الدعوة السلفية في الحبشة

Description
يأيها ٱلذين ءامنوٱ توبوٱ إل الله توبة نصوحا
Advertising
We recommend to visit

- بعدها عيونك احلى عيون بعيوني .
- انستا https://instagram.com/Z22X
- بوت حجز تمويلات @fpbot .
- قناة التمويلات | @ossss .
- لطلب التمويل | @sssso .
-

Last updated 1 month, 3 weeks ago

• قناة البصمات الخاصة ببوت فسنجون 💖

- قناة المطور : @KekoDev

- معرف البوت : @iizBot

- للتمويل : @kekoibot

حساب المطور : @HHHHD

Last updated 2 weeks ago

نحنُ الاول في كل شيء اما غيرنا فلهم التالي •●

المالك ستيفن ~~> @AliAbbas95

Last updated 11 months, 3 weeks ago

8 hours ago

ደ እነርሱ ከተጠጋ ደግሞ 'ሰለፍይ' የሚል ስያሜ ይሰጠዋል፡፡ ሶሃቦችን የተከተለ ሁሉ ይህ ስያሜ እንደሚሰጠው ኡለሞች ተስማምተዋል፡፡

ይህ ስያሜ ከቁርዓንና ከሐዲስ ያላፈነገጠ ከመጀመሪያው ትውልድ ጋር ለቅጽበት ያክል እንኳ የማያነጣጥል ስያሜ ነው፡፡ ሰለፎች ከተጓዙበት ጐዳና ካፈነገጠ ግን በሰለፎች መካከል እንኳ ቢሆን በዚህ ስያሜ አይጠራም፡፡”
በተጨማሪ “ሂልየቱ አጥ'ጧሊቢል ዒልም” በሚባለው ኪታባቸው ገጽ (8) ላይ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

“በቀጥተኛው ጎዳና ላይ ሰለፍይ ሁን!”
ሰለፍይ የሚለው መጠሪያ በታሪክ መጽሐፎችም ተዘግቦ ይገኛል፡፡

የታሪክ ጸሐፊው ኢማም አዝ'ዘህብይ - ረሂመሁሏህ - “ሙዕጀሙ አሽ'ሹዩኽ” በሚባለው ኪታባቸው (ጥራዝ 2\ ገጽ 280) ላይ ስለ ሙሐመድ ብን ሙሐመድ አል'በሕራንይ የሒዎት ታሪክ ሲገልጹ “ዲነኛ መልካም ሰለፍይ ነበር” በማለት አሞካሽተውታል፡፡
በዚሁ ኪታብ ( ጥራዝ 1\ ገጽ 34) ላይ ደግሞ የአህመድ ብን ኒዕመህ አል'መቅድሲይን የሒዎት ታሪክ ሲናገሩ “በሰለፎች ዓቂዳ ላይ ነበር” በማለት የምስክርነት ቃላቸውን ሰጠዋል፡፡

ትክክለኛው ሰለፍይና የነርሱን ካባ ለብሶ በነርሱ ስም ከሚነግደው ለመለየት እንዲሁም በነርሱ የመከተል ፍላጎት ያለው ሰው ብዥታ ውስጥ እንዳይገባ ወደ ሰለፎች መጠጋቱ ግዴታ ሆኗል፡፡ ጠመው የሚያጠሙ ቡድኖች ቁጥራቸው ሲበዛ የሐቅ ባለቤቶች እራሳቸውን ወደ ሰለፍ ያስጠጋሉ፡፡
አላህ ለነብዩ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - እና ለአማኞች የሚከተሉትን ቁርዓናዊ አንቀጾች አውርዷል፡-

{ فَإِن تَوَلَّوْاْ فَقُولُواْ اشْهَدُواْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ } آل عمران: ٦٤

ትርጉም
“እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡”
(አል'ዒምራን፡ 64)
{ وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلاً مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحاً وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ }
فصلت: ٣٣
ትርጉም
“ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ 'እኔ ከሙስሊሞች ነኝ' ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?” (ፉሲለት፡ 33)

{ وَمَا أَنَاْ مِنَ الْمُشْرِكِينَ } الأنعام: ٧٩

ትርጉም
“እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም፡፡” ( አል'አንዓም፡ 79)

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

8 hours ago

ጥያቄ 13፡- “ሰለፍይ” ተብሎ መጠራቱ እንደጐጠኝነት ይቆጠራል?

መልስ/ እውነተኛ ሰለፍይ ከሆነ በዚህ ስም መጠራቱ ችግር የለውም፡፡(²⁰) ከሰለፎች ጎዳና ውጭ ሆኖ “ሰለፍይ” ነኝ ማለቱ ግን ክልክል ነው፡፡ ለምሳሌ፡- አሻዒራ የሚባሉ ቡድኖች አህለሱናህ ወልጀማዓ ነን በማለት ይሞግታሉ፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ ምክንያቱም እነርሱ ያሉበት ጎዳና ከአህለሱናህ ወልጀማዓ ጎዳና ፍጹም ይለያል፡፡ ሙዕተዚላዎችም እንደዚሁ እራሳቸውን የተውሂድ ሰዎች አድርገው ይቆጥራሉ፡፡

كل يدعى وصلا لليلى وليلى لا تقر لهم بذاكا
ሁሉም ይሞግታል የኔ ናት ብሎ ለይላ
ለአንዱም አታረጋግጥ ፍቅሬ ላንተ ነው ብላ
አንድ ሰው አህለሱናህ ወልጀማዓ ነኝ ብሎ ከሞገተ የአህለሱናህ ወልጀማዓን መንገድ መከተል ተቃራኒውን ደግሞ መተው ግድ ይለዋል፡፡ ‘እሳትንና ውሃን’ ወይም “አርጃኖንና አሳን” በአንድ ላይ ማኖር ትችላለህ? በፍጹም ማኖር አትችልም፡፡ አህለሱናህ ወልጀማዓ ከኸዋሪጅ፣ ከሙዕተዚላና እራሳቸውን “ዘመናዊ ሙስሊሞች” ነን ብለው ከሚያስቡ ሂዝቢያዎች ጋር መቀላቀል ማለት የዘመኑን ጥመት ከሰለፍ መንሃጅ ጋር ማደባለቅ ማለት ነው፡፡ የመጨረሻውን ማህበረሰብ የሚያስተካክለው የመጀመሪያው ማህበረሰብ የተስተካከለበት መንገድ ብቻና ብቻ ነው፡፡
ተፈላጊው ቁምነገር ነገሮችን መለየትና ማጥራት ነው፡፡

=================================

(²⁰) ውድ አንባቢያን! ከስምንት መቶ ዓመት በፊት የነበሩት ሽይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ - ረሂመሁሏህ - እራሱን በአሊምነት አስቀምጦ የሚከተለውን አደገኛ ንግግር ለተናገረው 'ዳዒ' አሁን በአካል ተገኝተው ምላሽ የሚሰጡ ይመስላል፡፡

“ኢኽዋንነትን ሰለፍይነትን ተብሊግነትን ሱሩርይነትን በአንድ ሰው ላይ ግዴታ ያደረገ ጸጸት ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ከተጸጸተ መልካም ካለበለዚያ ግን ይገደላል”!! (©)

ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ - ረሂመሁሏህ - በፈታዋ ኪታባቸው (ጥራዝ 4 / ገጽ 149) ላይ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"አንድ ሰው ወደ ሰለፍ መዝሀብ እራሱን ቢያስጠጋ ወይም በዚህ ስያሜ ቢጠራ ነውርነት የለውም፡፡ እንዴውም ይህን ጉዳይ መቀበሉ ግዴታ እንደሆነ ኡለሞች ተስማምተዋል፡፡ ምክንያቱም የሰለፎች መዝሀብ ሐቅ እንጅ ሌላ ተልዕኮ የለውምና፡፡"

(©) ይህ ኪታብ ከተጠናቀቀ በኋላ “ሙጋለጧት” በሚል ርዕስ “አኢደል ቀረኒ” ከተወሰኑ ስህተቶቹ መጸጸቱን የምትገልጽ ትንሽ ወረቀት ድንገት በእጀ ገባች፡፡ በመሆኑም ከፍትሃዊነት አንጻር እርሱ ከተመለሰባቸው ስህተቶች መካከል አንዷን ብቻ ልጥቀስ፡-

አስራ አራተኛው ነጥብ፡- “ፊረ ሚነል ሒዝቢየቲ ፊራረከ ሚነልአሰድ” በሚለው ካሴት “ኢኽዋንነትን ሰለፍይነትን ተብሊግነትን ሱሩርይነትን በአንድ ሰው ላይ ግዴታ ያደረገ ጸጸት ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ከተጸጸተ መልካም ካለበለዚያ ግን ይገደላል” የሚል ንግግር ከዚህ ቀደም ተናግሬ ነበር፡፡
ይህ አገላለጼ ስህተት ነው፡፡ አላህንም ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ እኔ ለማለት የፈለግሁት ይህን የሰራ በርግጥ ሸሪዓን ደነገገ ለማለት ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ አገላለጼ ስህተት ነው ይቅርታን እጠይቃለሁ፡፡ የሰለፎች መዝሃብ ሊጓዙበትና ሊከተሉት ግድ የሆነ ትክክለኛ መዝሃብ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡”

ከጥቂት ስህተቶች ብቻ ሳይሆን ከአጠቃላይ ስህተቶች ተጸጽቶ መመለስ ፤ ጥቂቶች እንጅ ማንም ሰው በማያውቀው መንገድ በወረቀት ጠቅልሎ መላክ ሳይሆን ስህተቱ በተሰራጨበት ቦታ ሁሉ ግልጽ ማድረግ የሰለፎች ጎዳና ነው፡፡

ኢብኑል ቀይም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

“ወደ ቢድዓ ሲጣራ የነበረ ሰው ጸጸቱ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ሲያሰራጨው የነበረው የቢድዓና የጥመት ጎዳና ትክክል አለመሆኑን እውነታው እርሱ በተናገረው ተቃራኒ መሆኑን በአደባባይ ይፋ ማድረግ አለበት፡፡”

(ዑድ'ደቱ አስ'ሷቢሪን ፡ ገጽ 93)
እውነት በዚህ የከፍተኛ ዶክትሬት ዲግሪ ባለቤት ላይ የተገኘችው ስህተት አንድ ብቻ ነች? እስኪ “አል'ሚስክ ወል'ሚንበር” በሚባለው ኪታቡ (ጥራዝ 1\ ገጽ 189) ላይ የጻፈውን እናንብብ፡-

“ለተጠናቀቀው የነብዩ ሙሐመድ የስደት ዓመት ምን አዘጋጀን? እኔ ገርሞኛል አንተም ተገረም!1 ጧት ጧት የሚወጡ ጋዜጦችና የቴሌቪዥን ማሰራጫዎች ሁሉ የት ገቡ? በነብዩ ሙሐመድ ዳዕዋ ያንጸባረቀች አገር ታላቁን ነብይ አለማስታወስ ምን ይባላል? ለክብረ በዓሉ ድምቀት ትንሽ እንኳ ምሰሶ ወይም ድንኳን አለማዘጋጀት ምን ማለት ነው ?!!”

ይህን አገላለጽ በሌሎች አገሮች ከሚከበረው የመውሊድ በዓል ጋር እስኪ አነጻጽሩት? አይመሳሰልም? - ምስጋና ለአላህ ይገባው - ሱዑዲን ከልብ ወለድና ከቢድዓ ተከታዮች አላህ ጠብቋታል፡፡

ይህ ዳዒ ከላይ በተጠቀሰው ኪታብ ( ጥራዝ 1\ ገጽ 190) ላይ ደግሞ የሚከተለውን ንግግር ተናግሯል፡-

“እነዚህ ሰዎች ነገ የትንሳኤ ቀን ከረሱል ፊት ሲቀርቡ ምን ዓይነት ምላሽ ሊያቀርቡ ይሆን?!!”
ቅድም ከተናገረው ንግግር በፊት ደግሞ ረሱልን - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - አስመልክቶ የሚከተለውን ወሰን ያለፈ ንግግር ተናግሯል፡-
“ሕዝበ ሙስሊሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጻ እንዲወጣና እንዲስተካከል ላደረገው የዓለም አይን አንድ ቃል ወይም አንድ ታሪክ እንኳ አለመናገር?”

ነብዩን - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የዓለም አይን ብለው የሚገልጿቸው ሱፍያዎች መሆናቸውን ልብ በል!

እንዴት ስለነብዩ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - ታሪክ አንድ ቃል እንኳ አልተናገሩም ብሎ ሰለፍይ የሆኑ ዳዒዎችንና አሊሞችን ይኮንናል? በመጥፎስ እንዴት ይጠረጥራል? ምናልባት ታሪካቸው እርሱ በሚፈልገው የመውሊድና የሂጅራ በዓል ዓይነት እንዲወሳ ፈልጎ ካልሆነ በቀር ሰለፍዮች ስለነብዩ ታሪክና መልካም ገጽታ ስንት መጽሐፍ ጽፈዋል? አላህ ሆይ! ከንዲህ ዓይነቱ ቅጥፈት ሰላም አድርገን! ስለዚህ ዳዒ ተጨማሪ ዕውቀትን ከፈለግህ አስር ዓመት ታስሮ ከወጣ በኋላ የጻፈውን ጽሑፍ አንብብ፡፡

ሱብሃን አላህ! ትክክለኛ የሆነውን የሰለፎች ጎዳና ከሙብተዲዖች ጎዳና ጋር በአንድ ላይ ጨፍልቆ እንዴት ይናገራል?

ኑዋሪነቱ ሱዑዲ የትምህርት ደረጃው ደግሞ የከፍተኛ ዶክትሬት ዲግሪ ለሆነው ለዚህ ግለሰብ አንድ ጥያቄ ላቅርብ፡-
አንተ ሰለፍይ ካልሆንህ ምን መሆን ትፈልጋለህ?!
“ሰለፍይ” እና “አሰርይ” ተብሎ መጠራቱ ራስን እንደማመጻደቅ ተደርጐ ይቆጠራል? የሚል ጥያቄ ሸይኽ ዓብዱልዓዚዝ ብን ባዝ - ረሂመሁሏህ - ቀርቦላቸው የሰጡት መልስ የሚከተለው ነበር፡-

"በትክክል 'አሰርይ' ወይም 'ሰለፍይ' ከሆነ በዚህ ስያሜ መጠራቱ ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም ሰለፎች 'እከሌ ሰለፍይ ነው' 'እከሌ አሰርይ ነው' በማለት ይጥ'ጠሩ ነበር፡፡ ይህች ስያሜ ዘወትር መኖር ያለባትና ግዴታ የሆነች ስያሜ ነች፡፡”

((ጧኢፍ ከተማ በቀን 16/01/1413 ሒ. "ሀቁል ሙስሊም” በሚል ርዕስ ካዘጋጁት ትምህርት የተወሰደ፡፡))

ሸይኽ በክር አቡዘይድ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

“ 'አስ'ሰለፍ' 'አስ'ሰለፍዩን' እና 'አስ'ሰለፍያህ' የሚሉ መጠሪያዎች ከልብ ወለድና ከስሜት አግልለው ቀጥተኛ በሆነው የነብዩ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - መንገድ ከተጓዙት ሶሀቦችና እነርሱንም በመልካም ከተከተሉት ማህበረሰቦች ጋር ያስተሳስራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት 'አስ'ሰለፍ' 'አስ'ሰለፍዩን' ወ

1 day, 18 hours ago

بحر حقا بحر .بحر السنة

1 week, 1 day ago

ሜጋባይቱ የተቀነሰ

👇
🔊《ልዩ የሆነ ታላቅ ሙሃደራ በታላቁ ሸይኽ》

🔗ርዕስ:- ተውሒድ በመጀመሪያም በመጨረሻም

🔗 (التوحد أولا وأخيرا)

🕌በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ዓለም ባንክ በዳር አስ-ሱንና የሸሪአ እውቀት ማዕከል የተደረገ

#ማሳሰቢያ ተውሒድ እውቀት አዘል በሆነ መልኩ የተዳሰሰበትና አህባሾች የሚረጩት መርዘኛ ቫይረስ ሁሉ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች እየተነሱ ስሩ እንዲደርቅ ተደርጎ የተነገረበት ሙሀዶራ ነውና ማንኛውም ተውሒድ የሚያሳስበው ሁሉ (በተለይ የአሻኢራና የአህባሾች መርዘኛ እምነት መስፋፋት) የሚቆረቁረው ሁሉ ይሄን ሙሀዶራ በትእግስት በማድመጥ ማሰራጨት ላይ መቻኮል ያስፈልጋል።

🎙️በዱክቱር ሸይኽ ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አል ኢትዮጵይ አስሌጢ { ሀፊዘሁላህ}

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/Abdurhman_oumer/5472
.

1 week, 5 days ago

📓አዲስና ወሳኝ ተከታታይ ደርስ
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
↩️ عنوان፡- ➘➷➴
📒 هداية المستفيد في أحكام التجويد

↪️ ርዕስ፦➷➴➘
📒 ሒዳየቱል ሙስተፊደድ

╭─••°─═•°•═─•••─╮
📖  ደርስ ክፍል  06 📖
╰─••°─═•°•═─•••─

📄ኪታቧን በ𝕡𝕕𝕗 ለማግኘት
 ➘➷➴➘➷
https://t.me/abuzekeryamuhamed/6594

📝 المؤلف الشيخ محمد المحمود المشهور بأبي ريمة «رحمه الله»
📝 አሸይኽ ሙሀመድ አል’መህሙድ አላህ ይዘንላቸው

*🎙بِالْأَخِ أَبِـي زَكَـرِيَّا مُحَمَّدُ بِـنْ عَبْدِ اللهِ بِـنْ عَـلِيِّ الْـوَلْقِـطِيُّ «حفِظَهُ الله»🎙በወንድም አቡ ዘከሪያ ሙሐመድ አል-ወልቂጢይ አላህ ይጠብቀው
📱*👇👇👇👇👇
t.me/gubreahlelsunajemeat.me/gubreahlelsunajemea

1 week, 5 days ago

📓አዲስና ወሳኝ ተከታታይ ደርስ
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
↩️ عنوان፡- ➘➷➴
📒 هداية المستفيد في أحكام التجويد

↪️ ርዕስ፦➷➴➘
📒 ሒዳየቱል ሙስተፊደድ

╭─••°─═•°•═─•••─╮
📖  ደርስ ክፍል  05 📖
╰─••°─═•°•═─•••─

📄ኪታቧን በ𝕡𝕕𝕗 ለማግኘት
 ➘➷➴➘➷
https://t.me/abuzekeryamuhamed/6594

📝 المؤلف الشيخ محمد المحمود المشهور بأبي ريمة «رحمه الله»
📝 አሸይኽ ሙሀመድ አል’መህሙድ አላህ ይዘንላቸው

*🎙بِالْأَخِ أَبِـي زَكَـرِيَّا مُحَمَّدُ بِـنْ عَبْدِ اللهِ بِـنْ عَـلِيِّ الْـوَلْقِـطِيُّ «حفِظَهُ الله»🎙በወንድም አቡ ዘከሪያ ሙሐመድ አል-ወልቂጢይ አላህ ይጠብቀው
📱*👇👇👇👇👇
t.me/gubreahlelsunajemeat.me/gubreahlelsunajemea

2 weeks, 2 days ago

‏حال أهل العلم الراسخين الناصحين المتبعين للسلف الصالح
الذين لا يحرصون على تجميع الناس حولهم
ولا ينظرون إلى أن الناس يمدحونهم ولا يرفعونهم
وإنما ينظرون إلى ما بينهم وبين الله

وحال من يخالفهم

فلا طريق إلا ما سلكه أئمة السلف الصالح وأتباعهم
وإن كانوا قد أُهينوا من قبل هؤلاء فإن الله أكرمهم

⭕️ كلام قيم ونفيس

🎙للشيخ العلامة / د. ‎#صالح_الفوزان حفظه الله

🕓 [ ١٦ : ٣ ] 🕓

2 weeks, 3 days ago

ግጥም ስለ ሞት
በአቡ ያሲር
t.me/abdul_fettah
t.me/abdul_fettah

2 weeks, 4 days ago

ጋሼ ደፋሩ ጃሂል በደንብ ይዘባርቃሉሳ። ጨምረው ይዘባርቁ ሰዎች የበለጥ ተንኮላቸውን/ሴራቸውን እንዲያውቋቸው ያደርጋል።አልሃምዱሊላህ።

የስልጣን/የወንበር ስካር ከኸምር ስካር ይበልጣል አሉ ዑለሞች።ትክክል ብለዋል ወሏሂ ።

ጉድን ጉድ ይበልጠዋል አሉ።
ይህንን ዲን/ሃይማኖት አሏህ ያልናፈቃቸው ከፊሮችም ይታዘባሉ፣

ወንድማችሁ:- አቡ ፈውዛን አብዱሰላም።
https://t.me/abufewuzanabduselam

8 months ago

መውሊድ
➧➧➧➧➧➧➧

እራሱንም  ቢስት  ቢያጉረመርም
ወደድኩኝ እያለ-አዳሩን ቢጮህም

ጎሮሮውን አልፎ ልቡ ጋ አይደርስም
የረሱል መሀባ    በውስጡ የለም

ነቢዩን በመውደድ የሚበልጡት ከእኛ
አቡ በክር ዑመር  ....ታማኝ እውነተኛ
ኡስማን እና አልይ  ...   የረሱል ጓደኛ
መች ሰርተው አሳዩን እንድንሰራው እኛ

አባቷን ወዳጇ ከሁሉ አስቀድማ
መች አከበረችው ልጃቸው ፋጢማ
ከአባቱ በላይ አውቃለው ማለቱ
ቡዳነት ነው አሉ ሰዎች ሲተርቱ

መሀመድስﷺጭራሽ መች አከበሩት
የተወለዱበትን ቀን ፁሙት ነው ያሉት

እሱ አሁን መጥቶ  ከሺ አመት በኋላ
መውሊዱን ሊያከብር ጫቱን እየበላ

ሽርክን ሲያጨማልቅ   በመሀባ ጥላ
ውዴታው በልጦ ነው ከሰሃቦች ሁላ?

ያ  ሁሉ  ሰሃባ   __  ያ ሁሉ   ታቢዕይ
አትባዑ   ታእቢዮች   ኢማሙ ሻፊዒይ
አቡ  ዳውድ መስሊም  ቡኻሪ  ነሳኢይ
ኢብኑ ማጀህ አህመድ ታላቁ ቱርሚዝይ
አከበሩት የሚል  ማስረጃ  አለወይ?
ማስረጃው የት አለ -  አዩሀል አህባሺይ
ማስረጃው የት አለ  --ያ መዕሸረ ሱፊይ
በኖርማል አዕምሮ  አምጡት እንዲታይ

ሰላትን ሳይሰግዱ በጥዋትም በማታ
አበድን ይላሉ ...በረሱል ውዴታ

ትዕዛዝ ሳያከብሩ ክልከላ ሳይርቁ
ሽርክና ቢድዓን ለይተው ሳያውቁ
የነቢን ውዴታ -  ወላሂ አይጠብቁ

የውዴታው ትርጉም አረ መች ገባቸው
በፎርጂት አረዳድ  ተሞልቷል ልባቸው
በቢድዓው መአት  ታውሯል አይናቸው
የምለው የለኝም ጌታዬ  ይምራቸው

📱👇👇👇👇👇
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

We recommend to visit

- بعدها عيونك احلى عيون بعيوني .
- انستا https://instagram.com/Z22X
- بوت حجز تمويلات @fpbot .
- قناة التمويلات | @ossss .
- لطلب التمويل | @sssso .
-

Last updated 1 month, 3 weeks ago

• قناة البصمات الخاصة ببوت فسنجون 💖

- قناة المطور : @KekoDev

- معرف البوت : @iizBot

- للتمويل : @kekoibot

حساب المطور : @HHHHD

Last updated 2 weeks ago

نحنُ الاول في كل شيء اما غيرنا فلهم التالي •●

المالك ستيفن ~~> @AliAbbas95

Last updated 11 months, 3 weeks ago