ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

Description
ሽ ራ ፊ : ቃ ላ ት

ስ ባ ሪ ፡ ተ ረ ኮ ች

😊 - @Samvocado




https://linktr.ee/samueldereje
We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 2 weeks, 6 days ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 2 months, 1 week ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 2 months, 2 weeks ago

4 weeks ago

“Believe me, I know what it's like to feel all alone... the worst kind of loneliness in the world is isolation that comes from being misunderstood, it can make people lose their grasp on reality." ― Dan Brown, Inferno

And I wish you also knew this state of isolation. Sadly you don't. Or maybe that's good? But you won't ever be able to get too close. You'll always be on the periphery. I wish I could share more today.

I wish I could tell you more. Why I'm the way I'm. Why I say the things I say. And above all where all the anger & resentment comes from. I wish I could spell it out for you. The damages of the past became the builders of tomorrow's misery.

Someone else did the harm and someone else has to pay for it. How is that even fair you asked me? And I obviously had no answer. The silence between us is not due to lack of conversation. This silence has my screams in every fold.

I wish you could hear that. I wish you knew. My reality has now become your misery.

I'm now your inferno.

I'm extremely sorry.

Because I have a lot of unfulfilled wishes.

And Sorry about that...

Photo: Sosina Mengistu

1 month ago

ደስታ! ከረሜላ ብቻ አይደለም።

"ልጅ ሆኜ የሆነ ቀን ደስታ ከርሜላ ገዛሁ።  እንደልጅነቴ የኔ በሆነዉ ከረሜላ ያለቅጥ ደስ ብሎኝ ነበር . . ."

ሳዉቃት ልጅ ሆኜ ነዉ። አብሮ አድጌ ነበረች።  ቤቴ ቤቷ አጠገብ ፥ እናቴ የእናቷ ወዳጅ ነበሩ። አብሮ የተሰፋ ልጅነት አለን። ብዙ የሱዚ ገመዶች ቀምቼያት አልቅሳለች ፥ ብዙ  የዉሸት "መታኝ"ኞች ለእናቴ አቃጥራ ተገርፊያለሁ። 

ሰኞ ፥ ማክሰኞ ስትዘል የተደበቀ ፥ ጠጠር ስትለቅም ያልታየኝ ፥ አኩኩሉ ስትል ያልጎላ  ጡት አጎጥጉጣ  አይን ስትገባ  በለስ እንደበላ አዳም ዉበቷ ለአይኔ ተገለጠ።  ( ለእኔ ብቻ አይደለም - ለሃገሩም)

እንደሌላ ቁንጅናዋን ፥ ሴትነቷን ብቻ ሳይሆን ሳቋን ፥ እንባዋን እንዳየ። ሥሥ ጎኗን እንደፈተሸ ( በልጅ ልብም ቢሆን)።  ልጅ ሳለን በልፊያ ከፍም ካልን በጥልቅ ወሬ  ልብ ምቷን እንደመዘነ ፥ ቀድሞ ከንፈሮቿን እንደቀመሰ ፥ በሄደችበት እንዳጀበ  (በዚህ በእኩዮቼ ቢቀለድብኝም) ፥ ከእናት ከአባቷ በፊት ተጠሪዋ እንደሚባል አንድ ሰዉ ፤ ልመስክር። አመሏ ከመልኳ ይረቃል ። ከገጿ እኩል ግብሯ ያምራል። 

ላይወዷት ትከብዳለች!

፪ 

" ከረሜላዬ በእጄ እንዳለች ልጣጯን ብዙ ጊዜ ፈትቼ ብዙ ጊዜ አስሬያታለሁ። ልበላት አልቸኮልኩም! የኔ አይደለች?"

"የምኞት አስኳል አለመጨበጡ ነዉ ፤ ሰዉ ለያዘዉ አይጓጓዋም?" ይሉት ፍልስፍና አለ።*  እዉነት ይመስላል። ግን አንዳንዴ የጨበጡትም ያጓጓል። አንዳንዴ!

እናም ባደግን ቁጥር መላመዳችን ጎላ! ሳቋ የቀን ማጀብያዬ ሆነ። እቅፏን ብቻ ሳይሆን ኩርፊያዋን እናፍቅ ነበር። አብረን ዉለን ሲመሽ መግቢያችን ያባባናል። እልፍ ጊዜ ቻዉ እያለች ዳግም ከንፈሮቿ ወይ በወሬ ወይ በእኔ ከንፈር ይጠመዳሉ። ሰባ ጊዜ ቻዉ ብላኝ በሰባኛዉ ትሄዳለች። እያመናታች። የሸኘኋትን ልጅ እያናፈኩ ቤቴ እገባለሁ።  

የሆነ የሆነ ቀን የምናወራዉ የለንም። ጋደም ባልችበት ወደ ደረቷ እጠጋና ልብ ምቷን እሰማለሁ። የረጋ ፥ ጊዜ የጠበቀ ነዉ። ወደ ከንፈሯ ስጠጋ ግን ይፈጥናል። ስስማት ከልጅ ልቧ እኩል ትንፋሿ ይፈጥናል። ረግረግ ነበረች። የሆነ እድሜዬ ስሯ ሰርጓል። 

በዚህ ሁሉ ግለታችን ዉስጥ ጭኗን ከፍቼ አላውቅም። የሆነ የሆነ ቀን በእጄ የታፋዎቿን ግለት ለክቻለሁ። አልክድም! ግለቱ ይጋባ ነበር። ግን ቃሏ ይቆይ ስለነበር መሻቷን አልገፋሁም። ገና ዘመናት አብረን አይደለን?።

"የኔ ናት!" ፥ እንደዛ ብዬ ነበር።

"ጉጉቴ ሥሥቴን ሲያሸንፍ  የከረሜላዬን ልጣጭ በእርጋታ ገፍፌ ወደ አፌ ልከት ሳስጠጋ  ከእጄ ወድቃ እግሬ ስር  ያለ አፍር ላይ ወደቀች።  ላነሳት ያየኝ መኖሩን ልቃኝ ቀና ስል ከእናቴ ጋር ተያየን።
 " በል አንሳና ጣል"  ትዛዝ ነበር።

ከነሥሥቴ ሳላጣጥማት ሄደች - ከረሜላዬ! "

እድል ፍትህ የላትም። ተስፋ ከጤዛ ያጥራል። ሰዉ ስለፈልገ ብቻ አያገኝም። ሰዉ ስላልጠየቀም አያጣም። ይጠማል ፥ ሲለዉ ሳይደግስም ይጣላል።

እንዲህ ሆነ . . . አደገች ፥ አደኩ። ለዉጥ አሻች። እንደትናንት  በመሳም ልቧ አይመታ ፥  ከሆዷ መሳቅ ተወች።  ሁሉ ቀልድ ለዘዘባት ፥ ወሬችን ወደ ቅጽበቶች አጠረ።  መጣበቃችን ላላ። እኔ እና እሷ እንዳልነበርን። በወራት እኔ እሷን እና ብዙ ወንዶች ሆንን። 

በጊዜ እንደሸረሪቷ ቀስ በቀስ ሸረተት እያልን ከእኔ እጅ እሷ ፥ ከእሷ ልብ እኔ ሾለክን።

የሆነ እለት ምን ጆሮ ለባልቤቱ ባዳ ነዉ ቢሉ ከርሞም ቢሆን ሰማሁት። "ይቆይን ለሌላ እንዳላለች። ብዙ አንዳቀፈች ፥ ብዙ እንዳላበች። ዝግ ጭኗ ፥ ዛሬ መንገድ እንደሆነ።" እና ሌላም ያመመኝ ብዙ ነገር . . 

ግን ምስክር ነኝ።  ሰናይ እንደነበረች። ጸደይ ነፍስ እንደነበራት!

ከእሷ ወዲህ "መልክ ይረግፋል። አመል እንጂ ዉበት አላፊ ነዉ" ሲባል ሳቅ ያፍነኛል። የቱ ፈላስፋ ነዉ የአመልን ዘላለማዊነት የሰበከን?  የቱ አዋቂ ይሆን ጸባይን ከመልክ በላይ ያነገሰዉ? መልክም ፥ ጸባይም አላፊ ነዉ።  ጊዜ አይለዉጠዉ የለም። 

"ትወደኝ ነበር!"  ነበር እንኳ ይለወጣል።

.

@samuel_dereje

1 month, 2 weeks ago

ከዝቅ ይልቅ ፣ ከፍ ያድጣል። ማጣት ከወሰደዉ ምቾት የነጠቀዉ ይበልጣል።  

ሃገሬዉ " ችግር ነዉ ጌትነት ካላወቁበት" እንዲል!

@samuel_dereje

4 months ago

ከጊዜ በላይ መድሃኒት የለም ቢሉ ሰዉ የሌለበት ጊዜ ከምን ያድነኝ ነበር? ከዋግምት ይልቅ ሰዉ ህመም ይነቅላል። ከኮሶ የልብ ወግ ሆድ ያጥባል። የልጅነትን ምች ከዳማከሴ ይልቅ በወዳጅ ፍቅር ይታሻል። 

ቂሜን እንደክረምት አፈር ፥ ጨዋታ ሸርሽሮታል። ሳላዉቀዉ ጓደኞቼ ያጠቡት ህመም ነበር ። ሃዘኔን እንደቅርፊት አብሮ መሳቅ ልጦልኛል።  

ወዳጅ ትልቅ ጸበል ነዉ። ላመነ — የማያባረዉ ጋኔል ፥ የማያስወጣዉ ዛር የለም።

.

.

@samuel_dereje

4 months, 1 week ago

*ከለት እለት አንድ የአዲስ ትዉስታ ይፋቃል። አዲስ አበባን አዲስ ያረጓትን ህብር ማንነቶች የሰሩ ዉህድ ልጆቿ ፤ በልማት እጅ እንደጥሬ እየታፈሱ የትም ይበተናሉ። መሃል ለእነሱ ክልክል ሆኗል። በገንዘብ ሳይሆን በመደጋገፍ ካሳም የቆሙ እልፍ ረዳት አልባዎቿ ከጃጁበት ደጃፍ፥ ከቆረቡበት ደብር በአንድ ሌሊት ወና የከተማ ዳር ላይ ይተዋሉ። በዳር ከተማ — በዳሁበት ሰፍር ችምችም ዉስጥ እንደመቆም ቀላል አይደለም።

ስለትናንት ዛሬን በእግዜር ማለት ቅንጦት ነው። ለዉጥ አይቀሬ ነዉ። ግን እንደእህል የትም ለሚበተኑ የዘመናት የልጆቿ ትስስር ላፍታ የሚያስብ ቢኖር እወድ ነበር።

ክረምቶቿን በትቦዎቿ የተንቦራጨቁ ፣ አፈሮቿን ለብይ ጉድጓድ የቆፈሩ ፣ ቡሄዋን ፣ አበባዮሿዋን በየበሮቿ የጨፈሩ  ልጆቿ ቢመሯት እወድ ነበር።

...ሌላም ብዙ አዲስ "ሀ" አስብላኝ ሳዉቃት የወዳድኳትን  "ኢትዮጵያን" እናፍቅ ነበር።

ግን - በማንነት በላቆጠ ፖለቲካ ቅርቃር  ዉስጥ በነጋ ቁጥር ህይወት የሚጠልቅባትን ሃገር እያየሁ - ነገ መኖራችንንም እጠራጠራለሁ።*

.

@samuel_dereje

4 months, 1 week ago

በዓልና ማንነት የሆነ አይነት አንድ መመሳሰል አላቸዉ። እኛን እኛ የሚያደርገን ትዉስታቸን ብቻ አይደለም። ትናንቱን የረሳ አንድ ህመምተኛ ሌላ ሰዉ ሆኗል አንልም። የሆነ መንፈሱን ግን ያጣል። ጎደሎነት አለዉ። ሰዉየዉ ራሱን ሆኖም።

ካምፓስ እያለሁ አንድ ሁለት በዓል አሳልፊያለሁ። ያለ ቤተሰብ በዓል ያ ስሜት አለዉ። አዘቦትነት።

አዲስ አመት በምስርም ለዛ ይጠጋጋል። በዓል ነዉ ግን መንፈሱ የለዉም። የሆነ የጾም ቀን እሁድ . . .

እና መስከረም አንድ ነገ ነዉ :)

6 months, 2 weeks ago

"የማያዉቁት ሃገር አይናፍቅም?" ይላሉ!
አይመስለኝም!

ከምናብ በላይ ምን ይናፍቃል። ካልነኩት ሃር በላይስ ምን ይለሰልሳል። እንደተጨበጠ ነገር ሚዘነጋስ ምን አለ።  መናፈቅ ለስሜት ሥሥ መሆን አይደል?  አለመናፈቅ ይከብዳል።

ይልቅ .  . .

የማያዉቁት ጠረን ይናፍቃል?
ያላቀፉት ፣ ያላሸተቱት ፣ ያልተላመዱት? 

ባዶነት ለገመሰዉ ፥ ለጎደለ ልብ ተሸካሚዎች ፤ ካቀፉት አካል ፣ ከጨበጡት እጅ በላይ ያልነኩት መዳፍ ፣ ያልሳሙት ከንፈር ይናፍቃል።

በብዙ ተከበዉ ያላዩት "አንድ" መጥቶ ስለሚሞላዉ ባዶነት ለሚናዉዙ ሥሥ ልቦች ...

.... የማያዉቁት ጠረን ይናፍቃል።

@samuel_dereje

6 months, 3 weeks ago

A comment on "ሃይ ባይ ባጣዉ ፈሚኒዝም!"

እንደማህበረሰብ በብዛት ከሚነወሩ ሃሳቦች ቀዳሚዉ ፈሚኒዝም ነዉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያዎች ቀዳሚ የመነጋገሪያ ጉዳይ ከመሆኑ አኳያ የሃሳቡ ቀዳሚ አቀንቃኞች በተደጋጋሚ "ፈሚኒዝም የሚጠላዉ በያዘዉ ሃስብ ሳይሆን ሰዉ ስለፍልስፍናዉ ባለዉ የተዛባ መረዳት ነዉ" ሲሉ እንሰማለን። ይሄ ምን ያህል እዉነት ነዉ? ሃሳቡን ልክ አይደለም ብሎ እንደሚያምን አንድ ሰዉ ፈሚኒዝም ለምን መነቀፍ አለበት ከምልባቸዉ ምክንያቶች ቀዳሚዉን በዚህ ጹሁፍ በጥቂቱን ለማቅረብ እሞክራለሁ።

GENDER ROLE ( ጾታዊ ሃላፊነት)

ፈሚኒዝም ነባሩ ጾታዊ ስርዓት በወንድና በሴት መካከል ባለዉ ተፈጥሯዊ የአካልና ስነልቦናዊ ልዩነት ላይ መሰረት ማድረጉን ይክዳል። ታሪክን ብሎም አሁን ያለዉ የማህበርሰብ መዋቅር በጨቋኝ የአባታዊ ስርዓት የሚፈርጅበት መሰረታዊዉ ምክንያትም የጾታ ስርዓት የማህበርሰብ ፈጠራ ነዉ ብሎ መደምደሙ ነዉ። (Considering Gender as a social construct)

ይሄ ግን ልክ አይደለም። ሴትና ወንድ እንደሰዉ አንድ ቢሆኑም። የተለያየ የአይምሮ እና የአካል ተፈጥራዊ ባህሪ አላቸዉ። ፈሚኒዝም ያን አቅሎ በደምሳሳዉ ያየዋል።

ለምሳሌ - ሴቶች ከወንዶች ፍጹም የማይነጻጸር ሌሎች ሰዎችን የመረዳት ፣ ልጆችን nurture የማድረግ ጸጋ አላቸዉ። ወንዶች ደግሞ ከሴቶች የተሻለ አደጋ ለማጋፈጥ ዝግጁ የመሆን ( risk taking behaviors) ያን ለመጋፈጥ የሚያስችልም አካልዊ አቅም አላቸዉ። ከዉልደታቸዉ ጀምሮ ተፈጥሮ ለዛ ዝግጁ ታደርጋቸዋለች። ያ ብቻ ሳይሆን በ Aggression, Emotional Expression , በ Interest እና preference ይለያየሉ።

ያም ከወንድና ከሴት የሚጠበቀዉ ባህሪና ሃላፊነት የተለያየ ያደርገዋል። ባህል ደግሞ እሱን ያጸናል። እንጂ እንደነሱ መከራከሪያ ወንድ የተሻለ ሊደርግ የታሰበ ስርዓት ያመጣዉ ክፍፍል ስለሆነ አይደለም።

ተፈጥሮ ለማንም ፍትሃዊ አልነበረችም። ዛሬ ላይ ከመድረሱ በፊት የሰዉ ልጅ ቀዳሚ ግብ በህይወት መትረፍ ነበር። የባህል ሃላፊነት ደግሞ የማህበርሰቡ ቀጣይነት ማረጋገጥ ነዉ። የአንድ ህብረተሰብ ቀጣይነት የሚረጋገጠዉ በጤነኛ እና ዉጤታማ ህጻናት ላይ ነዉ። በሌላ አማርኛ በጤናማ ትዳር ላይ። ያን ማድረግ የሚያስችለዉ ብቸኛዉ መንገድ ለሁለቱም ( ባልና ሚስት) ተፈጥሯቸዉ የተስማማዉን ሃላፊነት ሲጫሙ ነዉ። ማህበርሰብ እንደሚለዉ ወንድ የወንድን ሃላፊነት ሲይዝ ( protector and provider ) ፣ ሴት የሴትን ሃላፊነት ስትይዝ ( Caring and Nurturing)።

እዚህ ጋር ግን በመግባባት ባል እና ሚስት በትዳራቸዉ አንተ ይሄን አድርግ አንቺ ይሄን አድርጊ ተባብለዉ የሚስማማቸዉን ሃላፊነቶች ሊከፋፈሉ ይችላሉ። ማህበርሰብ ግን ማጽናት ያለበት ለሁለቱም ተፈጥሮ የሚስማማዉን ባህሪ ነዉ።

በጊዜ ሂደት የቴክኖሎጂ መምጣትና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዉ ሁነቶች መቀየር ተፈጥሯዊ ልዩነቶችን በሚቻል ደረጃ ለማጥበብ ሞክሯል። በቴክኖሎጂ ረገድ የወሊድ መቆጣጠሪያ ፣ የቤት ስራ አጋዥ መሳሪያዎች ፥ በኢኮኖሚዉ በአለም ጦርነቶች ምክንያት የሰራተኛ ወንዶች ማነስ ሴቶችን ወደ ስራ እንዲሰማሩ ገፍቷል። ( ልብ በሉ የአባትዊዉ ስርዓት ተጠቃሚ የተባሉት እነዚሁ ወንዶች ናቸዉ ወደ ሞት ቀድመዉ የሚጋዙት። Sadly we are still in that déjà vu as a country)። ወዲፊትም ተፈጥሯዊ ልዩነቶችን ማጥበብ ቢቻል የጻታዊ ሃልፊነቶች እየተቀየሩ ሊመጡ ይችላሉ።

ነገር ግን ስርዓተ ጾታን ከተፈጥሮ ለይቶ ማየት ማህበራዊ መሰረቶችን የሚንድ ግልብ አስተሳሰብ ነዉ። ጾታዊ ሃላፊነቶች የምንረዳበት መነገድ ( ወንድ ማለት እንዲ ነዉ ፣ ሴት ማለት እንዲ ናት የምንለዉ ) የአንድ ህብረተሰብ የባህል እና የማንነት እምብርት ነዉ። እነዚህን ሚናዎች ማወክ ማህበራዊ ትስስርን ሊያዳክም እና የጋራ ማንነትን ወደ ማጣት ሊያመራን ይችላል።

ደሞም የፌሚኒዝም ጾታን ከስርዓተ ጾታ ( sex and gender) ለይቶ የመረዳት ፍልስፍና "ሰዉ በተፈጥሮዉ አይደለም ወንድ ሴት የሚሆነዉ ራሱ መወሰን ይቻላል። ሁለት አይነት ጾታ ብቻ አይደለም ያለዉ" የሚሉ የግብረሰዶማዉያን እና የትራስን ጀንደር ሃሳቦች መንገድ የጠረገ ነዉ። ያ ደግሞ ባህልን ብቻ ሳይሆን ሰዉ የመሆንን መሰረታዉ እዉነቶች ነዉ የሚንደዉ።

ለዛሬ ይሄ ይብቃን። ቀጣይ ከፍልስፍናዉ ልክ ያልሆነ ሌላ ሃሳብ ለማየት እንሞክራለን።

#feminism #radicalfeminism #culture #patriarchy

We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 2 weeks, 6 days ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 2 months, 1 week ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 2 months, 2 weeks ago