★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago
*🌿Good Morning እጅግ የምወዳችሁና መልካምን ነገር የምመኝላችሁ የሃገሬ ሰዎች!*
**እንኳን በሰላም ለዛሬዋ ቀን አበቃችሁ!
እስቲ የዛሬዋን ቀን አርፋችሁ ጀምሯት!
ቀንን አርፎ መጀመር ማለት እረፍትና እርካታ ፍለጋ ምንም ነገር ለማድረግ ከመታገል መረጋጋት ማለት ነው፡፡
ውስጣችሁ እርፍ እንዲል ማንም ሰው ሊቀባለችሁ አይገባም፣ ማንንም ሰው ማስደሰትም የለባችሁም፡፡ ስላረፋችሁ ግን ከሰዎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት ሚዛነዊ አድርጋችሁ የመያዝ መረጋጋት ታገኛላችሁ፡፡
ውስጣችሁ እርፍ እንዲል የትኛውም ስራ ስኬታማ መሆን የለበትም፡፡ ውስጣችሁን አሳርፋችሁና አረጋግታችሁ የምትሰሩት ስራ ራሱ መነሻው ስኬታማነት መሆኑን አስታውሱ፡፡
ከእነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ተነስቼ ከጀመርላችሁ ሌሎቹን እናንተው አስቧቸው፡፡
ምንም ነገር ስታደርጉ፣ የውስጣችሁን እረፍት ነገሩ እስከሚሳካ አታዘግዩት፡፡
መጀመሪያውኑ ፈጣሪ በሰጣችሁ ማንነት፣ ባላችሁ የሕይወት ራእይና አጠገባችሁ ካለምንም ቅድ-ሁኔታ በሚወዷችሁ ሰዎች እርፍ በሉ፡፡
ከዚህ አይነቱ ሁኔታ ስትነሱና ስትጀምሩ ሰዎችም ሆኑ ሁኔታዎች የእናንተን ስሜት እንደፈለጉ አያደርጉትም፡፡**
Dreyob
```
ታላቅ መሆን የሚቻለው ታላላቅ ሀሳቦችን በቋሚነት በማሰብ ነው!
በውስጣዊ ስብእናው ታላቅ እስኪሆን ድረስ ማንም ሰው በውጫዊ ስብእናው ታላቅ መሆን አይችልም፡፡ እስኪያስብ ድረስ ደግሞ ማንም ሰው በውስጣዊ ስብእናው ታላቅ መሆን አይችልም፡፡ የትኛውም ዓይነት ትምህርት፣ ንባብ ወይም ጥናት ሳታስቡ ታላቅ ሊያደርጋችሁ አይችልም፤
ሀሳብ ግን በጥቂት ቀናት ታላቅ ያደርጋችኋል!
በጣም በርካታ ሰዎች ማሰብን ሳይለማመዱ፣ ማሰብ የተከለከለ ነው የተባሉ ይመስል ብዙ መጽሐፍን በማንበብ ብቻ ታላቅ ነገርን ለማድረግ ሲሞክሩ ይስተዋላል፡፡ እንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች አይሳካላቸውም፡፡ በምታነቡት ነገር ሳይሆን በምታነቡት ነገር ላይ በምታስቡት ሀሳብ ነው አእምሯችሁን የሚገነባው፡፡
ማሰብ ከየትኛውም አይነት ስራ ከባዱና አድካሚው ነው፡፡ ስለዚህም ብዙ ሰዎች ከማሰብ መራቅን ይመርጣሉ፡፡ ብዙ ሰዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በሙሉ የሚያሳልፉት ያለማቋረጥ ደስታን በማሳደድ፣ ማሰብን ለማምለጥ በሚደረግ ጥረት ብቻ ነው፡፡ ብቻቸውን ከሆኑ ላለማሰብ ወደ ጌም፣ ወይም እንደ አስቂኝ ትዕይንት ያላቸው ነገሮች ይጓዛሉ፡፡ ብዙ ሰዎች ብዙ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ከሃሳብ በመሸሽ ነው፤ ለዛም ነው ባሉበት ቦታ ሆነው የሚቀሩት፡፡
ማሰብ እስካልጀመርን ድረስ በጭራሽ ወደ ፊት አንሄድም!
ማሰብ ስብእናን ይሰራል፡፡ ማሰብ እድገት ነው፡፡ ሳታስቡ ማደግ አትችሉም፡፡ ሳታስቡ ሀብታምም መሆን አትችሉም፡፡
ማንኛውም ሰው ሁለትና ሁለትን አባዝቶ አራትን አለማግኘት እንደማይችለው ሁሉ፣ ማንኛውም ሰው ለሀብት ሳይንሳዊ ህጎች እስከተገዛ ድረስ ሀብታም አለመሆን አይችልም፡፡
ከሀሳብ ውጪ ታላቅ ሊያደርጋችሁ የሚችል ነገር የለም! ከሀሳብም ውጪ ሀብታም ሊያደርጋችሁ የሚችል ነገር የለም!!
```
🌻እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!🌻
በዓሉ የሰላም ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
አንብብና ተግብረው!
አንድ ነገር ላሳይህ ነው፤ ተከተለኝ. . .
1- የ'ኖኪያ/Nokia' የመጀመሪያ ምርት ምን ይመስልሃል?
? የሽንት ቤት ወረቀት ነበር
2- የ'ሳምሰንግ/SAMSUNG' የመጀመሪያ ምርትስ?
? ግሮሰሪ ነበር
3- 'ላምበርጊኒ/ Lamborghini' እጅግ ውድና ቅንጡ መኪና አምራች ነው፤ የመጀመሪያ ምርቱ ግን ምን ነበር?
? የእርሻ ትራክተር ነበር
4- 'አይኪያ/Ikea'ን ታውቀዋለህ፤ ሃብታምና ዝነኛ ድርጅት ነው፤ ግን በምን ምርት ጀመረ?
? በእስክርቢቶ ነበር የጀመረው
5- የ'ኤል ጂ/LG'ስ የመጀመሪያ ምርት ምን ነበር?
? የፊት ቅባት/cream ነበር
ይህ የሚነግርህ የመጀመሪያ ምርትህ መነሻ ከየትም ሊሆን እንደሚችል ነው፤ ዋናው መጀመርህ ነው። የመጀመሪያ ምርት ወይም አገልግሎት ውጤታማ ላይሆን ይችላል። የቢሊየነሩ ቢልጌትስ አጀማመርም በውጤታማ ምርት አልነበረም።
ይህንን ግን ማንም አልነገረንም! ለምን?
1-ውብ ነህ!
2-የምትወደድ ነህ!
3-ተመርጠሀል!
4-ልዩ ነህ!
5-በአምሳሌ ተፈጥረሀል!
6-ጠንካራ ነህ!
7-ውድ ነህ!
8-ጠቃሚ ነህ!
9-ይቅር ተብለሀል!
10-ለዓላማ ተፈጥረሀል
???
? #ጠይቁ_ይመለስላችኋል 4ተኛ ዕትም
? #ሰይጣንን_አስርቡት 2ተኛ ዕትም
? #የነፍስ_ምግብ 2ተኛ ዕትም
? #ኦርቶጵያ 4ተኛ ዕትም
? #እስከማዕዜኑ 3ተኛ ዕትም
?#የተሰቀለው_ንጉሥ (በአማርኛ)
?ሲፈልጓችሁና ሳይፈልጓችሁ
ሰዎች ደግመውና ደጋግመው እንደሚፈልጓችሁ ከነገሯችሁ፣ በተቻላችሁ መጠን ለመስማት እድል ስጧቸውና ከዚያም ፍጎታችሁንና ውሳኔያችሁን ንገሯቸው፡፡ ይህ ተግባር፣ “ለሰዎች ተገቢውን ዋጋ መስጠት” ተብሎ ይጠራል፡፡
ሰዎች ደግመውና ደጋግመው እንደማይፈልጓችሁ ከነገሯችሁ፣ ዛሬ ነገ ሳትሉ ከሕይወታቸው ውጡላቸው፡፡ ይህ ተግባር፣ “የራስን ዋጋ ማወቅ” ተብሎ ይጠራል፡
?ፍቅር ከእግዚአብሔር ነውና
?ሁሉን ውደድ!
? በቃል የተሰበረ በመረቅ አይድንምና
? ለቃልህ ተጠንቀቅ!
? ለክረምት በጋ፣ ለሌሊት ቀን እንዳለው
? ላንተም ጊዜ አለህ! በርታ!
? ቀን የሚያመጣው ምን እንደሆነ አታውቅምና
? ነገ በሚሆነው አትመካ!
? ከትላንት ተማር፣ ዛሬን ኑር፣ ነገን ተስፋ አድርግ!
? እግዚአብሔር ከጎንህ አለ!
አታድርጉት!
• ገንዘብን ለማግኘት ብላችሁ ጤንነታችሁን አትሰው!
• ሰዎችን ላለማጣት ብላችሁ ከራሳችሁ ጋር አትለያዩ!
• ስልጣንን ለመጨበጥ ብላችሁ ከሕብረተሰብ ጋር አትጣሉ!
• አጉል ልማዳችሁን ላለመልቀቅ ብላችሁ ከሕይወት መስመር አትውጡ!
• ላለመሸነፍ ብላችሁ ቤተሰባችሁን አታፈራርሱ!
ይቅርባችሁ!
አእምሯችን አደጋን የማወቅና የመለየት አቅም አለው።
ደመ ነፍስህ የሆነ የተሳሳተ ነገር እንዳለ ከነገረህ፣ ያንን ስሜት ችላ አትበለው።**
ትስማሙበታላችሁ? ሀሳብ አስተያየቶቻቹሁን አካፍሉን።
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago