Broken Heart???

Description
#ግጥም?
#የፍቅር ጥቅሶች❤
#የተለያዩ ምክሮች?
#photo ?

Join
https://t.me/True_Loves_1

ሀሳብ አስተያት ከለቹ?
@AbdulferidM
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 Monate her

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 7 Monate, 1 Woche her

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 Monat, 1 Woche her

1 year ago

ብዙም መሻት የለኝ!
[ ሶፊያ አህመድ ]

ብዙም አላለምኩም ... ብዙም መሻት የለኝ ...
... እንደው ለአንዴ ብቻ ናፍቄህ ብትመጣ << ዓይንሽን ልይ ብዬ ነው >> ስትለኝ ብሰማ እዚህ ደረቴ ስር በተስፋ የምትጠብቅ ጠውላጋ ልብ ነበረችኝ ...

ስትሄድ እንደተውከው ሁሉም እንዲያው ሆኖ አለ።
( ለአላህ ብሎ የተወ ሽልማቱ ምን ይሆን እላለሁ? )

ከመውደድ ላይ መሽረፍ ከመኖር መጉደል ነው ልልህ እወዳለሁ ፥ መሄድህ ያጎድላል።
የነበረከኝን ያኽል የለኝም ማለት ስንት ዛሬዬን ከነገ አዳብሎ እንደበላው ባወቅህ እመኛለሁ። አንተን ያኽል አግኝቶ አንተን ያኽል ማጣት እንዲህ ነው የሚሉት አልሆነም ፥ ለወሬ አልተመቸም ....

ልመነው ልመነው የለኸኝም በቃ ሄደኻል አውቃለሁ
ግን እንዳለህ እንዳለህ ልቤን ይሞቀኛል ፥
እንዳለህ እንዳለህ ነው መተውም ከብዶኛል ፥

እንዲህ እንዲህ ሲሰማኝ ልቤን ከነ ግሳንግሷ ሰብስቤ እነሳለሁ ።

ብዙ ብዙ አላልምም ብዙም መሻት የለኝ ...

... ግን አንዴ ... ለአንድ ጊዜ ብቻ አይንህን ብሰናበተው መሄድህን ልትነግረኝ ተመልሰህ ብትመጣ ፥ መልሰህ መላልሰህ ደህና ሁኚ ስትለኝ ብትከርም ፥ ጊዜው እዚህ ባለቀብህ ፥ መሄዴ ነው፥ ልሂድ  በቃ፥  ሄድኩ እንዳልክ እንዲሁ ዘመናችን በተገባደደ መሄዳችንን አብሮ ባደረገው እመኛለሁ ...

ይኸው መጣ መጣ ሳቅህ በዚህ አልፏል 
የሚያበራ ነጭ እንቁ አይኔ ላይ አፍልቋል
ውብ ዜማው ደርሶኛል
ልቤን ኮርኩሮታል
ጆሮዬን ዳብሶታል ...

ይኸው መጣ መጣ ....

ቀድሞ ነገር የት ሄዶ ጨዋታና ሳቅህ በልቤ ተቀምጦ ... የመጣው ከዚህ ነው
የመጣው ከኔ ነው
አብረው እያሉ  መሄድ እንደምን ያለ ነው  ?

እንጃ!

ብዙም አላልምም  ብዙ ብዙ አይደለም ብቻ ግን አንድ ነገር ፥ ከዓይንህ መራቄ ቁም ነገርህ ቢሆን ፥ መጉደሌ ቢያጎድልህ ፥ ልብህን ስጋ አድርጎልኝ እንደኔ እንደእኔ መበሳሳትን ቢያውቀው ፥ እንክት እንክትክት ፥ ቡትርፍ  ቡትርፍርፍ ብሎብህ ብታየው ፥ መልሰህ መላልሰህ ወደኔ ብትመጣ ፥ በዓይኔ ብታገግም ፥ ፈውስህ ቢያደርገኝ እመኛለሁ ...

ሌላም ምኞት የለኝ ሌላም ህይወት የለኝ

ኮቴ አደምጣለሁ በሬን እከፍታለሁ ... ሀፍረት ሸብቦህ በር መቆርቆር አቅቶህ ከበር እንዳትመለስ ክፍቱን እተዋለሁ...

መስገጃዬ ላይ ሆኜ  መምጫህን አያለሁ ... ቀን በጎደለብህ ያመንከው በከዳህ መሸሻህ ቢያደርገኝ እጠባበቃለሁ ...( ከልቤ አይደለም )

ደጅ ደጁን አያለሁ ፥ በልሂድ በልቅር ... ልብህ ባዝናብህ በመንገድ ስትዋልል ድንገት ብንተያይ ካየችኝ ወዲያማ ለምን ልመለስ ብለህ ብትመጣ ብዬ ለአይንህ እንድመች ሆኜ እቀመጣለሁ ... እህህ እላለሁ...

ቀን ይነጋል ቀን ይመሻል ፥የወደደ ይመጣ ይንጎማለለዋል ፥
የመሸበት ጊዜ ደክሞ ይመለሳል ፥ አሁን ሁሉ ደክሞ የሚመጣም የለ።

አሁን አሁን ብዙም መሻት የለኝ ....
ትንሽ ትንሽ ብቻ ልቤ ልብ እንዲቀራት መናፈቅ እንዳይርቃት ቁሜ እለማመናለሁ...

ብዙም አልፈልግም ሌላም ምኞት የለኝ ..
ብቻ ብቻ መፈለግ ባይጠፋኝ ፥ መጠበቅን ባልረሳ ፥ ልቤ ትንሽ ብቻ ትንሽ ሙቅ ደም ቢቀራት እለምነዋለሁ ...
በመጠበቅ መኻል ፥  ባለፈ እድሜ መኸል ፥ ስለበድን ስሜት ፥ ስለበቃ መውደድ ፥ ስለጠፋ መሆኔ ሁሉ ይቅር ለኔ እላለሁ ...

ደግሞ ታበግነኛለህ ። ያሰነዳዳሁትን መልሼ አፈራርሳለሁ ። የጎዘጎዝኩትን ሰባስቤ አሽቀንጥሬ እጥላለሁ ።

ከራስ ጋር ሙግቻ
በይመጣል ይመለሳል ተስፋ እንደው መሰንበቻ

ደሞ እመለሳለሁ ... ንዴቴን ዋጥ አድርጌ ከጌታዬ ጋር አወራለሁ።
<< አግራው! አግራው! >> እላለሁ!
አንተን መርጠን መንገድ ለይተናል
<< ኹን >> የሚል ቃልህን መስማትን ናፍቀናል!
አንድ አድርገን!
<< ይሁን >> በለን!
<< ፈተናዬን አልፋችኋል! ፈቅጃለሁ! >> በለን!
( አምኛለሁ! )

ብዙም ብዙም የለኝ ፤ ምንም ምንም የለኝ
የቀረኝ አንድ ነው ...
ማልጄ እነቃለሁ ፤ ከጌታዬ አወራለሁ ፤ መልሱን ጠብቃለሁ ፥ ኮቴ አዳምጣለሁ ÷ በበሩ አሳልፌ ደጅ ደጁን አያለሁ ÷ በርጩማዬን ይዤ መንገድ ዳር አደፍጣለሁ ÷ ሽቲዬን ወትፌ ፥ ክርኔን በጉልበቴ ከታች አስደግፌ ፥ በመዳፎቼ መኸል አገጬን ቀብሬ ... እቀመጣለሁ .... እጠብቅሀለሁ!
.

1 year, 1 month ago

ሰው ሁን በይኝ☺️****

በቀደም ለት ጉንጬ መሐል
በከንፈሯ ብትዳብሰኝ?
ሙት አካሌ ፊት እንዳለኝ አስታወሰኝ፣

ደሞ ድንገት ቀልድ ነግራኝ
ስቄ ስቄ እንዳባራሁ ፤
"ጥርስህ ሲያምር?" ስላለችኝ
ዘላለሜን ማልቀስ ፈራሁ ፤

ተካተትኩኝ ከተፈጥሮ
እፍፍ?...
አልሸብኝ ድብቅ ውበት፤
እስቲ  ባክሽ አሁን ደሞ
ሰው ሁን ብለሽ ሹሚኝና
ሰው መሆኔን ልመንበት ፤

ሰው ተብዬ ልጠራበት?

#አስቱ (አስታውሰኝ ረጋሳ)

@True_Love04

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 Monate her

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 7 Monate, 1 Woche her

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 Monat, 1 Woche her