Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

ሰውና ~ ፍልስፍናው

Description
☞የዕውቀት መጀመሪያ አለማወቅን ማወቅ ነው፠ ~ማወቅ ደግሞ ከማሰብ ይጀምራል✔️
#የፍልስፍና_ስራ_ሰውን ለተፈጠረበትየሰውነትአላማ ማብቃትነው
❖ ጥንታዊ ፍልስፍናዎች<
❖ አስገራሚ አውነታዎች<
❖ ሳይኮሎጂ<
❖ አስደማሚ ታሪኮች<
❖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተንትኖት<
☞ጠቅልሎ የያዘ ለነፍስና ለስጋ የሚበጁ ለሰላማዊ ህይወትም ሆነ ለምድራዊ ቆይታ መሠረት የሚሆኑ አጅግ በረካታ ሀሳቦችን ለናንተ ያደርሳል
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago

1 month, 3 weeks ago

#አንድ_ቀን_ታረጃለህ!

በወጣትነትህ ሽማግሌውን አክብር

ጠንካራ ስትሆን ደካሞችን እርዳ

ሰዎች ሲሳሳቱ አታሳቃቸው

ምክንያቱም አንድ ቀን በህይወት ታረጃለህ፣

ደካማ ትሆናለህ፣ ትሳሳታለህም!!!

#ስሜትን_በብልኃት_መምራት መጽሐፍ
#EMOTIONAL_INTELLIGENCE

1 month, 3 weeks ago

🔥ድፍረት ማለት ያለ ፍርሀት መኖርና እየደነፉ ማውራት ማለት ሳይሆን ፣
ከሚገባው በላይ ብንፈራና ብንደነግጥም እንኳን ያሰብነውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አለማለት ነው ።

በአስቸጋሪ ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ተረጋግቶ መውጫ ቀዳዳ በመሻት  መውጣት የድፍረት አንድ አካል ነው

ድፍረት ማለት የፍርሀት አለመኖር ሳይሆን ፍርሀት ላይ የምንቀዳጀው ድል እንደሆነ ተማርኩ፤ ጀግና የሚባለው ፍርሀት የማይሰማው ሳይሆን ፍርሀትን መማረክ የቻለው ነው!

----ኔልሰን ማንዴላ

2 months ago

#እስከማዕዜኑ**.........

የደስታ ቀናት እንደ ሰማይ ሲርቁ…
ክፉ ቀናት እንደ አጀብ ሲከቡን…
ሞት አንድ አማራጭ ሆኖ ሲቀርብ…
ውስጣዊ ሰላማችን ሲረበሽ…
ለጥያቄዎቻችን ምላሽ ስናጣ…
እርጋታ ፈጽሞ ሲጠፋ….

…  ያን ጊዜ “ጌታ ሆይ እስከመቼ?” እንላለን፡፡ ደግሞም በልጅነት ሰቆቃ በአባቶቻችን አንደበት #እስከማዕዜኑ? እንላለን፡፡

እንባችን እንደ መጠጥ፣ ሀዘናችንም እንደ መብል ይሆንብናል፡፡ የቀናት ጠንሳሽ የሆነው አባታችን እግዚአብሔር ግን “ታገስ፣ የመጠበቅን ፍሬ ትበላለህ” ማለቱን ይቀጥላል፤

እኛም “አምላኬ ሆይ፣ እንዴት ልታገስ? እሰከመቼስ ልጠብቅ?” እንላለን፡፡

“እንደ ልጄ እንደ ዳዊት ቀና ሁን፣ እንደ ታላቁ ታጋሽ እንደ ኢዮብ ሁንልኝ፣ የቀጠርኩልህ ቀን ሲደርስ የመከራህን ቀናት አስረሳሃለሁ! እንደ ተወዳጁ ልጄ እንደ ወልድ ትንሳኤህ እስኪገለጥ እርጋታን ገንዘብህ አድርግ!” ይለናል፡፡ በቃሉ ያባብለናል፡፡

የህማማት ቀናቶቻችን እንደ ግዮን ወንዝ የረዘሙ ሲመስሉ፣ የህዝባችን እፎይታ፣ የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት እንደ ጌታችን መምጫ ቀን ሲርቁብን፣ ህይወት ከንቱ መኖርም ምናምንቴ መስሎ ሲታይ…  የስጋ ድካም ከዘለዓለማዊው እጣ ፈንታችን ሊያናጥበን ሲል… ያን ጊዜ የታላላቅ አባቶች ምክር፣ የቅዱሳን ጥበብ፣ የታጋሾች ምስክርነት ያስፈልገናል፡፡#እስከማዕዜኑ እና#ጠይቁ_ይመለስላችኋል 📕📕📕**

2 months ago

አንዳንዴ . . . ያለ ነው!አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም!

አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም!

አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም!

አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም!

አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም!

አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዘም!

አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አየቅተንም!

አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም!

አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም!

አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም!

2 months, 1 week ago

"ሁልጊዜ ከሰዎች የማነስ ስሜት የሚሰማህ ከሆነ የቅናት ማዕከላት የሆኑትን የማሀበራዊ ሚዲያዎች መጠቀም አቁም 🚫****"
ATOMIC HABIT Ⓑ

2 months, 2 weeks ago

ፈራችሁም አልፈራችሁም . . .

(“ገዢው ስሜት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

በተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደገሰገሱት ሃገራት በእኛም ሃገር ጥርት ያሉ ጥናቶች እየተዘጋጁ የሚቀርብልን ሁኔታ እያደገ እንደሚሄድ ተስፋ በማድረግ፣ እስከዚያው ግን በጥናታዊ አቅርቦት ከበለጸጉት ሃገሮች አንዳንድ መረጃዎችን በመበደር ለእንቆቅልሾቻችን መፍቻ መፈለጋችንን እንቀጥላለን፡፡

እንደምሳሌ ለመውሰድ፣ በአሜሪካን ሃገር ውስጥ በተደረገው አንድ ጥናት (የተለያዩ ጥናቶች የተለያዩ ውጤቶችን የማንጸባረቃቸው ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ) የሚከተለውን የፍርሃትን ገጽታ ከሃገራችን አውድ አንጻር እንድንመለከተው የሚያደርገንን መረጃ እናገኛለን፡፡

• ስልሳ በመቶው (60%) የምንፈራቸው ነገሮች ፈጽሞ ወደመሆን አይመጡም፡፡

• ሰላሳ በመቶው (30%) ከዚህ በፊት ፈርተናቸው የደረሱብን ሁኔታዎች ብንፈራም ሆነ ባንፈራ ከመሆን የማንቀይራቸው ነገሮች ናቸው፡፡

• ዘጠና በመቶው (90%) የምንፈራቸው ነገሮች ቢደርሱም ሆነ ባይደርሱ ብዙም የማይነኩንና አናሳ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

• ሰማኒያ ስምንት በመቶው (88%) ከጤንነታችን ጋር በተያያዘ ሁኔታ ይደርስብናል ብለን የምንፈራቸው ሁኔታዎች በፍጹም የማይደርሱብን ሁኔታዎች ናቸው፡፡

በዚህ ዓለም ላይ ምንም ሳይፈራ የሚኖር ሰው ተፈልጎ አይገኝም፡፡ ነገር ግን የፍርሃትን እውነታ በመቀበል፣ ብንፈራም ሆነ ባንፈራ ምንም ለውጥ ስለማናመጣባቸው ነገሮች መፍራትን በማቆም፣ የፍርሃትን ስሜት ለጥቅማችን በማዋል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግና ሕይወትን ቀና ብሎ በማጣጣም መኖር ፍርሃትን ያሸነፉ ሰዎች ልምምድ እንደሆነ ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡

ፈራችሁም አልፈራችሁም . . . ወደፊት!

2 months, 3 weeks ago

#ራስህን_አትዋሽ_ስልህ

ያንተን ገጸ -ባህሪ ማንም አይወድልህም። ሁሉም ሰው ያለህበትን ቦታ ነው የሚወደው።

ሁሉም ሰው የሚወደው ያለህን የሀብት ልክ ነው !

ሁሉም ሰው የሚወደው ያገኘኸን የግልም የሆነ የመንግስት ስራ ነው።

ያንተ መኪና፣ ቤት፣ ሳይክልህን፣ መንገድ ዳር ያለ አማላይ ቤትህን ሁሉም የሚወደው መኖርህን ሳይሆን ያለህን ነው! አንተን እሚወድህ የለም ወዲያ!

ኧረ ተረጋጋ ወንድሜ ማነው እንዲህ ያለው?😅

ወዳጄ ሲጀመር መወደድ የተፈጥሮ እንጂ የማግኘት የማጣት አይደለም። ቢኖርህ ቆንጆ፣ ቆንጆ ሴቶችን እንደ'ቃ ትገዛ ይሆናል እንጂ፣ መልከ ጥፉ እንኳ ልትወድህ አትችልም።

መኪና ቢኖርህ ጓደኛህ ከስራ ሲወጣ እንድትሸኘው፣ ማንም ሳይስቅልህ ሲቀር ይገለፍጥልህ ይሆናል እንጂ... ባለመኪና ስለሆንክ ብቻ ሊወድህ አይችልም።

ቤት ስላለህ ብቻ ኑሮ የጠበሳቸው ደርዘን ሴቶች ሊያገቡህ ፍቃደኛ ሊሆኑ ይችላሉ። አባ አንዷም ላትወድህ ትችላለች።

ብር ስላለህ ብቻ ጋባዥ ስለሆንክ ሰፈሬው አገጩ መሬት እስኪልስ ለጥ ብሎ ሰላም ሊልህ ይችላል። ያ ማለት ተወዳጅ አያስብልህም

ስልጣን ወይም አሪፍ ስራ ስላለህ ብቻ ''የተከበሩ'' ትሰኝ ይሆናል እንጂ ክብር ካንተ የራቀ ሊሆን ይችላል።

አባ ስላለህ ሳይሆን ስለማንነትህ ሰዎች ሊወዱህ ተፈጥሮ ነው።

ቤት፣ መኪና፣ ገንዘብ ያንተ ስለሆኑ የሰው ቀፎ የሆኑ ግለሰቦችን እንዳሻህ ትገዛ ይሆናል፤ ልባቸውን ግን አታገኘውም። ስለዚህ ያለህ መልካም ስብእና፣ ፍቅር እና ፍቅር ያስገኝልሃል።

☑️ 
ገንዘብ ገዢ ቢሆን ፣ መውደድ አይሸጥም
ምግባር የሌለው ሰው፣ ላፉ -ስ አይጣፍጥም
ስልጣን ምን ቢፈራ፣ ክብር እንዲሁ አይደል
ሁሉን እንዲያገኙ፣
መልካም ባህሪ እንጂ፣ በምግባር መታደል ነው!

3 months ago

የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!
ሕይወታችንን ማስመለስ ማለት በአጭሩ ሲተረጎም በአንድ ሰው፣ ሁኔታ ወይም ልምምድ ምክንያት ከደረሰብን ቀውስ የተነሳ በትክክል ማሰብ፣ መስራት፣ መተኛትም ሆነ መኖር እስከማንችል ድረስ የደረሰውን ሁኔታችንን እንደገና ወደቀድሞው ጤናማ ሁኔታ ማስመለስ ማለት ነው፡፡

•  የጎዳችሁና እስክትበቀሉት ድረስ ውስጣችሁን የሚያናድደው ሰው የወሰደባችሁን ሕይወታችሁን አስመልሱ!

•  ሰዎችን አምናችሁ በተወሰደባችሁ ቁሳቁስ ወይም ገንዘብ ምክንያት ዘወትር ከመቆጨታችና ከመቆዘማችሁ የተነሳ የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!

•  አፍቅራችሁ ትንሽ ከተጓዛችሁ በኋላ ያ ሰው ለእናንተ ምንም ፍላጎት እንደሌለው ብትደርሱበትም ካላችሁ የስሜት ትስስር የተነሳ ልትረሱት ባልቻላችሁት ሰው የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!  

•  ማንኛውንም ሰውም ሆነ ሁኔታ ከመፍራታችሁ የተነሳ ወደፊት መራመድ እስከማትችሉ ድረስ በመሆናችሁ ምክንያት የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!

ወደራሳችሁ ተመለሱ! ወደቀደመው ሰላማችሁ ተመለሱ! ወደእውነተኛው ማንነታችሁ ተመለሱ! ከምንም ሁኔታና ከማንም ሰው ጫና ውጪ ወደነበራችሁበት ሚዛናዊ ሕይወት ተመለሱ!

ንቁ! ወስኑ! ምክርና እገዛን ፈልጉ! የድሮውን ጤናማ ማንነታችሁን እንደገና የራሳች አድርጉ እንጂ የሰውና የሁኔታዎች ሰለባና መጫወቻ አትሁኑ!

መልካም ቀን!

Dreyob

3 months, 1 week ago

#ራስን_ለመግዛት_የሚረዱ_6_ነጥቦች!

  1. ደካማ ጎኖችዎን ይለዩ፦

ደካማ ጎኖቻችሁን ችላ ማለት እንዲጠፉ አያደርጋቸውም። ስለዚህ ጣፋጮችን መብላት የክብደት መጨመሮ ምክንያት ነው? ማህበራዊ ሚዲያ ማዘውተር ምርታማነትዎን ቀንሶታል? ድክመቶችዎን ይወቁ። ድክመቶችዎን ማወቅ አዎንታዊ ለውጥን ለመፍጠር የመጀመሪያው እርምጃ ነው።

  1. ግልፅ የሆነ ስልት ይቀምሩ፦

ከፍ ያለ ራስን የመግዛት አቅም በድንገት አይመጣም። ይልቁንም የአእምሮ ጡንቻን ለመገንባት የሚያግዝዎት ስልት ማበጀት ያስፈልግዎታል። ብዙ ጊዜ ወደ ጂም እንደመሄድ ያሉ ጥሩ ልምዶችን መጨመር አልያም ብዙ ሶሻል ሚዲያ መጠቀምን የመሰሉ መጥፎ ልምዶችን ማስወገድ ከፈለጉ እነዚህን ዓላማዎችዎን ወደ ተግባር ለመቀየር ዕቅድ ያስፈልግዎታል። በየቀኑ መውሰድ የሚያስፈልጎትን እርምጃዎችን በግልጽ ይዘርዝሩ።

  1. የሚፈታተኖትን ነገሮች ያስወግዱ፦

ቤትዎ ጣፋጮች ምግብ ከተከማቹ ክብደትን ለመቀነስ ራስን የመግዛትን አቅም ያዳክማል። ይልቁን እያንዳንዱን ኩኪስ፣ ቺፕስ እና ሌሎች ጣፋቾችን ላለመብላት በመሞከር ጊዜዎን ያባክናሉ። ድክመትዎ በየሁለት ደቂቃዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን መፈተሽን የሚያካትት ከሆነ ፌስቡክን የሚያግድ መተግበሪያ ይፈልጉ። ፈተናዎችን መገደብ በጊዜ ሂደት የበለጠ ራስን የመግዛትን አቅሞን እንዲገነቡ ይረዳዎታል።

  1. ምቾት ማጣትን ይለማመዱ፦

ምቾት ማጣትን ለማስወገድ መሞከር ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን የአጭር ጊዜ ምቾትን መሻት ብዙውን ጊዜ የረጅም ጊዜ ችግሮችን ያስከትላል። እናም በተሸነፉ ቁጥር ጭንቀትን መቋቋም እንደማይችሉ ለራስዎ ያሳምናሉ። ምቾት ማጣትን ይለማመዱ፤ ያ ማለት እርስዎ ከሚያስቡት በላይ ለተጨማሪ ደቂቃ መሮጥ ወይም ጣፋጭ ምግቦችን የመብላት ፍላጎትን መቃወም ባጠቃላይ ምቾት ማጣት ጠላት አለመሆኑን እንዲያምን አዕምሮዎን ያሰልጥኑ።

  1. ግቦቾን ያስታውሱ፦

ፈተናን ሲጋፈጡ ሊያገኟቸው የሚችሏቸውን ነገሮች ለራስዎ ያስታውሱ። ከግቦችዎ ጋር ሲጣበቁ የሚያገኟቸውን ነገሮች ሁሉ ዝርዝር ይፃፉ፤ ተስፋ ለመቁረጥ በሚፈተኑበት ጊዜ ዝርዝሩን ያንብቡ።

  1. ለውድቀት ያለዎትን አመለካከት ይቀየሩ፦

መሻሻል ብዙውን ጊዜ በቀጥታ መስመር ላይ አይመጣም። ስህተት ሰርተዋል ማለት ከዚህ በኋላ አይሳካሎትም ማለት አይደለም። ስህተት የመሻሻል ሂደት አካል ነው። ከእነዚህ ስህተቶች የሚመለሱበት መንገድ ነው በጣም አስፈላጊው ነገር፤ ከተሳሳቱት እርምጃዎችዎ በመማር በሚቀጥለው ጊዜ የተሻለ ለማድረግ ቁርጠኛ ይሁኑ።

3 months, 2 weeks ago

Learn to #say_NO!!!

ካስቀመጣችሁት የሕይወት መርህ እና እንዲሁም ለትክክለኛና ሚዛናዊ ለሆነው የግል ፍላጎታችሁና ፈጣሪ ከሰጣችሁ ማንነታችሁ አንጻር ግፊት ለሚያደርግባችሁ ሰውም ሆነ ሁኔታ በተረጋጋ መንፈስ “እምቢ” በማለት በራስ እድገት ላይ እስከምታተኩሩ ድረስ ሕይወትን ማጣጣምም ሆነ የወደፊት ራእያችሁን እውን ማድረግ እንደማትችሉ ላስታውሳቸሁ፡፡

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago