የሀዋሳና አካባቢዋ ሰለፊዮች

Description
ቻናሉ ሀዋሳና አከባቢዋን በተመለከተ ከሰለፊዮች ጋር ሀቅን የምንማማርበት ፣ አጥማሚዎችን የምናስጠነቅቅበት ፣ አወዛጋቢዎችን የምናጋልጥበት ፣ ግራ የተጋቡትን የምንመራበት መድረክ …ይሆናል። ኢን ሻእ አላህ
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

1 year, 2 months ago

የሙነወር ልጅ ሆይ! ሲሪብዱ ውኃ መስሎህ ደርሰህ ስታየው ባዶ ሆነብህ?! አይዞህ¡
—————
የሙነወር ልጅ አንድ የሸይኽ ዐብዱልሀሚድን የድምፅ ፋይል ቻናሉ ላይ ለቆ ሲያበቃ እንዲህ ይላል:- “ይሄው ዐብዱልሐሚድ ኢትዮጵያውያን ዒልም ፈላጊዎች የመን ውስጥ በሚገኙ ታዋቂ የሰለፊያ መርከዞች ሄደው እንዳይማሩ እያስጠነቀቀ ነው። ለንዲህ አይነት እንዳበደ ውሻ ሁሉን ለሚናከስ ሰው ፈፅሞ አክብሮት አይኖረንም።” አለ።

በመሰረቱ መች አክብሩኝ አሉዋችሁ?!። አንተም ሆንክ የቡድኑ አባላት አቅም አጥሯችሁ እንጂ በድብቅም በገሃድም አንዲት መንሃጃዊ እንከን ስታጡና ለትችት የሚያበቃ ግልፅ የሆነ ማስረጃ ስታጡ አማርኛ ከሽናችሁ በመሳደብ ረገድ ያስቀራችሁት ነገር አናውቅም!። "ተሳስተዋል" ብላችሁ ካሰባችሁ ማስረጃ ከማቅረብ ይልቅ አንተም ሆንክ ሳዳት ከማል የመንደርተኛ ስድብ የተሳደባችሁት ለዚያ ነው። እንዳበደ ውሻ አለያም እንደ ጀማሪ እብድ የምትለቁትንም ሆነ የምትናገሩትን መለየት ያቀታችሁ ወፈፌዎች እናንተው ናችሁ።
አስተዋይ ወገኖቼ ሆይ! ኢብኑ ሙነወር ወደለቀቀው የሸይኹ ንግግር ልመልሳችሁና እናንተው ፍረዱ!!

የተከበሩት ታላቁ ሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁላህ) ዝንባሌ ያለበትን ሁሉ ወባ እንደያዘው በሚያንቀጠቅጠው በተለመደው አንደበታቸው፣ ሲናገሩበት ጣፋጭ በሆነው ዐረቢኛ ቋንቋ ወደ የመን የሚሄዱ የዲን ተማሪዎችን እንዲህ በማለት ይመክራሉ:-
“እኔ ሁሉንም የዲን ተማሪዎች በምእራብም  በምስራቅም በኩል ያሉትን ሁሉ፣ የትኛውንም አንዳች ዝንባሌ ያለበትን የተመዩዝም ችግር  ይሁን፣ የኢኽዋንነት አለያም የተምይዕም ይሁን የሀጃዊራንትም ችግር ያለበትን… መድረሳም ይሁን ሸይኽ፣ አለያም ኡስታዝ ዘንድ፣ ወደ ደማጅም ይሁን ወደ ተዒዝ… (የመን ውስጥ የሚገኙ የአካባቢ ስም ናቸው) እንዳይሄዱ እመክራለሁ… እንደሰማነው ከሆነ እዛጋ ኢኽዋኖችም፣ ሙመይዓዎችም፣ ሺዓዎችም ሀጃዊራዎችም አሉ። እርግጥ ነው ሱኒዮችም ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን በተጨባጭ ስለነሱ የማውቀው ነገር የለም። በመሆኑም የዲን ተማሪዎችን ወደዛ እንዲሄዱ አልመክርም። ለእውቀት ፍለጋ ወጥተው ጥቅም ከማግኘታቸው ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላልና። ሸይኽ ሙሀመድ አል-ኢማም በኪታቦቹ የተወሰነ ነገር እንዳለባቸውና በንግግሩም ነጥቦች እንደተያዙበት፣ እንዲሁም እራሱ ወደ ሙመይዓ እንደሚያዘነብል ይነገርበታል።” ይላሉ።
(ዐረቢኛ የምትችሉ የሙነወር ልጅ የለቀቀውን ሸይኹን የድምፅ ፋይል በሚከተለው ሊንክ አውርዳችሁ አድምጡት)

⤵️⤵️
https://t.me/IbnShifa/1812

ወገኖቼ ሆይ! ታዲያ የቱ ጋር ነው የሸይኹ ስህተት?!። እንዲያውም ሸይኹን ጨምሮ ሱኒይ ሠለፊይ ወገኖችን በሀጃዊራነትና በሀዳዲይነት ነው ሲወርፉ የነበረው። አሁን ደግሞ ሸይኹ ከሀጃዊራዎችም ከሙመይዓዎችም መድረሳ ያስጠነቀቁበትን የድምፅ ፋይል ለቀው "ከሰለፊያ መርከዞች ያስጠነቅቃል" በማለት ለመወረፍ አቧራ ሊያስነሱ ይቃጣቸዋል። ለመሆኑ የትኛውን የሠለፊያ መርከዝ ስም ጠቅሰው ነው ያስጠነቀቁት?!

ይልቅ የሸይኹን ድምፅ ስሰማ "እውነትም ዑለማዎች የነቢያት ወራሽ ናቸው!" አልኩኝ። ምክንያቱም ነቢያት ህዝባቸውን ወደተለያየ ጥፋትና ጥመት እንዳይገባ ሲከላከሉ አሳልፈዋል!!። ነቢይነት ከተቋረጠ በኋላ ደግሞ የነቢያት ወራሽ የሆኑ እውነተኛ ሰለፊይ ዓሊሞች ህዝባቸው አውቆም ይሁን ሳያውቅ ወደ ጥፋት እንዳይገባና ሀቅ መስሎት በጥመት አንጃዎች እንዳይጠለፍ ይከላከላሉ!!። ለዚያም ነው ሸይኹ ወደ የመን የሚጓዙ የዲን ተማሪዎችን ከዝንባሌ ባለ ቤቶች (ከጥመት አንጃዎች) ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የመከሩት!!።

ካልቀጠፉ አይሆንላቸውም አይደል?! እራሱ  በለቀቁ የሸይኹ ድምፅ ሸይኹ እንዲህ ይላሉ:- “እርግጥ ነው ሱኒዮችም ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን በተጨባጭ ስለነሱ የማውቀው ነገር የለም።” ብለው እየለዩ፣ እሱ ግን “ልብ በሉ! በጅምላ ነው እያስጠነቀቀ ያለው።” በማለት ይቀጥፋል። ያው ወደ ቢድዐ ያዘነበለ ሁሉ ከውሸት ድርሻ አለው አይደል?!፣ ምን ያድርገው የመንሃጁ አመል ሆኖበት ነው!።

ከውስጣችሁ አንድ ቅን የሆነ አስተዋይ ሰው ይጥፋ?!፣ ትላንት ስትናገሩትና ስትፅፉት የነበረውን የሚጠቁምና የሚያስታውስ የአሁኑን አካሄዳችሁን ቢያንስ ከትላንቱ በማነፃፀር ለማስተዋል የሚጋብዛችሁ አንድ አስተዋይ ሰው ጠፋ?! ለሀቅ ከመወገን ይልቅ ለቡድኗ  መወገን ብቻ ሆነ፣ በቃ በአንድ ሳንባ መተንፈስ ነው?!። አንድ የተሻለ አስተዋይ ለቡድኗ ዘብ ከመቆም ይልቅ ለሀቅ የሚቆረቆር ሰው ከውስጣችሁ ይጥፋል? ! እንዳሻህ ስትናገር ስትፈነጭ የተናገርከውን ከማስራጨት ይልቅ ቆም ብሎ የሚያስተውል የለም?!

أَلَيْسَ مِنكُمْ رَجُلٌ رَّشِيدٌ
«ከእናንተ ውስጥ ቅን ሰው የለምን።» ሁድ 78

የሙነወር ልጅ ሆይ! በሰለፊይ መሻይኾችና ወንድሞች ላይ አንዳች ለቅጥፈታችሁ ግብኣት የምትሆን ስህተት ካገኘን ብላችሁ ለመልቀም ከመቋመጣችሁና ከሰለፊዮች መንሀጃዊ ችግር ከማግኘት ጥማታችሁ የተነሳ የሰለፊዮችን ስራ በተንሸዋረረ ዓይናችሁ ስለምትመለከቱት ሲሪብዱ ውኃ መስሏችሁ አሰፍስፋችሁ ቦታው ላይ ስትደርሱ ምንም የሌለው ባዶ ሆነባችሁ?!።

كَسَرَابٍ بِقِيعَةٍ يَحْسَبُهُ الظَّمْآنُ مَاءً حَتَّىٰ إِذَا جَاءَهُ لَمْ يَجِدْهُ شَيْئًا

«በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ የጠማው ሰው ውሃ ነው ብሎ እንደሚያስበው በመጣውም ጊዜ ምንም ነገር ሆኖ እንደማያገኘው ነው፡፡» አን-ኑር 39

ሲሪብዱ ማለት:- አላህ ቁርኣን ላይ እንደገለፀውም በርሃማ አካባቢዎች በርቀት ሲታይ ውኃ የሚመስል ነገር ግን በቅርበት ሲታይ ምንም ያልሆነ ባዶ ነው።
✍?ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

Telegram

[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

የታላቁ ሸይኽ ምክር! نصيحة فضيلة الشيخ العلامة عبد الحميد التمي حفظه الله لطلاب العلم الذين يذهبون الى اليمن ወደ የመን ለሚጓዙ የዲን ተማሪዎች ከታላቁ ሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁላህ) የተሰጠ ምክር! ይህ የሸይኹ ምክር የሙነወር ልጅ ሸይኹን ለመተቸት እንደማስረጃነት ከጠቀመኝ ብሎ ቆራርጦ ቻናሉ ላይ የለቀቀው ድምፅ ሳይቆራረጥ የተገኘ…

1 year, 2 months ago

? ማነው የአንድነት ፀር?

? ሙመይዓ የምታነሳዉን ማደናገሪያ ግልፅ ማድረግ

?ከማምታቻቸው ውስጥ ሰለፊዮችን አትላያዮ ለሚሉት በቂ መልስ

?لفضيلة الشيخ الدكتور
أبي أنس محمد بن هادي المدخلي
حفظه الله تعالى و رعاه

https://t.me/abuabdurahmen

1 year, 2 months ago

?ተግባራዊ ተመዩዝ ትልቅ የሰለፊይነት መገለጫ ነው።

?በዚህ የተመዩዕ ዘመን የነቢያትና የሰለፎች መንሃጅ የሆነው ተመዩዝ የሰለፊዮች ግልፅ መታወቂያ መሆን አለበት።

?ከአጥማሚ አንጃዎች የእውነት ተላቀቅ።
?ሚዛናዊና አዋቂ መሳይ መሃል ሰፋሪዎችን ተጠንቀቅ።

?ከአሸይኽ ዐብዱላህ አልቡኻሪይ ትምህርት የተወሰደ።

https://t.me/Abuhemewiya

1 year, 2 months ago

? ሙስጠፋ መደመሩን በድምፁ ሲያረጋግጥ ስሙት ?

ልብ በሉ እነ ሙስጠፋ ተባብረውና ስልጣን ተከፋፍለው የሚያጅቧቸው አካላት ጥመታቸውን አውቀውና አምነውበት ነው።

? "ሙጅሪሞች"
? "ኢኽዋኖች"
? "ሱሩሪዮች"
? "የሱነህ ጠላቶች" …

ከሙብተዲዕ ተለጥፈው ሲያበቁ "ጥቅም ለማስከበር ነው" የሚሏት ማታለያ የሁሉም ሙመይዓዎች መታወቂያ ነች።

? ከሙመይዓህ መንሃጅ ውጡ።

? ከሙብተዲዕ ጋር ተደምሮ ሰለፊያ የለም።

?እውነትን ለፈለጋት ግልፅ ሆናለች።

???ይቀጥላል

https://t.me/HAWASSA_SUNIY

1 year, 3 months ago

**ቀለል ባለ መልኩ የ
عيسى عليه السلام في ميزان الإسلام
لفضيلة الشيخ حسين بن محمد السلطي

የሚለውን የኪታብ ቂርአት
በሼኽ አብድልሀሚድ ለማግኘት

ከክፍል አንድ እስከ መጨረሻ ድረስ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

ክፍል አንድhttps://t.me/abuumuawiya/4092https://t.me/abuumuawiya/4092 ክፍል ሁለትhttps://t.me/abuumuawiya/4093https://t.me/abuumuawiya/4093 ክፍል ሶስትhttps://t.me/abuumuawiya/4094https://t.me/abuumuawiya/4094 ክፍል አራትhttps://t.me/abuumuawiya/4095https://t.me/abuumuawiya/4095 ክፍል አምስትhttps://t.me/abuumuawiya/4096https://t.me/abuumuawiya/4096 ክፍል ስድስትhttps://t.me/abuumuawiya/4097https://t.me/abuumuawiya/4097 ክፍል ሰባትhttps://t.me/abuumuawiya/4098https://t.me/abuumuawiya/4098 ክፍል ስምንትhttps://t.me/abuumuawiya/4099https://t.me/abuumuawiya/4099 ክፍል ዘጠኝhttps://t.me/abuumuawiya/4100https://t.me/abuumuawiya/4100 ክፍል አስርhttps://t.me/abuumuawiya/4101https://t.me/abuumuawiya/4101 ክፍል አስራ አንድhttps://t.me/abuumuawiya/4102https://t.me/abuumuawiya/4102 ክፍል አስራ ሁለትhttps://t.me/abuumuawiya/4103https://t.me/abuumuawiya/4103 የኪታቡን pdf ለማግኘት**https://t.me/abuumuawiya/4091https://t.me/abuumuawiya/4091

Telegram

Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)

ክፍል አንድ https://t.me/abuumuawiya/4092

1 year, 4 months ago

?የተከበሩት የአርሽ ተሸካሚ መላእክት ዱዓእ ለሰለፊዮች ይድረስ

? አስደማሚ ትስስር ፣ እውነተኛ ውዴታ ፣ ታላቅ ስኬት‼️

?ሱረህ ጋፊር 7 _9

በደንብ አስከምንረዳው ድረስ ደጋግመን እናድምጠው እናስተንትነውም።

ከሸይኽ ዐብዱረህማን ኢብኑ ናሲር አሰዕዲይ ተፍሲር:
:? تيسير الكريم الرحمن في تفسير كلام المنان

?አላህ ሆይ ዱዓው ከሚደርሳቸው ባሮችህ አድርገን !
https://t.me/Alkuraan_Wasuneh

1 year, 4 months ago

? አራቱ መሰረታዊ መርሆች!

?የምንጀምረው ቀዋዒድ አልአርበዕ የሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብዱልወሃብ ኪታብ ማብራርያ ትምህርት ነው።

?ያብራሯት  አሸይኽ ሳሊህ አል_ፈውዛን  አላህ ይጠብቃቸው።

?شرح قواعد الأربع
  لفضيلة الشيخ صالح بن فوزان بن عبد الله
الفوزان حفظه الله

?ሰኞ፣ ማክሰኞ    

?እሮብ፣ሀሙስ     

? ከአሱር ቡኃላ  11:00~11:30 ሰዓት ድረስ።

?አቡ አብዱረህማን

? ዛሬ ሰኞ ይጀመራል።

ኢን ሻእ አላህ❗️

የኪታቡን Pdf ለማግኘት ⤵️ ⤵️
https://t.me/Mustefatemam/2113

https://t.me/mustefatemam

Telegram

🎤ሙስጠፋ (አቡ አብዱረህማን)✍

https://t.me/Mustefatemam/2113

1 year, 4 months ago

*?ጥብቅ ማስታወሻ*

ሂዝቢዮች በዲኑ ላይ ከሚሰሯቸው ግፎች አንዱ ሀቅን መደበቅ እንደሆነ ይታወቃል።
አላህ ደግሞ በረህመቱ እነዚህን ሌቦች የሚያጋሉጡ ጀግኖች በየዘመኑ አሉት።

ዛሬ አንድ ደርስ ላይ አሸይኽ ዐሊይ አልሃሪሲይ (ሀፊዘሁላህ) ስለ ማተሚያ ቤቶች ተንኮል አንስተው ነበር።

በዚህም የአሸይኽ ሳሊህ ኢብኑ ኡሰይሚን ኪታቦች በብዛት የሚታተሙበት
  مؤسسة بن عثيمين الخيرية
ሙአሰሰህ (ድርጅት) ኢብኑ ኡሰይሚን ስለ ሂዝቢዮች ያስጠነቀቁባቸውን ብዙ ንግግሮች እየቆረጠ እንደሚያስቀር አጋልጠዋል ። ድርጅቱን የሚያንቀሳቅሱት ሂዝቢዎች ስለነበሩ ነው። ሌሎች ኡለማዎችም ይህን ማጭበርበር አስተውለው እንዳስጠነቀቁ ጠቁመዋል። በደርሱ ላይ ከነበሩ ጡላቦችም የሚገርሙ ድርጅቱ የቆረጣቸው ነጥቦች በምሳሌ ተነስተዋል። በተለይም ሂዝቢዮችን የሚነኩ እና ሰለፊያን የሚደግፉ ያሏቸውን ጉዳዮች ይሰርዛሉ ተብሏልና በዚህ ጉዳይ ከሚከተለው ድርጅት በኩል የሚመጡ እትሞች ላይ ጥንቃቄ ይደረግባቸው።
:مؤسسة بن عثيمين الخيرية
https://binothaimeen.net/foundothemen/

በዚህ ዘርፍ (የሸይኹን ኪታብ በማተም) የግብፅ እትሞች በጣም የተሻሉ እንደሆነም ሸይኻችንም ሌሎችም ኡለማዎች ይጠቅሳሉ። በአብዛኛው ግብፆቹ ትኩረታቸው ንግድ ላይ ብቻ ስለሆነ ያለውን ድምፅ እንዳለ እንደሚያትሙት ተስተውሏል።

አላህ ከሂዝቢዮች ተንኮል ይጠብቀን።

1 year, 4 months ago

? የመውሊድ ምግብ ሀራም ነው።

?ቢድዐን ከፍ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው።
? እነርሱን መተባበር ፣ ማጀገን፣ እውቅና መስጠትና ማበረታታት ነው።
? ለመውሊዱ የታረደውም ይሁን ሌላው ምግብ ሀራም ነው።

?ስለ ቢድዓህ ክፋት ለዚያውም የመውሊድን አደጋዎች ያወቀ አይዳፈርም።

?አሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን

https://t.me/FATTAWAS

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago