Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ንስር ሕክምና

Description
ለጥያቄ፡ ሃሳብ እና አስተያየት 👉 @nisiru

ማድረስ ትችላላችሁ።
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 Wochen, 2 Tage her

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 Tag, 13 Stunden her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 Monate, 2 Wochen her

1 week ago
ውድ የንስር ሕክምና ተከታታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ …

ውድ የንስር ሕክምና ተከታታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ።

እነሆ መልካም የጾም፣ የጸሎትና የጽሞና ሰሞነ ሕማማት ይኹንልን።

አምላካችን ከብርሀነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን!

© ንስር ሕክምና- @NisirHikimna

1 week, 5 days ago
1 month ago

🙋‍♂️ ስትሮክ እንዴት ይታከማል?(ክፍል-፫)©ንስር ሕክምና - @nisirhikimna

👨‍⚕️ የስትሮክ ሕክምናን ምንነት ጠቅለል አድርገን ለመመልከት ያክል በመጀመሪያ የትኛው የአንጎል ክፍል እንደተጎዳ እና ለዚሁም በመነሻነት ያስከተለው የደም ሥር መዘጋት ወይንስ የደም መፍሰስ የሚለውን በምን ምክንያት እንደኾነ ከታወቀ በኋላ እንዲሁም በተያያዥነት አብረው የተከሰቱ ውስብስነቶች (complications) እና መንስዔዎች (causes) ኹሉ ታሳቢ በማድረግ ከተገኘውን የምርመራ ውጤት ላይ ተመሥርቶ ይወሰናል።

💊 ስትሮክ አብዛኛውን ጊዜ በመድኃኒት ይታከማል። ይህም የደም መርጋትን ለመከላከል እና ለማሟሟት፣ የደም ግፊትን ለመቀነስ እና የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ ተብሎ የሚወሰዱ መድኃኒቶችን ያጠቃልላል።

፩. የመጀመሪያው ደረጃ በአጣዳፊነት የተከሰቱ ችግሮችን ማስተካከል እና ክትትል (stabilization & monitoring) ሲኾን ይኸውም በኹለተኛነት የሚከሰቱ ችግሮች ሳቢያ ከእንደገና በአንጎል ላይ የሚኖር ጉዳትን ለመቆጣጠር ያስችላል:-

🩺 የደም ግፊትን መጠን በተገቢው ልክ ማስተካከል

🫁 የኦክስጅን ፍላጎቱን ማገዝ

🧬 የደም ስኳር መጠኑን ማስተካከል

🌡 የሰውነት ሙቀትን በተገቢው መንገድ ማስቻል

🧪 የደም ውስጥ የሙልና ማዕድናት እንዲሁም የአሲድ-ቤዝ ውቅርን በአጥጋቢነት ማስተካከል

😴 እንፍርፍሪት (seizure) ከተከሰተ ማከም

🧠 የጭንቅላት ውስጠ ግፊት መጨመር ካለ ማከም

🫦 ምግብ ለመዋጥ አለመቻል (dysphagia) ካለ የምግብ ቱቦን በአፍንጫ ማስገባትና ከምግብ ማነስና ተያያዥነት ያላቸውን ውስብስብነቶች ኹሉ መከላከልና ማከም

🩸 የደም መርጋትን መከላከል

✍️ የጨጓራ ቁስለትን መከላከል

🦠 የሳንባ ምች እና የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽኖች ጋር የተያያዙ ውስብስብነቶች ከተከሰቱ ማከም

🫀 ከልብ ጋር የተያያዙ ችግሮችን መከታተልና ማክም

💊 የሕመም ስሜት ካለ እንደአስፈላጊነቱ ማስታገሻዎችን መስጠት

🔭 አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የአንጎል እብጠትን ለማከም አሊያም ለስትሮክ መንስዔነት የተጠቀሰውን የደም መፍሰስ በተለይም በአንጎል ፈሳሽ ቧንቧ ውስጥ ከኾነ በአደጋውን ለመቀነስ ሲባል ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግ የሚችልበት ኹኔታዎች አሉ።

ይቀጥላል...👇

@nisirhikimna

2 months, 1 week ago

እነሆ እንኳን ደስ አላችሁ !!!
ሰላም ውድ የንስር ሕክምና ቤተሰቦቻችን እንደ አምላክ ፈቃድ በቅርብ ጊዜያት በሰባት (፯) አይነት የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች በመቶዎች በሚቆጠሩ ረብ ያላቸው አርእስቶች እየመጣን ነው።

ዝግጁ ናችሁን፤ ጠብቁን !!!
ጥያቄ እና አስተያየት በዚህ አድርሱን 👉 @nisiru

🦅👇👇👇👇 🦅👇👇👇🦅

©ንስር ሕክምና - @nisirhikimna

2 months, 2 weeks ago
2 months, 3 weeks ago

ውድ የንስር ሕክምና ቤተሰቦቻችን እነሆ ስራዎቻችን ለብዙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ተደራሽ ይኾኙልን ዘንድ በቻናላችን ላይ የሌሎችን ማስታወቂያዎች ይለቀቃሉና፤ ስለኾነም ባለመሰልቸት ትታገሱን ዘንድ እንጠይቃለን።

*© ንስር ሕክምና*

4 months, 1 week ago
4 months, 1 week ago
4 months, 1 week ago
4 months, 2 weeks ago

የሳይነስ በሽታ (sinusitis) ምንነትምናልባትም አብዛኞቻችሁ አሊያም ሌሎችም ሰዎች ሊኾኑ ይችላሉ "እኔ ሳይነስ አለብኝ፤ እንዲህ ያለው ነገር ኹሉ ይቀሰቅስብኛል" ወዘተርፈ ብላችኋል፤ ወይንም ደግሞ ሲሉ ሰምታችሁ ይኾናል፤ ስለኾነም እስኪ ለዛሬ ደግሞ እነሆ በዚህ ላይ እነነጋ

👃 ሳይነሶች (sinuses) ተፈጥሯዊ እና በፊት እና የራስ ቅላችን አጥንቶች ውስጥ የሚገኙ እንዲሁም በአየር የተሞሉ ጉድጓድ አይነት ክፍሎች ሲኾኑ የሳይነስ በሽታ (sinusitis)ማለት ደግሞ እነኝሁ የአካላችን ክፍሎች በልዩ ልዩ አመክንዮዎች ሳቢያ ሲያብጡ / ሲበግኑ የሚከሰት የጤና ችግር ነው።

*↗️ መንስዔዎች (Etiology)፡
የሳይነስ በሽታ በቫይረሶች፣ በባክቴሪያዎች ወይም በፈንገስ* አሊያም በአለርጂዎች ምክንያትነት ሊከሰት ይችላል። የአፍንጫ ፖሊፕ (nasal polyp)፣ የሰውነት አፈጣጠር ችግሮች (anatomical abnormalities) እና የጥርስ ኢንፌክሽኖች(dental infections) ጭምር ከቦታዎቹ ቅርርብ ጋር ተያይዞ ወደዚህ የጤና ችግር ሊመሩ እና ሊያወሳስቡት ይችላሉ።

🧬 ምደባ/ክፍል (Classification)፡
👨‍⚕️ የሳይነስ በሽታ ከጊዜ ቆይታው(duration) እንዲሁም ከሕመሙ ክብደት አንጻር ተመስርቶ በሦስት ክፍሎች ሊመደብ ይችላል፤ ይኸውም አጣዳፊ የሳይነስ በሽታ (acute sinusitis) ከአራት ሳምንታት ላነሰ ጊዜ የሚቆይ ፤ መካከለኛ የሳይነስ በሽታ (subacute sinusitis) ከአራት እስከ አሥራ ሁለት ሳምንታት የሚቆይ ሲኾን ሥር ሰደድ የሳይነስ በሽታ (Chronic Sinusitis) ደግሞ ከአስራ ሁለት ሳምንታት በላይ ይቆያል።

**ክሊኒካዊ ባህሪያት/ምልክቶች (Clinical features):

የሳይነስ በሽታ ምልክቶች የፊት መወጠር እና መጨናነቅ (congestion)፣ የፊት ህመም ወይም ግፊት (facial pain/pressure)፣ ራስ ምታት፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ እና የማሽተት ስሜትን ማጣት ሊያጠቃልል ይችላል።

*💉 ምርመራ፡*-

የሳይነስ በሽታ መኖሩን ለማረጋገጥ የአካላዊ ምርመራ (physical examination) ፣ የምስል ምርመራዎች (እንደ ሲቲ ስካን ወይም ኤምአርአይ) እና የአፍንጫ ኢንዶስኮፒ/endoscopy) የመሳሰሉትን በመታገዝ ለማወቅ ይቻላል።

*💊 ሕክምና (Treatment)፡
👨‍⚕️የሳይነስ በሽታዎች ሕክምናው እንደየ ኹኔታው የሚለያይ ኾኖ፤ ለምሳሌነት በዋነነት መንስዔው በባክቴሪያዎች ምክንያት ከኾነም አንቲባዮቲክስ (የፀ ባክቴሪያ መድኃኒቶች) ይታዘዛሉ፣ አለርጂ ከኮነ ደግሞ የሚታወቁ ቀስቅሴዎችን በማስወገድ (Avoidance of triggers)፣ የአፍንጫ ኮርቲኮስትሮይድ (Corticosteroids) እና የህመም ማስታገሻዎችን ሊያካትት ይችላል፤ በቫይረሶች ሳቢያ የሚከሰቱት ግን በራሳቸው ጊዜ የመሻል ዕድል አላቸው።*

ከባድ በኾኑ እና ሌሎችም ተያያዥነት ያላቸው ብለን ከላይ የጠቀስናቸው እንደ የአፍንጫ ዕብጠት/ፖሊፕ (nasal polyp)፣ የሰውነት አፈጣጠር/አወቃቀር ችግሮች (anatomical abnormalities) እና የጥርስ ኢንፌክሽኖች(dental infections)** የመሳሰሉት ካሉ ደግሞ ቀዶ ጥገናም ሊያስፈልግ የሚችልበት ዕድል አለ።

*🩺 መከላከያ መንገዶች (Prevention Methods)፡-
👨‍⚕️* እነሆ በተለይም ለአለርጂ በምክንያትነት የሚያስነሱትን አካባቢያዊ ቀስቅሴዎችን ማስወገድ፣ ጥሩ የግል እና የአካባቢ ንፅህናን በመጠበቅ እንዲኹም ሲጋራ ማጨስን በማቆም የሳይነስ በሽታን ለመቆጣጠር ይቻላል።

ዋቢዎች (References):
1. CDC https://www.cdc.gov/sinusitis

2. AAO - HNS https://www.enthealth.org/conditions/sinusitis

3. Mayo Clinic. https://www.mayoclinic.org/diseases-conditions/sinusitis

©ንስር ሕክምና- @nisirhikimna

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 Wochen, 2 Tage her

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 Tag, 13 Stunden her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 Monate, 2 Wochen her