የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion 📩 @Share_Home
Last updated 1 month ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 4 months, 2 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 6 months, 2 weeks ago
✍
የዩሱፍ ወንድሞች………
ዩሱፍን መውሰድ በፈለጉ ጊዜ ለአባታቸው፦
?{وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ}
{እኛም ለእሱ ጠባቂዎች ነን።} አሉት
አባታቸው ግን፦
?{فَاللَّهُ خَيْرٌ حَافِظًا}
{አላህ የተሻለ ጠባቂ ነው።} አላቸው
በመጨረሻም…………
ወንድሞቹ ዩሱፍን ማጥፋት ፈለጉ; አላህ ግን ጠበቀው።**
?አቡ ዒርፋን!!
https://t.me/hamdquante
✍
*Mass media……
ሰዉን አበላሽቶታል ይላሉ;
ሐቂቃው ግን………
አበላሽቷቸው ሳይሆን ብልሽታቸው ነው ግልፅ ያደረጉበት!!*
✍
ተልቢስ ለምን??????
እውነቱን በግልፅ ተናግሮ ሰዉ ያሳመነው እንዲከተል ማብራራት እየተቻለ የራስን ዕይታ ለማጉላት እና የተከታይ ብዛት ለማስፋት የሚደረገው ተልቢስ ነው የተረጋጋ እና የጠነከረ ዳዕዋ እንዳይኖር ምክንያት የሚሆነው።
አላህ
{الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ}
ሲል እና ነብዩ ﷺ
«تركتكم على البيضاء»
ሲሉ እስልምናችን, መንሓጃችን, ዳዕዋችን ሙሉ ነበር። ምንም የሚጎለው የሚጨመርም ይሁን የሚስተካከል ነገር የለውም። የየመንም ይሁን የነጅድ፣ የሰለፍም ይሁን የኸለፍ ዑለማዎች ንግግርና ፈትዋ ሙሉ የሆነውን ዲን የሚያብራራ እንጂ የሚያስተካክል አይደለም። ስለ የትኛውም ሸሪዓዊ ነጥብ በቁርኣን በሓዲስ ከተቀመጠው ጥቅስ በኋላ በ“አዲስ ፈትዋ” ወይም በ“አዲስ በያን” የሚቀየር ፍርድ የለም።
ቁርኣን እና ሓዲስ በግልፅ ያስቀመጠው ነጥብ ላይ ማብራሪያ ካስፈለገ "መረጃው ይህ ነው: ዑለማዎች እንዲህ ብለው አብራርተውታል" ብሎ መግለፅ እየተቻለ;
ከመረጃ ተቃራኒ የሆነ አቋም መያዙ ሳይበቃ የዑለማዎች ንግግር በመጠምዘዝ እና የመረጃ አንገት በመስበር ተከታይ ላይ አለባብሶ ራስን ማንገስ መጨረሻው ለማያምር ሕይወት ከመጋበዙ በተጨማሪ ሰዎች ዘንድም ትዝብት እና ጥላቻ የሚቸር ተግባር ነው።
አላህ በእዝነቱ እና በቱሩፋቱ የሰው ልጆች ሳያስጠነቅቃቸው አይቀጣቸውም፤ ሳይመክራቸው አይወቅሳቸውም።
{وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّى نَبْعَثَ رَسُولًا}
{መልእክተኞች እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም።}
[አል_ኢስራ: 15]
{رُّسُلًا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى اللَّهِ حُجَّةٌ بَعْدَ الرُّسُلِ وَكَانَ اللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا}
{ለሰዎች አላህ ላይ መረጃ (ምክንያት) እንዳይኖራቸው አበሳሪ እና አስጠንቃቂ የሆኑ መልእክተኞች ላክን። አላህም አሸናፊ እና ጥበበኛ ነው።}
[አል_ኒሳእ:165]
አላህ ማንንም ከማሳወቁ እና ከማስጠንቀቁ በፊት እንደማይቀጣው ሁሉ ካሳወቀው እና ካስጠነቀቀው በኋላ በእሱ ላይ ቅንጣትም ያህል ያሻረከ ወይም የካደ የሆነን ሰው በፍጹም አይምርም።
{إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ}
{አላህ በእሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም።}
[አል_ኒሳእ:48]
በአላህ ያጋራም ይሁን በአላህ የካደ በፍጹም ዱንያም ላይ ይሁን አኼራ ላይ ከሙስሊሞች ሊሆን አይችልም። አይሆንምም። ሙሽሪክ እና ካፊር ገለፃው እና ቃሉ ቢለያይም የሚያሰጠው ፍርድ ግን አንድ ነው። ዱንያ ላይ ደምንም ሀብትም ሀላል ሲያስደርግ አኼራ ላይ ለዘላለማዊው እሳት ይዳርጋል።
ስለሆነም እያንዳንዱ ሙስሊም ከሁሉም ሙሽሪክ እና ከሀዲ የመጥራት እና የመራቅ ግዴታ አለበት። ሙሽሪክን "ሙሽሪክ" ከሀዲን "ከሀዲ" ብሎ ያልራቀ ወደ እነርሱ የተጠጋ ይሆናል።
የአላህ ወዳጅ እና መልእክተኛ: የነብያቶች አባት እና የመእመናን ባጠቃላይ አርኣያ የሆኑት የነብዩላህ ኢብራሂምﷺ አዋጅ ተመልከት፦
{قَدْ كَانَتْ لَكُمْ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ فِي إِبْرَاهِيمَ وَالَّذِينَ مَعَهُ إِذْ قَالُوا لِقَوْمِهِمْ إِنَّا بُرَآءُ مِنكُمْ وَمِمَّا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ كَفَرْنَا بِكُمْ وَبَدَا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةُ وَالْبَغْضَاءُ أَبَدًا حَتَّى تُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَحْدَهُ}
{በኢብራሂም እና ከእሱጋ በነበሩት መከተል አለላችሁ፤ ለህዝቦቻቸው "እኛ ከእናንተ እና ከአላህ ሌላ ከምታመልኩት የጠራን ነን: በእናንተም ክደናል፤ በአላህ በብቸኝነቱ እስክታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መሃል ዘላለማዊ ጥላቻ እና ጠላትነት ግልፅ ሆኗል" ባሏቸው ጊዜ አርኣያነት አለላችሁ።}
[ሙምተሂና:4]
እነዚህ ሦሥት ነጥቦች መሰረቶች ናቸው፦
1ኛ, አላህ ማንንም ሳያሳውቀው አይቀጣውም፤
2ኛ, አላህ በእሱ ላያ ቅንጣትም ላጋራበት አይምርም፤
3ኛ, በአላህ ላይ ከሚያጋራ ሰው መራቅ የሁሉም ግዴታ ነው።**
ከዚህ በኋላ ነው "ዑዝር ቢልጀህል" የሚለው ነጥብ የሚመጣው።
ዑዝር ቢል ጀህል ማለት፦
አንድ ሰው ነው: ሙስሊም ነው: እስልምና የሚያዘውን እየታዘዘ የከለከለውን እየተከለከለ አላህ ባስቻለው ያህል ሸሪዓን ተከትሎ የሚሄድ ነው። በሆነ ሰዓት ተግባሩ በአላህ ላይ መካድ ወይም ማጋራት የሆነ ተግባር ሰውየው ግን ይህ ነገር ሽርክ ይሁን ክህደት ሳያውቅ በጅህልና ይህንን ተግባር ይፈፅማል። ይህ ሰው ካለው ባህሪው ይህ የሰራው ሽርክ: ሽርክ መሆኑን ቢነገረው ወድያው የሚቆጠብ ሰው ነው። ታድያ ይህንን ሙስሊም ባለማወቅ ላይ ሆኖ ይህንን ሽርክ በመስራቱ ከእስልምና ይወጣል "ካፊር" ይባላል? ወይስ አይባልም? የሚል ነው።
ምንም በማያሻማ መልኩ ግልፅ የሆኑ የቁርኣን እና የሓዲስ ጥቅሶች የሚያመላክቱት እና ያልተበረዘ ጤነኛ የሆነ አእምሮ የሚያምነው ይህ ሰው ሙስሊም እንደሆነ ነው። እስልምናውን ይዞ እየኖረ ነገር ግን የሆነ በማያውቀው ነጥብ ላይ ሽርክ ቢያስገኝ ከዚህ ሽርክ እንዲርቅ ተነግሮት ተመክሮ "አሻፈረኝ" ብሎ እስካልቀጠለ ድረስ ይህ ሰው ከዚህ በፊት ከእሱ በግልፅ በሚታወቀው እምነቱ በእስልምናው የቀጠለ ይሆናል። ይህንን የሚያብራሩ መረጃዎች ብዙ ከመሆናቸውም ጋ አንድ ሓዲስ እንመልከት፦
ነብዩﷺ መካን ድል አድርገው ከከፈቱ በኋላ ሌሎች ጠላቶቻቸው ለመጋደል ሲዘምቱ ከፈትሕ በኋላ ወደ እስልምና የገቡትን ጨምሮ ብዙ አዳዲስ ሰዎች በዘመቻው ተከትለዋቸው ወጥተው ነበር። በዚህ ጉዞ ሁነይን የተባለ ስፍራ ሲደርሱ አንዲት ዛፍ ተመለከቱ። እቺ ዛፍ "ዛቱ አንዋጥ" ትባላለች: ሙሽሪኮች ለግዲያ በሚሄዱ ጊዜ ሰይፋቸው ያንጠለጥሉባታል። ምክንያቱም ይህ በማድረጋቸው "በረካ እናገኛለን" የሚል እምነት ስለነበራቸው ነው። እነዝያ ነብዩﷺ የተከተሉ አዳዲስ ሰለምቴዎች ይህንን ባዩ ጊዜ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ!
اجعل لنا ذات أنواط كما لهم ذات أنواط
ለእነርሱ ዛቱ አንዋጥ እንዳለችላቸው ለእኛም ዛቱ አንዋጥ ያድርጉልን" አሉ። ይህ ጥያቄያቸው ግልፅ የሆነ ሽርክ ነበር: ነገር ግን ገና አዲስ ሰለምቴ እና ብዙ የእስልምና ህግጋት ያልተረዱ በመሆናቸው ነብዩﷺ "ድጋሚ ላ ኢላሃ ኢለላህ በሉና ወደ እስልምና ግቡ" ብለው ሳይሆን ያሏቸው;
«سبحان الله! لقد قلتم كما قال قوم موسى»
«ለአላህ ጥራት ይገባው! የሙሳ ህዝቦች ያሉትን ዐይነት ነው ያላችሁት» ብለው ኮነኗቸው።
የሙሳ ህዝቦች የተናገሩትማ እንደውም ከዚህ የከፋ ነበር። አላህ ከፊርዓውን ተንኮል ጠብቆ ፊርዓውን አስምጦ እነሱ ካዳናቸው በኋላ ወደ ግብፅ ሀገር ሲሄዱ በገጠማቸው ክስተት የተናገሩት ነበር። አላህ እንደ ነገረን፦
??
?
✍
ነብዩላህ ኑኅﷺ ለ1ሺህ ዓመታት 50ዓመት እስኪቀረው ድረስ የሰው ልጆች ወደ እስልምና እንዲገቡ ሲጣሩ ቢቆዩም የተቀበሏቸው በጣም ጥቂቶች ነበሩ;
ወደ ሰፊናዋ እንዲገቡ ለእንስሳዎች በተጣሯቸው ጊዜ ግን እንስሳዎቹ ወድያው ጥሪያች ተቀብለው ወደ መርከቧ ገቡ!!*
ነብዩላህ ኑኅﷺ ልጃቸው ከዱንያ ጥፋት ከአኼራ እሳት እንዲድን ሲጣሩት "አሻፈረኝ" አለ;
ነብዩ ኢብራሂምﷺ ልጃቸው ሊያርዱት በጠሩት ጊዜ "እሺ መርኸባ" ብሎ ለመታረድ ተመቻችቶ ተኛ!!
የነብዩላህ ሉጥﷺ ባለቤት የአላህ ወዳጅ እና መልእክተኛ ከሆነ ነብይ ጋ እየኖረች ከሀዲ ነበረች;
የፊርዓውን ባለቤት የአላህ ጠላት እና አመፀኛ ከሆነው ፊርዓውን ጋ እየኖረችም ኣማኝ ነበረች!!*
ተውፊቁ ከአላህ ብቻና ብቻ ነው!!
?አላሁመ ወፍቀን?
✍
ማንነታችን የምንፈትሽበት ጥያቄ………
የሙሉ ሕይወትህ እንቅስቃሴህ እያንዳንዱ ንግግር እና ተግባርህ እንደ ፊልም አንድ በአንድ ተቀርፆ ተዘጋጅቶ ቤተሰቦችህ በተሰበሰቡበት ቢከፈት እና ሁሉም ቢመለከቱት………
ምንም ሳታፍር ሳትሳቀቅ አብረሃቸው ትመለከተዋለህ??? ወይስ???
እንግዲያውስ………
የምታፍርበት የምትሳቀቅበት ድርጊት ከሌለ እሰየው!!
ንግግሮችህና ተግባሮችህ ለዚህ ድፍረት የሚያሳጡህ ከሆኑ ግን እንግዲያውስ ወየውላችን¡¡
✍
የሽልማት ጥያቄ ይኖረናል!!
ከቀኑ ?9:00 ሰዓት ላይ ይጠብቁን
? ? ?
https://t.me/hamdquante
የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion 📩 @Share_Home
Last updated 1 month ago
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 4 months, 2 weeks ago
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 6 months, 2 weeks ago