Addis Standard Amharic

Description
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago

1 Monat, 1 Woche her
**ዜና፡ በ** [**#አምባሰል**](?q=%23%E1%8A%A0%E1%88%9D%E1%89%A3%E1%88%B0%E1%88%8D) **ወረዳ ባሳለፍነው ቅዳሜ …

ዜና፡ በ #አምባሰል ወረዳ ባሳለፍነው ቅዳሜ በተካሄደ ውጊያ ንጹሃን ሰዎች መቁሰላቸውና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ተናገሩ

#አማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን አምባሳል ወረዳ ሮቢት በተሰኘች ስፍራ እና አከባቢዋ ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደ ውጊያ ንጹሃን ሰዎች መቁሰላቸውንና በመኖሪያ ቤቶችና ከፍተኛ ውድመት መድረሱን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳንጠቅስ የጠየቁ የአከባቢው ነዋሪ፤ ከሮቢት ከፍ ብሎ ወደ ቋዲት በሚወስደው መንገድ መካከል በምትገኘው ፍልፈል በተሰኘች ስፍራም በተደረገ ውጊያም “አከባቢው በከባድ መሣሪያ መደብደቡን” ገልጸዋል።

"ፍልፈል ላይ የከባድ መሣሪያ ድብደባ ነበረ። ህዝቡም በዕለቱ ገበያ ነበር። ከገበያ መልስ ብዙ ሰው ቤቱ ሲደርስ በከባድ መሣርያ ጋይቶ ጠበቀው።" ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ያስረዱት ነዋሪው ሁለት ሰዎች እጅ እና እግራቸው ላይ ተመተው መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።

ተጨማሪ ይመልከቱ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=5952

1 Monat, 1 Woche her
ዜና: ባሳለፍነው የጥቅምት ወር ከፍተኛ የሳይበር …

ዜና: ባሳለፍነው የጥቅምት ወር ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ከተፈጽመባቸው ሀገራት #ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ናት ተባለ

በርካታ #የአፍሪካ ሀገራት ባሳለፍነው የጥቅምት ወር ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት የተፈጸመባቸው ቢሆን የኢትዮጵያን ያክል ግን አይደለም ተብሏል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የተፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን በመተንተን ደረጃ የሚያወጣው ቼክ ፖይንት ሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎች ይፋ ባደረገው የ2024 እ.አ.አ የጥቅምት ወር ሪፖርት መሰረት ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ከተፈጽመባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ሆናለች።

በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት በጨመረበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የስጋት መጠን 96 ነጥብ 8 በማስመዝገብ ኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ እንድትይዝ አድርጓታል፤ በአፍሪካ ደረጃ ከኢትዮጵያ በመቀጠል ተጋላጭ የሆነችው አንጎላ ስትሆን ያስመዘገበችውም 74 መሆኑን ሪፖርቱ አመላክቷል። ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ https://addisstandard.com/Amharic/?p=5946

1 Monat, 1 Woche her

ዜና: #በሀዋሳ ከተማ በቤንዚን እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሷል፣ በጥቁር ገበያ የቤንዚል ሽያጭ ተስፋፍቷል ሲሉ አስሸርካሪዎች አማረሩ

በሲዳማ ክልል ርዕሰ ከተማ በሆነችው ሀዋሳ የቤንዚን እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እየተባባሰ እንደሚገኝ እና ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆናቸውን አሽከርካሪዎች አስታወቁ፣ ዋነኛ መንስኤው በከተማዋ ተስፋፍቶ የሚገኘው የነዳጅ ጥቁር ገበያ ሽያጭ መሆኑንም አሽከርካሪዎቹ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

ለደህንነታቸው ሲሉ ሥማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በሀዋሳ ከተማ የታክሲ ሹፌር “አሁን ላይ በከተማዋ ነዳጅ በጥቁር ገበያ በሊትር እስከ 160 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ” ገልጸው: "ነዳጅ የሱቅ ሸቀጥ ሆኗል" ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

"ነዳጅ ከማደያዎች ይልቅ በየፌርማታው ነው እየተቸበቸበ የሚገኘው፤ ይሄን ደግሞ የጸጥታ አካላት ይቅርና ማንኛውም ነዋሪ የሚያውቀው ነገር ነው" ብለዋል።

ህገ-ወጥነትን በተመለከተም የክልሉ ንግድ ቢሮ ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር እና ከሚመለከታቸው የፖሊስ ኮሚሽን አካላት ጋር በመቀናጀት ግብረ-ሃይል ተቋቁሞ ቤንዚን በማታ እንዳይሸጥ መከልከሉ ተገልጿል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=5940

1 Monat, 2 Wochen her
**ትንታኔ፡ “በቀን አንዴ የምመገብበት ቀናቶች ብዙ …

ትንታኔ፡ “በቀን አንዴ የምመገብበት ቀናቶች ብዙ ናቸው፤ በትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ ኑሮዬ ተመሰቋቅሏል”_ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ

መንግሥት ከጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪን ተከትሎ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ወደ ከተማዋ በመመላለስ የሚሰሩ ሠራተኞች ለከፍተኛ የኑሮ ቀውስ መዳረጋቸውን ይገልጻሉ።

በርካታ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከተጨመረው ታሪፍ በላይ ተጨማሪ ክፍያ እያስከፈሉ እንደሚገኙም የመዲናዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ይህም በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደሩን እና “ቀድሞውኑ ትግል ከገጠሙት ኑሮ ውድነት ላይ ተጨማሪ ቀውስ እንዳስከተለባቸው” አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አስረድተዋል።

“ኑሮዬ ተዘበራርቋል፤ የመንግሥት ሠራተኛ ነኝ 4000 ብር በወር ይከፈለኛል። ከዚህ ቀደም ለትራንስፖርት በወር እስከ 2500 ብር አወጣ ነበር። በቅርቡ የታሪፍ ጭማሪ ከተደረገ በኋላ ደግሞ እስከ 3500 ከዛም በላይ አወጣለሁ። ይህ ማለት ሠርቼ ለትራንስፖርት ነው ደመወዜ የሚውለው ማለት ነው” ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የመዲናዋ ነዋሪ አማረዋል።

“በቀን አንዴ ብቻ የምበላባቸው ቀናቶች ብዙ ናቸው” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ የተናገሩት ሌላኛው የመነን አከባቢ ነዋሪ፤ “ ምግብ ሳልበላ ስለምውል ከድካሙም ጋር ተጨምሮ ያዞረኛል። እንደመውደቅ ያደርገኛል። ከዚህ ሁሉ በኋላ ቤቴ ስገባ እኔና ባለቤቴ ያለችውን ቤት ያፈራውን ከልጆቻችን ጋር ተቃምሰን እንተኛለን። ደግሞ ይነጋል። ይመሻል። ይሄው ነው በቃ ኑሯችን።” ብለዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=5869

1 Monat, 2 Wochen her
**ዜና፡ በ** [**#አማራ**](?q=%23%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB) **ክልል** [**#ምዕራብ\_ጎጃም**](?q=%23%E1%88%9D%E1%8B%95%E1%88%AB%E1%89%A5_%E1%8C%8E%E1%8C%83%E1%88%9D) **ዞን …

ዜና፡ በ #አማራ ክልል #ምዕራብ_ጎጃም ዞን በተፈጸመ የድሮን ጥቃቶች ታጣቂዎችን ጨምሮ ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸን ነዋሪዎች ገለጹ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም አቸፈር ወረዳ ዱርቤቴ ከተማ በተፈጸሙ ትናንት ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም የድሮን ጥቃቶች ጥቃቶች ታጣቂዎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ትናንት በከተማዋ ከባድ ውጊያ ሲካሄድ መዋሉን እና የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ለአዲስ ስታንዳርድ የገለጹ ነዋሪ “ቁጥራቸው 16 የሚደርሱ የፋኖ ታጣቂዎች በሥልጠና ላይ እያሉ ተገድለዋል” ብለዋል። ምንጩ “ከ3 በላይ ንጹሃን ሰዎች በቤታቸው ላይ ከአየር ላይ በተጣለ ቦንብ” ባሉት ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል።

ሌላኛው ስማቸውን ለደህንነታቸው በመስጋት እንዳይጠቀስ የፈለጉ ነዋሪ በትናንትናው ዕለት የድሮን ጥቃት መፈጸሙን አረጋጋግጠው እስከአሁን ” በጥቃቱ ከ30 በላይ ሰዎች ተገድለዋል” ብለዋል።

በተመሳሳይ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ስር በሚገኙ ከተሞች ጥቅምት 17 የተካሄዱትን ውጊያዎች ተከትሎ ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ለማንበብ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=5894

1 Monat, 2 Wochen her
[**#ትራምፕ**](?q=%23%E1%89%B5%E1%88%AB%E1%88%9D%E1%8D%95) **ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን አሸነፉ**

#ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን አሸነፉ

የሪፕብሊካኑ ተወካይ ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን በማሸነፋቸው 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን ወደ ዋይት ሃውስ የሚመለሱ ይሆናል።

በፍሎሪዳ የሪፐብሊካን ደጋፊዎች በተሰበሰቡበት ትራምፕ “አስደናቂ ድል ነው” ነው ሲሉ ተሰምተዋል።

ትራምፕ ምርጫውን ለማሸነፍ ከሚያስፈለገው 270 ድምጽ ከ279 በላይ ያገኙ ሲሆን ካማላ ሃሪስ በበኩላቸው 223 በላይ ድምጽ ማግኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ካማላ ሃሪስ ከምርጫ ውጤት ይፋ መሆን በኋላ ተዘጋጅቶ የነበረው ድግስም መሰረዙን ዘገባው አመላክቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “በእርስዎ የስልጣን ዘመን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን” ብለዋል።

1 Monat, 3 Wochen her
**ዜና፡ በመዲናዋ በአለባበስ ምክንያት የታገዱ ሙስሊም …

ዜና፡ በመዲናዋ በአለባበስ ምክንያት የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የአዲስ አበባ መጅሊስ ጠየቀ

#አዲስአበባ ከተማ በአለባበስ ምክንያት የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠየቀ።

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሚገኙ አራት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች “በኒቃባቸው ምክንያት” ከትምህርት ገበታ መታገዳቸው በሚዲያዎች ሲሰራጭ ቆይቷል።

ይህን ተከትሎ ምክር ቤቱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ትናንት በጻፈው ደብዳቤ፤ ካለፉት ሁእለት ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ በሚገኙ እንዳንድ ትምህር ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያት “ጫናና እንግልት” እየደረሰ ነው ብሏል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=5837

1 Monat, 3 Wochen her

#ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የቦርድ አባል ሆነው እንዳይሰሩ የሚከለክለው ድንጋጌ መሰረዙ በምክር ቤት አባል ተተቸ።

ትላንት በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የመገናኛ ብዙኃን ረቂቅ የአዋጅ ማሻሻያ ቀርቧል።

ማሻሻያው፤ የቦርድ አባላት እጭዎች የመመልመል እና የማጽደቅ ሂደት ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ የሚያስገድድ ድንጋጌን ያስቀራል በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል።

ረቂቅ የአዋጅ ማሻሻያው አሁን ካለው የሚዲያ ገጽታ ጋር የሚስማማ የማስተማር አቅምን በማሳደግ የህግ እና የስነምግባር ጥሰቶችን ለማስተካከል ያለመ ነው ተብሏል። ማሻሻያው በዋናነት የሚያተኩረው በአዋጅ ቁጥር 1238/2021 ተቋማዊ ድንጋጌዎቹ ላይ ነው።
ማሻሻያው የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት፣ የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመት እና የብሮድካስቲንግ አገልግሎት ፍቃድ ሰጪ ግዴታዎችን ያጠቃልላል ተብሏል።

ይመልከቱ!

1 Monat, 3 Wochen her

ዜና: #ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት በ72 ሰዓታት ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ

#የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር በሀገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በ72 ሰዓታት ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበ፤ ዲፕሎማቱ አሊ መሃመድ አዳን ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ ያዘዝኩት “ከዲፕሎማሲያዊ ሚናቸው ጋር የማይጣጣሙ ተግባራት እየፈጸሙ” በመሆኑ ነው ሲል አስታውቋል።

በሞቃዲሾ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአማካሪነት በመስራት ላይ የነበሩት አሊ ሞሃመድ “በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ የተደረሰውን የቪየና ስምምነትን የሚጥስ” ተግባር ፈጽመዋል ሲል ሚኒስቴሩ ትላንት ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫው አትቷል።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመግለጫው ዲፕሎማቱ ስለፈጸሙት የህግ ጥሰት ምንም ያለው ነገር የለም።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=5818

2 Monate her
በ [#አማራ](?q=%23%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB) ክልል በሶስት ወራት ውስጥ …

#አማራ ክልል በሶስት ወራት ውስጥ 37 ሰዎች በወባ በሽታ ምክንያት መሞታቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ 37 ሰዎች በወባ በሽታ ምክንያት መሞታቸውን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ።

በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር የተነሳ አስፈላጊ የቁጥጥር እና የክትትል ስራዎች ባለመከናወናቸው ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከ600ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ሲጠቁ 37 የሚሆኑት ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸውን በኢንስቲትዩቱ የወባ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑትን አቶ ዳምጤ ላንከርን ጠቅሶ የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል።

“የተከሰተው ወረርሽኝ ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅም” ያሉት አቶ ዳምጤ አክለውም በክልሉ አሁን ላይ በሳምንት ከ64 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን የሚገልጹ ሪፖርቶች እንደሚደርሳቸው ተናግረዋል።

በክልሉ ወረርሽኝ ተስፋፍቶባቸዋል ከተባሉ አከባቢዎች መካከል የ #አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን #ደቡብ_ጎንደር እና #ማዕከላዊ_ጎንደርን ጨምሮ በ40 ወረዳዎች ወረርሽኙ ተስፋፋቶ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago