★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago
እነሆ የፊታችን እሁድ ቀን 03/2/2017 ዓል ከምሽቱ 3:30 ወቅታዊ በሆነ ርዕስ በቀጥታ ስርጭት ይኖረናል።
በዕለቱ የጀማዓተ አትተብሊጝ አደጋ እና ለሹቡሃቸው ምላሽ መስጠት ላይ ያተኮረ ት/ት የሚሰጥ ይሆናል።
ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት ቻነል👇👇👇
https://t.me/butajira_Qirat_daewa_group
ከመጝሪብ ሰላት በኋላ በዚሁ ቻነል "ተወሱል"ን የተመለከተ ሙሓደራ በቀጥታ ስርጭት ይኖረናል፦
https://t.me/butajira_Qirat_daewa_group
በመውሊድ ዙሪያ ለበድሩ ሑሴን አሳሳች ንግግር የተሰጠ እርምት
~
መስከረም 26/2017
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
ዛሬ ቅዳሜ እና ነገ እሁድ ዘይነዲን መስጂድ ላይ የሚሰጠው የዑምደቱል አሕካም ደርስ አይኖረንም።**
እነሆ የፊታችን እሁድ ቀን 23/09/2016 ዓ·ል ከጥዋቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዝሁር የሚቆይ ለተማሪዎች ዳዕዋ እና ምክር በ"መድረሰቱል ዓባሲያ" (መድረሳ መስጂድ) ተሰናድቶ ይጠብቃቹኋል።
በዕለቱ የክረምቱን እረፍት ጊዜ በአግባቡ ትጠቀሙ ዘንድ ማስታወሻ እንዲሁም ምክር ይሰጣል። በተጨማሪም ሴት እህቶችን የሚመለከት ልዩ ትምህርት ይኖራልና ይህንን ፕሮግራም ትታደሙ ዘንድ መላው የቡታጅራ ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ተጋብዛችኋል።
@በሩሓማ በጎ አድራጎት ማህበር አስተባባሪነት!**
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
=
ከፊታችን ሰኞ ቀን 17/09/2016 ዓ/ል ጀምሮ ሁሉም የዘይነዲን መስጂድ የኪታብ ደርስ በነበረበት ይቀጥላል።
~~ ኡድሒያ ላይ የሚፈፀሙ ስህተቶች‼
➊~ ኡድሒያውን በምናርድበት ጊዜ ከአሏህ ውጪ ያለን አካል ስም መጥራት።
ይህ ተግባር ኡድሒያውን ወደ አሏህ ከመቃረቢያነት አውጥቶ ከአሏህ አርቆን ዝንት አለም የጀሃነም ማገዶ ወደሚያደርገን ሽርክ ይወስደዋልና እጅግኑ ልንጠነቀቅ ይገባል።ኡድሒያም ይሁን ሌላን እርድ በምናርድበት ወቅት ወደ አሏህ መቃረብን አስበንና የእርሱን ስም ብቻ አውስተን ማረድ ይኖርብናል።
➋~ የኡድሒያውን እንስሳ ከቦ በመቆም ተክቢራ ማለት፣ሶለዋት ማውረድና ዱዓ ማድረግ።
ይህ ተግባር በዲናችን ላይ የተጨመረ፤ የመልዕተኛችንን( ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ሱና የሚፃረር ተግባር ነው።ይህን በመገንዘብ እራሳችንንም ይሁን ቤተሰባችንን ከዚህ ድርጊት መጠበቅ አለብን።
➌~ የኡድሒያው እንስሳ ወደ ቂብላ ሳይዞር ከታረደ አይበቃም ብሎ ማመን።
በምናርድበት ጊዜ የኡድሒያውን እንስሳ ወደ ቂብላ ማዞር የተወደደ ተግባር ነው።ይሁን እንጂ ከቂብላ አቅጣጫ ውጪ የታረደ ኡድሒያ ግን አይበቃም አይባልም።ወዴትም አቅጣጫ አዙሮ ይረደው ወደ አሏህ መቃረብ አስቦና የአሏህን ስም ብቻ አውስቶ እስካረደው ድረስ ኡድሒያው ትክክል ነው።
➍~ ከብትን ወይንም ግመልን በምንጋራበት ወቅት ከሰባት መብለጥ።
ይህ ሐዲስ ላይ የመጣውን የቁጥር ገደብ መተላለፍ ነውና እንዲህ አይነቱን ተግባር ከመፈፀም ልንቆጠብ ይገባል።
➎~ ከሶላት በፊት ማረድ።
ከዚህ በፊት እንዳየነው ኡድሒያ መታረድ ያለበት የዒድ ሶላት ከተሰገደ በኃላ ነው።ከዒድ ሶላት በፊት የታረደ ከሆነ ግን ኡድሒያ መሆን አይችልምና በድጋሚ ሌላ ማረድ ግዴታ ይሆናል።
➏~ ለአራጁ በክፍያ መልክ ከኡድሒያው ስጋ ቀንሶ ወይንም ቆዳውን መስጠት።
ይህ ተግባር ግልፅ በሆነ መልኩ በሐዲስ የተወገዘ ተግባር ነውና መከልከል ይኖርብናል።የኡድሒያው ምኑንም ቢሆን በሶደቃ መልኩ መለገስ እንጂ መሸጥ አይቻልም።አይደለም ስጋውን ቆዳውንም ቢሆን መሸጥ የተከለከለ ነው።ቆዳውን ማድረግ ያለብን የተቸገረ ሰው ፈልገን መስጠት ነው፤ በሶደቃ መልክ የሰጠነው አካል ግን ቆዳውን ሽጦ መጠቀም ይችላል።ለአራጁ መከፈል ያለበት ከኡድሒያው ውጪ የሆነ ነገር ነው።
➐~ ኡድሒያውን ለሶስት ከፍሎ አንድ ሶስተኛውን ጓደኞቻችንንና ወዳጆቻችንን ጠርተን ማብላት፤ አንድ ሶስተኛውን ሶደቃ ማድረግ፤ የተቀረውን ደሞ ለራሳችንንና ለቤተሰባችን መጠቀም የተወደደ ተግባር እንጂ ግዴታ አይደለም።ከዚህም አልፎ እንዲህ ካልተደረገ ኡድሒያው ትክክል አይደለም ማለት ከሸሪዓ አንፃር ምንም ማስረጃ ያለው ነገር አይደለም።ይልቁንስ ግዴታው ከኡድሒያው ስጋ ትንሽም ቢሆን ሶደቃ ማድረግ ነው። ምክንያቱም አሏህ እንዲህ በማለት አዞናልና ፦
"فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ"( سورة الحج)
ከርሷም ብሉ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ፡፡(አል—ሐጅ፤28)
➑~ ለሞቱ ቤተሰቦቻችን ለብቻቸው አጅሩ እንዲደርሳቸው በማሰብ እራሱን የቻለ ኡድሒያ አዘጋጅቶ ማረድ።
ይህ ተግባር በሸሪዓችን ምንም መሰረት የለውም።ምክንያቱም መልዕክተኛችን ( ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም) በሕይወት እያሉ የሞቱባቸው ልጆችም ይሁኑ ሚስት ነበሩ።ነገር ግን ለአንዳቸውም ቢሆን ለይተው ለብቻቸው ኡድሒያ አዘጋጅተው ያረዱበት አጋጣሚ የለም።ስለዚህ እርሳቸው ያልሰሩትን ሰርቶ ወደ አሏህ መቃረብ መፈለግ ጥሜት ነውና እንጠንቀቅ።ነገር ግን ኡድሒያ ስናርድ አጅሩ በሕይወት ላሉትም እንዲሁም ለሞቱት ቤተሰቦቻችን አጅሩ እንዲደርስ ነይተን ማረዱ ችግር የለውም። የተወገዘው ለሞቱ ሰዎች ለብቻቸው ኡድሒያ አዘጋጅቶ ማረዱ ነው።
➒~ እራሳቸውን ችለው ለብቻቸው የሚኖሩ ልጆች ለራሳቸው ማረድ ይጠበቅባቸዋል።ወላጆቻቸው የሚያርዱት የሚሆነው ለራሳቸውና አብረዋቸው ለሚኖሩ ልጆቻቸው ነው።
➓~ ኡድሒያን ለማረድ የግድ አስሩን ቀን መፆም ያስፈልጋል ብሎ ማመን።
ይህ ስህተት ነው።አስሩን ቀን መፆም የተወደደ ተግባር እንጂ ግዴታ አይደለም።ስለዚህ ያልፆመም ሰው ቢያርድ ኡድሒያው ላይ ምንም ችግር አያመጣም።ምክንያቱም ሁለቱም እራሳቸውን የቻሉ የተለያዩ ዒባዳዎች ናቸውና።
➊➊~ ሶላት የማይሰግድ ሰውን ማሳረድ።
ሶላት የማይሰግድን ሰው አስመልክቶ አመዛኙና ከመረጃ አንፃር ግልፅና ጠንካራው አቋም ካፊር ነው የሚሉ ዑለሞች አቋም ነው።በዚህም መሰረት የማይሰግድ ሰው ቢያርደው ኡድሒያው ትክክል አይሆንም፤ ከሱም መብላት አይፈቀድም።
➊➋~ በዱልዱም ቢላ በማረድ ፤ እንስሳው አጠገብ ቢላችንን በመሳል እንስሳውን ማሰቃየት።
ይህ ድርጊት የመልዕተኛችን ( ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ትዕዛዝ የሚፃረር ተግባር ነውና መተው ይኖርብናል።ለማረድ ስንመጣ ቢላችንን አስቀድመን ስለን ነው መምጣት ያለብን።
"አንዳቹ ማረድ በፈለገ ሰኣት ቢላውን ይሳል ፤ እንስሳውንም ቶሎ ያሳርፍ "የሚለውን የመልዕተኛችንን ( ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ትዕዛዝ አንዘንጋ።
➊➌~ ሴት ልጅ ማረድ አትችልም ብሎ ማመን።
ይህ እምነት በሸሪዓችን ምንም መሰረት የለውም።አስተካክሎ ማረድ እስከቻለ ድረስ ወንድም ይሁን ሴት ቢያርደው ምንም ችግር የለውም።አስተካክሎ ማረድ የማይችል ከሆነ ግን ወንድም ይሁን ሴት ማረድ የለባቸውም።
➊➍~ ኡድሒያን ማረድ ዒባዳ መሆኑን መዘንጋት።
ስራዎች የሚለኩት በንያቸው ነውና ኡድሒያን ስናርድ ትልቅ አምልኮ መሆኑን በማሰብና የሚገኘውን አጅር ከአሏህ በመከጀል መሆን ይጠበቅበታል።ይህን ሳናደርግ ቀርተን እንዲው ዝም ብለን ለዒድ አል— አድሃ በኣል ማረድ የተለመደ ስለሆነ ብቻ የምናርድ ከሆነ እርዳችን ከዒባዳነት ወደ ዓዳነት ይቀየራል።ይህ ከሆነ ደሞ የኡድሒያውን አጅር አናገኝም ማለት ነው።ስለዚህ መጠንቀቅ አለብን።
~ والله تعلى أعلم بالصواب وإليه المرجع والمئاب ~
~~~~ ታላቁ የዓረፋ እለት~~ ~~
የዓረፋ እለት የሚባለው ከዙልሒጃ ወር ዘጠነኛው እለት እንዲሁም ሑጃጆች በዓረፋ ሜዳ ላይ ተገኝተው ትልቁን የሐጅ ሩክን የሚፈፅሙበት ቀን ሲሆን ፦
➊~ ይህ ዲን የተሟላና ምንም የሚጎድለው ነገር የሌለው መሆኑን፤ አዲስ ነገርን መፍጠር እንደማያስፈልግ የምትገልፀው፤አይሁዶች የቀኑባትና ለእኛ ሙስሊሞች ደሞ የዐይን ማረፊያችን የሆነችው፤ እንዲሁም እያንዳንዱን ሙብተዲዕ አንገት የምታስደፋዋ የቁርኣን አንቀፅ የወረደችበት እለት ነው።ይህችም አንቀፅ እንዲህ የምትለዋ አንቀፅ ናት ፦
"الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا ۚ "
ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡
ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡ 【አል-ማኢዳህ ፣3】
➋~ የዓረፋን ቀን መፆሙ ያለፈውን አንድ አመትና የሚመጣውን አንድ አመት ወንጀል እንደሚያስምር በሶሒሕ ሐዲስ የተነገረለት ታላቅ ቀን ነው።የዓረፋን ቀን መፆም ያለውን አጅር አስመልክቶ ሲጠየቁ መልዕክተኛችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" ﻳﻜﻔﺮ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﺍﻟﻤﺎﺿﻴﺔ ﻭﺍﻟﺴﻨﺔ ﺍﻟﻘﺎﺑﻠﺔ" ( ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ)
"የዓረፋን እለት መፆም ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል"【ሙስሊም ዘግበውታል】
እራሳችንንም ወዳጅ ዘመዶቻንንም ይህን ቀን በመፆም አደራ አደራ ልንል ይገባል።
➌~ በዓረፋ እለት የሚደረግ ዱዓ ከየትኛውም እለት ዱዓ ይበልጣል።ይህንን አስመልክቶ ነብያችን ﷺ ተከታዩን ብለዋል፦
"ﺧﻴﺮ ﺍﻟﺪﻋﺎﺀ ﺩﻋﺎﺀ ﻳﻮﻡ ﻋﺮﻓﺔ " ﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﻓﻲ ﻛﺘﺎﺑﻪ ﺍﻟﺴﻠﺴﺔ ﺍﻟﺼﺤﻴﺤﺔ
"ከዱዓዎቹ ሁሉ በላጩ የዓረፋ እለት ዱዓ ነው"【አስሲልሲለቱ አስሶሒሓህ】
ስለዚህ ሐጃዎቻችን በርካታ ናቸውና እለቱን እጃችንን ወደላይ በማንሳት አዛኙ ጌታችንን በመተናነስ መለመን በማብዛት ልናሳልፈው ይገባል።
➍~ አሏህ ለሐጅ ስነስረዓት ዓረፋ ሜዳ ላይ የተገኙ ሰዎች " አቧራ የለበሱ፤ፀጉራቸው የተንጨባረረ ሲሆን እኔን ለማምለክ መጡ" በማለት በመላኢኮች ላይ የሚፎክርበት እለት ነው።ይህን አስመልክቶ ሐዲስ ላይ እንዲህ የሚል ዘገባ እናገኛለን
"ﺇﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﻳﺒﺎﻫﻲ ﺑﺄﻫﻞ ﻋﺮﻓﺎﺕ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﺴﻤﺎﺀ" ( ﺭﻭﺍﻩ ﺃﺣﻤﺪ)
"አሏህ በዓረፋ ሰዎች የሰማይ ነዋሪዎችን( መላኢኮችን) ይፎካከራል"【ኢማሙ አሕመድ ዘግበውታል】
➎~ ከየትኛውም ቀን በበለጠ አሏህ በርካታ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያደርግበት እለት ነው።ይህን አስመልክተው የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፦
"ﻣﺎ ﻣﻦ ﻳﻮﻡ ﺃﻛﺜﺮ ﻣﻦ ﺃﻥ ﻳﻌﺘﻖ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻴﻪ ﻋﺒﺪﺍ ﻣﻦ ﺍﻟﻨﺎﺭ ﻣﻦ ﻳﻮﻡ ﻋﺮﻓﺔ" (ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ)
"ከዓረፋ እለት የበለጠ አሏህ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚደርግበት ቀን የለም።" 【ሙስሊም ዘግበውታል】
እናም በዚህ እለት እኛንም ሌሎች ሙስሊሞችንም መቀጣጠያዋ የሰው ልጅና ድንጋይ ከሆነችው የጀሃነም እሳት ነፃ እንዲያደርገን በአፅንኦት ዱዓ ልናደርግ ይገባል።
➏~ ሐጅ የሚያደርጉ ሰዎች በዓረፋ ሜዳ ላይ ቆመው ከሐጅ ማእዘናት መካከል ትልቁ የሆነውን ዓረፋ ሜዳ ላይ ቆሞ የተለያዩ ዒባዳዎችን መፈፀምን የሚያከናዉኑበት የተከበረ ቀን ነው።ይህን አስመልክተው የአሏህ መልዕተኛﷺ እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል ፦
"ﺍﻟﺤﺞ ﻋﺮﻓﺔ " (ﻣﺘﻔﻖ ﻋﻠﻴﻪ)
"ሐጅ ማለት ዓረፋ ነው"
【ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል】
ይህ አገላለፅ በዙልሒጃ ዘጠነኛው እለት የዓረፋ ሜዳ ላይ ተገኝቶ ከጥዋት ጀምሮ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ የተለያዩ ዒባዳዎችን በመፈፀም ያላሳለፈ ሰው ሐጅ እንደሌለውና ይህንን ማድረግ ከሐጅ ማእዘናት መካከል ትልቁ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
➐~ የዓረፋ እለት 'ተክቢራ ሙቀይየድ'( ከፈርድ ሶላቶች በኃላ የሚደረገው ተክቢራ) የሚጀምርበት እለት ነው።ከዓረፋ እለት ሱብሒ ሶላት ጀምሮ እስከ ዙልሒጃ አስራ ሶስተኛው እለት አስር ሶላት ድረስ ተክቢራ ሙቀይየድን እንላለን።
ይህ የተከበረ ቀን ዘንድሮ የሚውለው ነገ ቅዳሜ ( ሰኔ 8 ) ነውና ከዛሬዋ እለት ጀምሮ እራሳችንንና ሌሎችንም በማስታወስ ለዚህ ታላቅ ቀን እንዘጋጅ።
አሏህ በሰላም ያድርሰን፤የምንጠቀምበትም ያድረገን ‼‼
~~~ والله تعلى أعلم بالصواب وإليه المرجع والمئاب~~ ~
ዛሬ የኡድሒያውን እንስሳ ስትገዙ በሸሪዓዊው መስፈርት መሰረት እየመረጣቹ ግዙ!!
ኡድሒያና መስፈርቶቹ ‼‼
✔ኡድሒያ ማለት አንድ ሙስሊም የሆነ አካል ወደ አሏህ መቃረብን በማሰብ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ከቤት እንስሳት( ግመል፣ከብት፣በግ ፍየል) የሚያርደው እርድ ማለት ነው።
✔ "የኡድሒያ ሸሪዓዊ ብይን አስመልክቶ የኢስላም ምሁራን የተለያየ አመለካከት ቢኖራቸውም አቅሙ ላለው ሰው ኡድሒያን ማረድ ግዴታ ነው የሚለው አካሄድ በጣም ጠንካራ ነው።" ኢብኑ ኡሰይሚን (ረሒመሁሏሁ ተዓላ) ሸርሑ ሙምቲዕ(7:479) [ከትንሽዬ ማሻሻያ ጋር]
፠ ኡድሒያ ዒባዳ እንደመሆኑ መጠን ትክክል ይሆን ዘንድ ማሟላት ያለበት መስፈርቶች አሉ።ዒባዳ የተባሉ ነገሮች ሁሉ ሊያሟሏቸው ከሚገቡ የጋራ መስፈርቶች( ሙስሊም መሆን፣ኒያ፣ ኢኽላስ.......) በተጨማሪ ኡድሒያ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል። እነሱም ፦
➊~ ባለቤትነት
የምናርደው እንስሳ በሸሪዓዊ መንገድ የራሳችን ያደረግነው መሆን አለበት።የተሰረቀና ከሸሪዓ በሚጣረሱ መንገዶች የራሳችን ያደረግነውን እንስሳ ማረድ አይበቃም።መልዕክተኛችን( አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) እንዲህ ይላሉ
( ﺇﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻃَﻴِّﺐٌ ﻻ ﻳَﻘْﺒَﻞُ ﺇﻟَّﺎ ﻃَﻴِّﺒًﺎ )
"አሏህ ጥሩ ነው፤ ከስራዎችም ጥሩውን እንጂ አይቀበልም።"
➋~የሚታረደው እንስሳ በሸሪዓችን ለኡድሒያነት ከተመረጡት እንስሶች መሆን አለበት።እነሱም፦
ግመል፣ ከብት ፣በግ ፣ ፍየል
ከነዚህ ውጪ ያሉትን ማረድ ለኡድሒያነት አይበቃም።ነገር ግን ለስጋ አምሮት ብሎ አርዶ ቢበላ ምንም ከልካይ ነገር የለም።
➌~የሚታረደው እንስሳ የሚፈለገውን የእድሜ ክልል የደረሰ መሆን አለበት።ማለትም
~ ግመል ከሆነ አምስት አመትና ከዛ በላይ
~ ከብት ከሆነ ሁለት አመትና ከዛ በላይ
~ ፍየል ከሆነ አንድ አመትና ከዛ በላይ
~ በግ ከሆነ ስድስት ወርና ከዛ በላይ
መሆን ይጠበቅባቸዋል።
➍~ እንስሶቹ ለኡድሒያነት ብቁ ከመሆን ከሚከለክሉ ጉድለቶች የፀዱ መሆን አለባቸው።እነዚህም በሐዲስ ላይ እንደመጡት
~ ግልፅ የሆነ የሚያስታውቅ በሽታ፦ በነፃነት እንዳይንቀሳወሱ፣እንዳይበሉ የሚያግዳቸው በሽታ ያለባቸው መሆን የለባቸውም።
~ በጣም ከሲታ መሆን የለባቸውም።
~ አይናቸው በሚያስታውቅ መልኩ የተጎዳ ወይም የጠፋ መሆን የለበትም።
~ እግራቸው በሚያስታውቅ መልኩ የተጣመመ ወይም የተሰበረ መሆን የለበትም።
★ከላይ ከተጠቀሱት ጉድለቶች አንዱ ከተገኘ ኡድሒያው ትክክል አይሆንም።ስለዚህ ለኡድሒያ የምንገዛው እንስሳ ከላይ ከተጠቀሱትና ከነሱ የባሱ ከሆኑ ጉድለቶች የፀዳ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል።ነገር ግን ቀለል ያሉ ጉድለቶች ከሆኑ ኡድሒያውን ብቁ ከመሆን አያግዱትም።ለምሳሌ ቀንዱ የተሰበረ ቢሆን ይህ የተጠላ ይሆናል እንጂ ኡድሒያው አይበቃም አይባልም።
✂ እናም ወንድሜ ገና ሲታይ አለው‼ አለው‼የሚል ግርማ ሞገስ‼‼ ያለውን እንስሳ ገዝተህ በማረድ በዚህ ትልቅ ዒባዳ ወደ አሏህ ተቃረብ።
➎~ ኡድሒያው በሸሪዓው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መታረድ አለበት።
ይህም የዒድ ሶላት ከተሰገደበት ጊዜ ጀምሮ ከዒዱ ቀን ቀጥለው ባሉት ተከታታይ ሶስት ቀናት ውስጥ መሆን አለበት።ከዚህ የጊዜ ገደብ ውጪ ከታረደ ኡድሒያ መሆን አይችልም።
➏~ በግና ፍየል ከሆነ ለአንድ ሰው ብቻ ነው መታረድ ያለበት። መጋራት የፈለገ ሰው ከብትና ግመልን ለሰባት ወይም ከዛ በታች የሆኑ ሰዎች መጋራት ይችላሉ።ከብትና ግመልን ስንጋራ ግን ቁጥራችን ከሰባት መብለጥ የለበትም። አንዳንድ ጊዜ ከብት ዋጋው ሲወደድ ቁጥሩ ከሰባት ቢበልጥ ችግር የለውም የሚሉ ጥራዝ ነጠቅ ፈትዋዎችን ወደ ጎን መተው አለብን።ከብት ከተወደደ ዋጋው የሚቀንሰውን በአቅማችን ልክ ገዝተን የቁጥር ገደቡን መጠበቅ ይኖርብናል።
والله أعلم بالصواب وإليه المرجع والمئاب
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago