Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ሰውኛ ጥበብ

Description
ተሰጥዖዎን የሚያሳዩበት፣ የሚወዳደሩበትና የሚያሸንፉበት የጥበብ ትልቋ መሃደር!
Advertising
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 1 week, 3 days ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 3 days, 8 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago

6 months ago

የችግር ግዜ አጋር
(ካሊድ አቅሉ)

እንደብኩን ፍጥረት ለነገዬ ሳልል ሰጠሁሽ  
        መውደዴን ልቤን አራግፌ
ምሽትሽ ላይ ደረስኩ ያንን ቀትር ብርሃን
              በመኝታ አልፌ

ቀን ወዳጀ ብዙ ሁሉም ወጪ ወራጅ
          አጎብዳጅ ነው ላንቺ
"በርቺ ግፊበት ነው " ስህተት እንኳን
       ሰርተሽ መስመር ብትስቺ

ህይወት ስትመሻሽ ሲውጣት ጨለማ
        ለምን ይመስልሻል ?
ለመጓዝ ምነሳው ወዳንቺ ከተማ
የምሽት ግዜ ወዳጅ የችግር ግዜ አጋር
  አይሸልልም በቀን በፀሐይ ተመክቶ
በድቅድቁ መሀል መንገድ ለማሻገር
          የሚገኝ ነው በርቶ !

@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb
@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb

7 months, 4 weeks ago

የጠባቂ ፣ ፍልስፍና

ያሳረፍሽው ኮቴ ፣ በጉልህ ይታያል
           ከመንገዱ ጎልቶ
ዶፍ ዝናብም ወርዶበት፣ አልተንቀሳቀሰም
           ተቀምጧል እረግቶ፤

ምን አስበሽ ይሆን?
ከመንገድ እንዲቀር ፣የፈለግሽ ፍንጭሽን
በሀሳብ ተወጠርኩ፣ ውልኪዳንሽ ጠፋኝ
ዳርሽን ለማግኘት ቀን፣ ወራት አልበቃኝ ።

ሁለት ፅንፍ አለ አውርጄ አውጥቼ
           የደረስኩበት ጫፍ
እኔ እንድከተልሽ ፥ መግቢያሽን እንዳይ
የእግርሽን አሻራ አስቀምጠሽ ሄደሻል
              ከመሬቱ በላይ ፤

ወይንም ...

የሄድሽበት ጎጆ ፣ ሙቀት ከነፈገሽ
መምጣት አስበሻል ፣ በዳናሽ ተመርተሽ

#ካሊድ አቅሉ

@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb
@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb

8 months ago

ክብሪትን፣  አትናቁ

የአሀዱ ፍሬ ፣ ጭላንጭል መንደሯ
ብርሃን አፍልቃለች ፣ ጨለማን መንጥራ
እቺ ትንሽ መሳይ ፣ከሰል መሀል ገብታ
             የምትቀጣጠል
ሁሌ እገረማለው፣ ሀይልዋን ወስደናት
          እንጨትዋ ስትጣል
የሚንቦለቦለው የደመራን ችቦ ቆመው
                የሚያደንቁ
በጣም ይገርሙኛል የእሳቱን መነሻ
             ክብሪትን ሲንቁ ።

@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb
@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb

8 months, 1 week ago

ባልፈለግሽው መንገድ
(ካሊድ አቅሉ)
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
እንለያይ ብለሽ
መንገድ ስትጀምሪ፣
ይሄንን አስታውሺ
ከግዜ ብሃላ ባልፈለግሽው፣
መንገድ እንዳትመለሺ !

መፈለግ እውር ነው
መንገድ ይጋርዳል
ማጨብጨብ አብዝቶ፤
ወደታች ያወርዳል ።

ምንድነው መፋቀር
የምን ግዜ መፍጀት
ከራስ ተወዳጅቶ
ምድር ላይ ያስቀራል
ካንቀላፉት አለም መተኛትን ሰቶ !

ይሄ ሁሉ ገፍቶሽ . . .
" አንተ ጋር ምን አለ? "
ከፊት እየመራሽ ስትረግጪ በግምት
ስንት ፍካት ቀጨሽ ሳትራሪ በስሜት
ያጓጓል አውቃለው የፍካቱ አለም
ይሄ ሁሉ ሆኖም በግዜ ከነቃሽ ተመለሽ
                 ግድ የለም ፤

ግና ያንቺ ሁነት . . . .

የማስተዋሉን በር ሰርክ እየከፈትሽው
        ይሄው መዝጊያው ላላ
ፀብ ነው ሚጠብቀው ሳይነኩት
       ይወድቃል ከግዜ ብሃላ!

እንለያይ ብለሽ
መንገድ ስትጀምሪ፣
ይሄንን አስታውሺ
ከግዜ ብሃላ ባልፈለግሽው፣
መንገድ እንዳትመለሺ !
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb
@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb

8 months, 1 week ago

//ቆሜ - እንድጠነክር//
(ካሊድ አቅሉ)

በእንፉቅቅ ጉዞዬ አንሺ ሳልንተራስ
          የፍቅርሽ ወራጅ ነኝ ባልሽኝ ጋራ ምፈስ
መነሳት መሄዱን ገላዬ ቢናፍቅ
        ህመም ፈርቺ ነው እየቀረብኩ ምርቅ
የኔስ አፈጣጠር ገፍታርዬ በዝቶ መሬት ቅርቤ
                       ቢሆን
    ስቃይ ያልኩት ገዝፎ ደስታዬ ቢያላዝን
ትዝታሽ አለልኝ ዛሬን የሚያስረሳ
                ትናንቴን በመግደል ነገዬን ሚያነሳ
ልደግፍህ ብለው ምርኩዝ ሚያቀብሉኝ
                  እጅን በመለገስ ክንዴን ቢደግፉኝ
ለኔ ቆሞ መሄድ እግር አይደለም ችግር
         ፍቅርሽ ይበቃኛል ቆሜ እንድጠነክር!!!

@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb
@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb

8 months, 3 weeks ago

ቢሰፍሩሽ ቢሰፍሩሽ ሞልተሽ የምትፈሺ
አዎ አንቺ እኮ ነሽ ከልጅሽ ደሴት ላይ
             መኖር ምትቀድሺ  ።

ካሊድ አቅሉ
~ ~  ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ፍቅር ብቻ አይደለም  አካልም ውስጡ አለ
በእናትነት አጥር ልጅ በሚባል ድንበር
                አንሶ የታጠረ
መስጠት የእሱ ግብር ፦
እኔነትን መስጠት ፣
መራራትን መስጠት ፣
መንሰፍሰፍን መስጠት ፣
መስጠት መስጠት ብቻ መውሰድ
              ማይመጥነው
የእናትነት ግብር ሲያፈሱት ሚሞላ
          ምትሀትነት አለው ።

በንዋይ ማትገኝ ከስጦታ መሀል
ብቻዋን ቆማለች እናት የምትባል

ቢሰፍሩሽ ቢሰፍሩሽ ሞልተሽ የምትፈሺ
አዎ አንቺ እኮ ነሽ ከልጅሽ ደሴት ላይ
           መኖር ምትቀድሺ ።
አዎ እኮ ግብርሽ ነው . .  .
በመስጠት በርትተሽ መቀበል ምትረሺ !

አካል እና ነፍስ በሰው አምሳል አርገው
         ቆመው  ቢያስኬዱሽም
እውነቱን ልንገርሽ በነፍስ ነው እንጂ
          በእውን አንቺ የለሽም ።
                      .
                      .
                      .
ልጅሽ አካል ላይ ነሽ በድን ነው ሂያጅ
                     ገላሽ
እራስን አርግፎ ሌላ በመሙላት ውስጥ
             ህይወትን  የቀላሽ ።

@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb
@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb

8 months, 3 weeks ago
ሰውኛ ጥበብ
8 months, 4 weeks ago

አንድ እቅፍ
(ካሊድ አቅሉ)

ላንቺ ግዜ የተረታው
የወደቀው ሳር ቅጠሉ
ምን ቢሆን ነው አዘራሩ
ማማር ብቻ የማብቀሉ

ብዬ አልጠይቅም ባለሽበት
መቀጠል ማደስ ታውቂያለሽ
ይህው እዚ ጋር ብለው ሲጠቁሙሽ
     ከሰማይም ትርቂያለሽ

መች ፈጠረሽ ላገማመት ለቀላል ቃል
                 ፉክክሩ
ሰርክ ሳስብ ይደንቀኛል ይሄን ፀዳል
ግርማ ሞገስ ከሰው ልጅ ጋር ማጣመሩ!
ነገረ ስራዬን ልርሳ ልሰደድ ከቀዬ ደጃፍ
የተያዘው አለም ሁሉ ይፈታ የለ ባንቺ
               አንድ እቅፍ ።

@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb
@Sewgna_Tibeb   @Sewgna_Tibeb

9 months, 1 week ago

ኑሮህ ብርቅ አይደለም!
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
ሞተህ በሳምንታት ለሚረሳህ ዓለም
መሞትህ ነው እንጂ ኑሮህ ብርቅ አይደለም!
የት ገባህ የት ወጣህ ብሎ ያልጠየቀ
ትኑር ወይም ትሙት ደርሶ ያልፈለገ
ሞተ ሄደ ሲባል ጉድጓድ ምሶ መጥቶ
ነፍስ ይማር እያለ ንፍሮውን አንስቶ
ቆርጥሞ ለሚሄድ ለዚህ እስስት ዓለም
አሟሟትህ እንጂ ኑሮህ ብርቅ አይደለም!!

(ኪሩቤል አሰፋ)
@Sewgna_Tibeb @Sewgna_Tibeb
@Sewgna_Tibeb @Sewgna_Tibeb

9 months, 2 weeks ago

ሺህ ዓመት ንገሥ
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
:
:
:
ሺህ ዓመት ለመንገሥ ሺህ ዓመት የኖሩ፤
እነማን ነበሩ?
:
:
ይልቅ...
ፍቅርን ብለው ኖረው ፍቅርን ያወረሱ፤
ጥቂት ዓመት ኖረው ሺህ ዓመት ነገሡ።

ሁሉ በፍቅር ይሁን!

(ሄኖክ ብርሃኑ)
@Sewgna_Tibeb @Sewgna_Tibeb
@Sewgna_Tibeb @Sewgna_Tibeb

We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 1 week, 3 days ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 3 days, 8 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago