ጫፍ ላይ አደገኛ ሽቦ የተጠመጠመበት በጣም አስፈሪ ድባብ የተላበሰ ግዙፍ ስፍራ ነው፡፡በዛ ላይ .በተወሰነ ሜትር ርቀት በየሰዓቱ በሚቀያየሩ ቆፍጣና የጥበቃ ወታደሮች የሚታዩበት አስፈሪ ግቢ ውስጥ ነው ይዘዋቸው የገቡት፡፡
ይዞቸው ከመጡት መካከል አንድ ወደአንደኛው ፎቅ ይዟቸው ሄደና ወዳአንድ ቢሮ አስገባቸውና ምንነቱን ያለወቁት የሆነ ወረቀት አስፈርሞ በማስረከብ ቀሪውን ያዘና አነሱንም ልክ እንደወረቀቱ እዛው ጥሎ ወጥቶ ሄደ፡፡
ከዛ ከእነሱ ስለሚጠበቀው ነገር፤ ስለዋና ዋና የግቢው ህግ፤ማድረግ ስለሚገባቸው መድረግ ስለሌለባቸው ነገር የአንድ ሰዓት ገለፃ ከተሰጣቸው በኃላ ናኦል ወደ ወንዶች ህንፃ ኑሀሚም ወደ ሴቶች ህንጻ ተወሰድና ከሌላ ከአንድ ሰው ጋር የሚጋሩት የራሳቸው መኝታ ቤት ተሰጣቸው፡፡በዚህ ሁኔታ አዲሱን ህይወታቸውን አህዱ ብለው ጀመሩ፡፡
ወደእዛ ግቢ ገብቶ በቃችሁ ውጡ ከመባሉ በፊት ለመውጣት መሞከር መጨረሻው ሞት ብቻ እንደሆነ ያወቁት ግቢውን በረገጡ በቀናቶች ውስጥ ነበር፡፡እንደተባለውም ስልጠናው የተለየ እና በእነሱ ዕድሜ ደረጃ ላለ ወጣት ይቅርና ለሙሉ ወጣትም የማይሞከር ነበር….ግን ስልጠናውን በቃኝ አልቻልኩም ማለት እራስን ለሞት አሳልፎ ከመስጠት ውጭ ሌላ የሚያሰገኘው ነገር የለም፡፡ስለዚህ የማይቻለን መቻል የግዳቸው ነበር፡፡ወታደራዊ ስልጠናው ብቻ ሳይሆን መደበኛ ትምህርቱ እራሱ በጣም ጥብቅ በሆነ ስነምግባር የሚሰጥ ነበር፡፡አንድ ልጅ እዛ ግቢ ሲገባ ሶስተኛ ክፍልም ይሁን ስድስታኛ ክፍል የ5 አመቱን የሥልጠና ጊዜ ጨርሷ ከዛ ጊቢ ተመርቆ ሲወጣ የ12ተኛ ክፍል ማትሪክ ወስዶ መሆን አለበት ፡፡በዛ የተነሳ በአመት ሁለት ክፍሎችን መማር የግድ ይላል፡፡ደግነቱ የትምህርት አሰጣጡ እጅግ ዘመናዊና ሁሉ ነገር የተሞላለት አስተማሪዎቹ ልክ እንደእነሱ በልዩ ችሎታቸውና ብቃታቸው የተመረጡ ጂኒዬሶችና ነገሮችን በቀላሉ በማስረዳት ችሎታቸው የተመሰከረላቸውና ስለሆኑ ጫናዎቹ የሚጠበቀውን ያህል እንዳይከብዳቸው ያግዛቸዋል፡፡በዛ ላይ እያንዳንዱ ሰልጣኝ እንደ ዝንባሌው በተለያዩ የስፖርት አይነቶቹ መሳተፍና የቋንቋ ስልጠናውም በተመሳሳይ ሁኔታ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡በተለይ ከውጭ ቋንቋ እንግሊዘኛና አረብኛ ሲማሩ ከሀገር ውስጥ እንደየ ምርጫቸው ከሚያውቁት በተጨማሪ ሁለት ቋንቋ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡
ይሄ በሀገሪቱ የደህነነት መስሪያ ቤት በልዩ ፕሮጀክት እቅድ ተነድፎለት በጀት ተይዞለት እየተካሄደው ያለው ልዩ ስልጠና ለመጀመሪያው አንድ አመት ለሁሉም ተማሪዎች በጣም ከባድ አካልንም መንፈስንም በእኩል ደረጃ የሚያዝል ነበር፡፡ለዚህም ማሳያ በተቀመጠው ክራይቴሪያ ከተለያ ቦታ በተለያየ ዘዴ ተሰብስበው ከገቡ 80 ተማሪዎች መካከል በአመቱ መጨረሻ 17 ቱ መቋቋም አቅቶቸው ሞተው ነበረ፡፡ናኦልም እህቱ ከጎኑ ኖራ በየጊዜው ብርታት ባትሰጠው ኖሮ ከሞቾቹ መካከል መሰለፉ አይቀርም ነበር፡፡ለዚህ ነው መጀመሪያውኑ ሰልጣኞቹ ሲመለመሉ አስፈላጊው ክራይቴሪያ ዘመድና ጠያቂ የሌላቸው እንዲሆኑ የሚፈለገው፡፡
ኑሀሚ ግን ከሶስት ወር በላይ አልተቸገረችም ነበር….ካዛ በኃላ በየዲሲፕሊኑ ከፉክከሩ መድረክ ከፊት የምትሰለፍ፤ ለሁሉም ሰልጣኞች ምሳሌና ብርታት ሆና ነበረ የቀጠለችው፡፡አመስት አመቱ አልቆ ሲመረቁ ከአንድ ወንድ ጋር በእኩል ነጥብ አንደኛ በመሆን የወርቅ ዋናጫውን ተቀበለች፡፡ወንድሟ ናኦል 53 ተኛ ወጥቶ ተመረቀ፡፡እና 5 አመት ከኖሩበት ከእዛ ማሳልጠኛ ውስጥ ልክ እንደአገባባቸው በጨለማ መኪና ውስጥ ተሳፍረው እንዲወጡ ተደረገ.፡፡ከሰዕታት ጉዞ በኃላ ግን ልክ መስቀል አደባባይ አካባቢ መኪናዋ ቆማ ስታወርዳቸው የተቀበለቻቸው ምስራቅ ነበረች፡፡
በወቅቱ ሁለቱም ያለልዩነት ነበር የተጠመጠሙባት፡፡እሷም በደስታ እና በከፍተኛ እርካታ ነበር የተቀበለቻቸው፡፡ስታያቸው ከበፊቱ በጣም አድገው ሙሉ ወጣት ሆነው ስላየቻቸው እጅግ ተደስታ ነበር፡፡ከዛ መኪና ውስጥ አስገባቻቸውና ቀጥታ ወደወላጆቻቸው ቤት ነበር የወሰደቻቸው፡፡ከመኪና ስትወርድ አብረዋት ወረዱ…ሰፈሩን ሲያዩና የቆሙበትን ሲረዳ ሁለቱም ደንዝዘው ነበር..ቀጥታ ሁለቱንም መሀከላቸው ገባችና ግራና ቀኝ እጃቸውን ይዛ ወደ ግቢው በራፍ ይዛቸው ሄደች…ሁለቱም በዝምታና በድንዛዜ ተከተሏት..ካዛ አንኳኩታ ሰውዬው ሲወጣ የሆነ ነገር ትለዋለች ብለው ሲጠብቁ..ኪሶ ገባችና ቁልፍ በማውጣት..‹‹ይሄው ቃል በገባሁት መሰረት የወላጆቻችሁ ቤት ቁልፍ ››ብላ ኑሀሚ እጅ ላይ አስቀመጠችላት፡፡ኑሀሚ አላመነችም፡፡ በድንዛዛ እጇን አንቀሳቀሰችና ቁልፉን ከፈተች.. አሸከረከረች… ተከፈተ.. ተንደርድራ ወደውስጥ ገባች፡፡ ወንድሟም ተከተላት፡፡ በረንዳው ላይ እስኪደርሱ አልቆሙም…የሳሎኑን በራፍ ስትገፋው ተዘግቷል፡፡ እጆ ላይ ባለው ቁልፍ ሞከረች ፤ተከፈተ……፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ እነሱ ምንም ሳይለፉና ሳይጥሩ ነበር በምስራቅና በደህንነት መስሪያ ቤቱ ጥረት የወላጆቻቸው ቤት የተረከቡት፡፡
ከዛ ሁለት ወር ሰይቆይ ኑሀሚ በስልጠናዋ ባስመዘገበችው ብቃት ምክንያት ለተጨማሪ የሶስት አመት ስልጠና ወደ ራሺያ ተላከች፡፡
ናኦል ደግሞ ቤተሰቦቹ ቤት እየኖረ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ትምህርቱን እየተማረ በተደራቢነት ከምስራቅ በሚሰጠው መመሪያና ተልዕኮ መሰረት የፊልድ ስረዎችን እንዲላመድ ተደረገ፡፡
ናኦል ከትዝታው ባኖ ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ሰዓት ሲያይ በጣም ነበር የተገረመው….ከለሊቱ10፡20 ሆኗል …ላለፉት አራት ሰዓት በላይ ባለፈ ታሪኩ ውስጥ ሰምጦ በትዝታ ሲዋልል ነበረ፡፡አካሉም ብቻ ሳይሆን አእምሮውም ዝሏ ነበር ፡፡
/////
ኮሎምቢያ/አሞዞን ደን ውስጥ
ካርሎስ ከጥልቅ እንቅልፉ ባነነ እና አይኖቹን ገለጠ፡፡በድቅድቁ ጨለማ በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ግዙፍ ዛፍ ላይ ቆንጆና ወጣት ልጅ ደረቱ ላይ ተኝታ ነው ያገኘው…ያለበትን ሁኔታ አሰበና ፈገግ አለ፡፡ቀስ ብሎ ከደረቱ ላይ ቀና አድርጎ ሲያስነሳት ነበር ከገባችበት ጥልቅ ትዝታ የነቃችው፡፡
‹‹ወይ ሀሳቤን ጥዬ ተንፈላሰስኩብህ አይደል?››አለችው፡፡
‹‹አይ የተፈጥሮ ጥሪ አጨናንቆኝ ነው››
‹‹ማለት?››
‹‹ሽንቴን…ኩላሊቴ ልትፈነዳ ነው››
‹‹እ ..ነው..ወርደህ ልትሸና ነው?፡፡
‹‹አይ ምን አስወረደኝ..ብወርድ ሽንት ቤት የለ ..ሜዳ ላይ ነው የምሸናው፡፡ ማይደብርሽ ከሆነ እዚሁ ሆኜ ልለቀው ነው፡፡››
በጨለማ ውስጥ የማይታየውን ፈገግታዋን እየለገሰችው‹‹ምን ቸገረኝ..ልቀቀው.››አለችው
‹‹አመሰግናለው ››አለና ቆመ፡፡ ዚፕን መክፈት ሲጀመር.
‹‹እንዴ…››ብላ አጉረመረመች
‹‹ምነው?››
‹‹ቢያንስ ፊትህን ወደእዛ አዙር እንጂ››
እኔ ብቻ መስሎኝ እንደዛ ምወደው
ካላየሁት ብዬ የምጨናነቀው
በጠዋት በማታ ሁሌ ምናፍቀው
ዛሬ እዛነው ሲሉ ልሄድ የም መኘው
ዛሬ እዚህ ነው ሲሉ የምጠባ በቀው
እንደዚ ምወደው እኔ ምን ሆኜ ነው??
እኔ ብቻ መስሎኝ ይሁንልኝ ያልኩት
ለካስ ሁሉም ሰው ነው እንደኔ ሚወዱት
ቢሆንልኝ ብለው ሁልጊዜ ሚ መኙት
ለብቻዬ ላደርግ እንዲያ የደከምኩት
በጣም ትክክል ነኝ መውደ ዴን ወደድኩት
ለካስ እልፍ ሰው ነው --ኑሮን -የሚወዱት??
ኑሮ ተወደደደደ.......
ለካስ
?
#ZENBILL_STORE
በኢትዮጲያ ውስጥ ትልቁ የመገበያያ የቴሌግራም መድረክ ነው።
? ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ይግዙ!
ካሉበት ሆነው ይዘዙን
Last updated 2 years, 6 months ago
ማራኪ ცЯムŋの የጫማ መሸጫ ቻናል
✔ማራኪ ብራንድ የፈለጉትን ጫማ በፈለጉት ሳይዝ እና ጥራት እናቀርባለን!
With free delivery
🔰Contact me
👉 @Maraki2211 or Call 0913321831
Admin
@maraki2211
💯Spammed users⚠
@Marakibrand2bot
Last updated 3 months, 4 weeks ago