★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago
ፍቅሯ ልዬ ነው ደግነቷ🌿🌿🌿
እናቴ አርሴማ ሰማዐቷ😍🥰
⛪ 'ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቁመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትሆን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው።አምላጅነቷ አይለየን🤗❤️
🌺ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ🌺
**መስከረም 29 ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ሰማዕትነት የተበለችበት ቀን ነው። እንኳን አደረሳችሁ።
ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ትሰውረን።🙏❤**
**ያንደበቴ ጣፋጭ ውዳሴ
========///========
ያንደበቴ ጣፋጭ ውዳሴ
ምፅናናብሽ ታዛለ ነፍሴ
ከመቅደስሽ ፍቅር ተምሬ
ማርያም ማርያም ይላል ከንፈሬ
ልመናዬን ሰምተሻል
በረድኤት ቀርበሻል
በፍቅርሽ ተሸልሜ
አረፍኩኝ ከሸክሜ{፪}
ቃሌ ነው በተሰማ
ተማፅኖዬን ሳሰማ
በዙፋኑ ቀኝ ሆነሽ
ድንግል ታስምሪናለሽ {፪}
ማግኝት ማጣት አይደለም
ልመናዬ በአለም
አድይኝ ማስተዋሉን
እንድረዳው መስቀሉን {፪}
አይመራኝም በትሬ
ድንግል ቆመሽ ከበሬ
ምርኩዜ ብዬሻለው
አንቺን እደገፋለው {፪}**https://t.me/maedot_ze_orthodox
"ከግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ገዳም /ድርሳነ መስቀሉ ትርጓሜ በርእሰ አባ ኪዳነ ማርያም!
"በልዩ መንበሯ አገሯ ግሸን ማማሯ //፪//
ማማሯ ማመሯ አገሯ ግሸን ማማሯ// ፪//
👏👏👏🌿🌿🌿👏👏👏🍃🍃🍃👏👏👏🍃🍃🍃👏👏👏🌿🌿🌿👏👏👏🌿🌿🌿👏👏👏🍃🍃🍃👏👏👏
††† እንኳን ለግሼን ደብረ ከርቤ: ለብዙኃን ማርያምና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ግሼን ደብረ ከርቤ †††
††† ሃገራችን ኢትዮዽያ ሃገረ እግዚአብሔር መሆኗን ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል:: (መዝ. 67, አሞጽ. 9:7) ሕዝቦቿም የድንግል ማርያምና የቅዱሳን አሥራት ናቸው:: የኢትዮዽያውያንን ያህል ድንግል ማርያምን የሚወድ: ለቅዱስ መስቀሉ ክብርን የሚሰጥ: ቅዱሳንንም የሚዘክር ያለ አይመስለኝም:: "እመ ብርሃንም ፈጽማ ትወደናለች:: ለዚህ ደግሞ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም::"
ለዓለም እስከ አሁን ድረስ የሁለቱ (የታቦተ ጽዮንና የቅዱስ ዕፀ መስቀሉ) መገኛ እንቆቅልሽ ነው:: ለእኛ ግን ሁለቱም ያሉት በቤታችን ውስጥ ነውና እንመሠክራለን:: ክብር ለቀደምት አበው ይድረሳቸውና አስፈላጊውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ዋጋ ከፍለው ታቦተ ጽዮንን እና ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን አምጥተውልናል::
በዚህች ዕለትም የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በደብረ ከርቤ ግሼን ማረፉን አስበን በዓልን እናከብራለን:: ይኸውም ደጉ አፄ ዳዊት በሠይፈ አርዕድ የተጀመረውን ጥረት ቀጥለው: በኃይለ እግዚአብሔር አሕዛብን አስደንግጠው: እመ ብርሃንንም በጸሎት ጠየቁ::
የአምላክ እናትም ረድታቸው ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን ከኩርዓተ ርዕሡ: ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ከሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ እና ከብዙ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር ተላከላቸው:: እርሳቸው መስከረም 10 ቀን መስቀሉን ተቀብለው: በዓሉን በተድላ አክብረው በመንገድ በ1396 ዓ/ም ዐርፈዋል::
አፄ ዳዊት ካረፉ በኋላ ቅዱስ መስቀሉ ለ30 ዓመታት ተቀምጧል:: አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እስከ ነገሠበት 1426 ዓ/ም ድረስም ከ6 በላይ ነገሥታት አልፈዋል::
††† አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከነገሠ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ለቅዱስ መስቀሉ በመካነ ንግሡ ደብረ ብርሃን ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ሲያስብ ጌታችን በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" አለው:: ከዚህ ቀን ጀምሮ ደጉ ንጉሥ የመካነ መስቀሉን ቦታ ይፈልግ ዘንድ ከሠራዊቱ ጋር ብዙ ደክሟል::
በመጨረሻም በነገሠ በ10 ዓመታት ግሼንን አምባሰል (ወሎ) ውስጥ አግኝቷት ሐሴትን አድርጓል:: ቦታዋ በሥላሴ ፈቃድ በትእምርተ መስቀል የተፈጠረች ናትና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አንጾ መስቀሉን በብረት: በመዳብ: በናስ: በብር: በወርቅ ለብጦ: ዐፈር እንዳይነካውም አድርጐ አኑሮታል::
በቦታውም ተአምራት ተደርገዋል:: ጻድቁ ዘርዓ ያዕቆብም 'ጤፉት' የሚባል መጽሐፍን ጽፎ እዚያው አኑሮታል:: መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው:: ይህ የተደረገውም መስከረም 21 ቀን ነው::
††† ብዙኃን ማርያም / ጉባኤ ኒቅያ †
††† ዳግመኛ ይህች ዕለት 'ብዙኃን ማርያም' ትባላለች:: በቁሙ ሲታይ ድንግል ማርያም የብዙ ቅዱሳን የጸጋ እናት መሆኗን ያመለክታል:: በምሥጢሩ ግን በዚህች ዕለት በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት መሰብሰባቸውን የሚያጠይቅ ነው::
የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::
ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት በዚህ ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::
እነዚህ አባቶች 'ሊቃውንት' ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው:: እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: የጉባኤውን ዜና ግን ሕዳር 9 ቀን የምንመለከት ነንና የዚያ ሰው ይበለን:: ይህች ቀን ለአባቶቻችን የሱባኤ መጀመሪያ ናት::
††† ቅዱሳን ቆዽርያኖስ እና ዮስቴና †††
††† ቆዽርያኖስ ማለት አገር ያስጨነቀ የሶርያ ጠንቅ ዋይ (መተተኛ) የነበረ ሰው ነው:: ከሥራዩ ብዛት የተነሳ አጋንንትን የሚፈልገውን ያዛቸው ነበር:: በዚያ ሰሞን ታዲያ ወደ አንጾኪያ ሔዶ የለመደውን ሊሠራ አሰበ:: እንዳሰበውም ሔደ::
በአንጾኪያ ደግሞ ስም አጠራሯ የከበረ: ክርስትናዋ የሠመረ: ድንግልናዋ የተመሠከረና ደም ግባቷ ያማረ አንዲት ወጣት ነበረች:: ስሟም ዮስቴና (የሴቶች እመቤት) ትባላለች:: እንዲህ ነው ስምና ሥራ ሲገጣጠሙ::
በወቅቱ ደግሞ የእርሷ ጐረቤት የሆነ አንድ ሰው በቁንጅናዋ ተማርኮ 'ላግባሽ' ቢላት 'አይሆንም' አለችው:: ምክንያቱም እርሷ መናኝ ናትና:: በጥያቄ አልሳካልህ ቢለው በሃብት ሊያታልላት: 'እገድልሻለሁ' ብሎ ሊያስፈራራት: በሥራይ (በመስተፋቅር) ሊያጠምዳት ሞከረ:: ነገር ግን አልተሳካለትም:: ምክንያቱም ሟርት በእሥራኤል ላይ አይሠራምና:: በመጨረሻ ግን ወደ ቆዽርያኖስ ሔዶ "አንድ በለኝ" አለው:: ቆዽርያኖስም "ይሔማ በጣም ቀላል ነው" ብሎ ወዲያው አጋንንትን ጠራቸው:: "ሒዳችሁ ያችን ወጣት አምጡልኝ" ሲልም ላካቸው::
አጋንንቱ ወደ ቅድስት ዮስቴና ሲሔዱ ግን መላእክት ወርደው ቤቷን በእሳት አጥረውታል:: ተመልሰው "አልቻልንም" አሉት:: እርሱም "አንዲት ሴት ካሸነፈቻችሁማ እኔም ክርስቲያን እሆናለሁ" ብሎ አስፈራራቸው:: አጋንንቱም በማታለል አንዱ ሰይጣን እርሷን መስሎ ሌሎቹ ደግሞ አስረውት መጡ::
ቆዽርያኖስ ይህን ሲያይ ደስ ብሎት "ሠናይ ምጽአትኪ ኦ ዮስቴና እግዝእቶን ለአንስት-የሴቶች እመቤት ዮስቴና እንኳን ደህና መጣሽ" ሲል: ስሟ ገና ሲጠራ ደንግጠው አጋንንት እንደ ጢስ ተበተኑ:: "ለዛቲ ቅድስት በኀበ ጸውዑ ስማ: ከመ እንተ ጢስ ተዘርወ መስቴማ" እንዳለ መጽሐፍ::
ቆዽርያኖስም በሆነው ነገር ተገርሞ "ስሟን ሲጠሩ እንዲህ የራዱ ወደ እርሷማ እንዴት ይቀርባሉ" ብሎ ተነሳ:: መጽሐፈ ሥራዩን በሙሉ አቃጠለ:: ሃብቱንም ለነዳያን አካፍሎ ሒዶ ክርስቲያን ሆነ:: የሚገርመው ድንግል ነበርና ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ዲቁናና ቅስናን ተሾመ::
አምላክ መርጦታልና የቅርጣግና ዻዻስ ሆኖ ተመርጦ የክርስቶስን መንጋ በትጋት ጠብቋል:: ቅድስት ዮስቴናም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ ንጽሕናን ስታስተምር ኑራለች:: በመጨረሻም በዚህ ዕለት ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስቶስን ካልካዳችሁ በሚል ብዙ አሰቃይቶ አንገታቸውን አሰይፏል::
††† ቸር አምላክ በኃይለ መስቀሉ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: የቅዱሳኑን ጸጋ ክብርም አይንሳን::
††† መስከረም 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ግሼን ደብረ ከርቤ
2.ብዙኃን ማርያም
3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት
እንኳን አደረሳችሁ ውድ ኦርቶዶክሳውያን
" ንግስቲቱ#ግሸን_ደብረ_ከርቤ "
ከደሴ ከተማ በስተሰሜን ምዕራብ 82 ኪሎ ሜትር በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የምትገኘው ዳግማዊት እየሩሳሌም በመባል የምትታወቀው ግሸን ደብረ ከርቤ ከእምነትና ከአስተዳደር ጋር የተቆራኙ ታሪኮችን ይዛለች፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ያሳተመው የቱሪዝም ማውጫ እንደሚያትተው ግሸን ማርያም የተቆረቆረችው በ517ዓ.ም በአጼ ካሌብ የክርስትና አባት የሆኑት አባ ፈቃደ ክርስቶስ የተባሉ መናኝ ናቸው፡፡ አባ ፈቃደ ክርስቶስ የቅድስት ድንግል ማሪያምንና የእግዚአብሔር አብን ጽላቶች ከሃገረ ናግራን /ከዛሬዋ የመን/ ይዘው ረጅም ጉዞ ተጉዘው አቀበቱን መንገድ አጥተው ሲፈልጉ በገደሉ ላይ ንብ ሰፍሮ ማር ተንጣሎ በማየታቸው ቦታውን ሲያደንቁ ይህስ ‹‹አምባ ሰል›› ነው ያሉ ሲሆን ስል ማለት በአረበኛ ማር ሲሆን ትርጉሙ የማር አምባ ማለት ነው፡፡ አባ ፈቃደ ክርስቶስ ሁለት ጎጆዎች አሰርተው ያመጡትን የአብና የድንግል ማሪያምን ጽላቶች በማስገባት እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ሲያገለግሉ እንደቆዩ ይነገራል፡፡
አምባው በተፈጥሮው ቀራጺ ባለሙያ የሰራው መስቀል የሚመስልና ወደ አምባው ለመውጣት ከአንዲት በር በስተቀር እንደ ምሰሶ የተቀረጸ ገደል ያለበት ነው፡፡
ይህችም በር በአጼ ኃይለ ስላሴ በጠፍጣፋ ድንጋይ ደረጃ ከመስራቱ በፊት አምባውን ለመውጣትና ለመውረድ በገመድ ወይም በመጫኛ ወገብ ታስሮ ነበር፡፡
ግማደ መስቀሉ ተቀብሮበታል ተብሎ የሚታመነው የእግዚዓብሔር አብ ቤተ-ክርስቲያን በአጼ ዘርዓያዕቆብ እንደገና የተሰራ ሲሆን በዳግማዊ ሚኒሊክም ታድሷል፡፡ በውስጡ በርካታ ኃይማኖታዊ ታሪክ ያላቸው ስዕሎችና ቅርሶች አሉት፡፡
ደብረ ነጎድጓድና ደብረ እግዚዓብሔር በመባል ትጠራ የነበረቸው የግሸን ማሪያም በአጼ ዘርዓያዕቆብ እህት እማሆይ እሌኒ በኋላም በአጼ ኃይለ ስላሴ ባለቤት እቴጌ መነን ታድሳለች፡፡ ከዚህ ኃይማኖታዊ እምነት በተጨማሪ የግሸን አምባ ከመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ነገስታት ካቋቋሟቸው የፖለቲካ ተቋማት መካከል አንዱና ዋነኛው ነበር፡፡ የግሸን አምባ እንደ ቤተ-መንግስት ወህኒ ቤትነትና በተቋምነት ተቋቁሞ የነበረው ከአጼ ይኩኖ አምላክ በኋላ ነው፡፡
ግሸን በየዓመቱ መስከረም 21ና ጥር 21 ቀን እጅግ በጣም በርካታ ምዕመናን በተገኘበት ትከበራለች፡፡
እንኳን አደረሳችሁ ውድ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቼ
የአመት ሰው ይበለን
የግሸኗ እናቴ ናፍቀሽኛል
ፈቃድሽ ሁኖ አንዴ ደጅሽን ረግጨ ነበር
ድጋሜ ሀገራችን ሰላም አርገሽ ለደጅሽ አብቂኝ እናቴ
? #ሚስጥረ ስላሴ በጥቂቱ ❣️
?ምስጢረ ሥላሴ፦ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው። እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ ነው።
<= >የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል፦ እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው።
<= >እግዚአብሔር በስም ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው። እነዚህም፦ #አብ #ወልድ መንፈስ ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም፤ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም። "ዘፍጥረት1፡ 2 " "ምሳሌ30፡4" ።
>እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው፦ ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው። እነሱም፦
መውለድና ፤ማስረጽ ?የአብ
መወለድ፡ ?የወልድ
?መስረጽ፡ ?የመንፈስ ቅዱስ ፤ የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ። "መዝሙር2፡7"
<=>እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ
ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።
ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።
ለመንፈስቅዱስ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው። <=>የሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞችትርጉም
አብ፦ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸነው።
ወልድ፦ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው። "መዝሙር2፡7" መንፈስቅዱስ፦ ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ; ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው። "ኢዮብ26፡13"
የቅድስት ሥላሴ ረድኤት
በረከታቸው አይለየን አሜን
በቅንነት ቴሌግራም ይቀላቀሉ
?ቤቴ_ተዋሕዶ-ሚድያ?
?የማስታረቅ ጥቅም፣
ከንቱ እውቀት መሰብሰብም ያለው ጉዳት.....
የሚያስታርቁ ብፁአን ናቸው!
የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና
የሚያስታርቁ የሚለው ቃል ትርጉሙ ምንድነው?
ሰላም በእግዚአብሔር እና በሰዎች መካከል ማለትስ ምንድነው?
ሰላም በሰዎች መካከልስ እና ውስጣዊ ሰላም ምንድነው?
የተራራው ስብከት ከሚለው ከአባታችን ከብፁዕ ቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ መንፈሳዊ መጽሐፍ!!!
የቅዱሳን ምክር እንማር አድምጡ??❤️✅
? ቀኑ ከረፈደ ከመሸብኝ መጣሁ
ደጃፍህ ላይ ቆምኩኝ እንዳልገባ ፈራሁ
በደሌን ሳትመዝን ግቢ ብትለኝም
ኃጢያቴ ከበደኝ አላራመደኝም አላራመደኝም
የሰው እድሜው እኮ አጭር ነው ጥቂት ነው
እንዴት ነው ሳላውቅህ ዘመኔ ያለቀው
ጉብዝናየን ዓለም ስቃ ተጫውታብኝ
እንዴት ብዬ ልርገጥ ደጅህን በድፍረት ??
አዲስ መዝሙር አዳምጡት ??
@Halemikael Join & Share
?*?*?**@Tewahdotisfafa@Tewahdotisfafa@Tewahdotisfafa
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 day, 11 hours ago