- بعدها عيونك احلى عيون بعيوني .
- بوت حجز تمويلات @fpbot .
- قناة التمويلات | @ossss .
- لطلب التمويل | @sssso .
Last updated 2 days, 14 hours ago
• قناة البصمات الخاصة ببوت فسنجون 💖
- قناة المطور : @KekoDev
- معرف البوت : @iizBot
- للتمويل : @kekoibot
حساب المطور : @HHHHD
Last updated 1 month ago
نحنُ الاول في كل شيء اما غيرنا فلهم التالي •●
المالك ستيفن ~~> @AliAbbas95
Last updated 1 year, 6 months ago
? የቻት ሱስ ❴የጫት አይደለም የቻት❵
▱▰▱▰▱▰?
➧ ቻት (በሁለት ሰዎች መካከል ኦን ላይን ላይ የሚደረግ የፁሁፍ ንግግር) ነው። ይህ ንግግር ቴክኖሎጂ ካመጣቸው ጠቃሚና ጎጂ ጎን ካላቸው ነገሮች አንዱ ነው። የዚህ የቻት ሱስ በአብዛኛው በሁለት ተቃራኒ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚከሰት ሲሆን በተለይ በሱና ላይ በሚፍጨረጨሩ ሙስሊሞች ላይ የሸይጣን መረብነቱ ይበረታል።
➜ ኢስላም ለተቃራኒ ፆታ ያስቀመጠው ገደብ የስጋ ዝምድና ያላቸው ወይም በጋብቻ የተገናኙ ሰዎች እንዲሁም በጥቢም የተገናኙ ሰዎች የሚገና ኙባቸው ገደቦችና ከዚህ ውጪ የሆኑ ባዳ ሰዎች የሚገናኙባቸውን መስመር አበጅቶ ድንበር ከልሎ ያስቀመጠ ሲሆን ይህን ወሰን ሙእሚኖች እንዲተላለፉ ለማድረግ ቻት ትልቁን ሚና ይጫወታል አሰልጣኙም ብቃት ያለው ሸይጣን ነው።
➻ ታዲያ የዚህ የሸይጣን መረብ ዋነኛ ታርጌት የሆኑት ደግሞ በሱና ላይ የሚፍጨረጨሩት ናቸው። አይጥን መያዝ የፈለገ ሰው
ወጥመዱ``ን ስውር ቦታ አስቀምጦ አይጧ የምትፈልገውን ነገር ወደ ወጥመዱ በሚወስደው መንገድ ላይ እንደሚያደርገው ሁሉ ሸይጣንም እነዚህን የሱና እህትና ወንድሞችን
አንድ የዲን ጉዳይ በሚወራበት ግሩፕ ላይ በሚሰበሰቡበት ጊዜ ከዛ ውስጥ አንዱን ነጥሎ እገሊትን አየሃት ምን አይነት ኢማን እንዳላት እስኪ ንግግሯን ተመልከት አቂዳዋ ሚንሃጅዋ ቂራአትዋ ግንዛቤዋ ብሎ ምን አለበት በውስጥ መስመር እንድትበረታ ብታደርጋት በተቃራኒው ሴትዋንም እንደዚሁ አድርጎ ወደ መረቡ ካስገባቸው በኀላ በማያውቁት ሁኔታ በሁለቱም ልብ ውስጥ የተለየ ስሜት በመፍጠር ሱስ እንዲዛቸው በማድረግ እሷ ኦን ላይን ላይ ካልሆነች ወይም ካልሆ ምን ሆነህ/ሽ ነው በማለት በውስጣቸው የተፈጠረው ስሜት እንዲያውቁ በማድረግ ወደ ሌላ ምእራፍ እንዲሸጋገሩ በማድረግ የአላህን ድንበር እንዲጥሱ ወሰን እንዲያልፉ ካደረገ በኀሏ ይሳለቅባቸዋል
አንዳንድ ወሮበላ ደግሞ በዚሁ መረብ አማካይነት በኢማንና አላህን በመፍራት ህይወቱ የተሞላ በማሰመል ከባህር ማዶ ያለችውን ምስኪን ለትዳር የሚፈልጋት በመምሰል እስክትመጪ ሁኔታዎችን ላመቻች በማለት ያላትን ለማራቆት የተዋጣለት ድራማ ሲሰራ ቆይቶ ቆጣሪው የተመለሰ መብራት ይመስል በዛው ይጠፋል።
✅ ይህ የሸይጣን መረብ አማኞችን እንዴት አድርጎ ወደ ወጥመዱ እንደሚያስገባ ከዚህ መረዳት ይቻላል። በመሆኑም እባክሽ እህቴ ወደ ሸሪዓዊ የትዳር ህይወት ሸሪዓዊ በሆነ መንገድ ሄደሽ ግቢ አንተም ወንድሜ እንደዛው ከሸይጣን መረብ እራስህንና እህትህን አውጣ ስለሷ ኢማንና አላህን መፍራት በቻት መረጃነት እየቆጠርክ እንቅልፍ አትጣ በቻት መስካሪነት የተደነቀ አብዛኛው ኢማን የመወገዣው ጊዜ አይርቅም ፀፀቱም አይለቅም የሚበጀው የትም ሆኖ አላህን መፍራት ነው
=> በመጨረሻም «ሱና የሚጠፋው በጃሂል ድፍረትና በዓሊም ዝምታ ነው» እላችኀለሁ
አላህ ይጠብቀን
▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴
⚙ ? أَبُـــو عِـمْــرَان ❨??? ?????❩
? ••⇣⇣. ? ••⇣⇣
╰?????. ╰?????
?️ በ ????????~???????
? ⇣⇣⇣?⇣⇣⇣? ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
ሀሳብ ካለዎ
⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/AbuImranAselefybot
Telegram
Abu Imran Muhammed Mekonn
ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ ***💡*** ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ***⤵*** ***↪*** እቀበላለሁ ***↩*** ***⤴*** ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ
የደላው መች ቀረ......?!
*ሁሉም ይሞታታል አስጠላም አማረ
ሁሉም ይጓዛታል ያቺን የሩቅ ጉዞ
የሌለው ባዶውን ያለው ስንቁን ይዞ
ዛሬማ ምን አለ ባይሰግዱ ባይፆሙ
ይቸግራል እንጂ አላህ ፊት ሲቆሙ
ዛሬማ ምን አለ ቢጠጡ ቢሰክሩ
ይቸግራል እንጂ ሙተው ሲቀበሩ
ዛሬማ ማን አለ የሚያጋልጥሽ
ከቀብር ስትገቢ ይታያል ጉድሽ*
◈ ሸይኽ ሙሀመድ ወሌ (ረሂመሁላህ)
ዓጀብ ነው!! አላህ ኻቲማችን ያሳምረው!!
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
? ዐረብ አገር የምትኖሩ እህቶች ተጠንቀቁ
የኢስላም ሸሪዓ ለሴት ልጅ ትልቅ ክብርና እውቅናን የሰጠ በምድር ላይ በሴት ልጅ መብት ወደር የማይገኝለት መለኮታዊ ሸሪዓ ነው ። በተደጋጋሚ ለመግለፅ እንደሞከርኩት የምእራቡ አለም ሴት ልጅ ከሰው ትመደባለች ወይስ አትመደብም እያለ ጉባኤ ይጠራ በነበረበትና የዐረቡ አለም ሴት ልጅ ዘር የምታዋርድ አድርጎ በሚያይበት የአእምሮ ዝቅጠት ላይ በነበረበት ጊዜ ነው ኢስላም የሴትን ልጅ መብት ያወጀው ።
ሴት ልጅ በተለያዩ መለኮታዊ መመሪያዎች ከወንድ እኩል ቦታ ሰጥቶ ለዓለም ክብሯን ያሳየው ። በእናትነት ፣ በሚስትነት ፣ በእህትነትና በልጅነት ማእረግ ላይ አስቀምጦ አንገቷን ቀና እንድታደርግ ፈር ቀዷል ። ከዚህ ጎን ለጎን በስሜት ፈረስ ለሚጋልቡ ዐቅለ ደካሞች ክብራን እንዳታስደፍር ገደብ በማስቀመጥ የህይወት መስመር ዘርግቶላታል ። በየአንዳንዱ ህግጋቱ ሴትን አስመልክቶ እንከን የለሽና ምክንያታዊ የሆኑ ብይኖችን አስፍሯል ።
ምእራባዊያኖች ሴትን ልጅ ሸቀጥ ለማድረግና በቀን የፈለጓትን እንደ ሸንኮራ አኝከው ስሜታቸውን አርክተው ለመጣል እንዲመቻቸው ለማድረግ እንዳይችሉ የኢስላሙ ሸሪዓ ስለከለከላቸው ሴትን ጨቁኗል እያሉ ያላዝናሉ ። ለሴት ልጅ ከወርቅ በላይ ቦታ የሰጠው የኢምን ሸሪዓ ይተቻሉ ። ምክንያቱም አንድ ሰው ወርቅን ሸፍኖ ከሚያስቀምጠው በላይ ኢስላም ሴትን ልጅ ራስዋን ሸፍና ገላዋንና ክብራን እንድትጠብቅ ስላደረገ ለደመነፍሳዊ ፍላጎታቸው አልመች ስላለ ነው ። በዚህም ራቁቷን ሆና እንድትወጣና ዝንብ እንደሚወረው ቆሻሻ ልትሆን ይፈልጋሉ ።
በመሆኑም ሴቶች የጌታቸውን መመሪያ ባለመጠበቅ እንሰሳዊ ስሜታቸውንና የነዋይ አፍቃሪነት ጥማቸውን ለማርካት በሚሯሯጡ ወንዶች ለሚደርስባቸው በደል በምንም መልኩ ኢስላምን ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም ።
ለመግቢያ ያክል ይህን ካልኩኝ ወደ ርእሴ ልመለስ ።
ዐረብ አገር የሚኖሩ እህቶች ችግር ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ቢሆንም ለዛሬ ከትዳር ጋር የሚገናኘውን ጎን ለማይት እሞክራለሁ ። እንከን የለሹ የኢስላም ሸሪዓ ሴት ልጅ የትዳር አጓር ስታስብ ምንን መስፈርት ማድረግ እንዳለባት አስቀምጧል ።
በዚህም ሴት ልጅ ማየት ያለባት ሁለት ነገር ነው ። እሱም : –
አንደኛ – ዲን
ዲን ሲባል መስገድ ማለት ብቻ አይደለም ። አላህን የሚፈራ ፣ በተውሒድና ሱና ላይ ቀጥ ያለ ፣ ሶላቱን በጀማዓ የሚሰግድ ፣ አማናውን የሚጠብቅ ፣ የማይዋሽ ፣ የማይከዳ ፣ የማያታልል ፣ ከሰዎች ጋር ያለው ግብረገብነት የተስተካከለና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል ። ታዲያ አንድ ሰው በእነዚህ ባህሪያት ላይ ያለውን ቦታ ማወቅ የሚቻለው በቅርበት ከሚያውቁት ከሚኖርበት አካባቢ ጀማዓ ባለትዳር ከሆነና ለሁለተኛ ከሆነ በማይታወቅ መልኩ ከመጀመሪያዋ ሚስቱ ቤተሰቦች በኩል የራስ ሰው ልኮ በጥንቃቄ እንዲያጣራ በማድረግ እንጂ ሚዲያ ላይ በሚፅፈውና በሚያገረው ወይም በውስጥ መስመር በሚፃፃፉትና በሚያወሩት ወይም በኔት ወርክ ትስስር ባላቸው ጓደኞቹ በኩል አይደለም ።
ሁለተኛ – ስነምግባር
ስነምግባር ሲባል በጣም ትልቁን የዲን ክፍል ይይዛል ። ስበምግባ ( መልካም ፀባይ ) አስመልክቶ የመጡ መረጃዎች በጣም በረካታ ናቸው ። ነገር ግን አብዛው ሰው ቤት ውስጥ መጥፎ ይሆንና ውጪ ማር ነው ። ጥቂቱ በተቃራኒው ሊሆን ይችላል ። በመሆኑ ከላይኛው መስፈርት ባልተናነሰ መልክ ቱክረት ተሰጥቶት ሊጠና ይገባል ።
ዐረብ አገር የሚኖሩ እህቶች እነዚህን መስፈርቶች በተባለው መልኩ ከማጣራት አንፃር ዜሮ ናቸው ለማለት ይቻላል ። በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ በአጭር ጊዜ በሚዲያ ተዋውቀው ወንዱ መላኢካ መስሎ ቀርቦ ልቧን ካገኘ በኋላ እዛው እያለች ወደ ኒካሕ ይገባል ። መጀመሪያ አካባቢ እጇ ላይ ያለውን እስኪረከቡ ድረስ በጣም አሳቢ ለሷ ህይወት የሚጨነቁ በመምሰል ያለሙት ሲሳካ ሁኔታዎች መቀየር ይጀምራሉ ። ይህ በርግጥ የሁሉም ነው ባይባልም ጥቂት አላህን የሚፈሩ ሊኖሩ ይችላሉ ። የአብዛኛዎች ታሪክ ግን ከላይ የተገለፀው ነው ።
ሴቶቹ ከኒካሑ በኋላና ዐረብ ሀገር የተቃጠሉበትን ሳንቲም ከእጃቸው ወጥቶ ሁኔታዎች ሲቀያየሩ ስለሱ ማስጠናት ይጀምራሉ ‼። የዚህን ጊዜ ጫት ቃሚ ፣ ሶላት የማይሰግድ ፣ ሺሻ ቤት የሚውል ፣ ደርስ የሚባል የማያውቅ ወይም ሱፍይ ሆኖ ይገኛል ።
ምን ያደርጋል አሳዛኝ ህይወት ፍታኝ ሲሉት ይህን ያክል ካልከፈልሽ ማለት ይጀምራሉ ። በጣም የሚያሳዝነው በአብዛኛ አካባቢ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኛ የሚባሉት ጫት ቃሚና ሱሰኞች ይሆናሉ ። ሴቶቹ ፍቺ ሲጠይቁ ምንድነው ችግሩ ብለው ይጠይቁና ሱሰኛ ነው ዐቂዳው የተበላሸ ነው ሲባል ዐቂዳው ……… ውውው እያሉ ያላግጣሉ ። ሴቶቹ ቅስማቸው ተሰብሮ ሞራላቸው ወድቆ ለታክሲና ለካርድ እንኳን የሚሆን ሳንቲም አጥተው ለሁለተኛ ጊዜ ለግርድና ወደ ዐረብ ሀገር ይሄዳሉ ። ይህ የብዙ ዐረብ ሀገር የሚኖሩ እህቶች ታሪክ ነው ።
የሚገርመው እባካችሁን ኡስታዝም ይሁን የቻናል ባለቤት ወይም ግሩፕ ላይ የሚሳተፍ በውስጥ መስመር አተገናኙ ሲባሉ ትልቅ ስኬት የተከለከሉ የሚመስላቸው ቀላል አይደሉም ። የህይወታቸው መበላሸት የሚጀምረው በውስጥ መስመር መገናኘት የጀመሩለት ነው ።
ለማንኛውም ኒካሕ አሰራችሁ ሳይሆን ቀርቶ ኒካሕ አናወርድም ተብላችሁ የምትሰቃዩ እህቶች ነገሩ የተበላሸው መጀመሪያ ነውና ሶብር አድርጋችሁ በሽማግሌ በማስጠየቅ ነገሩን አስተካክላችሁ ኒካሓችሁ እንዲወርድላችሁ አድርጉ በምንም መልኩ የመጀመሪያው ኒካሕ ሳይወርድ ሌላ ኒካሕ እንዳታስሩ ተጠንቀቁ ።
አላህ ይርዳችሁ ።
Telegram
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka
↪️ የጁመዓ ኹጥባ (ምክር)
↩️ خطبة الجمعة؛
✅ ርዕስ፦ ➴➷➘
"«ከአርካኑል ኢስላም መሰረቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን ሐጅን በተመለከተ የተመጠነ ማብራሪያ»" በሚል አንገብጋቢ እና ወቅታዊ ርዕስ
عنوان:- ''شرح مفصل للحج الذي هو أحد أركان الإسلام.''
➴➴➴➴➴
====================
? በሸይኽ ሐሰን ገላው ሐሰን ሀፊዘሁሏህ
? لفضيلة الشيخ حسن بن غلاو حسن -حفظه الله-
? ግንቦት ‐ 30‐ 09 - 2016 E.C
? ባህር ዳር ከተማ መስጅደል ቡኻሪ
? بمدينة بحردار [إثيوبيا]؛ في مسجد البخاري
➴➴➴➴➴
====================
#size መጠን 5.42MB
#length 22:34 min
?መስጅድ:-አል-ቡኻሪ
?ባህር ዳር፣ ኢትዮጲያ
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
كن على بصيرة
? የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ
ክፍል ሶስት
ነብዩላሂ ኢብራሂም ዳዕዋቸውን ከንግግር ወደ ተግባር ለመቀየር ወሰኑ ። ለጣኦት አምላኪያን የሚያመልኩዋቸው ጣኦታት ያልተገዛቸውን መጎዳትም ሆነ የተገዛቸውን መጥቀም እንደማይችሉ ከዚህም በላይ ራሳቸውንም ከጥቃት የማይከላከሉ መሆናቸውን ማሳየት እንዳለባቸው አመኑ ።
የባአላቸው ቀን ጠብቀው ሁሉም ተሰባስበው ወደ በአሉ ሲሄዱ ነብዩላሂ ኢብራሂም መጥረጢያቸውን ተሸክመው ወደ ጣኦቶቻቸው አመሩ ። የተለያየ ስለት እንዲሁም ምግብም አጠገባቸው ተቀምጦ አዩ ‼ አትበሉም እንዴ እያሉ ያናግሯቸው ጀመር መልስ የለም ። ትልቁን ብቻ አስቀርተው ጣኦታቱን ፈላልጠው ጨረሱ ። ከዛም መጠረቢያውን በትልቁ ጣኦት ላይ አስቀምጠው ጥለው ሄዱ ። ጣኦትአምላኪያኖቹ ከባአል ማክበሪያ ሲመለሱ በጣኦቶቻቸው ላይ የተሰራውን ጉድ አዩ ። ስለጣኦቶቻቸው ደካማነትና ስለራሳቸው ዐቅለቢስነት ከማሰብ ይልቅ በአማልክቶቻችን ላይ ማነው ይህን የሰራው እያሉ መጠያየቅ ጀመሩ ። ኢብራሂም የሚባል ነው ተባለ ፈልገው ጠየቋቸው ። እሷቸውም ትልቁን ጠይቁት የሚናገር ከሆነ ብለው መለሱ ።
ይህን ክስተት ቁርኣን በሚቀጥለው የአል ንቢያ ምእራፍ ከ59 – 67 በዝርዝር ያስቀምጥልናል : –
قَالُوا مَن فَعَلَ هَٰذَا بِآلِهَتِنَا إِنَّهُ لَمِنَ الظَّالِمِينَ
«በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራ ማነው እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው» አሉ፡፡
قَالُوا سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُ إِبْرَاهِيمُ
«ኢብራሂም የሚባል ጎበዝ (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል» ተባባሉ፡፡
قَالُوا فَأْتُوا بِهِ عَلَىٰ أَعْيُنِ النَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَشْهَدُونَ
«ይመሰክሩበት ዘንድ በሰዎቹ ዓይን (ፊት) ላይ አምጡት» አሉ፡፡
قَالُوا أَأَنتَ فَعَلْتَ هَٰذَا بِآلِهَتِنَا يَا إِبْرَاهِيمُ
«ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራህ አንተ ነህን» አሉት፡፡
قَالَ بَلْ فَعَلَهُ كَبِيرُهُمْ هَٰذَا فَاسْأَلُوهُمْ إِن كَانُوا يَنطِقُونَ
«አይደለም ይህ ታላቃቸው ሠራው፡፡ ይናገሩም እንደ ኾነ ጠይቋቸው» አለ፡፡
فَرَجَعُوا إِلَىٰ أَنفُسِهِمْ فَقَالُوا إِنَّكُمْ أَنتُمُ الظَّالِمُونَ
ወደ ነፍሶቻቸውም ተመለሱ፡፡ «እናንተ (በመጠየቃችሁ) በዳዮቹ እናንተው ናችሁም» ተባባሉ፡፡
ثُمَّ نُكِسُوا عَلَىٰ رُءُوسِهِمْ لَقَدْ عَلِمْتَ مَا هَٰؤُلَاءِ يَنطِقُونَ
ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡ፡፡ «እነዚህ የሚናገሩ አለመኾናቸውን በእርግጥ ዐውቀሃል፤» (አሉ)፡፡
የዚህን ጊዜ ጥሩ መግቢያ አገኙ ። ጠንከር ባለ ሁኔታ ዳዕዋ አደረጉላቸው ። ይህንንም ቁርኣን በዛው ምእራፍ በሚቀጥሉት አንቀፆች ላይ ይነግረናል :–
قَالَ أَفَتَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكُمْ شَيْئًا وَلَا يَضُرُّكُمْ
«ታዲያ ለእናንተ ምንም የማይጠቅማችሁንና የማይጎዳችሁን ነገር ከአላህ ሌላ ትገዛላችሁን» አላቸው፡፡
أُفٍّ لَّكُمْ وَلِمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
«ፎህ! ለእናንተ ከአላህ ሌላ ለምትገዙትም ነገር፤ አታውቁምን» (አለ)፡፡
ጣኦት አምላኪያኑም በመረጃ ሲሸነፉ ሐቅን ከመቀበል ይልቅ ወደ ሀይል ተሸጋገሩ ። ይህ የሁሉም የባጢል ተከታዮች ባህርይ ነው ። መረጃ ሲያጡ ጡንቻን መረጃ ያደርጋሉ ‼ ።
ኢብራሂምንም አቃጥሉ ጣኦቶቻችሁንም እርዱ አሉ ። ይህም እውነታ ቁርኣ በሚቀጥለው አንቀፅ ያስቀምጠዋል : –
قَالُوا حَرِّقُوهُ وَانصُرُوا آلِهَتَكُمْ إِن كُنتُمْ فَاعِلِينَ
«ሠሪዎች እንደ ኾናችሁ አቃጥሉት፡፡ አማልክቶቻችሁንም እርዱ» አሉ፡፡ (በእሳት ላይ ጣሉትም)፡፡
ዐቅለ ቢሶቹም ነብዩላሂ ኢብራሂምን ለማቃጠል ወሰኑ ። ጥፋታቸው ጣኦታትን ራቁ አላህን ብቻ ተገዙ ማለታቸው ነው ። በወቅቱ የነበረው መንግስት ግንብ ገንቡና እሳት አቀጣጥላችሁ እዛ ውስጥ ጣሉት ብሎ አዘዘ ። ይህን ክስተት ቁርኣን እንዲህ ብሎ ይነግረናል : –
قَالُوا ابْنُوا لَهُ بُنْيَانًا فَأَلْقُوهُ فِي الْجَحِيمِ
«ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ ፡፡
በመንግስት ትእዛዝ ከፍታው 30 ሜትር ጎኑ የተራራ ጫፍ የሚሆን ምሽግ ተገነባ ።
ማንኛውም ህዝብ እንጨት እንዲሰበስብ ታዘዘ ። ሴት ወንድ ፣ አዋቂ ልጅ ሁሉም ወደ 40 ቀን አካባቢ ስራውን ትቶ መሰብሰብ ጀመረ ። በዚህ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ክምር እሳት ተለኮሰበት ። ነበልባሉ ከሰማይ አሞራ ይጠልፍ ነበር ይባላል ።
ጣኦት አምላኪያን ጉድ ተሰሩ ‼ ። ኢብራሂምን እንዴት በዚህ እሳት ይወርውሩ ? የሰው ሸይጣን መጥቶ ወስፈንጥር ( ምንጀኒቅ ) ዛሬ በዘመናዊ መልኩ መድፍ የሚባለው አይነት ማለት ነው እንዲሰሩና እዛ ላይ አድርገው እንዲወረውሩዋቸው ሐሳብ አቀረበ ። እንደተባሉት አደረጉ ። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ጅብሪል መጣ ምን ትፈልጋለህ አላቸው ? ነብዩላሂ ኢብራሂምም ካንተ ምንም አልፈልግም ። አላህ በቂዬ ነው ምን ያማረ መጠጊያ ነው አሉ ። ወዲያውም የአላህ እርዳታ መጣ ። አላህ እሳትን አናገረ ። ይንንም ቁርኣን እንዲህ ብሎ አረጋገጠው : –
قُلْنَا يَا نَارُ كُونِي بَرْدًا وَسَلَامًا عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ
الأنبياء ( 69 )
«እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አልን፡፡
فَأَرَادُوا بِهِ كَيْدًا فَجَعَلْنَاهُمُ الْأَسْفَلِينَ
الصافات ( 98 )
በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው ፡፡
አላህ ካለ ይቀጥላል ።
Telegram
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka
?አዲስ የአቂዳ ኪታብ ቂርአት
? اسـم الكتـاب፡- ➘➷➴
⬅️ مـن أصـول عقيـدة أهـل السنـة والجمـاعة
➡️ ሚንኡሱሊ አቂደቲ አህሊሱነቲ ወልጀማአህ!
?تأليف፡- الشيـخ صالـح بـن فـوزان بـن عبـد اللَّـه الفـوزان
▶"ደርስ ቁጥር 5⃣
?أبو عبد الرحمن المرسي(حفظه الله)
?የኪታብ ??? ለማግኘት⇩⇩
https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi/2834
⤵ክፍል አራትን ለማግኘት↘↘
https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi/2959
ሌሎች ትምህርቶችን ለማግኘት ⤵
?⇘»https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi
?⇘»https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi
? محاضرة مهمة بعنوان:
? الحج لحظة بلحظة ?
?️لفضيلة الشيخ العلامة:
محمد بن صالح العثيمين
- رحمه الله تعالى -
⏳ المدة | 01:10:47
??
ትውስታ
እነ ኢብኑ ሙነወር ከ3 አመት በፊት መሪ የጠመዘዙ ግዜ የተገጠመች ግጥም ብጤ
የሴት ፈተና ታሪክ
https://t.me/abuabdurahmen
- بعدها عيونك احلى عيون بعيوني .
- بوت حجز تمويلات @fpbot .
- قناة التمويلات | @ossss .
- لطلب التمويل | @sssso .
Last updated 2 days, 14 hours ago
• قناة البصمات الخاصة ببوت فسنجون 💖
- قناة المطور : @KekoDev
- معرف البوت : @iizBot
- للتمويل : @kekoibot
حساب المطور : @HHHHD
Last updated 1 month ago
نحنُ الاول في كل شيء اما غيرنا فلهم التالي •●
المالك ستيفن ~~> @AliAbbas95
Last updated 1 year, 6 months ago