Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

Ameen Tube አሚን ቲዩብ

Description
"ألا بذكر الله تطمئن القلوب"
"ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ"
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago

1 month, 4 weeks ago
Ameen Tube አሚን ቲዩብ
2 months, 4 weeks ago

አፈር ሳልለብስ ሳልበላ አመዱን
ምራኝ ኢላሂ ስቻለሁና መንገዱን
T.me/elaftube

3 months ago
በነቢያችን ላይ ሶለዋት እናውርድ እስቲ !!!!

በነቢያችን ላይ ሶለዋት እናውርድ እስቲ !!!!

3 months, 1 week ago

ህዝቡ በውሸትና በሃሰተኛ ምስክርነት ታዋቂ የሆነባት አንዲት መንደር ነበረች።

በዚህ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው በድብቅ ሊያገባ ከሸንጎው መሐል ገባ። ሸይኹ ምስክሮች ባሉበት ዘወጅቱከ ሲሉት ቀቢልቱ እያለ ጋብቻውን አፀደቀ።

ከወራት በኋላ ባል ሚስቱን ከቤት አስወጥቶ ሜዳ ላይ ጣላት። ስለክብሯ ሳይጨነቅ አመናጭቆ አባረራት። በገነች። እያነባች እጇን ወደ ሠማይ እንደዘረጋች ስሞታዋን ልታሰማ፣ ስለፍትህ ልትጮኽ ቃዲው ዘንድ ደረሰች።
"ምስክሮች በተጣዱበት በሐላል አግብቶኝ ሲያበቃ በበደል አረንቋ ማኖሩ ሳያንስ አዋርዶ አባረረኝ" በማለት ስሞታዋን አሰማች።

ቃዲው ባልየው ከነሁለቱ ምስክሮች እንዲገኙ ጠይቆ የተፈጠረውን ቢጠይቅ ልጅቷን እንደማያውቋት ምለውና ተገዝተው ተናገሩ። እንደውም ከዚህ ቀን በፊት አይተናትም አናውቅ በማለት ካዱ። በውሸት ላይ ተባበሩባት።

ዳኛው ሁለቱን ምስክሮች በጥልቅ ተመለከተና ወደ ሴትዮዋ ዞሮ "በባልሽ መኖርያ ግቢ ውስጥ ውሾች አሉን?" ሲል ጠየቀ።
"አዎ" አለች ዕንባዋን እየጠረገች።
"የውሾቹን ምስክርነት ትቀበያለሽን?" አላት ዳግም እየጠየቃት።
ግራ በመጋባት መንፈስ ውስጥ ተውጣ "አዎ" አለች።
"ውሰዷት ውሾቹ ከጮኹባት ውሸታም ናት፤ በዝምታ ወደ ቤቱ እንድትገባ ከፈቀዱላት የቤቱ ባለቤት ናት" አለ ዳኛው።
ምስክሮቹ እርስ በእርስ ተፋጠጡ።
"እነዚህም በውሻው ምስክርነት መሰረት ውሸታሞች ናቸውና ግረፏቸው" ሲል አዘዘ።

ውሾች ከህዝቦቿ በላይ ታማኝ የሆነባት መንደር ምንኛ ከፋች!!
t.me/ameentube

3 months, 1 week ago

ስልኩን አንሥቶ ቅርብ ጓደኛው ጋር ደወለ።
"እናቴ ታማለችና ለመድኃኒት የሚሆን ገንዘብ አበድረኝ" በማለት ጠየቀው።
"እማ ምን ሆነች"
የሆነውን ሁሉ ነገረው "አቅም አንሷታል መድሀኒቱ የግድ ያስፈልጋታል" በማለት አስረዳው።
"እሺ እፈልጋለሁ ከአንድ ሰአት በኋላ ደውልልኝ" ብሎት ስልኩ ተዘጋ።

ደቂቃዎችን በስስት እየቆጠረ ሰዓቱ ደረሰ። በቀጠሯቸው መሠረት ዳግም ደወለ። ስልኩ ዝግ ነበር! ደጋግሞ ደወለ ስልኩ ግን አይሰራም። ያ የቅርብ ጓደኛው ያ መደገፊያው ችግሩን አስረድቶት ስልኩን ጠርቅሞ መዝጋቱ ቅስሙን ሰበረው። መሸሻ እንደሌለኝ እያወቀ እንዴት ሲል ራሱን በአግራሞት ጠየቀ። ምድር ጠበበችው። የሚደገፍበት ሰው አጣ። እምዬን እንዴት ይታደጋት?! ምድር ተከፍታ ብትውጠው ተመኘ። በአጽናፈ ሰማይ መጠለል እንደማይችል ያህል ተሰማው። ስለእናቱ በጣም አዘነ። አምርሮም አለቀሰ።

ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ እየተጋባ በሐዘን በብስጭት በዕንባ ወደ ቤት ተመለሰ። እናቱ ተኝታ ነበር። ፊቷ ላይ የእረፍት ስሜት ይነበባል። አጠገቧ የመድሀኒቱ ብልቃጥ ተቀምጧል። ሁኔታው ግራ ቢገባው እህቱን ጠየቃት። "መድሃኒቱን ማን ገዛው?" አላት።
"ጓደኛህ ማዘዣውን ወስዶ መድሀኒቱን ገዝቶ መጣ" አለችው።

ዓይኖቹ የደስታ እንባን አቀረሩ። እየሳቀ ጓደኛውን ፍለጋ ወጣ። በሩጫ ወደ ቤቱ አቀና። በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ዘለቀ።
"ደግሜ ደጋግሜ ደወልኩልህ ስልክህ ግን ዝግ ነበር" አለው። "አዎ ስልኬን ሸጬ ለእናታችን መድኃኒት ገዛሁበት ለዛ ነው ዝግ የሆነው" ሲል መለሰለት።

የማወጋችሁ ስለ እውነተኛ ጓደኝነት ነው..!
t.me/ameentube

3 months, 1 week ago

ሁሉም ነገር ሲበዛ ይረክሳል፣ ጥሩ ባህሪ ብቻ በበዛ ቁጥር ይወደዳል።

3 months, 3 weeks ago
3 months, 3 weeks ago
3 months, 4 weeks ago
በሀገረ እንግሊዝ የምትኖር አንዲት ሚስኪን ትውልደ …

በሀገረ እንግሊዝ የምትኖር አንዲት ሚስኪን ትውልደ ሶማሊያዊት ሙስሊም ሴት እርዳታን ለማግኘት ወደ አንድ ድርጅት ደወለች። አምላክ የለም በሚለው እምነቱ የሚታወቀው ሰው የስልኩን እጀታ አነሳና አዳመጣት። ፋጡማ ቤቷ የሚላስ የሚቀመስ አለመኖሩን በመንገር ለችግሯ መፍትሄ እርዳታ ያደርግላት ዘንድ ተማፅና ቁጥሯን እና አድራሻዋን ሰጥታ ስልኩን ዘጋችው።

ምግብና ሌሎች እርዳታዎች ተዘጋጅተው ወደ አድራሻዋ እንዲያደርስ ለግል ጸሃፊው መመሪያ ሰጠ። እንዲህም አለ፡- "የእርዳታውን ምንጭ ከጠየቀችሽ ከሸይጣን የተሰጣት ስጦታ መሆኑን ንገርያት" በማለት ሴትየዋ ላይ እየተሳለቀ አዘዛት።

ፀሐፊዋ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ሸክፋ ወደ ሴትየዋ ቤት አቀናች። ምስኪኗ ሴት በደስታ እያነባች የተላከላትን ተቀብላ ወደ ውስጥ ለመግባት በመራመድ ላይ ሳለች ጸሃፊዋ "የዚህን እርዳታ ምንጭ ማን እንደላከልሽ ማወቅ አትፈልጊምን?" ስትል ጠየቀቻት። ይህች ማንበብና መጻፍ የማትችል ሙስሊሟ ፋጡማ የሰጠችው ምላሽ እምነት አልባውን ዶ/ር ቲሞሲ ቬንተርን አስተሳሰብ ቀይራ እስልምናን እንዲቀበል አደረገው ስሙንም ዐብዱልሀኪም ሙራድ ብሎ እንዲሰይም አስገደደው።
ምላሿ ይህ ነበር፡-
"ለማወቅ አልፈልግም ማንነቱም ግድ አይሰጠኝም። ጌታዬ አላህ አንድን ነገር ከፈለገ ሰይጣኖችም እንኳ ቢሆኑ ይታዘዙታልና"

t.me/elaftube

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago