beki_book

Description
የስነ ፅሁፍ ስራዎች ለውድ አንባብያን !

> ልቦለድ
> ወግ
> መጣጥፍ
> አጫጭር ታሪኮች
> philosophy idea

በብዙ ይገኙበታል #join

#በረከት_ዘውዱ @Beki_book @bereket_zewde
Advertising
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc

6 months, 2 weeks ago
10 months, 1 week ago

ውሽማዬ

#ክፍል ሁለት

ከሁለት ሳምንት በኋላ የባዬ ቤት ተንኳኳ እየሩስ ነበረች " ሰላም ነው ባዩ ዛሬ ማታ ተገናኝተን መዝናናት እንችላለን ባለቤቴ ስራ አዳር ነው " እዩ የምርሽን ነው እንዴ እኔ እኮ ቀልድሽን መስሎኝ ነበረ " አይደለም ባይዬ ቢያንስ ዘላለም ሆኖ ከሚጫነኝ ድብርት ከዳንኩኝ ብዬ ነው " ታድያ ሰው በጠበል እንጂ በአልኮል ይድናል እንዴ ? " ኧ..... " አለች በድንጋጤ " ስቀልድ ነው እዩዬ አንድ ሰዓት ላይ ፒያሳ ማህሙድ ጋ ጠብቂኝ " እሺ ባዩዬ ደህና ዋል " ።

አንድ ሰዓት ላይ  እየሩስ ባዬን ፒያሳ ማህሙድ ሙዚቃ ቤት አጠገብ ቆማ እየጠበቀች ነው ባዬ ከኋላዋ መጥቶ ለብዙ ደቂቃ ተመለከታት ከጊዜያትም በኋላ ረዥም  እና ዓማላይ ቁመናዋ መልኳ በነጭ ቀሚሷ ላይ ፋክቶ ተመለከተው ድንገት ዞራ ስታየው " አምሮብሻል ባክሽ የቅዳሜዋን መልዐክ መስለሻል " አላት " አንተም በዚ አለባበስህ ሚስት ማግኘትህ አይቀርም " ብለሽ ነው " እሺ ወዴት እንሂድ " እየሩስ ጠየቀች " አንድ የማቀው ግሮሰሪ አለ ትንሽ ከተራመዱ በኋላ እንኳን ደህና መጣሽ ብሎ ወደ ግሮሰሪው ገቡ ግሮሰሪው ሰፋ ያለ ነው ጥንድ ጥንዶች ዳር ይዘው ይጠጣሉ አንዳንድ ብቸኛ ወንዶች ከመጠጥ ቀጂዎች አጠገብ ይስተዋላሉ ሶስት ሰዓት ላይ ነገሮች ተቀያየሩ ዘፈኑ ሞቀ ዳንስ ተጀመረ ግሮሰሪው በአንድ እግሩ ቆመ ጥንዶች ተያይዘው ሲጨፍሩ ይስተዋላል ባዬ የእየሩስን እጅ ይዞ ለዳንስ ጋበዛት ማሪንጌቻ ቡጊ ሳልሳ ሁሉንም ጨፈሩ ሰዓቱ ሳይታወቅ ለሊት ሆነ እየሩስ የናፈቃት ተዝናኖት ተዝናንታ ተመለሱ ።

በሌላም ቀን ደገሙት ከ ሁለት ወራት በኋላ አንድ ሰዓት ላይ እየሩስ የባዬን ቤት አንኳኩታ ጠራችው ። ተዝናንተው ሲመለሱ በሩን የከፈተላቸው የእየሩስ ባለቤት ነበረ ሁለቱም ደነገጡ የእየሩስ ባል እየሩስን በጥፊ መቶ ወደ ቤቱ አስገብቷት ተመለሶ ባዬን በእልህ እያየው " ሌላ ነገር ሳይፈጠር ነገ ቤት ፈልገህ ከዚህ ጊቢ እንድትለቅ " ብሎት ወደ ቤቱ ገባ  እየሩስ አይኑን ለማየት አፍራ ፊቷን አዙራ ተኝታለች " በስራሽ ማፈር የነበረብሽ ሳታደርጊው ነበረ " ብሎ ትራሱን ይዞ ወደ ሳሎን ሄደ " እየሩስ እየፈራችም ቢሆን ወዴት ነው ? " ብላ ጠየቀችው  ኮስተር ብሎ በዚህ ሳምንት የፍቺውን ሂደት እጀምራለሁ እስከዛው ግን መኝታ እንለይ ብዬ ነው " ብሏት ወደ ሳሎን ገብቶ ተኛ ። ጠዋት አራት ሰዓት አካባቢ ባዬ እቃ እየጫነ ነው እየሩስ " ባዬ ወዴት ልትሄድ ነው ቤት አገኘህ እንዴ ? " እናቴ ቤት ሆኜ እፈልጋለሁ እዩዬ ከባለቤትሽ ጋ እንዴት ሆናችሁ ? " በዚህ ሳምንት የፍቺ ሂደት እንደሚጀምር ነገረኝ " ፍቺ ⁈ በመሐላችን ምንም እንደሌለ አልነገርሽውም ? " ሊያዳምጠኝ ፍቃደኛ አይደለም " በኔ ምክንያት ነው ይሄ ሁሉ የሆነው እኔ ነኝ ህይወትሽን የረበሽኩት " አይደለህም ባይዬ የኔ ጥፋት ነው ባለቤቴ መጣ ቻው በቃ " ብላው ሄደች ።

ባዬ ባደረገው ነገር ራሱን እየወቀሰ አጋጣሚውንም ተጠቅሞ የራሱ ለማድረግ ቢፈልግም የእየሩስን ህይወት አበላሽቶ የራሱን ህይወት መስራት እንደማይችል ህሊናው እንደማይፈቅድ ያውቃል ከመሠናዶ ትምህርት ቤት ጀምሮ ቢያፈቅራትም እሷ የምታፈቅረውና የምትወደው ሰው እንዳለ ትዳር መመስረቷ ደጋግሞ ሲያብበት ራስ ወዳድነቱ ገዝፎ ታየው ወደ እየሩስ ባለቤት መስሪያ ቤት ሄደ " ይቅርታ ዶክተር ልግባ " ግባ " የመጣሁት ከእየሩስጋ ምንም ግንኙነት እንደሌለን እና ለትዳሯ ታማኝ እንደሆነች ልነግርህ ነው እኔም ከዚ በኋላ አጠገቧ እንደማልደርስ ለማሳወቅ ነው " የ እየሩስ ባለቤት ረጋ ባለ ድምፅ " እየሩስ ህይወቴ ናት ከኔጋ ማግጣለች ፍታት ብትለኝ እንኳ እንደማልፈታት እና እንደማምናት እወቅ ነገር ግን ትንሽ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማት ነው " አለው " ባዬ ተመስገን ብሎ በረዥሙ ተነፈሰ " ዶክተር በነካ እጅህ ትንሽ ትንሽ አዝናናት ተፈላጊነቷ ሚታይበት ቦታ ውሰዳት ድጋሚ ወደ ህይወትህ እንደማልመጣ ቃል እገባለሁ" ብሎ ተሰናበተው ።

ደራሲ በረከት ዘውዱ

@beki_book

10 months, 2 weeks ago

ውሽማዬ

" በሀይሉ......በሀይሉ...." አንተ በሀይሉ በሩ በሀይል ይንኳኳል በሀይሉ ከተኛበት እንቅልፍ ነቅቶ በሩን ከፈተው " እዩ ምነው በዚ ሰዓት " ዛሬ ተኬ ስራ አዳር ነው እና ወጥተን እንዝናና ልልህ ነው " በይ እኔ ደክሞኛል ስራ ውዬ ነው የመጣሁት እንቅልፌን ልተኛበት " ባይዬ በናትህ ከተዝናናሁ ስንት ጊዜዬ " እና ላንቺ መዝናናት ሲባል ባዬ እንቅልፉን ማጣት አለበት " ባይዬ ተው ግን " የሆንሽ አሳዛኝ እሺ ልብሴን ልቀይር ጠብቂኝ " ።

ማታ አምስት ሰዓት ላይ ፒያሳ አራዳ ማህሙድ ሙዚቃ ቤት አለፍ ብሎ ከሚገኝ ግሮሰሪ ባዬ እና እዩ እየጠጡ ይጨፍራሉ " ወይ እዩ ተካልኝ መንገሻ ቀደመኝ እንጂ ማግባትስ አንቺን ነበረ " ባዬ ደሞ ስንዝናና እንደዚህ አትበለኝ አላልኩህም እኔ እና አንተ ንፁህ ጓደኛሞች ነን ተካልኝ ደሞ ባለቤቴ ነው የልጄ አባት " እሱማ ልክ ነሽ እዩዬ ለምንድነው ግን ከሱጋ ማትዝናኑት ?" ተኬ ቁም ነገረኛ ሰው ነው ቤት ውስጥ እንኳ ስንጠጣ ከ ሁለት ቢራ በላይ አይጠጣም ጭፈራውንም ብዙ አይሞክርም ወግ አጥባቂ ነው ከመቶ አለቃ አባቱ የወረሰው ባህርይ ይመስለኛል ሰውነቱም እንዳንተ ለመውረግረግ አይሆንም " ኮስማና ነህ እያልሽኝ ነው ¡ " አንተ አልክ በል አሁን እንደንስ ።

አዲስ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአስረኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነው እየሩስን የማውቃት የምንቀራረብ ጓደኛሞች ነበርን ደርግ ከ ት.ነ .ግ ጋር ጦርነት ሲጀምር 1978 ለጦርነት ሄድኩኝ ከ 4 ዓመታት በኋላ ጦርነቱን ኢ ህ አ ዴ ግ አሸንፈ ከጦርነት የተረፍነው ወታደሮች ወደየ መንደሮቻችን ተመለስን እየሩስ በጣም ተለውጣ ነበረ የከፍተኛ ትምህርቷን አጠናቃ ወደ ዩኒቨርስቲ መግባቷን ነገረችኝ ሳንገናኝ ልንለያይ ቢሆንም ደስታዋ ደስ አሰኘኝ እኔም ስራ መፈለግ ጀመርኩ በመጨረሻም አንድ የሙሽራ ልብስ መሸጫ ቤት ተቀጠርኩ ከአራት ዓመት በኋላ አንድ አዲስ ሰማያዊ ቮልስ ዋገን መኪና ከሱቃችን በር ላይ ቆመ ቁመናዋ ድንቅ መልኳ የሚያምር እንስት ከመኪናው ወረደች በሹፌሩ በኩል ትከሻው ደንደን ያለ ረዘም ያለ የጀነራል አቋም ያለው ሰው ወረደ ልጅቷ ወደ ሱቃችን ስትገባ ዐይኔን ማመን አቃተኝ እየሩስ ነበረች አይን ለዓይን ተያየን ደነገጥኩ ግን ደግሞ ለሷ የልብ ጓደኛሞች ብቻ ነበርን  ሰውየው ጎርነን ባለ ድምፅ " ለሰርጋችን የሚሆን ልብስ በትእዛዝ ለማሰራት ነበረ " አለኝ እኔም እየሩስን እያየሁ እባክዎ ጌታዬ አረፍ ይበሉ " እርሷ ናት ባለቤትዎ " አዎ ምነው ? " አይ ቆንጆ ናት ልዕልት ነዋ ሚያገቡት " አንቱ ብለህ አታዋራኝ በማዕረግም በእድሜም ካንተ አልበልጥም " ለሌላ አይደለም ያው ደንበኛ ንጉስ ነው እርሷንም ቢሆን እንደዚህ ነው ማወራት " ተለክተው ከወጡ በኋላ ለ አስራ አምስት ቀን ቀጠሮ ተያዘ በ አስራ አምስተኛው ቀን መጥተው ሲለኩ እየሩስ ትንሽ እንደ ሰፋት ነገረችኝ አውቄ እንዳሰፋሁት እና ተመልሳ የምትመጣበትን አጋጣሚ ለመፍጠር እንደሆነ ነገርኳት ግን ፍቃደኛ አልነበረችም ከወራት በኋላ ስራ ቀየርኩ ።

በተማርኩት construction surveying ሙያ የመንገድ ቅየሳ ስራ ጀመርኩ contractor engineer እስክሆን ድረስ ተቀጥሬ ሰራሁ  ከ ሁለት ዓመት በኋላ ፒያሳ ወርቅ ቤት ለእናቴ ወርቅ ልገዛ ወደ ወርቅ ቤት ሳቀና ከወርቅ ቤቱ ውስጥ እየሩስን ከባለቤቷ ጋ አገኘኋት ቤታቸውንም አጣርቼ ያለችበት ሰፈር ተከራየሁ ከሁለት ወራት በኋላ ከነ እየሩስ ጊቢ የተለቀቀውን ቤት ተከራየሁ እየሩስ ከቶ እንዳማታውቀኝ ዳግም ተዋውቀን ጎረቤታሞች ሆንን አንድ ለሊት ጠጥቼ ወደ ጊቢ ስገባ እየሩስ የቤታቸውን በር ከፍታ ወጣች " ምነው በለሊት የት አምሽተህ ነው አለችኝ " ከጓደኞቼ ጋ ተዝናንቼ እየመጣሁ ነው አልኳት ፊቷ ላይ ምኞትና ሀዘን አነበብኩ ምነው አንቺን ባለቤትሽ አያዝናናሽም እንዴ " ብዬ ጠየቅኳት ከሀዘን ስሜቷ ሳትወጣ ተዝናንታ እንደማታውቅ ነገረችኝ " እንዴት አያዝናናሽም ዞር በይልኝ ልናገረው ስል " ኧረ ተረጋጋ የለም ይህን ሳምንት ስራ አዳር ነው " አለችኝ ለሊቱን ውጪ ተቀምጠን ስናወራ አጋመስን " በል ደህና እደር አንድ ቀን ታዝናናኛለህ " ብላኝ ወደ ቤቷ ገባች  ።

#ክፍል ሁለት ........

ደራሲ በረከት ዘውዱ

@beki_book

10 months, 4 weeks ago

ትብታብ

ክፍል ሶስት

አሌክስ ትምህርት ቤት በጊዜ ደረሰ ተማሪዎች ተከትለውት ወደ ክፍሉ ገቡ እንደተለመደው ዳራቸውን ይዘው ተቀመጡ አሌክስ ፈገግ ብሎ " የዛሬውን ትምህርት ከመጀመራችን በፊት ጥያቄ ያለው ካለ እድሉን እንስጠው " ተማሪዎች በዝምታ ጥያቄ እንደሌላቸው ተናገሩ " እሺ እኔ አንድ ጥያቄ አለኝ በህይወታችሁ የምትፈሩት እና ባይደርስብኝ የምትሉት ነገር ምንድነው ? " ሲል ጠየቀ ተማሪዎች ተራ በተራ እጃቸውን እያወጡ " ሞት ፣ አጊኝቶ ማጣት ፣ የሚረዳን ሰው አለማግኘት ፣ ብቸኝነት " እያሉ መለሱ " እንደ እውነቱ የሰው ልጅ ፍርሀት እንደ ሰው ማንነት እንዳለበት ሁኔታ ይወሰናል ሞትን ግን ለምን እንፈራዋለን " ሲል በድጋሚ ጠየቀ አንድ ተማሪ " መምህር የማጣት መጨረሻ ስለሆነ እና የማንመለስበት መንገድ ስለሆነ " አለው አሌክስ በተማሪው መልስ እየተገረመ " ልክ ብለሀል ሞት ከወሰደ አይመልስም የሰው ልጅ ፍርሀት ማሰሪያው ሞት ነው ! ወደ ዛሬው ትምህርታችን እንግባ " ብሎ ማስተማሩን ቀጠለ ።

አመሻሽ ላይ የአሌክስ ቤት ይንኳኳል " ሁለት ነጠላ ዘቅዝቀው የለበሱ ሰዎች ፊቱ ቆመዋል አንዱ ፊቱን አጨፍግጎ " አሌክስ መርዶ ልንነግርህ ነው እናትህ አርፈዋል " አሌክስ ደነገጠ እየጮኸ እያለቀሰ ወደ እናቱ ቤት ደረሰ አስክሬናቸው ወደተገነዘበት ክፍል ገብቶ እየጮኸ አለቀሰ ወንድሙም እህቶቹ እያለቀሱ ነው ፣ ሰልስት ሆነ እስከዚህ እለት አሌክስ እና ወንድሙ ምንም አላወሩም አሌክስ ፊት ነስቶታል ከአንድ ሳምንት በኋላ የአሌክስ እናት ጎረቤት አሌክስን ቤታቸው ጠርተው ልጄ ይህን እናትህ ናቸው ያስቀመጡት ብለው የታሸገ ወረቀት ሰጡት አሌክስ ብቻውን በሆነበት ሰዓት ከፍቶ ማንበብ ጀመረ " ዓለሜ እኔ እናትህ ሁነኛ በሽታ ካጠቃኝ ዘመን አልፎታል ያው ፈጣሪ በፈቀደው ቀን መሄዴ አይቀርም ግን በዚህ ሁሉ ጊዜ ይህን ስላልነገርኩህ ይቅርታ ዓለሜ ሚሊዮን ወንድምህ ነው እኔ በማልኖርበት ጊዜ ማን ያፅናናው ይሆን ብዬ ሳስብ አንጀቴ ይነድብኛል እህቶችህ አግብተው ሄደዋል ያለኸው አንተ ብቻ ነህ ዓለሜ ትዝ ይለኛል አባትህን ካጣሁ በኋላ ሞክሬ የማላውቀውን ስራ መስራት ጀመርኩ ብዙ ስራ ሞከርኩ ግን አልሆነም ሁሉም ወጣት ብትሆኚ አሪፍ ነበር እያሉ ይሸኙኛል ሚሊዮኔ ገና የ ዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ነበር ለሊት ለሊት ማን አለኝ እያልኩ ሳለቅስ ይሰማኛል የፋሲካ በዓል ሰሞን ከትምህርት ቤት እየቀረ ኩሊነት ሰርቶ ባመጣው ብር የቤት አስቤዛ ለናንተም የበዓል ልብስ ገዝቶ መጣ እናቴ ከዚ በኋላ እኔ አለሁልሽ አለኝ ካንጀቴ እያለቀስኩ መረቅኩት እንባዬ የሀዘንም የደስታም ነበር ዛሬ ላይ ሆኜ ያንን ቀን ብቻ ሳስብ ሁሉንም ጥፋቱን እረሳዋለሁ አንተን እና እህቶችህን እያስጠና ሲያድር እሱ ትምህርቱን አቁሞ እናንተን ትምህርት ቤት እያደረሰ ወደ ስራ ሲሄድ ምን ያህል አልቅሶ ይሆን ብቻ ግን ልጄ እሱን መሸከም እንዳትሰለች ደሞ ወንድምህ ነው አይከብድህም ቢከብድህም አንድ እሱ እንዲ የከበደህ አራት ሰው ተሸክሞ ደከመኝ አለማለቱን አስታውስ " ይላል አሌክስ በእንባ ታጅቦ አነበበው ።

ሰውነት ድክመት ነው አይደል ዛሬ ላይ ስንቆም በራሳችን ጥረት እና ጉልበት የቆምን ይመስለናል ሰዎች ስለ እኛ መቆም ዋጋ እንደከፈሉ እንዘነጋለን ፣ አሌክስ ወደ ቤት ገብቶ ሚሊዮንን አቅፎት አለቀሰ እባክህ ወንድሜ ይቅር በለኝ ብሎ አለቀሰ ሚሊዮንም ይቅር በለኝ እያለ አለቀሰ ፣ ሚሊዮን ከአሌክስ ጋ ተነጋግሮ ማገገሚያ ገባ ከ 6 ወራት በኋላ ሚሊዮን ከሱስ ነፃ ሆነ አሌክስ በከፈተለት እንጨት ቤት ይወደው የነበረውን የእንጨት ስራ ጀመረ ።

#በረከት_ዘውዱ

@beki_book

11 months ago

ትብታብ

ክፍል ሁለት

አሌክስ በጠዋት ተነስቶ ሰዓቱን ሲያየው አስራ ሁለት ሰዓት ዛሬ በጊዜ ተነስቷል ቁርስ በልቶ ማታ የሰራውን pdf ደግሞ አነበበው ትንሽ እንደከለሰ ሰዓቱ ሲደርስ ወደ ስራ ጉዞ ጀመረ መንገዱ ክፍት ስለሆነ በጊዜ ደረሰ ፣ ትንሽ ደቂቃዎች ስለነበሩት ቡና ለመጠጣት ከትምህርት ቤቱ ፊት ለፊት ወደ ሚገኝ ካፌ አመራ ካፌው በረንዳ ላይ ተቀመጦ መንገደኞችን ይታዘባል ፣ ፓርኪንግ የሚሰሩ ሰዎችን እና ባለመኪኖችን ጫማ የሚያስጠርጉ ሰዎች እና ሊስትሮዎችን ያወዳድራል " የፓርኪንግ ሰራተኞች እና የ ባለመኪኖች ልዩነት ግልፅ ነው የሊስትሮዎች እና የጫማ አስጠራጊዎች ልዩነት ግን ከላይ እና ከታች መቀመጥ ነው አሁን ከሊስትሮው እና ከጫማ አስጠራጊው ማን የበለጠ ገንዘብ እንዳለው ማወቅ አንችልም ምናልባት ከአለባበስ ተነስተን ልንገምት እንችላለን ይህ ደሞ ዝንጥ ብለው በኪሳቸው ዶዲ ሳይዙ ሚንቀሳቀሱ ሰዎች እንዳሉ ካለማስተዋል የተነሳ ነው " ይህን እያሰበ ክፍል የመግቢያ ሰዓት ደረሰ ከመደበኛው ሰዓት አምስት ደቂቃ አሳልፎ ክፍል ገባ የ philosophy ክፍል እንደ ሌሎች አይነት ተማሪዎች አይረበሽም መምህሩ ፀጥ በሉ ተሳተፉ አይልም ተማሪዎች መቼ እንደሚያወሩ መቼ ዝም ማለት እንዳለባቸው ያውቃሉ አሌክስ ወደ ክፍሉ ሲገባ ተማሪዎች ከራሳቸው ጋ እየተወያዩ ነው whit board አጥፍቶ ማስተማሩን ጀመረ ።

" እንዴት አደራችሁ ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት የህይወት ክህሎት ስልጠናውን ጨርሰናል ዛሬ መደበኛ ትምህርት እንጀምራለን ከዛ በፊት ጥያቄ ያለው ተማሪ ካለ እድሉን ይጠቀምበት " አንድ ተማሪ እጁን አውጥቶ " መምህር ሶስት ነገሮች እንዲብራሩልኝ እፈልጋለሁ እውነት ልክነት እና መልካምነት ማለት የሰው መልካም ፣ የሰው ትክክል እና ፣ የሰው እውነተኛ አለ ካለ ደግሞ ሰዎች በሌሎች አይን ለምን እንደ ውሸታም እንደ ስህተት እና እንደ መጥፎ ይቆጠራሉ " ብሎ ጠየቀ አሌክስ ጥያቄውን ካደመጠ በኋላ " መልካም ጥሩ ጥያቄ ነው የሌሎችን እምነት ወይም አስተሳሰብ አልቃወምም ግን ልክነት እና መልካምነት ሁኔታዎች ይመስሉኛል ማለት የሁኔታዎች እንጂ የሰው ልክ የለም የሁኔታዎች እንጂ የሰው መልካም የለም ስለ እውነት የማውቀው እውነት መስፈርቱ እውነት እንደሆነ ነው ፣ ሰዎች ከሁኔታዎች ጋ ይቀየራሉ እና ማንነታቸው ያሉበትን ሁኔታ ቅርፅ ይይዛል እላለሁ " ብሎ ንግግሩን ሲጨርስ ጥያቄውን የጠየቀው ተማሪ አጨበጨበ አሌክስ የዛሬውን ትምህርት ማስተማር ቀጠለ ።

ምሳ ሰዓት ሲደርስ ለምሳ ወደ እናቱ ቤት ሄደ እመይ ምሳ አዘጋጅታ እየጠበቀችው ነበረ እግሩ ገና ከመግባቱ " እመይ እንዴት ዋልሽ " ውይ ልጄ መጣህ እንዴ በዛው እጅህን ታጠብ ና ተቀመጥ " እመይ የዛሬው ምሳ ልዩ ነው ፍክት ብለሻል ምን ተገኘ " ልጄ ነገ በዋስ ይወጣል ዓለሜ " አለች እመይ አሌክስ ወንድሙ ለ ብዙ ጊዜ ታስሮ ሲፈታ ዛሬም ድረስ እመይ እንደ መጀመሪያ ጊዜው ምትቀበለው ነገር ይገርመዋል " ዓለሜ እባክህን በማርያም ይዤሀለው አባት በሌለን ጊዜ እንደ አባት ሆኖ አንተን እኔን እህትህን ለማቆየት ያደረገውን አትርሳ ተስፋ አትቁረጥበት አየህ ልጄ ሰው ጥሩ ቢሆን ከራሱ አልፎ ሌሎችንም ይጠቅማል መጥፎ ሲሆንም መጀመሪያ ራሱን ጎድቶ ነው ሌሎችን ሚጎዳው ስራው ቢያሳዝንህም እዘንለት እንጂ አትዘንበት " እሺ እመይ " በል ልጄ ምግቡን ብላ ።

#በረከት_ዘውዱ

@beki_book

11 months, 1 week ago

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

። ክፍል ሁለት እንዲቀጥል #like ወይም #comment
። በመስጠት ሀሳባችሁን አጋሩ

@beki_book

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

11 months, 1 week ago

ትብታብ

አሌክስ ጠዋት ተነስቶ ሰዓቱን ሲያየው ደነገጠ ማታ pdf እየሰራ ስላመሸ የድካም እንቅልፍ ወስዶት ነው ፣ ፊቱን ታጥቦ ቁርስ ሳይበላ ቦርሳውን ይዞ ወደ ስራ መንገድ ጀመረ ፣ አንድ መኪና መንገድ ዘግቶበት ክላክስ እያስጮኸ " መንገዱን ልቀቅ እንጂ " እያለ ይጮሀል በኋላ የመንገዱን መዘጋት መንስኤ ለማየት ሲሞክር አንዱን ሌባ ፖሊሶች አንበርክከው ይገርፉታል የሌባው እናት ኧረ ልጄ ታማሚ ነው እያሉ ያለቅሳሉ አንዳንድ ሰዎች ከበው ያያሉ ፣ ከፊት መንገዱን የዘጋው መኪና ሹፌር ነገሩን ለማረጋጋት እንደወረደ ያያል ሌባው በእጁ የታቀፈውን የመኪና ስፓኪዮ ነጥቀው አንስተው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዘውት ሄዱ እናትየው እያለቀሱ ከኋላ ተከተሏቸው መንገዱ ተከፈተ ወደ መኪናው ገብቶ መንገዱን ቀጠለ ።

አሌክስ የ philosophy መምህር ነው ፣ ሰሞኑን በትምህርት ቤቱ ለገቡት አዲስ ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና እየሰጠ ነው ፣ ተማሪዎቹ ቀድመውት ክፍል ውስጥ ተገኝተዋል " ስላረፈድኩኝ ይቅርታ " ብሎ ንግግሩን ቀጠለ " ትላንት ዛሬ ስለምንወያይባቸው የህይወትን ክህሎት ማዳበር ላይ አራት ጉዳዮችን አንስተን ነበረ የሚያስታውሰኝ ፍቃደኛ ሰው አለ ?" አንዱ ተማሪ እጁን አውጥቶ " ስኬት ፣ ስጋት ፣ ውድቀት እና ውሳኔ ናቸው " አለ " አመሰግናለሁ አዎ ፣ ስጋት ፣ ውሳኔ ፣ ውድቀት እና ስኬት ናቸው ሰው ስጋቱ ለውሳኔው መሠረቱ ነው ውሳኔው ለውድቀት ወይም ለስኬቱ ይዳርገዋል የሰው ልጅ ስጋት መኖር ከመፈለግ ይመጣል አሁን ካለበት ህይወት የተሻለ ህይወት የመኖር ስጋት ወይም አሁን ባለበት ህይወት የመኖር ስጋት " ይህን እያለ አንድ ተማሪ እጁን አውጥቶ ጥያቄ ጠየቀ " መምህር ሰው እንዴት ስለመኖር ስጋት ያድርበታል እኔ ያስተዋልኩት ሰው ለመሞት እንደሚሰጋ እንጂ ለመሞት እንደሚሰጋ አይደለም " አሌክስ ፈገግ ብሎ " መልካም ጥሩ ጥያቄ ተማሪዎች አለመፈለግ በራሱ መፈለግ እንደሆነ ስንቶቻችን እናውቃለን ፣ አንድ ሰው የሆነ ነገር ማድረግ ካልፈለገ በተዘዋዋሪ ያንን ነገር አለማድረግ ይፈልጋል ማለት ነው ፣ አንድ ሰው ለመሞት ይሰጋል ማለት መኖር ይፈልጋል ማለት ነው በሌላ አገላለፅ ሞት የሚያሰጋን መኖር ስለምንፈልግ ነው " ።

ክላስ ጨርሶ እንደወጣ ወደ እናቱ ቤት ሄደ ቤት የሉም ነበረ ፣ ከጊቢው እየወጣ እናቱ መጡ " እመይ የት ሄደሽ ነው " እናቱ እንባዋ እየቀረረ ዛሬም ፖሊሶች እያዳፉ ጣቢያ ይዘውት ሄዱ አሁን ምሳ አድርሼለት እየመጣሁ ነው " አሉት አሌክስ ጠዋት ያየውን ለማስታወስ እየሞከረ " ዛሬም ሰርቆ ተያዘ " አዎና እንግዲ አመል መች ይተዋል ቁማር ለመጫወት እና አረቄውን ለመጠጣት ሲል " ለመሆኑ አንቺ ምሳ በልተሻል " ገና አሁን መምጣቴ ነው " ወይ እመይ አሁን እንግባና እንብላ ብሎ ምግቡን አቀራርበው እየበሉ " ምነው ዓለሜ ሚሊዮን ላይ እንዲ ጨከንክበት ! ለኛ ብሎ ስንት ነገር እንደሆነ እያወቅክ አንተን ለማስተማር ትምህርቱን አቁሞ ያገኘውን ስራ እየሰራ ተሸክሞ አሳድጎህ በተራህ ጨከንክበት ምነው ልጄ የአንድ አብራክ ክፋይ ሆናችሁ " ብለው ጠየቁት " ምነው እናቴ እኔስ የወንድሜ እንዲህ መሆን የትኛውን ደስታ ሰጥቶኝ ነው ያልሞከርኩት ምን አለ ማገገሚያ ጠበል ሆስፒታል ሳይካትሪስት ምን የቀረኝ አለ ? ግን እሱ ለመዳን ፍቃደኛ አይደለም እመይ ለሊት እንቅልፍ እያጣሁ እያለቀስኩ የምፅፈው መፅሀፍ ስለ እኔ እና እሱ ታሪክ አይደለም አርዓያዬ መከታዬ መካሪዬ የምለው ሰው ህይወት ፊቷን አዞረችብኝ በሚል ምክንያት ራሱን ከእኛም ከሰዎችም አሸሸ በሱስ ተደበቀ የተደበቀበት ሱስ ይዞት ጠፋ ፣ ከስራው ከሰዎች ከፈጣሪው ከራሱም ራቀ ፣ መከርኩት የስራ ሀሳብ አቀረብኩ መነሻ ገንዘብ ብዬ ያለኝን ሰጠሁት ሁሉንም በመጠጥ እና በቁማር አወደመው እመይ ታድያ እሱን ለፈጣሪ እና ለጊዜ ትቶ በፀሎት ከማሰብ ውጪ ምን ማድረግ እችላለሁ " እያለ አምርሮ አለቀሰ እናትም እያለቀሱ " ቢጨንቀኝ ነው ልጄ የሚያድነው ነገር ባጣ ነው " ብለው አምርረው አለቀሱ ።

ክፍል ሁለት ........

@beki_book

11 months, 1 week ago

የሟች ሚዜ

ሳሚን ያወቅኩት ሀይ ስኩል ዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነው ወንድሜ እንደሞተ ከለገጣፎ አዲስ አበባ አክስቴ ጋ መጣሁ አክስቴ ባሏን ፈታ ከልጇ ጋ ብቻዋን ነው ምትኖረው ጠዋት አስራ ሁለት ሰዓት ወጥታ ማታ አስራ ሁለት ሰዓት ትመጣለች ፣ የቤቱን ስራዎች መስራት እና ልጇን መንከባከብ የኔ ሀላፊነት ነበር አክስቴ ቅዳሜ እና እሁድ ታግዘኝ ነበረ ፣ ለአዲስ አበባ አዲስ ስለነበርኩ ጓደኛ ለማፍራት ብዙ ጊዜ ወሰደብኝ ወደ ትምህርትና ቤት ብቻዬን ነበር ምመላለሰው የአክስቴን ልጅ ከትምህርት ቤት ለማምጣት እንዳይረፍድብኝ እየቸኮልኩ እራመዳለሁ ፣ አብዛኛውን ጊዜ ትምህርት ቤት ስለ ወንድሜ እና እናቴ ሞት እያሰብኩ ብቻዬን እሆናለሁ ፣ ሳሚን ያን ጊዜ ነበር ያወቅኩት ፣ ከትምህርት ቤት ስወጣ ልሸኝሽ አለኝ እንደምቸኩል ብነግረውም ከኔ እኩል መፍጠን እንደሚችል ነግሮኝ ሸኘኝ ተዋወቅን ፣ ነገሮች ሲደጋገሙ ጓደኞች ሆንን ብቸኝነት ተሽቀነጠረ በጓደኝነት ከነፍን አክስቴ ፊልድ ከሆነች አልፎ አልፎ ፓርቲ ደይ በሚል ሰበብ እንጠጣለን አስራ ሁለት ስንደርስ እንደሚያፈቅረኝ ነገረኝ እኔም ስለማፈቅረው ጥያቄውን ተቀበልኩ ።

እኔ ማትሪክ ውጤት መጥቶልኝ ደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ ተመደብኩ ከ አራት ዓመት በኋላ በ አካውንቲንግ ተመረቅኩ ፣ ሳሚ ከዱርዬዎች ጋ እንደገጠመ እና በጣም አደገኛ ሱሶች እንደጀመረ እናቱ ነገረችኝ ፣ ትላንት ፊቴ ላይ ድቅን አለ ፣ ኩርፊያዬን አይቶ ቀኑ ሚረበሸውን ፣ ከእኔጋ ጊዜ ለማሳለፍ ጓደኞቹን የገፋውን ፣ እንዝናና ካልኩት ብር ከየትም ተበዳድሮ የሚያመጣው ሳሚ ፣ አራት አመት ስንቆይ ከንፈሩን እንኳ ስስመው ደንግጦ ሳምንት ያኮረፈኝ እኔ ላይ ስሜቱን መወጣት ያልፈለገው ጓደኞቹ ፋራ እያሉት ስሜቱን ገዝቶ በፍቅር ያነገሰኝ ሳሚ ዛሬ በቁሙ እንዳጣሁት ተሰማኝ ፣ ካለበት ፈልጌ ሳገኘው በአፉ ተርዚና ይዟል በአንድ እጁ ሲጋራ በአንድ እጁ ጫቱን አቅፎታል ሲያየኝ ምንም አልመሰለውም ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ ተነስቶ በአጠገቤ አለፈ ተከተልኩት ሳሚ ሳሚ አንድ ጊዜ እናውራ አልኩት " ሀና እኔ አልሆንሽም በቃ እኔ ላንቺ አልመጥንሽም " ብሎኝ መልሴን ሳይጠብቅ ሄደ ።

ጥዬው ስለሄድኩ ይሆን ምናለ ከሱጋ ፍቅር ባልጀምር ምን ነበር ባንገናኝ እያልኩ ሳስበው አመሸሁ ጠዋት እንደ ነጋ ወደ ቤቱ ሄድኩ ፣ እናቱ ሲቀሰቅሱት ስካሩ አለቀቀውም " ኤጭ አንቺ ለምን መጣሽ ለምን አተይኝም " አለኝ እንደማልተወው እና ነገሮች መስተካከል እንደሚችሉ ነገርኩት ፣ ግን ሊያደምጠኝ ፍቃደኛ አልነበረም ፣ ከእናቱ ጋ ተማከርኩ ፀበል እንድወስደው ተነጋግረን ለሳምንት ቀጠሮ ያዝን እህቱ በመሐል ደወለች ድምጿ እየተቆራረጠ እያለቀሰች " ሳሚ ሞተ ተለየን " አለችኝ የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም እየበረርኩ ቤታቸው ስደርስ ድንኳን ተጥሏል እናት እና እህቱ ሳጥኑን አቅፈው ያለቅሳሉ ፣ የማላውቀው ስሜት ወረረኝ እየተንደፋደፍኩ አለቀስኩ ፣ ሳሚ የጫት ብር ለመሙላት ሰርቆ ሲሮጥ መኪና ገጭቶት ህይወቱ አለፈ ፣ ወደ ራሱ ተመልሶ ተጋብተን አንድ ላይ እንኖራለን ያልኩት ተስፋ ነፋስ እንደበዛበት ሻማ ጠፋ ፣ ህይወት የምወዳቸውን ሰዎች ልትነጥቀኝ የቆመች የሰርግ ሳይሆን የሞት ሚዜ ምታደርገኝ እስክትመስለኝ ድረስ አዘንኩ ።

#በረከት_ዘውዱ

@beki_book

11 months, 2 weeks ago

ተዐምር
"""" "'''''"""""""""

ማርታ ፊት ለፊቷ ጠረጴዛ ላይ ካለው አልበም ፎቶ እያየች እያለ ከአልበሙ ጀርባ ያረጀ ወረቀት አገኘች የተፃፈውን ፅሁፍ ማንበብ ስላልቻለች ልጇን ጠራቻት " ተዐምር ተዐምር ልጄ ነይ እስቲ አንብቢልኝ " አለች ተዐምር ወረቀቱን ተቀብላ ስታየው ከላይ " ልጄ ይህን ወረቀት ካገኘሽው ለእናትሽ ሳትሞት አንብቢላት ለእናንተ ያለኝ ፍቅር ከኖርኩትም በላይ እንደነበረ ትረዱታላችሁ " የሚል ፅሁፍ አለው ፣ ተዐምርም ደብዳቤውን ቁጭ ብላ ማንበብ ጀመረች " ጆሊ ነበርኩኝ የጭነት መኪና ላይ ረዳት ሆኜ ነበር ምሰራው እኔ እና ጭስ ያልወጣንበት ቀዳዳ የለም ከሰማንያውም ብሔረሰብ ሴቶች ጋ ተኝቻለሁ ብል ውሸት ሊመስል ይችላል ልጃ ገረድ የለ ያላያገባች የወለደች የቀረኝ የለም ኤልያስ ከተባለ የጅማ አጋሮ ሰዎች ጆሯቸው ይቆማል ። ተዘመረልኝ ወጣትነቴ እየተጠቀምኩበት ያለፍኩት ይመስለኝ ነበረ ፣ ያልተዝናናሁበት ሪዞርት ካየሁት ሳልጠጣበት የወጣሁበት ባር የለም ፣ ከትግሬዋ ጋ ከመይ ከመይ ፣ ከኦሮሞዋ ጋ ጫልቱ ጫልቱ  ፣ ከአማራዋ ጋ ውቤ ውቤ ፣ ከጉራጌዋ ጋ ገረ ገረ እያልኩ ወጣትነቴን ሴትና አልኮል በማሳደድ አጠፋሁት ።

ወይ ኤልያስ ዘመን ሲቀየር ነገሮች አብረው ተቀየሩ ፣ ህይወት ለኔ ዋዛ እንደሆነች መስላ ጠልፋኝ ነበረ የሚያውቁኝ ሰዎች " ኤልያስ ቆሞ መቅረቱ ነው " ብለው ያሙኝ ነበረ ፈጣሪ ወደ ህይወቴ ማርታ የምትባል መልአከ ህይወት ላከ ፣ ማርታን ያወቅኳት ፓስታ ቤት እየሰራች ነበረ ፣ ውብ ነበረች ሌላ ጊዜ እንደምቀርባቸው ሴቶች ልቀርባት ያልሞከርኩት ነገር የለም ግን የዋዛ አልነበረችም ቀኖች በሄዱ ቁጥር ለሷ ያለኝ ስሜት ተቀየረ  ተቀራረብን የሆነ ቀን ስለ ህይወቷ በትንሹ አጫወተችኝ አግብታ እንደፈታች እና የአንድ ልጅ እናት እንደሆነች ልጇ የባሏ እናት ጋ እንደሚኖር እሷ ብቻዋን ተከራይታ እንደምትኖር ባሏም ሰካራም እንደሆነ እና ሰካራም እንደምትጠላ ነገረችኝ ። የበፊት ህይወቴን ነገርኳት እናም ከዚህ ህይወት መውጣት እንደምፈልግ ነገርኳት ማርቲ ቀስ በቀስ ለወጠችኝ እሷን ለማስደሰት ስል አልጠጣም አልቅምም አላጨስም ገንዘብም መያዝ ጀመርኩ ከማርቲ ጋ በጣም ስንግባባ ጊዜ ስናሳልፍ አብሮ የመኖር ሀሳብ መጣ  አዲስ ቤት ተከራይተን መኖር ጀመርን የድሮ ጓደኞቼ የሚያውቁኝ ሰዎች " ኤልያስ ቫይረስ ሳይዘው አይቀርም ይሄኔ ከእሷም ጋ ሚኖረው ሁለቱም ታማሚ ሆነው ነው  " እያሉ እንደሚያሙኝ ሰማሁ ፣ በርሜል ሙሉ ሀሜት አንድ እንጀራ አይጋግርም ብዬ ጆሮዬን ደፍኜ ህይወቴን ቀጠልኩ እገባባቸው የነበሩ ባሮች ፣ እተኛቸው የነበሩ ሴቶች በሙሉ አስጠሉኝ ፣ የድለላውንም ስራ ቤት ሆኜ መሥራት ጀመርኩ ።

ማርቲ ከእኔም ከእሷም ብር አጠራቅማ ትንሽዬ ሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ ከፈትን ፣ ትንሽ እንደሰራች ሴት ልጅ ወለድን  ስሟንም ተዐምር አልነው ልጃችን ህይወታችንን ይበልጥ አሳመረችው ፣ ፈጣሪ እንደ ሀጥያቱ የከፈለው ሰው ላለመኖሩ ምስክር ነኝ ማርታን ከሞት ህይወት መውጫ በትር አድርጎ ሰጠኝ ፣ አንዳንዴ ያለምንም ስራ ያለምንም ድካም ያለምንም እቅድ በህይወታችን የሚመጣ የፈጣሪ በረከት አለ ፣ አምላክ በማርታ በኩል ለኔ ቸርነቱን ገለጠ ፣ ከብኩነንት ከበድንነት ህይወቴን ለመለሰችው ማርታ ህይወቴን ሰጥቼ ላፈቅራት ወሰንኩ ልጄንም በንፁህ ልቤ ወደድኳት በህይወት እስከነበርኩበት ጊዜ ሁሉ በሙሉ ልቤ እወዳችሁ ነበረ " አልያስ ይላል ።

እናት እና ልጅ ተቃቅፈው አለቀሱ ተዐምር " እናቴ አንቺስ አባቴን ሳታውቂው ህይወትሽ እንዴት ነበረ ? " ብላ ጠየቀቻት ማርታ ፊቷ ላይ ያለውን እንባ እየጠረገች " ልጅ እያለሁ እናቴ ለአንድ ሀብታም ሰው ዳረችኝ ሰካራም ነበረ ይማታል ሰውን ከጥፍሩ ቆሻሻ አይቆጥርም አንድ ልጅ ወለድኩ ፣ ስወልድ ይበልጥ አስጠላሁት ምቱ ስካሩ ስድቡ ጨመረ ይህን መቋቋም ሲያቅተኝ ባለቤቴን በህግ ፈታሁት ያለምንም ንብረት ክፍፍል ልጄን ጥዬ ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ ፣  ያኔ የህይወት መንገዶች ተዘግተውብኝ ነበረ የወንድምሽን አባት ፈትቼ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ሄድኩ ግን የምኖርለት ነገር ስላልነበረኝ ብዙ መልፋቱ መስሎ አልታየኝም ትንሽ ብር ይዤ ሀገሬ ተመለስኩ ከዚያም ፖስታ ቤት ተቀጥሬ እየሰራሁ ብቻዬን ተከራይቼ መኖር ጀመርኩ አባትሽ መልእክት ለመላክ ይመላለስ ነበረ በዚህ ተዋወቅን በብዙ ፈተንኩት ፣ ከበፊት ህይወቱ እኔን እንደመረጠ ራሱን በመግዛት አሳየኝ ፣ እንክብካቤው ለሴት ያለው ክብር ለመኖር ያለው ፍላጎት አብሬው እንድኖር አስገደደኝ በፈጣሪ እገዛ ጎጆ ወጣን ፣ ህይወታችን ቀስ በቀስ ተቀየረ አንቺ ስትወለጂ አባትሽ ተዐምር ብሎ አወጣልሽ ፣ ልጄ ህይወት ላይ ለመኖር ዳግም እድል እንደማግኘት ያለ ተዐምር ያንን ደግሞ እንደመጠቀም ያለ ጥበብ የለም " እያለች ወረቀቱን አልበሙ ውስጥ ከተተችው ።

#በረከት_ዘውዱ

@beki_book

11 months, 2 weeks ago

ሳልሞት ቅበሩኝ

ለኛም ፀሀይ ወጣ ከድህነት ጨለማ ወጣን ህይወት እጇን ዘረጋች አባዬ ቤቱን ሰርቶ ወደ መጨረሻው ደረሰ ቤቱ የ ውስጥ ስራ ( finishing ) ስራ ሲቀረው ከ አንድ ወር በኋላ ቤቱን ጨርሼው እንገባለን እያለ በስራ በድካም ቀኑን ሲንከራተት እንደዋለ ማታ ላይ ጠራኝ " ብሩኬ ብሩኬ ውሀ ስጠኝ " አለኝ ቤቱ ስለተረባበሸ እስክሰጠው ትንሽ ቆየሁ ውሀውን ይዤ ስመጣ አባቴ አተነፋፈሱ ተቀይሯል ጮህኩኝ እናቴ እህቶቼ ተሰበሰቡ ተረባርበው መኪና መጥቶ ወደ ሆስፒታል መንገድ ጀመሩ ፣ ትንሽ ቆይተው ሲመለሱ አባቴ ተሽሎት መስሎኝ ነበር ለካ አባቴ መንገድ ላይ ህይወቱ አልፏል መኪናው የተመለሰው ለዛ ነበረ ።

ለምን ? ህልሙን ለማሳካት ጫፍ ላይ ደርሶ ከ አንድ ወር በኋላ አዲሱ ቤት እንገባለን እያለ ተስፋውን ጥንካሬውን ህልሙን ሁሉንም አፈር ለምን በላው ? ብሩኬ " እኔ አባትህ ያለ እረፍት ነው ቤቱን ምሰራው አንተ ትምህርትህ ላይ በርታ " እያለኝ " ቤቱ በ አንድ ወር ውስጥ ያልቃል ገናን በአዲሱ ቤታችን ነው ምናከብረው " እያለኝ ሞት ለምን ቀደመው ፈጣሪ እርጅና አይናቸውን የጋረዳቸው የልጃቸውን ደስታ ማየት የሚሹትን እናቱን ለምን አልወሰዳቸውም ልጃቸውን በማጣት ህመም አንጀታቸው እስቲቆስል ማልቀሳቸውን ማዘናቸውን ለምን ፈለገ ።

አባቴ በጣም መልካም ሰው ነበረ ! አቶ አሸናፊ ከተባለ የሰፈር ሰው ሁሉ የሚታየው መልካም ነገር ነው እኔንም ሰፈር ልጫወት ስወጣ ተልኬ ስወጣ ወደ ትምህርትቤት ስሄድ ያዩኝ ሰዎች ሁሉ " የአቶ አሸናፊ ልጅ እደግ የእርግብ እንቁላል እባብ አይሆንም ያሳድግህ " ይሉኛል እህቶቼም በፀባያቸው በጨዋነታቸው ሁሉም ሰው ይስማማበታል እናቴም እስከዳር መልካም ሰው ነች አባቴን በሁሉም ነገር ታግዘው ነበረ ትመክረዋለች ሰላሳ ዓመት በትዳር ሲኖሩ ችግሮቻቸውን በጠብ ለመፍታት ሞክረው አያውቁም ሁሌም እኛ ስንተኛ ሲነጋገሩ እሰማለሁ ከስድስት ወር በኋላ እናቴ አባቴ የጀመረውን ቤት ሰርታ ጨረሰች ።

አዲሱ ቤት ከገባን በ ዓመቱ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ለትምህርት ሄድኩኝ ከእናቴ ጋ በስልክ እናወራ ነበረ ለእረፍትም ስሄድ እንገናኛለን ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ስሆን ታላቅ እህቴ የቤቱ የመጀመሪያ ልጅ ተሞሸረች አምስተኛ ዓመት ተማሪ ስሆን ታላቅ እህቴ የቤቱ ሁለተኛ ልጅ ተሞሸረች ከ ሁለት ወር በኋላ እኔም electrical mechanical engineering ተመረቅኩ እናቴ ሁሌም " ምን ነበረ አሹ በህይወት ኖሮልኝ ይህንን ወግ ማዕረግ አብረን ብንካፈል ምን ነበር የዘራውን አጭዶ ቢሆን ፈጣሪ ስድስት ዓመት መታገስ አቅቶት ነው " ትላለች አንዳንዴም ደግሞ " ፈጣሪ ትክክል ነው ነገሮች ሁሉ ለመልካም ናቸው " ትላለች ።

አባቴ ተስፋ ነበረው እውነትም የሆነ ሊቀድመው የፈለገ ነገር እንደ ነበረ ተረድቶ ነበር ልቡን ትንሽ ይደክመው ነበር ግና ጥንካሬው ምንም በሽታ እንደማያጠቃው ሰው ነበር ሁሌም ልንተኛ ጊዜ ከመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች አስር አስር ምዕራፍ ያነብልኛል ረዥም ከሆነ ደግሞ አምስት ምዕራፍ አንብቦልኝ ከመፅሀፍ ቅዱስ ካነበበው ይመክረኝ ነበረ ። አሁን ላይ ሆኜ ምን ነበር አባቴ በህይወት ኖሮ ተመርቄያለሁ ስራ ይዣለው በመንፈሳዊ ህይወቴም ጥሩ ላይ ነኝ አባቴ ይህን ሁሉ አብሮኝ ሆኖ ብናየው ብዬ እመኛለሁ ።

ሰውነት ድክመት ነው አይደል ስንኖር ነገ ወይ ዛሬ መሞታችንን አናስተውልም መኖር ብቻ እንደተፈቀደልን ሳይሆን እንደፈቀድን የምንኖር ይመስለናል እስከፈለግነው ጥግ እንድድምንሄድ እናስባለን መንገዱ ላይ እንቅፋት ወይንም ገደል እንዳለ እንዘነጋለን ሁሉን ነገር ይዘን የምንሄድ ይመስለናል ። ህይወት መወለድ መኖር መሞት ብቻ እንዳልሆነ አባቴ አስተምሮኝ አልፏል ለስጋው መጠለያ እንደደከመው ሁሉ ለነፍሱ ስጋውንም ሲያደክም ተናግሮ ብቻ ሳይሆን ሆኖም አስተምሮኛል ።

#በረከት_ዘውዱ

@Beki_book

We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc