ከ ደጋጎቹ ዓለም

Description
Comment @Kedegagochu0bot
Advertising
We recommend to visit

Your own Memes centre.

Memes | Memes | Memes

Last updated 3 years, 3 months ago

Retrouvez tous les encore disponible

Last updated 1 month ago

RETROUVEZ TOUTES LA SAGA POWER DANS CE CANAL 💯💯💕

NOTRE GROUPE DE DISCUSSION :

https://t.me/+4FF4MKYpUPI3ZWI0

Last updated 1 month, 1 week ago

2 months, 3 weeks ago

وَلَا تُطِعْ كُلَّ حَلَّافٍ مَّهِينٍ
هَمَّازٍ مَّشَّاءٍ بِنَمِيمٍ

ነገርን በሰዎች መሃል የሚያመላልስን ሰው አትታዘዝ።ጀምዓን በታኝ፣ጓደኝነትን አውዳሚ ነው። በዚህ ምክንያት ስንት ጓደኝነት ጠፋ።አንድ ሰው መልካምን ቢሰራ፣ ቢናገር ይህን የሚያስተላልፍ ሰው ያን ያህል ነው። መጥፎን ከተናገረ ግን ይህን የሚያስተላልፉ ሰዎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።

ቀደምት ደጋጎች ከ ነገር አመላላሽ የሚመጣን ነገር በር በመዝጋት ይታወቃሉ። አንድ ጊዜ ወህብ ቢን ሙነበህ رحمه الله ዘንድ አንድ ሰው ሲተላለፍ "የሆነ ሰው ሲሰድቦት አይቻለሁ" ይላቸዋል። ወህብም " እንደው ሸይጣን ካንተ ውጪ የሚልከውን ሰው አጣ?! ለ ሸይጣን መልእክተኛ አትሁኑ።" ብለው መለሱለት።

رسائل من القرآن

2 months, 3 weeks ago

ያለፈው ወንጀልህ ይቅር እንዲባልልህ በቀሪ እድሜህ ራስህን አስተካክል።

ኢብን ከሲር رحمه الله

2 months, 3 weeks ago

ሃላል የሆነ ስራን ፈልጎ ከቤቱ የሚወጣ ከሰዎች ፈተና መግጠሙ የማይቀር ነው።

ህይወትን እንዴት መግፋት እንዳለብህ ማሰብህ በራሱ ምንዳ አለው። ወንጀልህን ያስምራልና አታስብ።

"እንዴት መኖር እንዳለብህ ከማሰብ፣ ከመጨነቅ ውጪ የማይማር ወንጀል አለ።" ብሏል አንዱ ሰለፍ

ሃላል የሆነ ከስብን መፈለግ፣ ያንንም ለቤተሰብ ማበርከት ሚስተካከለው የሌለው ታላቅ የመልካም ስራ በር ነው ብሏል ኢብኑ ተይሚያህ رحمه الله

2 months, 4 weeks ago

ሰዎች ስላንተ የሚሉት ብዙም አያሳዝንህ። የተናገሩት ውሸት ከሆነ፤ ሳትሰራው የሚመዘገብልህ መልካም ስራ ይሆንልሃል። እውነት ከሆነ ደግሞ ቅጣቱ የፈጠነብህ ወንጀልህ ነውና ተቀበለው።

ኢብን ሙፍሊህ አል ሀንበሊይ رحمه الله

الآداب الشرعية

3 months ago

እውቀትን ፈለግኩኝ፣ የተወሰነ ያክል አገኘሁ።
አዳብን ፈለግኩ፣ ነገር ግን ባለቤቶቹ ሞተው አገኘኋቸው።

አብደላህ ኢብን ሙባረክ رحمه الله

3 months ago

إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَى اللَّهِ

ምንዳህ በአሏህ እንጂ ሌላ በማንም አይደለም።

ከጠቢባን አንዱ ከስስታምነት የባሰ መጥፎ ነገር አለ ወይ? ተብሎ ተጠይቋል። "አው፤ የዋለውን መልካም ውለታ የሚናገር ሰው ነው" ሲል መልሷል።

በምትሰራው መልካም ስራ ፊት ሁሉ አሏህን አድርግ።ከማንም ምንዳን አትጠብቅ።የሰዎች ጭብጨባን፣ ተከታይ ማብዛትን አትፈልግ።

ሰዎችን የፈለግክበት ስራ ሁሉ ለሰው ነው። አሏህን የፈልግክበት ስራም ለ አሏህ ነው።የ ኢብኑል ቀይ-ዩም ንግግር ትንሽ ያስፈራል "ስራህ ኢኽላስ ከሌለው አትድከም።"

إذا لم تخلص، فلا تتعب!

3 months ago

ለ አሏህ ባለህ ፍራቻ ልክ ፍጡራን ያከብሩሃል።ለ አሏህ ባለህ ውዴታ ልክ ፍጡራን ይወዱኃል። ለ አሏህ በተጠመድከው ልክ ፍጡራን ባንተ ጉዳይ ይጠመዳሉ።

ያህያ ቢን ሙዓዝ رحمه الله

3 months, 1 week ago

((يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمْ وَاخْشَوْا يَوْمًا لا يَجْزِي وَالِدٌ عَنْ وَلَدِهِ وَلا مَوْلُودٌ هُوَ جَازٍ عَنْ وَالِدِهِ شَيْئًا))

በዚህ አንቀጽ ላይ አባት ለልጁ የማይጠቅምበት፣ ልጅም ለ አባቱ የማይጠቅምበት ቀንን እንድንፈራ ያስጠነቅቀናል።

የ አባት አለመጥቀም ከልጅ አለመጥቀም ቀድሞ መጠቀሱ:- ልጅ ለ አባቱ ከሚጠቅመው በላይ አባት ለልጁ ስለሚጠቅም ነው ይላሉ። አባት ለ ልጁ ያለው ፍቅርም ልጅ ለ አባቱ ካለው ፍቅር በእጅጉ ይበልጣል።

#አባት

3 months, 1 week ago

በቀደምት ደጋጎች ጊዜ ከባዱ ፈተና እውቀትን ፍለጋ የሚደረግ ጉዞ ነበር። ለዚህም ብዙ ሊቃውንቶች እውቀት ፍለጋን የሚደረግ ጉዞን  አስመልክቶ ብዙ ኪታቦችን ጽፈዋል። ዛሬ ላይ ያ ችግር የለም።

ዛሬ ላይ ከባዱ ችግር ለዚህ ጉዳይ ቦታ አለመስጠት፣ እውቀትን በመቅሰም ላይ ትእግስት ማጣት እና ጽናት አለመኖር ናቸው።

ሌላው እውቀትን መማር ስንጀምር በራሱ ከየት መጀመር እንዳለብን እውቀቱ ያላቸውን ሰዎች አለመጠይቅ፣ የዚህንም አካሄድ ቢሆን እኔ አውቃለሁ በሚል አስተሳሰብ ራስን ገድቦ ማስቀመጥ ሌላው ፈተና ነው።

ከየት፣ በምን መጀመር እንዳለብን እወቀቱ ያላቸውን ሰዎች ከመጠየቅም አንፈር፣ እውቀትን ለመፈለግ ያለንም ሞራል ይጨምር።

አሏህ ያስተካክለን

5 months, 4 weeks ago

ከሚገርመው ነገር ውስጥ

አሏህን አውቀሃው አትወደውም፤ ወደርሱ የሚጣሩትን እየሰማህ መልስ ከመስጠት ግን ወደኋላ ትላለህ። ከርሱ ጋር በመሆን የምታገኘውን ትርፍ እያወቅክ ከርሱ ውጪ ላለ ነገር ስትለፋ ትኖራለህ። የቁጣውን ሃይል ከማወቅህ ጋር ጀርባ ሰጥተህ ትሄዳለህ።እርሱን በመታዘዝ የሚገኘውን ጣእም ትተህ ወንጀል በመስራት የሚደርስብህን የብቸኝነትን ህመም ትመርጣለህ። ልብህን በአልባሌ ንግግሮች ለማስደሰት እየጣርክ በርሱ ንግግር፣ እርሱን በማስታወስ ልብህን ስለማስፋት ግን ቅንጣት አታስብም። ከርሱ ውጪ ባለ ነገር ላይ ልብህን በማንጠልጠልህ የደረሰብህን ወይም የሚደርስብህን የልብ ስብራት፣ ወደርሱ ከመመለስ ውጪ የማይወገደውን ባዶነት እያወቅክ ወደርሱ ግን አትሸሽም።
ከዚህ የበለጠ የሚያስደንቀው ግን እርሱ ሊኖርህ እንደሚገባ እና እርሱን በጣም እንደምትፈልግ እያወቅክ፤ ከሱ እየራቅክ ከእርሱ የሚያርቅህን ነገር መፈለግህ ነው።

ኢብኑል ቀይ-ዩም رحمه الله

We recommend to visit

Your own Memes centre.

Memes | Memes | Memes

Last updated 3 years, 3 months ago

Retrouvez tous les encore disponible

Last updated 1 month ago

RETROUVEZ TOUTES LA SAGA POWER DANS CE CANAL 💯💯💕

NOTRE GROUPE DE DISCUSSION :

https://t.me/+4FF4MKYpUPI3ZWI0

Last updated 1 month, 1 week ago