Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

Description
ሽ ራ ፊ : ቃ ላ ት

ስ ባ ሪ ፡ ተ ረ ኮ ች

@Samvocado


https://linktr.ee/samueldereje
Advertising
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 2 days, 12 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 2 days, 20 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago

3 weeks, 2 days ago
2 months ago

አይመስልም አዉቃለሁ።  አካሌ አካልሽን ከቀናት በላይ አያዉቀዉም።
እፍኝ ቀናት እንጂ  ወራት አልተቃቀፍንም።  በእቅፌ ከነበርሽበት ሄደሽ የናፍኩሽ ቀናት ይረዝማል። ግን ልብ ይሄን መች ግድ ይላል። አይምሮ እንጂ . . . 

አልተዉኩሽም! ግን  ታግያለሁ። ደሞም መስሎኝ ነበር!  መሰለኝ እንጂ አልሆነም። እዛዉ እዛዉ እንደሚያገረሽ ስቅታ ናፍቆትሽ ሄደ ስለዉ እየመጣ ችላ ልለዉ ከበደኝ።

ናፍቆት ስቅታ ሆኖ ልገላገል ስምሽን ስጠራ ብዉል ወይ ስቅታሽ አልተወኝ ወይ ስምሽን አልተዉኩ። ይኀዉ ልቤን ደግፌ አለሁ . . .

@samuel_dereje

2 months, 1 week ago

- `የእኔና እሷ ነገር  -
       - ፩ -

ተረት ካልሆነ የአዋቂ "ብልጥ ልጅ" የለም። ማንም ጥሎ እንጂ የያዘዉን ይዞ አያለቅስም።  የሰዉ ልጅ አሳሽ ነዉ። የሚሻል ያሳዳል። ሌላ እንደሚገባዉ ያመነ እለት የጨበጠዉን ይለቃል። 

ያላመንኩት አንድ ነገር።
ስትሄድ ፥ ግራ ገብቷት አይደለም! ይሻልን አሽታ ነበር። 

ያላመንኩት ሌላ ነገር።
ያኔ . . . ልወዳት ጀምሬ ነበር።`

@samuel_dereje

3 months ago
3 months, 1 week ago

`ታዉቂያለሽ?

ሲዘንብ እንደምትናፍቂኝ ፥  ሲያካፋ እንደምራብሽ?  መሬት ሲርስ ከንፈርሽን እንደምጠማ ፥ ጣሪያ ሲጮህ ጎጆዬ ዝም እንደሚዉጠዉ? 

ታምኛለሽ?  ከጋቢ ትዝታሽ እንደሚሞቀኝ ፥ ከጸሃይ ድምጽሽ እንደሚያደምቀኝ?  ባቅፍሽ ደመናዉ እንደሚተን ፥ ብስምሽ ዳግም ጸደይ ፥  ዳግም በጋ እንደሚሆን?

ልንገርሽ? በበጋዉ ካፍያ ገና ለሚመጣዉ ክረምቱ እንደፍራሁ? ሰማይ ሳምንት ቢጠቁር አካሌ የአመት እንደቆፈ ፥  አይኔ መንፈቅ እንዳነባ? 

እናማ  . . . ሲዘንም ፈራለሁ። 
ብዙ ፍቅር ፥  ብዙ እዉነቴ ሳይገባሽ እንደ ጸሃይ
ደመናዉ ይጋርድሽ ይሆን እላለሁ።`@samuel_dereje

4 months ago

ደስታ! ከረሜላ ብቻ አይደለም።

"ልጅ ሆኜ የሆነ ቀን ደስታ ከርሜላ ገዛሁ።  እንደልጅነቴ የኔ በሆነዉ ከረሜላ ያለቅጥ ደስ ብሎኝ ነበር . . ."

ሳዉቃት ልጅ ሆኜ ነዉ። አብሮ አድጌ ነበረች።  ቤቴ ቤቷ አጠገብ ፥ እናቴ የእናቷ ወዳጅ ነበሩ። አብሮ የተሰፋ ልጅነት አለን። ብዙ የሱዚ ገመዶች ቀምቼያት አልቅሳለች ፥ ብዙ  የዉሸት "መታኝ"ኞች ለእናቴ አቃጥራ ተገርፊያለሁ። 

ሰኞ ፥ ማክሰኞ ስትዘል የተደበቀ ፥ ጠጠር ስትለቅም ያልታየኝ ፥ አኩኩሉ ስትል ያልጎላ  ጡት አጎጥጉጣ  አይን ስትገባ  በለስ እንደበላ አዳም ዉበቷ ለአይኔ ተገለጠ።  ( ለእኔ ብቻ አይደለም - ለሃገሩም)

እንደሌላ ቁንጅናዋን ፥ ሴትነቷን ብቻ ሳይሆን ሳቋን ፥ እንባዋን እንዳየ። ሥሥ ጎኗን እንደፈተሸ ( በልጅ ልብም ቢሆን)።  ልጅ ሳለን በልፊያ ከፍም ካልን በጥልቅ ወሬ  ልብ ምቷን እንደመዘነ ፥ ቀድሞ ከንፈሮቿን እንደቀመሰ ፥ በሄደችበት እንዳጀበ  (በዚህ በእኩዮቼ ቢቀለድብኝም) ፥ ከእናት ከአባቷ በፊት ተጠሪዋ እንደሚባል አንድ ሰዉ ፤ ልመስክር። አመሏ ከመልኳ ይረቃል ። ከገጿ እኩል ግብሯ ያምራል። 

ላይወዷት ትከብዳለች!

፪ 

" ከረሜላዬ በእጄ እንዳለች ልጣጯን ብዙ ጊዜ ፈትቼ ብዙ ጊዜ አስሬያታለሁ። ልበላት አልቸኮልኩም! የኔ አይደለች?"

"የምኞት አስኳል አለመጨበጡ ነዉ ፤ ሰዉ ለያዘዉ አይጓጓዋም?" ይሉት ፍልስፍና አለ።*  እዉነት ይመስላል። ግን አንዳንዴ የጨበጡትም ያጓጓል። አንዳንዴ!

እናም ባደግን ቁጥር መላመዳችን ጎላ! ሳቋ የቀን ማጀብያዬ ሆነ። እቅፏን ብቻ ሳይሆን ኩርፊያዋን እናፍቅ ነበር። አብረን ዉለን ሲመሽ መግቢያችን ያባባናል። እልፍ ጊዜ ቻዉ እያለች ዳግም ከንፈሮቿ ወይ በወሬ ወይ በእኔ ከንፈር ይጠመዳሉ። ሰባ ጊዜ ቻዉ ብላኝ በሰባኛዉ ትሄዳለች። እያመናታች። የሸኘኋትን ልጅ እያናፈኩ ቤቴ እገባለሁ።  

የሆነ የሆነ ቀን የምናወራዉ የለንም። ጋደም ባልችበት ወደ ደረቷ እጠጋና ልብ ምቷን እሰማለሁ። የረጋ ፥ ጊዜ የጠበቀ ነዉ። ወደ ከንፈሯ ስጠጋ ግን ይፈጥናል። ስስማት ከልጅ ልቧ እኩል ትንፋሿ ይፈጥናል። ረግረግ ነበረች። የሆነ እድሜዬ ስሯ ሰርጓል። 

በዚህ ሁሉ ግለታችን ዉስጥ ጭኗን ከፍቼ አላውቅም። የሆነ የሆነ ቀን በእጄ የታፋዎቿን ግለት ለክቻለሁ። አልክድም! ግለቱ ይጋባ ነበር። ግን ቃሏ ይቆይ ስለነበር መሻቷን አልገፋሁም። ገና ዘመናት አብረን አይደለን?።

"የኔ ናት!" ፥ እንደዛ ብዬ ነበር።

"ጉጉቴ ሥሥቴን ሲያሸንፍ  የከረሜላዬን ልጣጭ በእርጋታ ገፍፌ ወደ አፌ ልከት ሳስጠጋ  ከእጄ ወድቃ እግሬ ስር  ያለ አፍር ላይ ወደቀች።  ላነሳት ያየኝ መኖሩን ልቃኝ ቀና ስል ከእናቴ ጋር ተያየን።
 " በል አንሳና ጣል"  ትዛዝ ነበር።

ከነሥሥቴ ሳላጣጥማት ሄደች - ከረሜላዬ! "

እድል ፍትህ የላትም። ተስፋ ከጤዛ ያጥራል። ሰዉ ስለፈልገ ብቻ አያገኝም። ሰዉ ስላልጠየቀም አያጣም። ይጠማል ፥ ሲለዉ ሳይደግስም ይጣላል።

እንዲህ ሆነ . . . አደገች ፥ አደኩ። ለዉጥ አሻች። እንደትናንት  በመሳም ልቧ አይመታ ፥  ከሆዷ መሳቅ ተወች።  ሁሉ ቀልድ ለዘዘባት ፥ ወሬችን ወደ ቅጽበቶች አጠረ።  መጣበቃችን ላላ። እኔ እና እሷ እንዳልነበርን። በወራት እኔ እሷን እና ብዙ ወንዶች ሆንን። 

በጊዜ እንደሸረሪቷ ቀስ በቀስ ሸረተት እያልን ከእኔ እጅ እሷ ፥ ከእሷ ልብ እኔ ሾለክን።

የሆነ እለት ምን ጆሮ ለባልቤቱ ባዳ ነዉ ቢሉ ከርሞም ቢሆን ሰማሁት። "ይቆይን ለሌላ እንዳላለች። ብዙ አንዳቀፈች ፥ ብዙ እንዳላበች። ዝግ ጭኗ ፥ ዛሬ መንገድ እንደሆነ።" እና ሌላም ያመመኝ ብዙ ነገር . . 

ግን ምስክር ነኝ።  ሰናይ እንደነበረች። ጸደይ ነፍስ እንደነበራት!

ከእሷ ወዲህ "መልክ ይረግፋል። አመል እንጂ ዉበት አላፊ ነዉ" ሲባል ሳቅ ያፍነኛል። የቱ ፈላስፋ ነዉ የአመልን ዘላለማዊነት የሰበከን?  የቱ አዋቂ ይሆን ጸባይን ከመልክ በላይ ያነገሰዉ? መልክም ፥ ጸባይም አላፊ ነዉ።  ጊዜ አይለዉጠዉ የለም። 

"ትወደኝ ነበር!"  ነበር እንኳ ይለወጣል።

.

@samuel_dereje

4 months, 3 weeks ago
5 months ago
5 months, 1 week ago
ዥ ን ጉ ር ጉ ር …
5 months, 2 weeks ago
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 2 days, 12 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 2 days, 20 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago